አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ቶማስ በቀለ

ሌላም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አራታችን ተስማምተን ነው
እየተባለ ለሚዲያ የሚነገረው አራታችን መቸ የት ነው
የተስማማንው? በማለት ከለማ መገርሳ ከአብይ አህመድ ጋር ህወሀትን እና ባርነትን ምርጫቸው ያደረጉትን ደህዴንን ትንፋሽ አሳጥቷቸዋል።
ያልተዘመረለት ያልተዘፈነለት ልበ ሙሉ ደፋር ገዱ አንዳርጋቸው። ይሄን ሰው ጎበዝ መላው የአማራ ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን ልንጠብቀው ግዴታ አለብን

ህወሓት ከሌሎች ክልሎች በማንሳት ወደ ራሱ ክልል ሊወሰደው የነበረው የመብራት ዕቃ / ትራንስፎርመር / በሕዝብ ትግልሳይሳካለት ቀረ ፡፡

ቶማስ በቀለ

መጋቢት 07ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሲሆን የህወሓት መብራት ኃይል ሰራተኞች ያለ ሕዝብ ፍቃድ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ ሙሴባምብ ከተማ በደርግ ጊዜ የተተከለን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ የሆነን የመብራት ትራንስፎርመር በመንቀል ወደ ትግራይ የመውሰድ ሙከራ በሕዝብ ቁጣና ተቋውሞ ገጥምት ለጊዜው መውሰድ አልቻለም ፡፡

በዚህ ግጭት የተወሰኑ ከትግራይ የመጡ የመብራት ኃይል ሰራተኞችና ዕቃውን ለመጫን ያመጣቸው 2 ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ፡፡ ሁኔታው ከፍ ወዳለ ግጭት ሲያመራ የህወሓት ወታደሮች ጣልቃ በመግባት ከ30 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ወጣቶችን አፍነው የተወሰኑትን ወደ ሳንጃ ሲወስዱ የተወሰኑትን ደግሞ ወደ ጎንደር ተወስደው እስካሁን አድራሻቸው አልታወቀም ፡፡

በመሆኑም የአካባቢው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ ጫካ የገባ ሲሆን እስከአሁን ከተማዋን የህወሓት ወታደሮች እንደሰፈሩባት ነው። ይህ ድርጊት ክልሉን እየመራሁ ነው የሚለው ብአዴን እንደማያውቅ የመረጃ ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል ፡፡ በአካባቢው ውጥረት እንደነገሰ ይገኛል ፡፡


ድል ለሕዝብ !!!