ከሚኪ አማራ


በባለፉት ሁለት ምርጫዎች መብራት ሊገባላችሁ ተብለዉ ፖል ቆሞ ገመድ ተዘርግቶ ንብረቱ ከጥቅም ዉጪ ሆነዉ የቀሩትን የተወሰኑትን
————————-
1. አማራ ክልል፡ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከ 7 አመት በፊት የመብራት ፖል ተክለዉ የምሰሶ እንጨቱም እያረጀ የወደቀ
2. አማራ ክልል፡ ባንጃ ወረዳ ጉበላ አካባቢ ፖል ከተተከለ 6 አመት የሞላዉ ፖሎችም ስራ ሳይሰሩ አርጅተዉ ወዳድቀዋል
3. አማራ ክልል፡ ከጎንደር ላይ አርማጭሆ ወደ ሮቢት የሚሄድ የገጠር ከተሞች ፖል ከተተከለ 11 አመት የሆነ
4. አማራ ክልል፡ ደጀን አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች የመብራት እንጨት ተተክሎ እየበሰበሰ ካለ 11 አመቱ
5. አማራ ክልል ፡ ከደሴ ተነስቶ በዙሪያዉ ላሉ የገጠር ከተሞች ፖል ከተዘረጋላቸዉ 5 አመቱ
6. አማራ ክልል፡፡ ከደብረታቦር ወደ ፋርጣ ቀበሌዎች ፖል ከተተከለ 6 አመት ያለፈዉ
7. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ከአንበሳሜ ከተማ -ሰኔማርያም ቀበሌ እና ጎሃ ቀበሌ እንዲሁም ደወል ቀበሌ መጀመሪያ የተተከለው ፖል ኤሌክትሪክ ሳይለቀቅበት በማርጀቱ ሁለተኛ ዙር አዲስ ፖል ተተክቶ እስካሁን የኤሌክትሪክ ሀይል ያልተለቀቀበት
8. አማራ ክልል፡ ከ ከላላ አቤት ወሃ(ደቡብ ወሎ) ፖል ከተተከለ 4 አመት
9. አማራ ክልል፡ ሰሜን ሸዋ ካሉት ወረዳዎች ውስጥ አጣዬ/ኢፍራታ እና ግድም ወረዳ አላላ ይምለዋ ቀበሌ ከ7 አመት በፊት ፖል ተተክሎ የአካባቢው ሰው የመብራት ብር አዋጥቶ ለመንግስት ግቢ ካደረገ 7 አመት ሞላው።
10. አማራ ክልል፡ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ የመብራት ፖልና ገመድ ከተዘረጋ ወደ 6 ዓመት ሁኖታል ሆኖም ግን መብራት የለዉም ፖሎቹ ወዳድቀው ከጥቅም ዉጪ ሆነዋል፡፡
11. አማራ ክልል፡ በሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀርቡ ወልዴ ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፖልና ገመድ ተዘርግቶ ነገር ግን አገልግሎት የማይሰጥ፡፡
12. አማራ ክልል፡ ምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሶ ወረዳ ግንደወይን ከተማ የዛሬ 7 አመት የቆመዉ ፖልና ገመድ እንጅ መብራት ተለቆበት የማያዉቅ
13. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ አካባቢ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ምሰሶወችና ገመዶች ያለጥቅም ተበላሽተዋል፡፡
14. አማራ ክልል፡ ደ/ጎንደር ከእስቴ ወደ ቆማ የተተከለው ፖል ምርጫ ሊደርስ ሲል እንቅስቃሴ ይጀምሩና ምርጫው ሲያልፍ ይተውታል 8 ዓመት ሞላው ፖሉም እየወደቀ ነው፡፡

ጭራሽ መብራት የሚባል ገብቶላቸዉ የማያዉቁ ወረዳወች
—————————-
1. ሰሜን ጎንደር ዞን
-በየዳ ወራዳ
-ጠለምት ወረዳ
-ምስራቅ በለሳ
-ምእራብ አርማጭሆ
-ላይ አርማጭሆ
-ጃናሞራ ወረዳ
2. ዋግህምራ ዞን
-ሰሃላ ሰየምት ወረዳ
3. አዊ ዞን
-ዚገም ወረዳ

