በኢትዮጵያ ዙሪያ ያሉ አጎራባች አገሮች ከወያኔ የዉሸት ወዳጅነት አጉራ እዬወጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእስር ቤት ይፈታ ማለትም ጀምረዋል። ይህ አቋም የሚያኮራ ደስ የሚያሰኝ ነዉ። ለአፍሪካ ዉለታ ለሰራ ህዝብ ተገቢ ምላሽም ነዉ። እየዋሹለት እስካሁን በተጭበረበረ ዲፕሎማሲ መቆየት ሳይጸጽታቸዉ አልቀረም። ቢያንስ አብዛኛዉ አገራችን ከአገሩ ታሪክ ጋር ያጣመረዉ ፍትህ የሚሻዉ ሕዝብ ማለት ይቻላል
ጎረቤት አገሮች ኢትዮጵያን የሚያዉቋት በህዝቡ ጥንካሬ የኢትዮጵን ዳርደንበር ከቅኝ ገዚወች ወረራ ደሙን አፍሶ አጥንቱን ከስክሶ ነጻ የሆነ ህዝብ ባቻ ሳዕሆን ለአፍሪካ የቅኝ ጋዛት ነጻነት ፋና ወጊ ግንባር ቀደም አራያ ህዝብ በመሆኑ ነዉ።
ከ27 ዓመታት የግፍ አገዛዝ በኋ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ህዝቡን እጨፈጨፈ ዘረኛ መንግስት ሁኖ መቆዬቱ ከጊዜ ወደጊዜ እዬተከሰተላቸዉ የጥፋት መንገድ ይዞ ሲቀጥል በመገንዘባቸዉ እና አፍሪካንም የሚበክል አስቸጋሪ ቡድን መሆኑን ስለተረዱ ከወያኔ የዉሸት የወዳጂነት ቁርኝት እመፈታትን እዬፈለጉ ነዉ። ምክናያቱም ኢትዮጵያ ተጎዳች ማለት አፍሪካ መጎዳት ብቻ ሳይሆን ምስቅልቅሏ ይወጣል ብለዉ በማመናቸዉ ነዉ።
በአገራችን 4,338 ዓመታት ጉዞ፤ ከስነ ልቦና ዘመን ጀምሮ በሽምግልና/በገዳ አስተዳደር፤ በሃይማኖት ተማጽንዖ ብዙ አስተዋጽዖ ያደረግ ህዝብ ለመሆኑ ብዙ የታሪክ ማስረጃወች አሉ፤ የአለም ሊቃወንት ይመሰክራሉ፤ ከመጽሃፍ ቅዱስ እስከ ድርሳናት ተነበዋል። ይህን የመላዉ አፍሪካ አካል የሆነዉን ታሪክ ጎረቤት ወዳቾቻችን ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ። በመቻቻል እራሱን ሲመራ የቆዬ አሁንም ሊመራ የሚችልን ህዝብ በግፍ ደምም መታጠቡን በማወቃቸዉ ከወያኔ የዲፕሎማሲ እስር ቤት ሹልክ እያሉ በመዉጣት ላይ ናቸዉ። ደግ ነዉ ፤እሰዬዉ ያሰኛል። ይህ አፋኝ አምባ ገነን ብዙ እንደማይቆይ አዉቀዉታል ማለት ነዉ፤ እኛም አዉቀናል፤ ከሚቀረዉ ታላቅ ባለ እንቁ ታሪክ ህዝብ ጋር በመቆማቸዉ ይወደሳሉ።
ይኸዉና ወገኖቸ ወያኔ ከመጣጀምሮ የባህል ፤ የሽምግልና፤ የአባገዳዎች ሌሎችንም የችግር አፈታትን የምንጠቀምባቸዉ እሴቶቻችን ወያኔ በመናቅ እዬረገጡ፤ እያበላሹ። የሃይማኖት አባቶችን ወደሰይጣንነት ቀይረዉ ለህዝብ እንዳይቆሙበዘር ያንበረከኩ ቡድኖች ናቸዉ። በወያኔ የተደራጁ ጳጳሳት የክህደት ስራ እዬሰረ ለሆዳቸዉ ብቻ እያደሩ ለሰይጣ የተገዙ ሁነዋል።
በነዚህ ጉግ ማጉግ የጨለማዉ ዓመታት ገዢወች የሃይማኖት አባት የለ፤ ሽማግሌ ጠፍቶ ሁሉም እንደነሱ ጫካኝ መነኩሴ ሁኖ 3 አሥር ዓመታትን ያበላሹ ናቸዉ። ለህጻናት፤ ለአዛዉንት፤ ለወጣት ደም መፍሰስ ደንታ የሌላችዉ ቀሳዉስት ሆኑዉ ከርመዋል። እጅግ ያማል። አዎ ይህንን ሁሉ ታዝበዉ ዘግበዉ ፤በምሁራን ገምግመዉ አጎራባች አገሮች አሁን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መቆም ይሻለናል ብለዉ እዬወሰኑ ያሉት ለራሳቸዉ ሰላምና ብልጽግና ወሳኝ ነዉ በሚል እምነት ነዉ።
