(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛና አክቲቭስት እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች 12 ሰዎች በፖሊስ ታፍሰው መወሰዳቸውን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዘገበ::

እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ታፍነው የተወሰዱት ጀሞ በሚገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤት የሽልማት ፕሮግራም በተደረገላቸው ወቅት ነው:: እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ ታፍሰው የተወሰዱት ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው::
1) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
2) ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማህተመ ወርቅ
3)ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
4) አቶ አንዱዓለም አራጌ
5) አቶ አዲሱ ጌታነህ
6) ጦማሪ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ
7) ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን
8) ጦማሪና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
9) ወይንሸት ሞላ
10) ይድነቃቸው አዲስ
11) ስንታየሁ ቸኮል
12) ተፈራ ተስፋዬ

ሌሎች የዘ-ሐበሻ ምንጮች በበኩላቸው እነ እስክንድር ነጋ ታፍሰው ከመወሰዳቸው በፊት በተሰበሰቡበት ፖሊስ እንደመጣና ግቢው ውስጥ የተሰቀለውን ባንዲራ እንዳወረደው ከዚያም የተሰበሰባችህበትን ዓላማ ፖሊስ ጣቢያ ሄዳችሁ ታስረዳላችሁ እንደተባሉና ፖሊሶቹ በወታደር መኪና አፋፍሰው እንደወሰዷቸው ገልጸውልናል::