በአገራችን ኢትዮጵያ የታየው የተስፋ ጭላንጭል አሁንም በወያኔ ሴራ ከሸፈ። በሕዝቡ ያላቋረጠ ትግልና ግፊት የፖሊቲካና የህሊና እስረኞችን ለመፍታት መንግሥት የወሰነው ውሳኔ በውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ የተስፋ ጭላንጭል እንዲያይ ስበብ ሆኖ ነበር። በአገራችን ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍንና በእኩልነት ላይ የተመሰርተ የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲኖር የሚፈልጉ ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ወዳጅ የሆኑ አገሮች ሁሉ ጥሩ ለውጥ ያመጣል ብለው ተስፋ ጥለውበት ነበር።

ሆኖም ወያኔ በተለመደው ድርቅናና ሌብነቱ በማወናበድ የብዙወቹን ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ በጊዜአዊ አስቸኳይ አዋጅና በወታደራዊ አገዛዝ ለመተካት የህዝብ ተወካዮች ሳያጸድቁት በራሱ ስልጣን ተግብሮታል። በአገሪቱ እየታየ የነበረውን ሰላማዊ አንቅስቃሴ፤ እየታየ የነበረውን የሰላማዊ ሽግግር ተስፋ አደብዝዞታል። እራሱ የተናገረውንና ቃል የገባውን የፖሊቲካና የዲሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት ውሳኔ በአጭሩ ቀጭቶታል።

የፖሊቲካና የህሊና እስረኞችን፤ እንዲሁም የሰብዓዊና የሃይማኖት መብት ታጋዮችን መፍታቱ እሰየው የተባለለት ጥሩ ጅምር ቢሆንም፤ የአገራችንን ችግር ለመፍታትና ያለውን የፖሊቲካ ግለት መፍትሄ ለመስጠት ግን ይህ ጀማሮ ብቻ በቂ አይደለም። ሁሉን የሚያሳትፍ መድርክ መፍጠርና ታዓማኒንት ያለው አመራር መፍጠር ብቻ ነው ሰላማዊ ሽግ ግር ሊያመጣ የሚችለው።

በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን እንደለቀቁ በቴሌቪዥን መስኮት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስተር፤ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት አፋጥኖ ሰላምና መረጋጋት፤ ፍትህና እኩልነት የሰፍነባት አገራችን እትዮጵያን ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ያስረክባል ተብሎ የተገመትውና፤ ለዲሞክራሲው ምህዳር መስፋት ምክኒያት ይሆናል ተብሎ የታለመው ተስፋ እ ንደማለዳ ጤዛ በኣጭሩ ረግፏል። እንዲያውም የጠቅላይ ሚኒስተሩ መውረድ ለኣስቸኳይ ጊዜ አ ዋጁ ምክኒያት ታስቦ እንድሆነ በሚያስገምት መልኩ፤ የወያኔ መሪወች የህዝቡን ተቃውሞ ለማዳፍን ብፍጥነት የወታደራዊ አስተዳደር ለመፍጠር አዋጁን ተጠቅመውበታል።

ከእስር የወጡትን የፖሊቲካ የሃይማኖትና የሰባአዊ መብት ታጋዮችን፤ ሕዝቡ በታልቅ አክብሮትና በደመቀ ሁኔታ ሲቀበላቸው ያየው ወያኔ፤ ለሱ ያልሆነና ከሱ ያልመጣ ነገር ሁሉ ስለማይጥመውና ስለማይስማማው ወርቅም ቢሆን ድንጋይ ነው ብሎ ይጠለዋል እንዲሉ፤ ሕዝብ ተሰባስቦ ስለተፈቱለት ደስታውን እንዳይገልጽ፤ የመግድያና ማፈኛ የሚሆነውን ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጠቀም ሰላምዊ ህዝብ እየገደለ ይገኛል።

አሳፋሪው የወያኔ ተግባር የተክናወነብት የካቲት 10 ቀን 2010 ወያኔን እርቃኑን አስቀርቶታል።

ዚህ እለት በተደረገው የሕዝብ ተውካዮች ስብሰባ 539 ከጠቅላላ የምከር ቤቱ አባላት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ ው 359 ካጽደቀው ብቻ ሊያልፍ የሚገባው ጊዚያዊ አዋጅ በ346 ድምጽ ብቻ አሸነፍኩ ብሎ በማስጨጨብጨብ ሲያጭበረብር እጅ ከፈንጅ ተይዟል። በምክር ቤቱም ውስጥ በንጻነት እጅ የማውጣት መብት እንደሌለ ተስተውሏል።

አንድ ተወካይ ለወከለው ህዝብ ፍላጎት ሲል በውሳኔ ኣስጣጥ ላይ የፈለገውን መቃወምና መደገፍ ካልቻለ፤ ድምጽ የሚሰጠው፤ ከኋላውና ከፊቱ ያለውን ተመልክቶ ከሆነ እንድም በራስ አለመተማመን ነው አለያም ደግሞ በፍርሃትና በጥርጣሬ ተከቦ እንድሚሰራ የተገነዘብነው ትርኢት ነው። ሆኖም በዚህ የካቲት 10 የሕዝብ ተወካዮች ስብሰባ 88 ድምጽ ተቃውም፤7 ድምጽ ተአቅቦ ያልተገኙ 8 በአጠቃላይ 103 ተቃዋሚ በተወካዮች መገኘታቸው ሊያስምሰግናቸው ይገባል።

ሰሞኑን የመንግስት ወታደሮች፣ በሞያሌ ንዋሪ በሆኑ ንጹሃን ዘጎች ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ጨፍጨፋ እናውግዛለን፣ ይህን አረመኒያዊ ግድያ የፈጸሙ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ለፍርድ እንዲቀርቡ አጥበቀን እንጠይቃለን።

ALF ወያኔ በአገራችን ሕዝቦች ላይ በኣስቸኳይ አዋጅ ስም እያደረገ ያለውን የሰው ህይወትና የንብረት ማውደም ዘመቻ ተጠያቂ የሚሆንበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን። ፤የአፋር ኣስተዳደርም የአፍር ሕዝብ ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሃላፊነቱን መወጣት እንዲችል ለማስጠንቀቅ እንወዳለን።

በመጨረሻም በሰላማዊ መንገድ ለነጻንትና ለመብት ለሚታገሉት ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ምላሹን ጥይት ያደረገው የወያኔ አስተዳደር ከዚህ አጸያፊ ተግባሩ እንዲቆጠብ ለማሳሰብ እንወዳለን።

ሕዝቦች በትግላቸው ነጻነታቸውን ይቀዳጃል። አዲስቷ ኢትዮጵያ ለሁሉም ሕዝቦቿ የተመቸች ዲሞክራሲያዊትና ፍት ሃዊ ት ሆናለች።

የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