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር አንዱን ከሌላዉ ማጋጨት በአገራቸዉ ዉስጥ ብዙ ጎልቶ የማይታይ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለኛ የሚተርፍ በሽታ ነዉ ከሚል ዉሳኔ ስለደረሱ መሆኑ አያጠራጥርም። የህዝባችን የትግል መዓበልም በማየታቸዉ እንዲያዉም አምባ ገነን ብቻ ሳይሆን በመላዉ ኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠላ ቡድን ጋር ሽርከኛ ሁኖ ማበር ፋይዳ ስለሌለዉ ከቆየንበት የዲፕሎማሲ እስር ቤት ተፈትተናል የሚል ጠንካራ አቋም እያንጸባረቁ ነዉ።
ነገር ግን ለፋታም መዘንጋት የሌለበት ቁም ነገር የማታ ማታ ወሳኙ የኛ የኢትዮጵያዉያን ቆራጥ የተባበረ አንድነትን የተላበሰ ትግል ነዉ። ወዳጆቻችን ድል ስናደርግ እንኳ ደስ ያላችሁ ለማለት ዝግጁ ናቸዉ። በተለያዬ መልኩ ህዝብ ወዶ ለመረጠዉ መንግስት የእርዳታ እጃቸዉን ለመዘርጋትም የሚያግዳቸዉ የለም።
አሁንም እንደገና የኛ መልክት ሁሉን ያሳተፈ አስቸኳይ የሽግግር መንግስት እንጠይቃለን። ይጠራ እንላለን። ይህ መልክት በስልጣን ላይ 27 ዓመታት ለቆዬዉ ድርጅት ነዉ። ጊዜዉ በጣም ሳይዘገይ፤ ከዉድቀት በኋላ ሳይሆን አሁን ነዉ። በበሰበሰ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስተር መሾም የቃቃ ጨዋታ ነዉ።
ወደመጨረሻየ እስኪ የአቶ ኤርያስ ለገሰን አቋም ጫፉን ቀንጨፍ ላድርግ።በኢሳት ዉይይት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር እንዲፈጽሙ የጠየቁትን አምስት ጥያቄ እኔም እጋራለዉ፤ ጥያቄ ቁልፍ የምኞት ጥያቄ ነዉ እኔም ምኞቴ ነበር። ነገር ግን የወያኔ አዲስ ሹም ሊፈጽመዉ ሊያስፈጽመዉ ፍጹም አይችል፤ ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቃል ብላ ስትከተል ዋለች ነዉ። እንዲያዉም አጉል ከአበደ ዉሻ ጋር ትግል ማጋጠም እንደማለት ነዉ። የተለከፈ ዉሻ ወዲያዉ መወገድ አለበት እንጂ በሰፈር አካባቢ ከቆ በልክፍት ያዳርሰዋል። ተስፋ የሌለዉ ጭዋታ ነዉ። የአቶ ኤርሚያስ ጥያቄ ጭራሹን የወያኔ ነጠብጣብ መዋቅር ባለበት ስርዓት ዉስጥ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ምንም ማድረግ አይችልም። በመዋቅሩ የተረጨዉ አሁንም ማቆሚa የሌለዉ መርዙ ቀላል አይደለም። ለይቅርታ እንኳን ጭራሽ ቦታ የሌለዉ ቡድን ነዉ።
እሺ፤ አዲሱ ሹም አስቸኳ ጊዜ አዋጁን ያንሳ!፤ ግለሰቡችም አሰርኩ ማለት ይችል ይሆናል፤ ነብሰ ገዳዮችን ማለቴ ነዉ።