መታሰቢያነቱ   እውነትንና   ፍትህን   ለማስፈን   ለሞቱ፣   ለተሰቃዩ፣   ለተሰደዱ ውድ ወገኖቼ /የኢትዮጵያ ሕዝብ/ ብሎም የመላው የአማራ ተወላጆች በመጨረሻም የሰው   አስተሳሰብ ለአላችሁ  በሙሉ፡፡

አክሎግ ቢራራ (ዶር)
አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ይህነ ፅሑፍ እስከምፅፍበት ጊዜ ድረስ ሰው ነኝና በማወቅም ባለማወቅም      በስህተት ለደገፍኩት አስተሳሰብም ሆነ ተግባራት ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ይቅር እንደምትሉኝ ተስፋ በማድረግ ባለችኝ አቅም የተሰማኝንና ያየሁትን ለመግለፅ   በበጎ   ህሊና   ተነሳሁ፡፡   እስካሁን   ምንም   ሳላደርግ ተጠርጥሬ   በተንገላታሁበት   ጥንካሬን   አግኝቻለሁ፡፡   ይህንንም   የፃፍኩት   ከቂምና   ከጥላቻ   ነፃ መሆኔን  በመግለፅ  ነው፡፡

ወደ ገደለው ልግባ በፌብራዋሪ 2017 እትም ፎርብስ የሚባል መፅሔት ቦሌ አውሮፕላን  ጣቢያ በአጋጣሚ  እጄ  ገባ  ጭካኔ  የተሞላውን  የአገዛዙን  ባለሥልጣናት  ሙሰኝነት  እና  ሀገር፣  ወገን ገዳይነት   ‹‹   Ethiopia’s   Cruel   Congame   ››   በሚል   ወደ   ውጭ   ሀገር   ገንዘብን   እያሸሹ ልጆቻቸውን  እያስተማሩ በወገኔ ላይ ግፍ እየሰሩ መሆኑን ተረዳሁና ለወገኔም ሆነ ሰው  ለሆነ ሁሉ  ‹‹  አባይን  በጭልፋ››  በሚል  ላካፍልና  ልገልፅ  ተነሳሁ፡፡

1ኛ. 30 ቢሊዮን የአሜሪካ መንግስት ብቻ ለኢትዮጵያ ህዝብ የረዳውን መዝረፋቸውና ባለሥልጣናቱ ከ 30 ቢሊዮን ያላነሰ ዶላር ስልጣን ከያዙ ጀምረው ማሸሻቸው እጅጉን አቃጠለኝ (ይህ መፅሐፍ በአለም አቀፍ ደረጃ አድናቆት ያለውና እውነትን ለመግለፅ የሚተጋ መፅሔት እንደሆነ አረጋገጥሁ)

2ኛ. የ2008  ዓ.ም  የሥራ  ዘመን  የፌደራል  ዋና  ኦዲት  መ/ቤት  ለፓርላማው  የ2007 ዓ.ም የኦዲት  ሪፖርት  3.2  ቢሊዮን  ብር  የተዘረፈ  መሆኑን (በጉድለት የገለፀውን) ስሰማ ህግና ሰው ያልሰማው ዘረፋን ለእግዚአብሔር   ተውኩት……….   የአዲስ   አበባ   አስተዳደርም   በተጨማሪ በ2008 በጀት ዓመት 1.4 ቢሊዮን ብር  ያለአግባብ  መባከኑን  የከተማው  ኦዲት መስሪያ ቤት አስታወቀ ጉድ ለጆሮ  አይከብድ  አሉ……… ያልተሰበሰበም 500 ሚሊዮን ብር አለ ብሎ ጨመረበት እንዲሁም ያልተወራረደና ለማን እንደተከፈለ ማስረጃ የሌለው 200 + 257  = 457 ሚሊዮን  ብር  ለውሎ  አበል  353  ሚሊዮን  ብር  የአገዛዙን  ባለሥልጣናት ጉድ ገለፀ፡፡

 

