March 15, 2018
በእነ ተሻገር ወ/ሚካኤል ክስ መዝገብ 35 ሰዎች ተከሰው ነበር። 32ቱ ሲፈቱ 3ቱ በእስር ላይ ይገኛሉ።በእስር ላይ ከሚገኙት መካከል በካቴና የተቆራኙት 4ኛ ተከሳሽ አባ ገ/እየሱስ ኪ/ማርያም እና 5ኛ ተከሳሽ አባ ገ/ስላሴ ወ/ኃይማኖት ናቸው። (3ኛው 2ኛ ተከሳሽ ነጋ ዘላለም ነው።)
መነኮሳቱን ሁለት አካላት ብቻ ሊያስሯቸው ይችላሉ። አንዱ አሳሳቹ ሳጥናኤል ነው። እሱን በፀሎት አሸንፈውታል! ሁለተኛው እንደ ዶክተር መረራ ቀልድ አከራዮች “ሰይጣንስ በፀበል ይወጣል፣ ከአንተ ይሻላል” ያሉት ኢህአዴግ ነው!
ሰይጣንን በፀሎት አሸንፈውታልና አላሰራቸውም። ዶክተሩ በቀልዳቸው ከሰይጣን ይብሳል ያሉት ኢህአዴግ ግን እንዲህ በካቴና አቆራኝቷቸዋል! ልብሳቸውን አውልቁ እያላቸው ነው፣ አውልቁ የተባሉት ዝም ብሎ “ልብስ” አይደለም። ምንኩስና ነው! ስንቶች አንገታቸውን የሰጡበት እምነት! ሰይጣን ክፉ ለሰራለት ዋናጫ የሚሸልም ቢሆን ምንኩስናን አስወልቃለሁ ብሎ ከሚታትረው ኢህአዴግ ውጭ ማንም “ሞዴል” አድርጎ ሊሸልም አይችልም ነበር።