መብራት ገብቶላቸዉ ከዛም እስከ ሁለትና ሶስት አመት በላይ የተቋረጠባቸዉ ወይም አንዴ ብቻ ብልጭ ብሎ በዛዉ የጠፋባቸዉ
——————————
1. ምእራብ ጎጃም ዞን- ቋሪት፤ደጋ ዳሞትና ሜጫ ወረዳ
2. ሰሜን ወሎ- የቡግና ወረዳ
3. ደቡብ ጎንደር-ታች ጋይንት
4. አዊ ዞን-አየሁ ጓጉሳ ወረዳ፤አንክሻ ወረዳ፤ጓንጓ
5. ምስራቅ ጎጃም- ይቦኝ ወረዳ (ድጓጺወን ዋና ከተማዉ)፤ እነሴና ሳር ምድር (መርጦ ለማሪያም ከተማ)፣ ሁለት አጅ እነሴ
6. ሰሜን ጎንደር-ምእራብ በለሳ፤ጭልጋ፤ ታች አርማጭሆ

የመብራት ማከፋፈያ sub-station ሊሰራላቸዉ ተብሎ ከ10 አመት በፊት ከአለም ባንክ እርዳታ ተደርጎላቸዉ ነገር ግን ገንዘቡ ተበልቶ ማከፋፈያዉም ሳይሰራላቸዉ የቀሩ፡፡ ይሄንም በባለፈዉ የአማራ ክልል መንግስት በቴሌቪዥን አቅርበዉት ነበር፡፡
—————-
1. ሰሜን ጎንደር- የሻዉራ ማከፋፈያ ጣቢያ
2. አዊ- የዳንግላ ማከፋፈያ ጣቢያ
3. ደቡብ ወሎ- የኮምቦልቻ ማከፋፈያ ጣቢያ
4. ምስራቅ ጎጃም- የደጀን ማከፋፈያ ጣቢያ
5. ሰሜን ወሎ- የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ
6. ምእራብ ጎጃም- የቡሬ ማከፋፈያ ጣቢያ
7. ሰሜን ጎንደር- የጭልጋ ማከፋፈያ ጣቢያ
8. ምእራብ ጎጃም-የፍኖተሰላም ማከፋፈያ ጣቢያ

ተጨማሪ አንዳንድ እዉነታዎች
—————-
-አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ በአማራ ክልል ዉስጥ በአማካኝ ለ 10 ወረዳ ያገለግላል፡፡ለምሳሌ ደቡብ ወሎ የአቃስታ ማከፋፈያ ጣቢያ ለ 11 ወረዳ ያገለግላል፡፡ ለዛዉም ወፍጮ ለማስነሳት እንኳን የማይችል በ 66 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ መስመር፡፡ ለዚህም ነዉ አብዛኛዉ ክልሉ ላይ መብራት በፈረቃ የሚሰጠዉ፡፡ አንድ ወረዳ መብራት እንዲያገኝ እስከ 2 ወር ፈረቃ ይጠብቃል፡፡ 10 ወረዳ እስከ 4 ሚሊየን ህዝብ ወይም የትግራይ ክልልን ህዝብ የሚያክል ይሆናል ማለት ነዉ፡፡

-ህዝቡ ወፍጮ ለማስፈጨት ከአንድ ወረዳ መብራት አለበት ከተባለዉ ወረዳ እስከ ሶስት ቀን በመጓዝ አስፈጭተዉ ይመጣሉ፡፡

-ክልሉ ላይ ወደ 120ሺህ የሚሆን ህዝብ ገንዘብ ለትራንስፎርመር፤ ኤሲ እና ቆጣሪ አዋጥቶ ለ9 አመት እየጠበቀ ይገኛል

-ክልሉ አንድ ከተማ ላይ አንድ ትራስፎመር ከተቃጠለ በአማካኝ ለመጠገን ወይም ለመቀየር 4 አመት ይፈጃል (የክልሉ መንግስት ሪፖርት ነዉ)

