በጎጃም መተከል በአሁኑ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ እና ዳንጉር ወረዳዎች (በተለይም አይሲድ እና ቆታ ቀበሌዎች) ያሉ እረጅም አመት ያስቆጠሩ ተፈጥሯዊ ጫካዎችን በመጨፍጨፍ መጠነ ሰፊ ከሰል የማዉጣት ስራ እየተሰራ እንደሆነ በአካባቢዉ የሞኖሩ ወገኖች ይገልጻሉ ።
የአካባቢው ነዋሪዎች እና የአይን እማኞች እንዳሉት ሰሞኑን እንኳን 100 ተሳቢ ያላቸው ከባድ የጭነት መኪኖች በተመሳሳይ መልኩ ከሰል ጭነዉ የወጡ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ 20 ትራንስ ኢትዮጵያ ማህበር በመባል የሚታወቁት የህወሓት መኪኖች ከነተሳቢያቸው ጭነዉ ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዉለዉ የአካባቢዉ ባለስልጣናት ሁኔታውን ለማጣራት በዉይይት ተጠምደዋል።
ቁጥራቸው 20 የሞሆኑ የህወሃት ባለተሳቢ ከባድ የጭነት መኪናዎች ከቤንሻንጉል ክልል ደን በመጨፍጨፍና ክሰል በማክሰል ወድ ትግራይ መቀሌ ሲያጓጉዙ (በስዕሉ የሚታየው ትራንስ ኢትዮጵያ ማህበር በመባል የሚታወቁት ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረት ከሚዘርፍባቸው የጭነት መኪናዎች አንዱ ነው)
የአካባቢው ሰወች እንደሚሉት
1. የጉባ ወረዳ የአባይ ግድብ የሚገነባበት መሆኑ እየታወቀ የአካባቢዉን በረሀማነት ለመቀነስ ተጨማሪ ዛፎች መትከል ሲገባ ለምን ደኑ ሲጨፈጨፍ ክልሉ ዝምታን መረጠ?
2 . ከሰሉ ተጭኖ የት ነዉ የሚጓጓዘዉ (ያዉም 120 ከባድ የጭነት መኪናዎች ከነተሳቢ)?
3 . ከጉባ በአሶሳ መስመርም ሆነ ከጉባ በግልገል ቻግኒ መንገድ በፌደራል ፖሊስ የሚጠበቅ ጥብቅ ኬላ እያለ ቁጥራቸው 100 የሚሆኑ ከባድ ባለተሳቢ ከሰል የጫኑ መኪናዎች እንዴት ሊያልፍ ቻለ?
(Tesfaye woldesilase)
Source – Welkait.com

