በተለይም ከደርግ ውድቀት ወዲህ በኘሮ. (..) መስፍን ወ/ማርያም ፊት አውራሪነት የአማራ ሕዝብ ህልውናንና ማንነትን የሚክዱ ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች አማራ የሚባል ብሔረሰብ ወይም ነገድ የለም!” በማለት በአማራ ሕዝብ ማንነት ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደቆዩና እየፈጸሙም እንዳሉ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

በተለይ ፕሮ. (..) መስፍን ተቆርቋሪ በመሰለ አቀራረብ ስልሳዎቹን የጃንሆይ ምኒስትሮች (ዋና ሹሞች) ከማስፈጀት ጀምሮ በአማራ ሕዝብ ላይ በስውር ጥቃት ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩ የአማራ ሕዝብ ጠላት ናቸው፡፡ ባለፈው ለእኒህ ሰው በጻፍኩት ማስጠንቀቂያ ላይ አስተያየት ከሰጡ ወገኖች ጋር ስመላለስ እንደገለጽኩት ሰውየው ሌላው ቀርቶ ኢሰመጉን መሥራች አባል ሆነው በሊቀመንበርነት ይመሩ የነበሩት ወያኔና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን የዘር ማጥፋት ጥቃት ተቆርቋሪ በመሰለ አቀራረብ ተአማኒነትን በተላበሰ ሽፋን ስልታዊ በሆነ መንገድ የሚፈጸመውን ጥቃት አፍኖ ወይም የተፈጸመውን ፍጅት በትክክል እንዳይዘገብና ገጽታውን በትክክል በሚገልጽ መልኩ ተገቢው መግለጫና ዘገባ (report) ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዳይቀርብ የማድረግ ሸፍጥ የተሞላበት ደባ ሲፈጽሙ ነው የቆዩት፡፡

ይሄም በመሆኑ ሰውየው ሊቀመንበር በነበሩበት ዘመን ለአንድ ጊዜም እንኳ ቢሆን ኦነግ ወያኔና ሌሎች ግብረአበሮቻቸው በተለያየ ጊዜ በየቦታው ያንን ያህን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ ጥቃቱ በአማራ ዘር ላይ ያነጣጠረና ድርጊቱም የዘር ማጥፋት ጥቃት መሆኑን የሚገልጥ መግለጫና ዘገባ ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚያደርጉት ኢሰመጉ እንዳያወጣ በማድረግና ለአጥቂዎቹ ሽፋን በመስጠት ሰውየው ፀረ አማራ ተልእኳቸውን ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ ኢሰመጉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው በአማራ ላይ ጥቃት ሲፈጸም በአማሮች ላይ ጥቃት ተፈጸመ!” እያለ መዘገብና መግለጫ ማውጣት የጀመረው፡፡ ከዚያ በፊት ግን በዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ!” እያለ ነበረ ይዘግብና መግለጫ ያወጣ የነበረው፡፡ ሰውየው ይሄንን ሁሉ የተቀናበረና ሸፍጥ የተሞላበት ስውር ጥቃት በአማራ ሕዝብ ላይ ለምን እንደሚፈጽሙ ትግሬ መሆናቸውን በቅርቡ ከተናገሩ በኋላ ግልጽ ሆኗል፡፡

እኒህ ሰውየ የእስከዛሬው ሳይበቃቸው ፀረ አማራ ጥቃታቸውን ዛሬም በመቀጠል በትናንትናው ዕለት የአማራን ሕዝብና የሠማዕቱን ፕሮ. (..) ዐሥራት ወ/ኢየሱስን ስምና ክብር በእጅጉ የተዳፈረና ያዋረደ ሥነምግባርና ግብረገብነት የጎደለው ጽሑፍ በድረ ገጽ አውጥተዋል፡፡ ይህ በእኒህ ሰውየና በመሰሎቻቸው በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የአማራ ሕዝብን ለሥነልቡናና ለወላዊ ሰብእና ጉዳት እየዳረገ ያለ ህልውናን የመካድ የማንነት ጥቃት መቆም ስላለበት አማራ የለም!” የሚሉ ግለሰቦችን የሕዝባችንን ፊርማ በማሰባሰብ መክሰስ እንዳለብን ሐሳብ አቀርባለሁ፡፡

አውቃለሁ በዚህ በወያኔ አገዛዝ ዘመን ፍትሕ በሀገራችን የለም! ይሁንና ፍትሕ ባይኖርም ፍርድን ለታሪክና ለእግዚአብሔር ለመተው ፍትሕ እንደሌለ እያወቅንም በአማራ ሕዝብ ላይ ህልውናውንና ማንነቱን በመካድ ሥነልቡናውንና ወላዊ ሰብእናውን በመጉዳት ጥቃት እየፈጸሙብን ያሉ ማሰብ የተሳናቸውን ሥነምግባር የጎደላቸውን ግለሰቦች እንከሳለን!!!

በዚህም መሠረት በቅድሚያ አማራ የለም!” በማለት በሕዝባችን ላይ የሥነልቡና ጥቃት ሲፈጽሙ የኖሩና እየፈጸሙ ያሉ ይሄንን ወንጀል ለመፈጸማቸው በቂ መረጃ የተያዘባቸውን ግለሰቦች ሙሉ የስም ዝርዝር ከነመኖሪያ አድራሻቸው አስተያየት (comment) መስጫ ሳጥን ላይ በማስቀመጥ ለሕዝባችን ያለንን ፍቅር፣ ክብርና ተቆርቋሪነት እንድንገልጽ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

የስም ዝርዝራቸውንና መረጃዎችን ለቅመን ከያዝንና ካሰናዳን በኋላ የሕዝባችንን ፊርማ በማሰባሰብ ቀጥታ ክሳችንን የምንመሠርት ይሆናል!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com