-ሱዳን ያለማቋረጥ 100 ሜጋ ዋት ሃይል ከኢትዮጵያ ለሱ ተብሎ ጎንደር አዘዞ ላይ በተሰራ የማከፋፈያ ጣቢያ አማካኝነት ያገኛል፡፡ ወያኔ በአመት አስከ 100 ሚሊየን ዶላር ይሰበስባል፡፡

-ለሱዳንና ለጅቡቲ የሚሸጠዉ 200 ሜጋ ዋት ሃይል አሁን አማራ ክልል ባለዉ እየተቆራረጠ በሚሰጠዉ መብራት መጠን ብንወስደዉ እስከ 6 ሚሊየን ህዝብ ይጠቅም ነበር፡፡

– በአሁኑ ሰአት 1/3ኛዉ የኤሊክትሪክ ሃይል አማራ ክልል ዉስጥ ይመረታል፡፡ ይሄን ኤሌክትሪክ ሃይል ለማምረት በመቶ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ገበሬ መሬቱን ለግሷል፡፡ እያንዳንዱ ገበሬ ከበለስ ተነስቶ ወደ ትግራይና አዲ አባባ የሚወስደዉ ማስተላለፊያ መስመር መሬቱ ላይ ያለምንም ካሳ ተተክሎበታል፡፡

መልካም ቀን

የብርሸለቆ የእርሻ ልማትና የአማራ ገበሬወች

 

 

 

 

 

 

 

ከሚኪ አማራ

————————–—-
የብር ሸለቆ እርሻ ልማት በፍኖተሰላም አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የእርሻ ልማት ነዉ፡፡ባጋጣሚ በዚህ እርሻ ልማት ምክንያት መሬቱን ተቀምቶ ፍኖተ ሰላም ከተማ የአንድ የመንግስት ቢሮ ዉስጥ በጥበቃነት ተቀጥሮ 6 ልጆቹን የሚያሳድግ ምስኪን አማራ እንዴት ከመሬቱ ተነቅሎ እንደተባረረ አዋራኝ፡፡ ኑሮየን አስተካክል ይሆናል ብሎ ወደ ደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ሄዶ ለተወሰነ አመታት እዛ እንደኖረ ከዛም መሬቱና ምርቱ በሳት ተቃጥሎበት የዛሬ ሶስት አመት አካባቢ እንደተመለሰ አጫወተኝ፡፡

የእርሻ ልማቱ የማን ነዉ
————————-
የብርሸለቆ እርሻ ልማት ጃቢጠናህ ወረዳ ዉስጥ በፍኖተ ሰላምና ቡሬ መካከል ወደ ደቡብ ከማንኩሳ ከተማ ከ5-8 ኪሎ ሜትር ተገንጥሎ የብር ወንዝ ተፋሰስ ላይ በሰፊዉ ተንጣሎ የሚገኝ የእርሻ ቦታ ነዉ፡፡ ይህ ሰፊና ደልዳላ የእርሻ መሬት ቀይ አፈር (ላይ በር) እና ጥቁር አፈር (ታች በር) ተብሎ የሚከፋፈል ሲሆን በሁለቱ መካከል የወያኔ ወታደር ማሰልጠኛ (ብር ሸለቆ) ይገኛል፡፡

