
25 March 2018
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርተር ከታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሌሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች አቶ ፍቃዱ ማኅተመ ወርቅ፣ አቶ አንዷለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጦማሪ ማኅሌት ፈንታሁን፣ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ጦማሪ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)፣ አቶ ይድነቃቸው አዲስ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ ተፈራ ተስፋዬና አቶ አዲሱ ጌታነህ ናቸው፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት በመኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁላቸው የምሳ ግብዣ ላያ ተሰባስበው በነበሩበት ወቅት መሆኑንም ሪፖርተር ማወቅ ችሏል፡፡ የታሰሩበት ምክንያት ግን ምን እንደሆነ አልታወቀም፡፡
