እንደ መነሻ ፤
የሊግ ኦፍ ኔሽን ፈርሶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተወለደበት ምክኛት ኢግ ኦፍ ኔሽን የአገሮችን ሉአላዊነትና እንዲሁም የድንበር ላይ ግጭቶችን ሁሉ በግዜው መቅጨት ባለመቻሉ እንዲህ አይነት ትናንሽ የሚመስሉ ትንኮሳዎች አድገው የሁለተኛው የአለም ጦርነትን ማስከተሉ በዚህም እስከ ስልሳ ሚሊዮን ያህል ሰው ማለቁ ነው። ኢትዮጵያም ባቅሟ የእዚህ ጦርነት አካል በመሆኗ አንድ ሚሊዮን ያህል ሰው ገብራለች።
የተባበሩት መንግስታት ከተመሰረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1947 ወዲህ የአገር ሉአላዊነት ተጥሶ አሜሪካ ስለፈለገ ብቻ በጉልበት የተፈጠረች አዲስ አገር ከቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ “ኮሶቮ” ብቻ ናት። ያም ሆኖ ለኮሶቮ እውቅና ያልሰጡ በርካታ አገሮች አሉ። ይኸውም ምንድን ነው፤ አንዲት አገር ከነበረችበት እናት አገሯ ወጥታ ነጻ አገር እንድትሆን መሟላት ያለባቸው ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ።
፩ ህዝበ ውሳኔው የአብላጫውን ድምጽ ማግኘት አለበት፣
፪ አገሪቱ በህዝበ ውስኔ እንድትገነጠል እናት አገሯ መስማማቷን ለተባበሩት መንግስታት በይፋ መተማመኛውን መስጠት አለባት።
ኤርትራ ሉአላዊ አገር ሆና እንድትወለድ መለስ ዜናዊ ፈቃደኛ መሆኑን ለተባበሩት መንግስታት በደብዳቤ አሳውቋል።
የደቡብ ሱዳን ህዝብ ህዝበ ውሳኔ አድርጎ የራሱን ምርጫ እንዲወስን አልበሽር የተስማማው ኮሎኒ ፓወል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር በነበረበት ዘመን ከጆን ጋራንግ ጋር ናይሮቢ ላይ ባደረገው ድርድር ነበር ።
የወያኔ ስጋት፤
ወያኔ በአጋበሰው ግዙፍ ሃብት፣ በሰራው ህልቁ መሳፍርት ብሔራው ወንጀልና ከምንም በላይ በሉአላዊት ኢትዮጵያ ላይ ካለው ጥላቻ አንጻር የሚሰማው ጥልቅ የሆነ ፍርሃት አለ። እቅዱን ሳይጨርስ የተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ ወደ ለውጥ ቢያመራ ብቸኛው ማምለጫ መንገዴ ብሎ የሚያምናቸው እና የግድ መፈጸም ያለባቸው ሶስት ቁልፍ ነገሮች አሉ።
፩ ኢትዮጵያ ለኦጋዴን ነጻነቷን መስጠት አለባት፤
፪ ኢትዮጵያ ለጋምቤላ ነጻነቷን መፍቀድ አለባት፤
፫ በመጨረሻም ኢትዮጵያ ለትግራይ ነጻነት መስማማት አለባት።
እንደ አለም አቀፍ ህግ ደግሞ የወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ የሚለው አካል በፊርማው ካላጸደቀው ይኽ የደደቢት ማኔፌስቶ የመጨረሻ ምኞት የጨነገፈ ሽል ሆኖ መቅረት ብቻ ሳይሆን ከነወለዱ የሚያስከፍለውን ዋጋ ሰው ሆኖ ማሰብ አይቻልም። ሰሜን ሶማሊያ ዛሬ ድረስ ሉአላዊት አገር መሆን ያልቻለችው የፈራረሰችውን የሞቃዲሾ ሶማሊያ ፈቃድ ባለማግኘቷ ነው። ሞቃዲሾ ነገ ጠንክራ ብትወጣ ሰሜን ሶማሊያን መልሶ ከመዋጥ የሚያግዳት ምንም አይነት አለም አቀፍ ህግ የለም።
ሲጠቃለል፤
ህዝባዊ ንቅናቄው እያየለ ከመጣና ለውጥ አይቀሬ ከሆነ በመጨረሻው ሰአት ላይ ዶ/ር አቢይ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ ሶስት አገር የማፍረስ ፍጻሜ ለማጠናቀቅ የመጨረሻውን ሚስማር ለመምታት ምን ያህል ፈቃደኛ ይሆናል የሚለው የወያኔ ቁልፍ ስጋት ነው።ከዚህ ስሌት አንጻር ወያኔ ቢሆንለት ይሁን ብሎ እንደጎለተው እንደ ኦጋዴኑ አብዲ ካልሆነም እንደ ደመቀና ሽጉጤ ያሉ አይምሮዋቸው ውስጥ ባለው አንጎል ሳይሆን ጨጏራቸው ውስጥ ባከማቹት ፈርስ የሚያስቡ የጋማ ከብቶችን ማስቀመጥ ቢችል ስጋቱን በብዙ እጥፍ እንደሚቀርፍለት ብሎም አገር የማፍረሱን ሂደት አልጋ ባልጋ እንደሚያደርግለት ሳይታለም የተፈታ ነው።የዶር አቢይም ነገር ለወያኔ አይጥለው አይጨብጠው ትኩስ ድንች የሆነበት ለዚሁ ነው።