3ኛ.  በራሳቸው  ያደረጉት  የመሬት  ነጠቃ  ሳያንስ  በውጭ  ሀገር  ኩባንያዎች  በስተጀርባ ጋምቤላ ላይ ብቻ 122,664,000 ሄክታር ባለሥልጣናቱ መዝረፋቸውን ብሎ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብር የተበደሩበት መሆኑን ደሳለኝ ራህመቶ የሚባል በፃፈው መፅሐፉ ላይ አጋለጠ የሚገርመው በእነ ኢሳያስ ባህረ አማካይነት የብር ወለዱና ግብሩ እዚህ ግባ የማይባል ከሌላው ህዝብ በተለየና አድሎ በማድረግ ይህችን አገር ዘረፉ፡፡ ይህን ስገልፅ   በሌሎች   ክልሎችም   ከዚህ ባልተናነሰ   ሰፊ   ምዝበራ   ተካሂዷል፡፡   ግን የኢትዮጵያ ህዝብና ወጣት በርሃብ አለንጋ በስደት ይረግፋል ይሰቃያል  ይሞታል፡፡

4ኛ.  በኤፈርት  ስር  ያሉ  ካምፓኒዎች   1/   ሞሶቦ   ቁጥር  1   እና   2   2/   ሱር ኮንስትራክሽን 3/ ትራንስ ኢትዮጵያ 4/ መስፍን ኢንጂነሪንግ 5/  ጉና  ኮርፖሬሽን  6/ ሜጋ ኮርፖሬት 7/ ውቅሮ ሳባ  ቆዳ  ፋብሪካ  8/  አዲግራት  መድሐኒት ፋብሪካ 9/ ኢዛና የወርቅ ማዕድን 10/ ብሩህ ተስፋ ላስቲክ ፋብሪካ 11/ ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ 12/  ህይወት  ሜካናይዜሽን  13/  ተከዜ  ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ 14/ አድዋ እምነበረድ ፋብሪካ 15/ አድዋ  ጨርቃ  ጨርቅ ቁጥር 1 ቁጥር 2 ቁጥር 3 ፋብሪካዎች 16/  መስፍን  ትንሽ  መኪና መገጣጠሚያ 17/ ስታር መድሐኒት አስመጪና አከፋፋይ 18/ ደደቢት የብድር ተቋም 19/ ፔርሊ የተሸከርካሪ ጎማ አከፋፋይ 20/ ጥጥ መዳመጫ ሁመራ ፋብሪካ 21/ ኤክስፕረስ ትራንዚት 22/ ድምፀ ወያኔ 23/ ዋልታ ኢንፎርሜሽን 24/ ሬዲዮ ፋናና ቴሌቪዥን 25/ ወጋገን ባንክ 26/ አፍሪካ ኢንሹራንስ   27/ በውጭ  ሀገራት  ያሉ  ብዙ  የቤት  ኪራይ  28/  ረስት  29/  ትልማ 30/ የትግራይ አካል ጉዳተኞች 31/ የህወሀት መረዳጃ 32/ አበርገሌ የፍየልና  የበግ  ማድለቢያ  33/  የቻይና  ኤፈርት  ወርቅ ቁፋሮ  34/ የኤፈርት ወርቅ ቁፋሮ  ሽሬ  እና  የመሳሰሉት  በተለያየ  መፅሀፍና መፅሔት የተጋለጡና የኢትዮጵያ ህዝብ ደም መምጠጫ ተቋማት ሲሆኑ ሌሎች በስውር የሚዘረፉትን ጊዜ ያወጣዋል የትግራይ ተወላጆች እነ አብርሃ  ደስታ  ተቆርቋሪዎች  በጥናት  አረጋግጠዋል፡፡ በአጠቃላይ  ከ200  ቢሊዮን  በላይ  ሀገራዊ  ዘረፋና  ምዝበራ  ተካሂዶበታል፡፡

5ኛ. በአማራ ክልል የሚገኙ የምዝበራ ተቋማት ለጌቶቻቸው  ከሚያቀብሉት  ባሻገር የአማራን ህዝብ በስም ባለቤት ነው እያሉ ባለሥልጣናት ከነቤተሰቦቻቸው የሚናጥጡበትን በዝርዝር ለማጋላጥ አቅሜ የፈቀደውን ያህል ልሞክር፡

