የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል
የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 27 የጨለማ ዘመን አሳር ፍዳውን ያሳየው የወያኔ ጀግንነት ሳይሆን የሃያላኑ ሀገራት ቀጥተኛና ሁለንተናዊ ድጋፍ መሄኑ ድብቅ አይደለም።
ከነዚሁ ባእዳን ሃይላት ውስጥ የእንግሊዝ መንግስት ሸፍጥ በዋነኝነት ይጠቀሳል፤ በተለይ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል እንግሊዝ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የሱማሌ ሚሊሻ በሚል ሽፋን ከትጥቅ እስከ ስንቅ በመስፈር አስታቅፋ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የደረሰባቸውንና እየደረሰባቸው ያለውን ማህበራዊ ምስቅልቅል እያየንና እየሰማን እንገኛለን፤ እንዲሁም ከነፃነት አርበኞቻችን ተምሳሌት የሆነው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በግፈኞቹ እጅ ከወደቀ እንሆ ሶስት አመትን እስቆጥሯል፤ እኛም ተቃውሟችንን ስናሰማ አመታትን አስቆጥረናል፤ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት የሚገባው የእንግሊዝ መንግስት በተለይም አሁን ያለውን የእስረኞችን መፍታት ተንተርሶ ግፊት በማድረግ ከቤተሰቡ እንዲቀላቀል ማድረግ ሲገባቸው ምንም የሚታይ ነገር ባለማድረጋቸውና ሌላም ተዛማጅ ሃገራዊ እውነቶችን ለአለም በተለይ ለእንግሊዝ መንግስት ለማሳወቅና ተቃውሟችንንም ለማሰማት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጅቷል እርሶም በቦታው በመገኘት አጋርነትዎን እንዲያሳዩ ተጠርተዋል።
ቦታ – ኢንግሊዝ ኤምባሲ
አድራሻ – 3100 Massachusetts Ave NW
Washington, DC 20008
ቀን – ሰኞ March 26th, 2018
ሰዓት – 9፡00 AM
የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!
