ይድረስ ለፋኖ፣ ቀሮና ዘርማ ወጣኒያን! መንግስት የሚባለው ተቋም አርጅቶ ለመበስበሱ አንዱ አስረጅ ከህዝቡ መሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መነጠሉና ጥቂት ነፍጥ ባነገቡ ነፍሰ በላዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ የእለት እለቱን መኖር መጀምሩ ነው። ይዅውስ እንዴት ይገለጣል ቢባል የሚያውጀውን አዋጅ የሚተገብር ቀርቶ የሚሰማ መጥፋቱ ነው። አስቃለሁ ብሎ መድረክ ላይ የወጣ ቀልደኛ የሚስቅለት ቀርቶ ፈገግ የሚልለት ሰው ቢያጣ የሚደርስበት አይነት መቀዣበር ውስጥ ህወሃት ወድቆ መገኘቱ የመጨረሻውን እርሾ ጨልጦ ለመጋገሩና እህል ውሃው ለማለቁ አንዱ መገለጫው ነው።

ዛሬ በተራቸው ህዝቡን የመምራት የሞራል የበላይነቱን የጨበጡት ደመዎዝ የማይከፍሉት፣ ቋሚ ቢሮ ኖሮዋቸው ማንነታቸው የማይታወቁ፣ ነገር ቃላቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል መሬት ላይ የማይወድቅና ህዝብ የሚከተላቸው ፋኖ፣ ቄሮና ዘርማ የመሳሰሉት የህዝብ አብራክ ናቸው። በጎቸ ድምጼን ያውቁታል” እንዲል ህዝቡ ባይነ ስጋ ባያያቸውም ቅሉ ድምጻቸውን ይለያቸዋል። “ነፋስ ሲነፍስ ድምጹን ትሰማለህ፤ ከወዴት እንደሆን ግን አታውቅም” እንደተባለ ህዝቡ እነርሱን ቃላቸውን ሰምቶ ለመከተል በቁመተ ስጋ ልያችሁ ልለያችሁ አላለም። የሞራል የበላይነት ባለበት እምነት አለ። እምነት ባለበት ደግሞ ሌላ ማረጋገጫ አያስፈልግምና። ጀግና በክፉ ቀን እንዲወለድ ይኽ ድቅድቅ ጨለማ አምጦ የወለዳቸው ወጣኒያን ግማደ መስቀሉን ተሸክመው የህዝባችንን ተስፋ ትንሳኤ ዳር ከሚያደርሱት መካከል አንድኛዎቹ እንደሆኑ ህዝቡ በደመነፍሱ የተቀበለው ጉዳይ ነው።

ትናንት በኢሳት እንደተዘገበው የገዢው መንግስት ጉጅለዎች በመሃል አገር ዘርፈው ያቁምትን ንብረት እየሸጡ ወደ ደደቢት መመለስ መጀመራቸውን ከባህር ዳርና አካባቢው ምንጭ ጠቅሶ ዘግቦታል። ይኽ በእጅጉ የሚያስቆጭ ነው። የተሰረቀን ንብረት የገዛ የሸጠ ያሻሻጠ እኩል ወንጀለኛ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ይደነግጋል። ፋኖ ቄሮና ዘርማ በማያልቀው ትጋታቸው በማይታበለውም አንደበታቸው በዚህ ጉዳይ ቁርጥ ያለ አቋም ካልያዙ ትግሉ ላይ የራሱን ጥላሸት ማሳረፉ አይቀርም። በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ከወያኔና ጉጅሌው ጋር የተነካካ ማንኛውንም የሚንቀሳቀስም ይሁን የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ፣ ያሻሻጠ፣ በወለድ አገድ የያዘ ወይንም በአደራ መልክ የተረከበ ሰው ውርድ ከራሴ መሆኑን አውቆ ከዚህ በኋላ ለሚወሰድበት ማንኛውንም አይነት የማያዳግም እርምጃ ሃላፊነቱ የእርሱና የእርሱ ብቻ መሆኑን አውቆ ከዚህ አይነት በአገርና በህዝብ ሉአላዊነት ላይ ከሚፈጸም ብሔራዊ ወንጀል እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ ጥብቅ የሆነ ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላፉ ይሁን። አደራ!!!