ጥረት  ኮርፖሬት  በሚባል  ስም  ከ20  በላይ  የመዝረፊያ  ተቋማት       ተቋቀመው  የህዝብ  ደም ይመጡበታል   እድሜው   በበሽታና   በድህነት   እንደማቅቅ   ይሰሩበታል፡፡   ‹‹የራበው   ሰው   ሌላውን ትቶ   የሆዱን   ረሀብ   ያዳምጣል   በሚል   የማፈሪያ   አባባላቸው   ግፍ   ይፈፅሙበታል   የተወሰኑ

 

ባለሥልጣናት   ከነቤተሰቦቻቸው   ይናጥጡበታል፡፡   ታደሰ   ጥንቅሹ   (በጥረት   ሠራተኞች የህብኡ ስም ቀበሮው  (Fox)  ከነዘርማንዘሩ  ኔትወርክ የሚዘርፈው

5.1. ከአምባሳል ንግድ ሥራዎች እና ድርጅቱ /ኩባንያው ሲመሰረት ቀድሞ   ለህውሃት   ዋና ሰላይ  በነበሩት  በአቶ  ሰለሞን  ተቀባና  በህውሃት  ውስጥ ታጋይ በነበሩት በአቶ ወንደሰን ከበደ (ፈረንጁ) አጋፋሪነት እንዲደራጅ በብዙ ሚሊዮን ብር ከሀገሪቱ በተለይ ከአማራ ክልል ህዝብ የተዘረፈ ብር ተመድቦ ነበር ሆኖም ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እናቀርባለን በሚል  አርሶ  አደሩን አርተፊሻል    የኬሚካል    ማዳበሪያ    ተጠቃሚና    ኦርጋኒክ (ተፈጥነቱ) እንዲጠፋና የተለያዩ በሽታዎችና መሬቱ (ድንግል የኢትዮጵያ መሬት ኬሚካል እንዲጠጣ አድርገው የአለማዳበሪያም ምርት እንዳይሰጥ አደረጉት) የተፈጥሮ ማዳበሪያ የለመደውን ህዝብ ጎዱት የሚገርመው በግፍ ከአርሶ አደሩ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለራሳቸውና ለመሰሎቻቸው     ባለሥልጣናት     መናጠጫ  አደረጉት    ህውሃቶችም በለፀጉበት  የሚገርመው  ኦዲት  ሳይደረግ   ተመዝብሮ   ከ100ሺ   ሚሊዮን ብር በላይ ተመዘበረ አቶ ሰለሞንም ከነቤተሰቦቻቸው በካሊፎርኒያ ተመቻችቶላቸው ተሻገሩ የሚያሳዝነው ብዙ ደሃ ሠራተኞች ሚስጢር እንዳያወጡ ሲባል ተባረሩ ሰነዶችም እንዲጠፉ ተደረገ ትዝ የሚለኝ የሚስታቸው ወንድም እንኳን (አማኑኤል) የእነ አርሴናልን ጨዋታ አውሮፓ  ሄዶ  ይመለከት  ነበር፡፡

5.2. በአቶ  ሰለሞን  ተቀባ  ምትክ  ሌላ  ደም  መጣጭና  ግፈኛ  በእነ  አቶ  ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ተመልምለው አዲስ የዘረፋ ስትራቴጂ ቀይሰው በሥራ አስኪያጅነት አቶ ሙሉጌታ ቦጋለ፣ በጥረት  ዳይሬክተርነት  አቶ  ታደሰ ካሳ (ቀበሮው) የአማራ ክልልን ህዝብ ብሎም የሀገሪቱን ሀብት ለመሰሰል   ባለሥልጣናት   እና   ለራሳቸው   ከነቤተሰቦቻቸው   እንዲናጥጡበት  ተመቻቸ የመጀመሪያው  ተግባር  ቀደም  ሲል  የነበሩትን አቶ ፋሲል (የአምባሰል ም/ሥራ አስኪያጅ ሚስታቸው የአቶ ታደሰ ካሳ ዘመድ) ከአምባሰል ወጥተው በግል የፀረ አረም  እና  ተባይ  ኬሚካ ከአምባሰል በብቸኛ አከፋፋይነት እንዲሰጣቸው (ዳውንት ፒ ኤል ሲ) ተብሎ   ከውጪ   ሲገዛ ጀምሮ  ለአርሶ  አደሩ  እስኪከፋፈል  ድረስ  ዘረፋውን  አጧጧፉት፡፡  የሚገርመው  አቶ  ሙሉጌታ ቦጋለ  እየዘረፉ  ለበላይ  ባለሥልጣናት የሚያከፋፍሉት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ሲሆን ሚስጥር   ሊያውቁ   ይችላሉ   የሚባሉ   ሚስኪን   ባለሙያ   ሠራተኞች   በአጭር ጊዜ በየአመቱ እንዲባረሩ ተደርጓል ሴቶችንም እየቀጠሩ በርካሽ ወሲብ እስከ አለቆቻቸው መጫወቻ በማድረግ የኩባንያውን ገንዘብ ባልገውበታል የኩባንያው የተሸለ መልክ ያላቸው ሴቶች እነሱ ጋር ካልማገጡ እነደማይኖሩ ስለሚያውቁ የአባወራ ሚስቶች ሁሉ አብረው ማግጠዋል፡፡   ለምሳሌ

