♦ሮቢት ላይ መሳሪያ አናወርድም ተብሎ ውጊያ አለ!
♦አርማጭሆ ከባድ ውጊያ ላይ ነው!
♦ከትግራይ የመጣው 4 ኦራል አጋዚ ሊማሊሞ ታገተ!
♦መሳሪያ እንዲገፉ ወደ ገጠሩ አቅንተዋል!
♦ለህዝባችን መረጃው በፍጥነት ይድረስና ይቅደማቸው!

ሙሉነህ ዮሃንስ

በ12 ኦራል የተጫነ የአጋዚ ሰራዊት ወደ ሰሜን ጎንደር ተሰማርቷል። ስድስቱ ወደ አርማጭሆ መስመር እያለፉ መሆናቸው ሲታወቅ ቀሪው ስድስት ኦራል ወደ ዳባትና ደባርቅ መስመር እያለፉ ነው። ከትግራይ በኩል ወደ ጎንደር በ4 ኦራል ተጭኖ ሲመጣ የነበረው አጋዚ ሊማሊሞ ላይ መንገድ ተዘግቶበት መታገቱ ታውቋል። ወያኔ ጎንደር ላይ ሙሉ ጦርነት በድጋሜ ከፍቷልና ከህዝባችን ጎን እንሰለፍ። በቻልነው ሁሉ እንደግፍ።

በዚያ አካባቢ የሚኖር አንዱን ሰላማዊ ገበሬ የወያኔ ወታደሮች ሊያስሩት ሲሄዱ ገበሬዉ አንሰጥም በማለቱ ግጭቱ ተቀስቅሷል። ከፍተኛ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ቅጥረኛው ወታደር ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርጓል።

የአጋዚ ሰራዊት ተልእኮ መሳሪያ ለማስወረድ እንደሆነ ስለታወቀ የገጠሩ ገበሬ ህዝብ በተለይ ከፍተኛ ጥንቃዌ እንዲያደርግ ሁሉም ህዝብ ተረባርቦ መልእክት ያድርስ። የገቢያ፣ የማህበራት፣ የሰንበቴና ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች የተለየ ደፈጣ አድርገው መሳሪያ ሊገፉ እንዳሴሩ ታውቋልና ልዩ ጥንቃቄ ይደረግ።

የጎንደር ህዝብ የሃገር ድንበርን ከወረራ፣ ነፃነትና ክብሩን እንዲሁም ህልውናውን ሲያስጠብቅ የኖረው ጥሪቱን አሟጦ በሚታጠቀው መሳሪያ ነው። ይህ ጀግና ህዝብ ልክ እንደ መይሳው እጅ አይሰጥም። እንኳን መሳሪያውን ዱላውን አያስነካም። በ11ኛ ሰአታቸው ተቅበዝብዘው የሚሄዱት አጋዚዎች እድለኞች ከሆኑ ነፍሳቸውን አትርፈው መሳሪያቸውን ግን ተማርከው ሊመለሱ ግድ ይላቸዋል። ቢሆንም ለገበሬው ህዝባችን ፈጣን መረጃ ቀድመን በየ ቦታው በማዳረስ ልንረባረብ ይገባል። ዝም እንዳትሉ!

እጅ አንሰጥም!