*ታሳሪዎቹ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል
ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ ሂደት ላይ የሚገኙ 19 ሰዎች ትናንት መጋቢት 15/2010 በባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ታውቋል። እስረኞቹ እንቅስቃሴያቸውን ምርጫ ቦርድ የሚያውቀው እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ በባህር ዳር የተገኙትም ቅድመ ምስረታ ጉባኤ ለማድረግ ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች እና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
እስረኞቹ ለእስር የተዳረጉት ውይይታቸውን አጠናቀው ምሽት ላይ ጣና ዳር ለእራት በተሰባሰቡበት ሁኔታ እንደሆነ ተገልፆዋል። እስረኞቹ በተያዙበት ወቅት ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል። በእስር ላይ ከሚገኙት መካከል፣
1ኛ፣ አቶ ጋሻው መርሻ
2ኛ፣ የሱፍ ኢብራሂም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረና አሁን ጠበቃ)
3ኛ፣ ተመስገን ተሰማ (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
4ኛ፣ በለጠ ሞላ (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
5ኛ፣ አቶ ሲሳይ አልታሰብ
6ኛ፣ በለጠ ካሳ (የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረ)
7ኛ፣ ዳንኤል አበባው
8ኛ፣ ንጋቱ አስረስ (የአማራ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ) እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን አጠቃላይ ቁጥራቸው 19 ነው።
አማራ የለም ማለት ህወሓት/ኢህአዴግ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈፅመውን ወንጀል ከለላ መስጠት ነው። ዘርን መሰረት አድርጎ የሚፈፀም ወንጀል የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው! ብዙ አማሮች በማንነታቸው ምክንያት ተለይተው ከፍተኛ ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል። ዘራቸውን እንዳይተኩ የዘር ፍሬያቸው ተኮላሽቷል። አማራ የለም ማለት እነዚህ ወንጀሎችን ከለላ እንደመስጠት ይቆጠራል። አማራ የለም ማለት፣ ቃላትን አሳምሮ እንደመፃፍ፣ እንደመናገር ቀላል አይደለም።
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ “አማራ የለም” ለሚሉ መልስ ሲሰጡ፣ “ጠላቶቻችን ግን አማራን ለማጥቃት ፈልገው አላጡትም” ብለው ነበር።
ዛሬም ድረስ አማራ አለ፣ የለም ጉዳይ ላይ መሆናችን ያሳዝናል!