 

ዮርዳኖስ የምትባል የታደሰ ካሳ ፀሐፊ ምንም ብቃት ሳይኖራት  በዳሽን  ቢራ ከ30 ሺ በላይ ደመወዝና ጥቀቅማ ጥቅም እነዲከፈላት መኪና እንዲሰጣት ተደርጋለች አቶ ሙሉጌታ ቦጋለ ም ለአማገጧቸው ሴቶች በ3ና በ4 እጥፍ ደመወዝ  በማሳደግ  ያማግጣሉ  በዚህ  ያልተስማሙ  ሴቶች ከሥራ  እነዲባረሩ ተደርጓል የሚገርመው ቅጥር፣ እድገት፣ በኩባንያው ህግና በአዋጅ 377/96 ሳይን በራሳቸው ፈቃድ እና በመሰል ባለሥልጣናት ፈቃድ   ነው፡፡   ለምን   ትክክለኛ   አሰራር በሲስተም  እንዲሰፍን  አይደረግም  የሚል ቢገኝ ወዲያዉ ምክንያት ተፈልጎ እነዲባረር ማድረግ ባህል ሆኗል ይስሙላ  ቦርድ  የሚባለውም  ምንም  የሚለው  የለም  ይልቁን  ይተባበራል፡፡

5.3. የአምባሰል የውጪም ሆነ የሀገር ውስጥ ግዢ በአቶ ሙሉጌታ ቦጋለ የፈለጉትን ኮሚሽን

/ፈርቅ/ እየያዙ ይገዛሉ፡፡ በዚህም በቢሊዮኖች ብር የሚገመቱ የግል ሀብትና   የመሰሎቻቸው መበልፀጊያ  ሆኗል

ማሳያ የሚሆኑ ምሳሌዎቸን እንጥቀስ

 

5.3.1. ሰነዶችን እነዲያጠፉና እነዲያቃጥሉ ታማኝ አደግዳጊ አመራርና ሠራተኞች ተመርጠው የግፋቸውና   የምዝበራቸው   አስፈፃሚ   እነዲሆኑ   ተደርገዋል   በዚህም 1/ አቶ አንተነህ ዘገየ ምክትል 2/ አቶ አህመድ  ያሲን ምክትል 3/  አቶ አማኑኤል የማነ (ኤርትራዊ) የፋይናንስ ሥራ አስኪያጅ 4/ አቶ ዘነበ ሀጎስ (ኤርትራዊ) ኮርፖሬት ሰርቪስ 5/ ልዑል ገ/መስቀል  (ኤርትራዊ)  መካኒክ  ሓላፊ  6/  ወ/ሮ  ፅጌሬዳ  ከለለው  (ትግሬ  (ሴቶችን  በማቃጠርና ሰነድ  በማቃጠል ከታይፒስትነት  ወደ  መምሪያ  ሥራ  አስኪያጅነት በማሳደግ  መሳሪያ  ያደረጓት)  7/  አቶ  መልካሙ ያረጋል   (ሾፌር (ለማንኛዉም  ጉዳይ   ተላላኪና   ሚስጥር   ጠባቂ)   አመላላሽ   (ሴቶችንም  ሆነ የተዘረፈን) 8/ አቶ አበረ ይንገስ (የባ/ዳር ሥራ አስኪያጅ) በአማራ ክልል ህዝብ የተጫወተበት ባንዳ 9/ ተመስገን ጣፈጠ  ጽ/ቤት  ኃላፊኛ አድራጊ ና አደግዳጊ ፤

