March 16, 2018

የፓርቲውን ሊቀመንበር ብሎም የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመርጠው የኢህአዴግ ምክር ቤት በመጨው ሳምንት መጀመሪያ እንደሚሰበሰብ ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ — የፓርቲውን ሊቀመንበር ብሎም የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመርጠው የኢህአዴግ ምክር ቤት በመጨው ሳምንት መጀመሪያ እንደሚሰበሰብ ተገለፀ፡፡እየተካሄደ ያለውን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ አስመልክተው ለመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን አስተያየት የሰጡት የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው ይሄንን የገለፁት፡፡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ማን መመረጥ እንዳለበት ለመግባባት የሚሞክሩት ከምክር ቤቱ ስብሰባ በፊት ነው ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ያብራሩት ደግሞ የገዥው ፓርቲ የቀድሞ አመራር አባል አቶ ገብሩ አሥራት ናቸው፡፡
ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ። VOA Amharic
