በዋልድባ መነኮሳት ላይ በወያኔ እየደረሰባቸው ስላለው ግፍና መከራ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዝም ማለቷን አስመልክተው አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ የሰጡትን ልብ የሚመስጥ ትምህርተ ወንጌል አቅርበንላችኋል።
- የዋልድባ መነኮሳት ላይ በወያኔ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ማለትም በኤሌክትሪክ መጠበሳቸው፣ ተዘቅዝቀው መገረፋቸው፣ በአንድ ልብስ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየታቸው፣መዋረዳቸውና ገዳማቸው ለፋብሪካነት መፈራረሱ በአጠቃላይ በተዋህዶ ምዕመና ላይ የተከፈጠ ጦርነት ነው።
- በዋልድባ ገዳም በሚገኙ ሴት መነኮሳት ላይ በትግራይ ሚሊሻዎች መደፈር እንደሚፈጸምባቸው ቢነገርም አቡነ ማቲያስና ሲኖዶሳቸው እንዲሁም የወቅቱ መምህራን ነን ባዮች ምንም አልመሰላቸውም።
- ድንግላዊያን፣ ገዳማዊያን፣ መናንያንና በአጠቃላይም ቤተክርስቲያኒቱ ስትጠፋና ስትዋረድ የምዕመናን በስፋት አለመቃወምና በአንድነት አለመንቀሳቀስ ይህንን ትውልድ በታሪክ ሲያስወቅስ የሚኖር ጉዳይ ነው።
-
- አገር ቤት ያለችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስለ እስረኞች መፈታት ምንም ስትናገር አልተሰማችም
- በጠራራ ቀን በአደባባይ ላይ ንጹሃን በጥይት ረፍርፎ እንደ ተራ ነገር “በስህተት ነው የተገደሉት” ማለት በወያኔ ህይወት እንዴት እንደረከሰች ማረጋገጫ ሲሆን አእጅግ አስደንጋጭ የሆነ የወንጀል ድርጊት ነው።
- በአባ ማቲያስ የሚመራው ሲኖዶስ ከአገዛዙ የሚለየው በዓርማ እንጅ በዓላማ አይደለም።
በተለያዩ የቤተክርስቲያንና የአገር ጉዳይ ላይ አዘውትረው ለምዕመናን መልዕክት የሚያስተላልፉት ታላቁ አባት ቀሲስ አስተር አየ ጽጌ የዋልድባ መነኮሳትን አስመልክተው በቅርቡ ያስተላለፉትን መልዕክት ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ አቅርበንላችኋል።
መምህር ዘበነ ለማ እንደ ቀሲስ አስተርአየና አባ መዓዛ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ ወያኔ የሚፈጽመውን ወንጀል ማውገዝና ማጋለጥ ሲገባው “ፖለቲካ ውስጥ አልገባም” እያለ ማጭበርበሩና በዚህም ለአገዝዙ ድጋፍ መስጠቱ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል። በቅርቡም የዋልድባ መነኮሳት ይፈቱ በማለት ግልጽና ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ ፈርቶ ጥግጥጉን “መነኮሳት ይፈቱ” የምትል ድፍን ያለች ቃል ወረወረ መባሉ አልኩባይነቱን የሚያሳይ እንጂ አምኖበት አይደለም የሚሉ የሱን አካሄድ የሚከታተሉ ምዕመናን እየተናገሩ ነው። እንደ መምህር ዘበነ ዓይነቶች በውጭ እየኖሩ ሐቁን ከመመስከር መራቃቸውና መንቦቅቦቃቸው ተጠሪነታቸው ለወያኔ እንጅ ለክርስቶስ ላለመሆኑ ተጨማሪ መረጃ ማጣቀስ አስፈላጊ አይደለም። መምህር ዘበነ ከእውነታው ለመደበቂያ ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ “ከፕሮቴስታንቶች ጋር እየተጋደልኩ ነው” የሚለውን ማዘናጊያ በማጋለጥ በቅርቡ “መምህር ዘበነ ለማ ስለዋልድባ መነኮሳት መፈታት መጮህ ትቶ አልባሌ ጉዳይ ውስጥ ገባ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሁፍ ይህንን በመጫን ይመልከቱ። https://www.mereja.com/amharic/v2/3316