ከላይ የጠቀስኩትም ሆነ ለጊዜው ስማቸውን ያላስታወስኳቸው ጋሻ አጃግሬዎች የህዘብ ሀብት እንዲዘረፍ የድርሻቸውንም በመጠቀም ምስኪን ሰርቶ አዳሪ  ሠራተኛም  ገና  ሊያውቁ  ይችላሉ በሚል    ይሰቃያሉ    ይባረራሉ፡፡ለምሳሌ በ2005 ዓ.ም በአንድ ዓመት ብቻ ባለሥልጣኖቹ የሾሙዋቸዉ  የበታቾቻቸዉንም      መሣሪያ  እያደረጉ  120  ምስኪን  ሠራተኞች ያለምንም ጥፋት ተባረዋል ከ50 ያላነሱ ከደረጃ ዝቅ ተደርገዋል አንገት እነዲደፉ ተደርገዋል፤፤

ሌላው የሚገርመው ለባለሥልጣኖቹ መባለግ ምቹ ሁኔታ የሚያመቻቹ ሲታመሙ እንኳን በኩባንያው ሀብት እነደ ጌቶቻቸው የውጪ ሀገር      ህክምና      ይደረግላቸዋል፡፡

 

ለምሳሌ 1/ አማኑኤል የማነ (ፋይናንስ ሓላፊ) 2/ አበረ ይንገስ (የአማራ ክልል ሥራ አስኪያጅ) 3/ ስንታየሁ ቀጭኔ (የሠራተኛ ማህበር ተወካይ ነኝ ብሎ   ከባለሥልጣን   ጋር   የሚለጠፍ ከውጪ   ሀገር   መድሀኒት   እንደፈለገ ይገዛለታል) ዉጪ ሀገር ይታክማሉ ለማሳያ ከላይ የጠቀስኳቸውና ጥቂት መሰሎቻቸው ኩባንያው በቢሊዮን እነዲዘረፍ የሚያመቻቹና  የሚጠቀሙ ናቸው፡፡  ባለሥልጣናቱማ  ከነቤተሰቦቻቸው  ህክምናቸው  በውጪ  ሀገር  ነው፡፡

ደሀውና ምሁሩ ጀነራል ሀይሌ ጥላሁን ለህወሃት ስላላደገደገ  ና የማያምንበትን ግፍ ስለተከላከለ ከመከላከያ ተባሮ ከነቤተሰቡ ሲቸገርና ሲሰቃይ ከመለስ ሞት በኋላ በዚሁ መስሪያ  ቤት ቢቀጠር  እንደጠላት አይተው 1 ቤት ሳይኖረው ሲሞት እንኳን አስከሬኑ ከኪራይ ቤት ወጥቶ  ተቀበረ

ከላይ ስሙ የተጠቀሰው አበረ ይንገስ በአማራ ክልል ህዝብ ላይ በበለጠ ግፍ እነዲፈፀም  አድራጊ ፈጣሪ  ነው፡፡   ለምሳሌ  ኤክስፓየርድ   የሆነ   ፀረ   ተባይና   ፀረ አረም በሽተኛ እነዲሆን ለገበሬው እነዲሸጥ ግፍ ከመስራቱና በማድረግ   በባለሥልጣናቱ   የሚመሰገን   ነው፡፡   ለምሳሌ   ያመጣዉ ኢምፓክት ከሀገሪቱ ውስጥ በስኳር በሽተኞች ብዛት የተረጋገጠ ጥናት የሚያሳየው  የጎንደርን ህዝብ  ነው፡፡

ሌላው ግፍ ለማህበረሰቡ ጥራት ሌለው ማቴሪያል እየገዛ ያልተመጣጠነ ገንዘብ ከአማራ  ብድርና ቁጠባ      ተቋም      እየተበደሩ      ገበሬው      ሳይወድ      በግዱ ባለእዳ እየሆነ ይሰቃያል ለማሳያ ያህል፤