ወያኔ ሁኖ እኮ ያልጨፈጨፈ የሌም። አስቸኳ ጊዜ አዋጁ አሁን ተደጋግሞ ይፋ ሆነ ኢንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ለ 27 ዓመታት በመሳሪያ አፈሙዝ ደግኖ በወታደር ተገዝቷል። አሁን አዋጁ ቢነሳም በጓሮ በር መተዉ ያፍናሉ ይገላሉ፤ ቤት ያፈርሳሉ በጉልበት ነጥቀዉ የወሰዱትን መሬት አስፍተዉ ህዝብ መቸረሱን አያቆሙም። በአሁኑ ሰዓት እንኳን ሥብሰባ ላይ ተቀምጠዉ ህዝብ እያስጨፈጨፉ ነዉ፤ ሰላማዊ ገበሬ በጎንደር በጎጃም እያሳፈኑ ነዉ፤ ለመንት ታጋይ የሆኑት የፍቅር የአንድነት አቀንቃኞች ምሁራን እነ ስዩም ተሾመ እነታዬ ደንደኣ,፤ በቀጣዩም ነብስ ያላቸዉን የህዝብ ወገን አድብተዉ ለመጨረስ የተዘጋጁ መሆናቸዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አዉቆ እራሱን በመከላከል ከማጥቃት ዉጭ ሌላ ምርጫ የለዉም። ይህ የማይሸራረፍ በዚህ ዘመን የገጠመን መወጣት ያለብን ሃቅ ነዉ።
እንዲያዉም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚያመጣዉ ችግር ይኖራል የሚል እምነት አለኝ። ይህም አይዟችሁ የጥገናዉ ጊዜ ስለሚወስድ ነዉ እያሉ ትግሉን ያቀዘቅዛል የሚል ጨዋታ አለ። እዉነታም የያዘ ጥርጣሬ ነዉ።ከምን ጋር የዋለች ጊደር ………. ተምራ መጣች ነዉና። እናም ትግሉ ተዘናግቶ ቀዝቀዝ ሲል ወያኔ አገግሞ ይነሳና የእርስ በእርስ ግጭቱን ይቀጥላል፤ የነጻነት ቀን እጅግ ይራዘማል። ቀስ በቀስ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስተር በኢህአዴግ ስም የተጻፈ መግለጫ ከማንበብ ዉጭ በመረጃ የተደገፋ አመራር ሊሰጥ አይችልም።
ኢህአዴግ በተባለ መንደር ከእንግዲህ አስተዳደር አቁሟል። ሁላችንም እርማችን እናዉጣ። የወያኔ ዉስብስብ ችግር ሊወገድ የሚችለዉ አገሪቱ ሰላምና መረጋጋት የሚገኘዉ የህዝብ አሜነታና ተሳትፎ ያገኘ የሽግግር መንግስት ሲቋቋም ብቻ ነዉ።
ህዝብ ላይ ወንጀል የፈጸሙሙ ወደ እዉነተኛ ፍትሃዊ ፍርድ የሚቀርበዉም ለህዝብ የቆመ ስርዓት ባለበት አገር ነዉ። እነሱ በሾሙት ጠቅላይ ሚኒስተር ከጦርነት ፤ ከአፈና ፤ከስርቆት ዉጭ የሚፈጸም አገራዊ ጉዳይ አይኖርም። ዜጎች እየታሰሩ መሰቃየታቸዉ ጭራሽ አይቆምም። በወያኔ ባህል አስሮ ቶርች ማድረግ እና ስብዕናን የመንካት አባዜ ሱሳቸዉ ነዉ።
ሌላዉ አንቀጽ 39 ወይም የዘር ፖለቲካ የህልዉናቸዉ መሰረት በመሆኑ የሚፈትሸዉ አዲስ ሥራት ብቻ ነዉ። የአፍሪካ አገሮች ይህን የዘር በሽታ ለማስወገድ እዬሰሩበት ነዉ። አሁን ስለኢትዮጵያ ህዝብ ጭፍጨፋና ጭቆና መናገር መጀመራቸዉ ድንገት የመጣ አይደለም ።ልቁንስ በዉስጣቸዉ ቋጥረዉት ለአመታት የቆዩት ጊዜዉን ጠብቆ የመጣት የህዝቦች አንድነት እንቅስቃሴ ዉጤት ነዉ።
መልክታችን
አስቸኳይ በዉስጥም በዉጭም ያለዉን ተቀናቃኝ ሁሉ ያሳተፈ ሰላማዊ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
በአዋጅ ስም ህግ ወጥ የሆነ ህግ አስፈጻሚ በሌለቤት ሥርዓት መሳሪያ ለማስፈታት የሚካሄደዉ የአፈና ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም
ለህዝባቸዉ የቆሙ እዉነት በመናገራቸዉ የታሰሩ አቶ ሥዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደአ በአስቸኳይ ይፈቱ
ህዝብ ሙሉ በሙሉ የተቃወመዉ አስኳ ወታደራዊ አዋጅ በፍጥነት ይነሳ
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ዳንኤል ጎበዜ