የላይኛዉ ክፍል ወይም ላይ በር ተብሎ በአላሙዲ ስም የተያዘ ነገር ግን የትግራይ ባለስልጣናት እንደሆነ ሰዉ ያዉቃል የተለያየ የእርሻ ልማት ያለዉ ሲሆን በቆሎ፤ጤፍ፤ማንጎ፤ሻይ ቅጠል እንዲሁም የቅባት እህሎች ይመረቱበታል፡፡
የታችኛዉ ክፍል ታች በር እጅግ ሰፊ የእርሻ ቦታ ሲሆን በሺወች የሚቆጠሩ የአማራ ገበሬዎች በ19 90ወቹ መጨረሻ አካባቢ ተፈናቅለዉ ወደ ጉራ ፈርዳ እንዲሰደዱ የተደረጉበት ጡረታ በወጡ የህወሃት ኮሎኔሎችና አሁን እዛዉ ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ዉስጥ ያሉ የህወሀት መኮነኖችና እንዲሁም በነሱ አማካኝነት ከትግራይ በመጡ ቤተሰቦቻቸዉ የተያዘ ሲሆን፡፡ በተለይ በ1999 አ.ም ባካባቢዉ በነበሩት የህወሀት ወታደሮች ከብቶቻቸዉን እንዲያስሩ፤የሚያርሱትን መሬት እንዳያርሱ ጥብቅ ትዛዝ አስተላልፈዉ ገበሬዎች እንዴት እርስታችን ሳንሞት በቁም እንወረሳለን ብለዉ በማመፃቸዉ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት የደረሰባቸዉ ሲሆን ይሄን ያነሳሳሉ የተባሉ የአካባቢዉ ታዋቂ ሽማግሌወችም የደረሱበት ሳይታወቅ ይሄዉ 10 አመት ሆናቸዉ፡፡

የአማራ ገበሬወች ጉዳይ
————————
ከላይ አንደጠቀስኩት በጠመንጃ አፈሙዝ መሬታቸዉን በጠራራ ፀሀይ የተዘርፉ ሲሆን ግማሾቹ ወደ ደቡብ ክልል ተሰደዉ ወያኔ እዛም ተከታትሎ ሄዶ ከጉራ ፍርዳ እንዳባረራቸዉ እናዉቃለን፡፡ ነገር ግን መጀመሪያዉኑም ከመኖሪያቸዉ ያፈናቀላቸዉ የራሱ የህወሀት ወታደርና ባለሃብት ነበር፡፡ ግማሾቹ እዛዉ ከወያኔ መኮነኖችና መሬቱን ከወሰዱት የትግሬ ባለሃብቶች እንደገና በኪራይ በመከራየት ሲያርሱ ይኖራሉ፡፡ መከራየት አቅሙ ያለፈቀደላቸዉ ገበሬወች ደግሞ ሚስትንና ልጆቹን ይዞ በቀን 6 ብር እየተከፈለዉ ሲያርም፤ሲያጭድና ሲወቃ ይዉላል፡፡ በአካባቢዉ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ጥበት እንዲሁም ብዙ የህዝብ ቁጥር ያለዉ ሲሆን የህወሀት ኮሎኔሎች በማናለብኝነት የተራ ገበሬን መሬት በመንጠቅ ከፍተኛ በደል እያደረሱ ይገኛሉ፡፡ ጎጃም አካባቢ ባሉ ከተሞች በልመና ኑሯቸዉን እየገፉ የሚኖሩት ከ98 ፐርሰንት በላይ መሬታቸዉ በዚህ አካባቢ የተቀሙ ሰወች ናቸዉ፡፡ አሁን የህወሃት ወታደሮች የያዙት የመሬት ስፋት 20km x30 km ባጠቃላይ ከ 600 መቶ ሰኩየር ከ.ሜ. በላይ የሚሆን የምስኪን አማራ ገበሬ መሬት ተዘርፎ ለወታደር መጠቀሚያ ሁኗል፡፡

የጉልበት ብዝበዛ
—————–
ይህ የእርሻ ልማት ለትምህርት ያልደረሱ የአማራ ወጣቶችን በተለይም ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን አካባቢ የሚገኙ ልጆችን በቀን በአማካኝ ከ3 እስከ 6 ብር ብቻ በመክፈል ከፍተኛ የሆነ የጉልበት ብዝበዛ የሚካሄድበት ቦታ ነዉ፡፡ ህጻናትን ከትምህርት ቤት በማስቀረት በቀን 3 ብር መክፈል ምን አይነት አረመኔነት እና በደል እንደሆነ ለሁሉም ሰዉ ግልጽ ነዉ፡፡ እንዲሁም አልፎ አልፎ ገንዘብ የለንም በማለት ልጆችን በማስፈራራትና እስር ቤት ነዉ ምናስገባችሁ በማለት የሰሩበትን ሳይከፍሉ የሚቀሩበት ጊዜም አለ፡፡ይህ እንግዲህ የሚሆነዉ በወላጆቻቸዉ ንብረት ላይ ነዉ፡፡