ሀ/ አቶ ሙሉጌታ ቦጋለ ከቻይና አገልግሎት የማይሰጥ የውሃ ፓምፕና ሳንክሽን ሆዝ ብቻ 18 ሚሊዮን ብር ኮሚሽን /ፈርቅ/  በልቶ  በግድ  አርሶ  አደሩ  እነዲገዛ  ተደርጓል  እነዲሁም  ጥራት የሌለው   ወኪንግ   ትራክተር ኮሚሽን  /ፈርቅ/  ተበልቶበት   እያለ   ግብርና   ቢሮ   ገዝቶ በአብቁተ(በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቌም) አማካይነት ለገበሬው እንዲሸጥ   ግዳጁ   ተጣለ፡፡ ይህም  ሆነ  በየስቶሩ(ማከማቻ  ክፍል)  ጥቅም  ሳይሰጥ  ተበላሽቶ  ተቀምጧል  በዚህም  በሚሊዮን የሚገመት  ብር  ተበልቶበታል፡፡  ተዘርፎበታል፡፡

ለ/ በከተማም የተሰራው ግፍ ለማሳያ ያክል ልጥቀስ

 

አስራ  ስድስት  ሺህ  ካሽ  ሬጅስተር  መረጃና  ጥራት  የሌለው  ለአማራ ክልልና አዲስ አበባ ብሎም ለተወሰኑ ሌሎች ክልሎች በገቢዎች መ/ቤት አስገዳጅነት ለነጋዴው እነዲሸጥ ተደርጎ በየጊዜው

 

ከህዝብ ገንዘብ እንዲዘረፍ እየተበላሸ በእነሱ እነዲጠገን እየተደረገ (በአምባሰል)    ህዝቡ እነዲበዘበዝ  ተደርጓል፡፡  እነሱ  ግን  (ባለሥልጣኑ)  እነ  አቶ  ሙሉጌታ  ቦጋለ    በውጪ  ሀገር  ግዢ ወደ  አስር  ሚሊዪን  ብር  ኮሚሽን  /ፈርቅ/  በልተውበታል፡፡  ግምታቸው  ከ20  ሚሊዮን  ብር  በላይ ስፔር  ፓርት  በሙስና  የገባ  በተድበሰበሰ  ሰነድ  (በትክክል  በማይታወቅ)  ከኔትወርካቸው  ወይም በሚያቀርቡአቸዉ  ዘርፈውታል  ገቢዎች  ያልተረከበው  በሺዎች  የሚቆጠር  ሰነድ  (ማጭበርበሪያ) ቃሊቲ  መጋዘን  ተቀምጧል፡፡

ሐ/ አግባባቸው በግልፅ ያልሆነና በተድበሰበስ ሰነድ ከ20 የማያንሱ ሪል ማሽኖቸች  /ትላልቅ የመስኖ   ማሽኖች/   በሙስና   ተገዝተው   ገብተው   በመጨረሻ   ለስኳር ኮርፖሬሽን በመመሪያ እነዲሸጡ ተደረገ የሚገርመው ልዑል ገ/መስቀል መካኒኩ (ኤርትራዊ) ተልዕኮ ተሰጥቶት ስፔሩ እነዲሰረቅ እንዲወጣ   ተደርጎ   ለስኳር   ኮርፖሬሽን   ስፔሩ   በተጭበረበረ   አኳኋን   ኖቫ   የሚባል ጋራጅ እየታረዱ ብዙ ገንዘብ እነዲዘረፍና እነዲወጣባቸው ተደርጓል፡፡  በዚህም  ከ120  ሚሊዮን ብር    በላይ    ተዘርፎበታል፡፡    የሚገርመው   ለአቶ   አባይ   ፀሐዬ   በመረጃ   በማስደገፍ   ጥቆማ ብንሰጣቸው ፀጥ አሉ፡፡ (በወቅቱ ስኳር ኮርፖሬሽንን ይመሩ ስለነበር)

