March 19, 2018
ባለው እሁድ ማለትም ማርች 17 2018 በዋሽንግቶ ዲሲና አካባቢው ጤና ለጣና 2018 በሚል መርህ በተደረገውና በርካታ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችና ኢትዮጵያውያን በተከኙበት በተካሄደው ዝግጅት ከትኬት ሽያጭ፣ ከእርዳታ እና ከተለያዮ ቁሳቁሶች ሽያጭ ከ140 ሺህ ዶላር በላይ ተገኝቷል። እንዲሁም ቁጥራቸው 15 የሚሆኑ በዲሲና አካባባው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጣናን ለመታደግ የለገሱትን ገዝንዘብ ገቢ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በተጨማሪም በዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኘው የመድሃኒ አለም ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች፣ ቀሳውስት እና ምንመዕናን ከአባላት በሚሰበሰብ ዋጋው 70 ሺህ ዶላር የሚሆን አንድ ማሽን ገዝተው ለማበርከትና ጣናን ለመታደግ እየተደረገ ያለውን አለም አቀፍ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቃል መግባታቸው ዓለማቀፉ የጣና መልሶ ማቋቋም ማህበር (Global Coalition for Lake Tana Restoration) ገልጿል።
ጣና ሐይቅን የመታደግ ዓለም አቀፍ ጥሪ – ጤና ለጣና፤ ያለ ልዩነት ለጣና ጤንነት! GOFUNDME ገጽ
ቪድዮ – በዋንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጤና ለጣና 2018 የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግችት በከፊል ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=bQvwaGsMFAY
ምንጭ ፡ ወልቃይት