የሚመረተዉ ምርት የት ይገባል
————————–—-
በዘህ እርሻ መሬት የሚመረተዉ ጤፍና በቆሎ ወታደሮቹ አገር ዉስጥ ገቢየያ ላይ የሚቸበችቡት ሲሆን ነጭ ቦለቄዉን ደግሞ ወደ ናዝሬት ከተማ ማበጠሪያ በረንዳ ተወስዶና እዛ ተበጥሮ ለዉጭ ገቢያ ይቀርባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የፌደራል መንግሰትም የአማራ ክልል መንግስትም የሚያዉቀዉ ነገር የለም፡፡ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ኮሎኔሎችና ፌደራል ላይ ባሉ በህወሃት ባለስልጣኖች ብቻ የሚታወቅ ሲሆን ገቢዉ ለነዚሁ ሰወች የግል ጥቅም ብቻ የሚዉል ነዉ፡፡
ልክ እንደ ብር ሸለቆ ሰቲት ሁመራ ሰፊ የመንግስት የሚባል በኮሎኔሎች የተያዘ የእርሻ ልማት ነበር፡፡ ይሄን የእርሻ ልማት ግን ለትግራይ ገበሬዎች አከፋፍለዉ የሰጡ ሲሆን የአካባቢዉ ህዝብም በዚህ ተጠቃሚ ሁኗል፡፡ የሁመራን የእርሻ ልማትን ካከፋፈሉ በኋላ ግን ወታደሮቹ ወደ ብር ሸለቆ በመምጣት ገበሬዉን ቀምተዉ ማረስ ከጀመሩ ከ 10 አመት በላይ ሁኗቸዋል፡፡

አማራ ክልል ዉስጥ ብዙ አካባቢወች በምርትና መሬት እጥረት ምክንያት በሴፍቲኔት የሚኖሩ ሲሆን በሽወች የሚቆጠሩ ወጣቶችንና መሬት የሌላቸዉን ሰወች ሊታደግ የሚችሉ ምርታማ የሆኑ አካባቢች እንደ ብር ሸለቆ የእርሻ ልማት፤የአየዉ የእርሻ ልማት፤ ዘለቀ እርሻ ልማት፤የበለስና ጃዊ የእርሻ ልማት የትቂት የህወሃት ወሮበሎች መፈንጫ ሁኗል፡፡ በነዚህ አካባቢ የሚመረተዉ ምርትም ሆነ ገንዘብ ለአካባቢዉ ህብረተሰብ ምንም ጥቅም እንደማይሰጥ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ነዉ በባለፈዉ ቆቦ አካባቢ በነበረዉ የህዝብ አመጽ የመጀመሪያ ሰለባ የሆነዉ ባካባቢዉ የገበሬዉን መሬት ዘርፎ የህወሃት ኮሎኔሎች ምርት የሚያመርቱበት የዘለቀ እርሻ ልማት ነበር፡፡

ብአዴን የመልካም አስተዳደር ችግር እቀርፋለዉ ካለ እነዚህን 5 ወይም 6 አካባቢ ከ 10 እና 15 ሰዉ ባልበለጠ የተያዙ ነገር ግን እስከ 50 እና 60 ሺህ የአማራ ገበሬና ወጣት ሊጠቀልል የሚችል የእርሻ ልማቶች ለህዝቡ ያከፋፍል፡፡ በአካባቢዉ ያለዉ ህብረተሰብም ጫና ማድረግና በየስብሰባዉ ማንሳት አለበት፡፡