መ/ ለአማራ ክልልና ለአዲስ አበባ ውሃ ስራዎች ቧንቧና አክሰሰሪ በአምባሰል በኩል  እነዲገዛ ተደርጎ   ጥራት   የሌለው   ከቻይና   የተገዛ   እና   ሙስና   የተሰራበት ስለሆነ ህዝቡ በማቴሪያሎቹ ብልሽት ውሃ እየቆመበትና እየተቋረጠበት   ይሰቃያል፡፡   ባለሥልጣኖቹ   ግን   የተጣራ   ውሃ እየጠጡ  /ሃይላንድ/ በህዝቡ ሃብትና ጫንቃ ተቀምጠው ይዝናናሉ ልጆቻቸውንም በውጭ  ሀገር አሞላቀው  ያስተምራሉ፡፡

ሠ/  ለብዙ  ባንኮች  የሚሆን  ተብሎ  ግዙፍ  ጄነረተሮች  በሙስና  ተገዝተው  አገልግሎት ሳይሰጡ ተበላሽተው ተቀምጠዋል ከዚህ ውስጥ የተሸለ የተባለውን     ለአቶ     ታደሰ     ካሳ     በነፃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ሌላ  አንድ  ደግሞ  ልዑል   ገ/መስቀል   /ኤርትራዊ/   ሸጦ    ተጠቅሞበታል   የቀረውም  ስፔር በራሱ ፈቃድ ጋራዝ ከፍቶ ያለምንም እገዳ ያውጣ እየተባለ ተቸብችቧል፡፡   እነ   አቶ ሙሉጌታ  ቦጋለ  ና  መሰሎቻቸው  በልፅገውበታል  ገንዘባቸውን  በውጭ  ሀገር  እያሸሹ  ይኖራሉ፡፡

ሌላው ለERP (ለሲስተም ኔትወርክ) ተብሎ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶ  ምንም እስካሁን   ተግባራዊ   አልሆነም   ይህም   ሙስና   ያመቻቹበት   ነው፡፡   በታደሰ   ካሣ   (ቀበሮው) ኔትወርክ  ተዘርፎበታል፡፡

 

ረ/  በአጠቃላይ  የተጠቀሱትን  ጥቆማዎች  ይዞ  የሚያጣራ  ነፃ  አካል  ቢገኝ   ይጋለጣል ለምሳሌ

/ለማሳያ/ ያህል ጠቀስናቸው እንጂ ምዝበራውና ግፉ ከገለፅነው ያልገለፅነው ይበልጣል፡፡ ለዚህም  ሰነድ  የሚያውቀው  ዘረፋ  ሁሉ  ይካሄዳል  ለምሳሌ  ለተወሰኑ  ኩባንያዎች  ፕራዶ  መኪና ግዢ  ከውጪ  ሀገር  ይፈፀም  ተብሎ  አምስት መኪናዎች ለኩባንያዎቹ ሲሰጥ አንድ  ተጨማሪ ፕራዶ  (6ኛ) ለአቶ ታደሰ ካሳ አቶ ሙሉጌታ ቦጋለ ውሰድ ብሎ ሰጥቷል የሚያሳዝነው በወቅቱ የመኪና ርክክብ የሚመለከተው የሎጀስቲክ ሠራተኛ ያለሰነድ ወጪ  ይሁን  ብሎ  በማዘዝ  ምን እነዳረጉት  ሳይታወቅ   በሥራ   ላይ እንዳለ (ወርቁ ቸርነት የጎጃም ልጅ) ድንገት ታሞና ፓራላይዝድ ሆኖ አሳካሚ   ሳይገኝ   ሞተ፡፡   በደሀ   ሠራተኛ   ግፍ   ይሰራል   ተቆጥረው   የማያልቁ ንብረቶች  ሰነድ  የማያውቃቸው  ብዙ  ናቸው፡፡

