መጋቢት 16/2010
(ቢቢኤን) የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችንና ጨምሮ ወንድም ሙሀመድ አባተ፣ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፣ ወጣት ኤሊያስ ኸድር እና ወጣት ሙጂብ አሚኖ “ጀግኖቻችንን እናመሰግናለን!” በሚል መሪ ቃል ሰማያዊ ፖርቲ ባዘጋጀው የምሳ ፕሮግረም ላይ ከታላላቅ ኢትዮጲያዊ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ አክቲቪስቶች ጋር ተገናኝተው የትውውቅና በአንድነት ጉዳይ ላይ መከሩ።
ዛሬ መጋቢት 16/2010 ሰማያዊ ፖርቲ ባዘጋጀው ግብዣ ላይ በርካታ የሃገራችን ስመ ጥር ፖለቲከኞች፣ የፖርቲ አመራሮች፣ አክቲቪስቶች፣ ጦማሪያን፣ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን ጨምሮ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ የቀድሞ የሸሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሸህ መከተ ሙሄ፣ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው፣ ወንድም መሀመድ አባተ፣ ወንድም ኤሊያስ ከድር እንዲሁም ሌሎች ተገኝተዋል።
ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ ፖለቲከኛው በቀለ ገርባ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ፣ ፖለቲከኛ እስክንድር ነጋ፣ ብርጋዴል ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ ዩናታን፣ ጦማሪ ማህሌት፣ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ፣ አክቲቪስት ኤሊያስ ኸድር፣ አክቲቪስት ሙጂብ አሚኖ፣ አክቲቪስት ፍሬው ተክሉ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ እማዋይሽ አለሙ እንዲሁም በርካታ በቅርቡ ከተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ከእስር የተለቀቁ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች ተሳትፈውበታል።
በፕሮግራሙ ላይ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ በቅርብ ከእስር የተለቀቀችው እማዋይሽ አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በፍቃዱ ሃይሉ፣ አክቲቪስት ኤሊያስ ከድር፣ ብርጋዴል ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፖርቲ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ የኔሁን ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ህብረት ከሌለ ሁል ጊዜም በገዢው ስርዓት ጭቆናው እየተባባሰ እንደሚሄድ ይህንን ግን ለማስታገስና ለማሸነፍ እንደዛሬው ህብረታችን በአንድነት ለኢትዮጲያችን ስንል መቀጠልና በቀጣይም መድረኮች ላይ ተቀራርበን በመነጋገር ከጨቋኙ ስርዓት ቀንበር መላቀቅ እንችላለን ተብሏል፤ በተለይም አዲሲቷን ኢትዮጲያን ለመገንባት ብሔራዊ ማንነትን ማነፅና በአንድነይ ላይ የተመሰረተ ኢትዮጲያችንን ያቀፈ ፖለቲካዊ እርምጃን ስንጓዝ ነው ተብሎ ሃሳብ ከመድረኩ ላይ ተሰንዝሯል።
ጥሪው የተላለፈላቸው በተለይም በቅርብ ጊዜያት ከተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ከእሥር የተፈቱ ወገኖች በዚህ መድረክ መገናኘተቸው እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም በሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሰፋ ባለ መድረክ በመነጋገር አዲሲቷን ኢትዮጲያ በመገንባት ረገድ በሚደረገው ርብርብ ላይ አስተዋፅዖ በማበርከት ሃገራዊ ግዴታቸውን እንደሚወጡ መክረዋል።
የምሳው ግብዣ እንደተጠናቀቀና የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦች ንግግር ካደረጉ ቡሃላ “በሃገራችን ኢትዮጲያ የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የማትጠልቅ የዲሞክራሲ ፀሃይ እንድትወጣ ሲታገሉ ለከፍተኛ እንግልትና እስራት በመዳረግዎ ለከፈሉት መስዋዕትነት ያለንን ከፍተኛ አክብሮትና ምስጋና፤ ለወደፊትም ለሚያደርጉት ትግልና መስዋዕትነት ሰማያዊ ፖርቲ ከጎንዎ መሆኑን እንገለፃለን” የሚል የምስክር ወረቀት ጥሪው ለተላለፈላቸው ግለሰቦች ተሰጥቷል።
ኢትዮጲያችን ካለችበት የጭቆና አገዛዝ ለማላቀቅ ህብረታችን ጥንካሬያችን ነውና በዚሁ እንቀጥላለን የሚል መልዕክት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና አሰተላልፈዋል።

