March 19, 2018

የአስችኳይ ጊዜ አዋጁ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ በህወሃት የተወሰነ ዉሳኔ ነው። በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የኦህዴድ አመራርና በአቶ ገዱ የሚመራው የአማራ ክልል መስተዳደር አስቸኳy ጊዜ አዋጁን አለትቀበለም። ሰሞኑን እየተደረገ ባለው የኢሓዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቶቴ ስብሰባ ” አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አራታችን (የኢሓዴግ ድርጅቶች) ተስማምተን ነውእየተባለ ለሚዲያ የሚነገረው አራታችን መቸ የት ነውየተስማማንው? ” የአቶ ገዱ ቡድን ከለማ ቡድን ጋር በመሆን የጦፈ ከክርክር ከሕወሃት እያደረጉ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ሕወሃት እነ ገዱንና ለማን በስብሰባ አጥምዶ ግን ከስብሰባ ዉጭ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩን ቀጥሏል። ይዘጋል የተባለው ማእለካልዊ ዜጎች እየታጎሩ ነው። ባለፉት ጥቂ ቀናት ውስጥ ከታሰሩ ወገኖች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡

1. ታዬ ደንደአ (የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ ሃላፊ)
2. ስዩም ተሾመ(ጦማሪና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
4. ሙሉቀን ቴክኖ (ቴክኖ የቅፅል ስሙ ነው)
5. አብርሃም (መንገድ ትራንስፖርት ሰራተኛ)
6. አብዮት ጥላሁን
7. መሳፍንት መዝገቡ (ዱቼ)
8.ማርቆስ አብርሃም