ሰ/ ከሁሉም በላይ ለአብነት ያክል ጠቃቅሰን እንጂ በህወሀቶች የተዘረፈና በልዩ ልዩ ግለሰቦች (እነ መተና እና ሌሎች የአመራሩ ሽርክና  የናጠጡ ነጋዴዎች መክፈል የሚገባቸው የዱቤ ሽያጭ የወሰዱትን  ብር  ገቢ ያላደረጉት ከ100 ሚሊዮን ብር  በላይ  አልተሰበሰበም)  መረጃው ሌላው  ይቅር እና ለመንግስት  ገቢ  መሆን  የሚገባው  ግብርና  ታክስ  ገቢ ባለመሆኑ እንኳ ኦዲት አድርጎ የሚያውቅ የገቢዎቸ ባለሥልጣን የለም ለምሳሌ የህንፃው ሊፍት የተገዛበት መረጃ የለም ጉምሩክም አያዉቀዉም  ብዙ  ጊዜ  ተበላሽቶ  የሚቆም  ነው፡፡  በዚህም  ተዘርፎበታል፡፡  ብቻ የህዝብ  ገንዘብ  በሆነ  ባልሆነው  ይዘረፋል፡፡

ሸ/ ለመድሀኒት ፋብሪካ ግንባታ ተብሎ የወጣውና ተግባራዊ ያልሆነው   በሚሊዮኖች   ብር ተበልቶበታል፡፡  ለምሳሌ  አርቲማዚያ  ማምረት  ተብሎ  (መድሀኒት  ግብአት  ተክልና  ምርት)   4 ቢሎዮን   ብር ወጥበት ምርቱም ምን እንደተደረገ መሳሪያዎቹም የት  እንደደረሱ የሚታወቅ የለም ኦዲት የሚያደርገም የለም አንድ ብር እንኳ ገቢ አላስገኘም፡፡

  1. ስለ ኩባንያው የሰው ኃይል ትንሽ ነገር አንበል ይኽውም እንደገለፅነው በኔት ወርክ የተጠላለፈ እና በዘመድ አዝማድ የታጠረ ከመሆኑ በላይ እዚህ ውስጥ   ዘመድ   ሌለው ባለሥልጣን   የለም   ማለት   ይቻላል፡፡   (ከቦርድ ጀምሮ እስከ  መምሪያ  ስራ  አስኪጅ  የፈለጉትን ያስቀጥራሉ)  ሌላው ሴቶችንም በማማገጥ ይቀጥራሉ የሚያሳዝነው ዘመድ የሌለውና ኔትወርክ የሌለው   በሙያው   የተቀጠረ   ሚስኪን   ሰራተኛ   በስቃይ   እድሜውን   እየገፋ   ሲመረው   እየለቀቀ ይሄዳል፡፡  እነ  ታደሰ  ካሳ  (ቀበሮው)  በአንፃሩ እንደ እነ መላኩ አለማየሁ እና እንደነ ዋሴ አባይ የመሳሰሉት ሚስት  እና  ልጅ  ሳይቀር  ያስቀጥሩበታል፡፡

 

ሲጠቃለል   በሀገር   እና   በወገን   ስም   እየተዘረፉ   መኖር   አይቻልም፡፡   ‹‹ፀሐይ ያየውን    ሰው ሳያውቀው   /ሳያየው/   አይቀርም   ››   ይላሉ   አበው ስለዚህ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በሰፈሩት ቁና መስፈር አለና ታሪክ እንዲመዘግበው በኩባንያው ውስጥ ሲጀመር ጀምሮ የነበርኩ ስለሆነ ከብዙ በጥቂቱ ይን ስለእውነት ዘግቤአለሁ፡፡ እድሜና ጤና  ከሰጠን  እነ ወርቅነህ መኮንን የሚባሉት ባለሥልጣናት ከጥቁር አባይ ትራንስፖርት ከመሰሎቻቸው ጋር የዘረፉትን ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ብቻ የአቅሜን ያክል   አጋልጣለሁ፡፡   የሌሎች   ካምፓኒዎችንም   ዝርፊያና   ግፍ   ለመግለፅ እግዚአብሔር እውነትን እንድገልፅ ይርዳኝ ዕድሜ ይስጠኝ!!

‹‹  ከፍጡራን  መጀመሪያ  ሙስና  የሰራ  ሳጥናኤል  ነው›› የሚሳነው  ለሌለ  ለመድሃኒዓለም !!

እነዚህ የሰይጣን ውላጆች ናቸው ከእምአእላፍ ዘጎሞራው!

አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ)