ዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2010 ዓም ከረፋዱ 4.00 ሰዐት አካባቢ ብዛት ያለው የአገዛዙ ሠራዊት ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ወደ ታች አርማጭሆ ሙሴባንብና ጅንግር አካባቢ ተንቀሳቅሶ ነበር፡፡ አስቀድሞ በጅምላ ከገበሬዎች ቤትና ንብረት ላይ ተኩስ የከፈተው የአገዛዙ ሠራዊት ገበሬው ራሱን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ወደቀጠናው የገቡ ወታደሮች በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
ከሰዐት በኋላ ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው ገብቶ የሳንጃ፣ የአሽሬና ሙሴ ባንብ አካባቢ የጦርነት ቀጠና እንደሆነ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው፡፡

ስርአቱን “ያቆሙት” ሁለት መሰሶዎች
መስቀሉ አየለ
ሕዝባዊ አመጹን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ግምት ውስጥ በማስገባት የህወሃት ነርቭ እንደሚበጠስና የሁሉም ነገር ፍጻሜ ይሆናል የሚል መደምደሚያ እዚህም እዚያም ይነፍሳል።ባላዳምጠውም የሃሳቡ መነሻ የኢሳት ውይይት መሰልኝ። በእርግጥ የጉጅሌው የገንዘብ ጡንቻ መሟሸሽ አንድ መልካም ጅምር እንጅ ብቻውን የስርአቱ ግብአት መሬት ይሆናል ብሎ ማመን በኔ እምነት አጠፌታ ነው። በዝምባቡዬ የታየው ሃይፐር ኢንፍሌሽን አንድ ዶላር አምስት መቶ ሽህ የዝምባቡዬ ብር በመድረሱ አገሪቱ አንድ ሚሊዮን ድፍን ብር ለማተም ተገደደች፥ በሂደት ደግሞ በዘመናዊው የአለም ታሪክ ባልታየ ሁኔታ የአገሪቱ ከረንሲ መሞቱን የባንኩ ገዥ በይፋ አዎጀና በምትኩ የአሜሪካንን ዶላር መጠቀም ጀመሩ። ሙጋቤ ግን ቀጥሎ ነበር።
የሶሪያውን አሳድ ብናዬው አገሪቱ ላይ ከሚነደው እሳት በተጨማሪ ሶሪያ ካላት ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ 4 ሚሊዮን አገሩን ለቆ ወደ ባእድ አገር ተሰደደ። አስር ሚሊዮን እዚያ አገር ውስጥ ተፈናቀለ። በቤቱ ተቀምጦ ኑሮውን መግፋትም ሆነ ግብር ለመክፈል የሚሞክረው ከቀረው ስድስት ሚሊዮን ውስጥ ለመስራት እድሜውና አቅሙ የፈቀደለት ብቻ ነው። ቢሆንም ግን አሳድም እስካሁን አለ።
ምን ለማለት ነው፤ ወያኔም ደግሞ ሁለት አገሮች እስከተሟሉለት ድረስ አሁንም የተሰወሰነ እርቀት መሄድ ይችላል።
፩ ደመዎዝ ብቻ መክፈል እስከቻለና
፪ ወታደሩ የአመጹ አካል እስካለሆነ ድረስ ማለት ነው። የስርአቱ አይዲዮሎጅ አለ ከተባለ “አማራ ጠላትህ ነው” የሚለው ጉጅሌዎቹን የተጣባቸው ለምጽ ነው። ይህ ደግሞ ከራሱ መንደር ለሰበሰባቸው ስካቬንጀሮች እንጅ ከመሃል አገር ተጠርንፎ ለሄደ ወታደር ምኑም አይደለም። ምስኪኑ ወታደር የተያዘው በመናኛ ደመዎዝ ብቻ ነውና ደመወዝ የለም የተባለ ቀን የሚሆነው ግልጽ ነው።ስለዚህ የምንተወው የትግል ግንባር ሊኖር አይገባም። ጋን በጠጠር ይደገፋልና። ትንቅንቁም የግድ ዘርፈ ብዙ መሆን ያለበት ስንል ለዚሁ ነው።
