March 27, 2018

ሰሞኑን ወያኔ ሁሉንም ነገር ዘግታ በራሷ ብቻ በምታወራው ውዥንብር እንዲሁም በሕቡዕ በሰማራቻቸው አዛኝ ቅቤ አንጓች በሁኑ የውስጥ አርበኞቿ ሕዝብን በወሬ ማዕበል ለመፍታትና ተስፋ ለማስቆረጥ ያላደረገችው የለም፡፡ ከውስጥ ምንም አይነት መረጃ ባይደርሰንም ምን እየሆነ እንደሆን ለመረዳት ግን ብዙም ያላዳገተን ግን ብዙዎች ነን፡፡ እኔ የፖለቲካ ተንታኝ አደለሁም ግን የነገሮችን ሂደት ለማስተዋል ከውዥንብር ወሬ ይልቅ መሠረታዊ አካሄዶችን ማስተዋልን እመርጣለሁ፡፡ እስኪ ከዚህ በኋላ እንኳን እንንቃ፡፡ ወያኔ እስከዛሬም የነበራት አረመኔነትና ወሮበላነት፣ ወሬ በሰፊው ምንዛት እንጂ ስልትም ጉልበትም እንደሌላት እናውቅ ነበር፡፡ ምድረ ትግሬ ወያኔ አርዝመን ብናስረው የለቀቅነው መስሎታል፡፡ እስከዛሬ የነበረው ችግራችን መለያየታችን ነው፡፡ የዶ/ር አብይ መመረጥ አንድ ጥሩ እርምጃ ቢሆንም ግን ጮቤ አያስረግጠንም፡፡ ከዛ ይልቅ ሳይታሰብ ነገሮች በወያኔ ላይ ድብን ብለው እየጠበቁ እንደመጡ እያስተዋልን ነው፡፡

88 የፓርላማ ኣባላት ተቃውመውት ውድቅ ያደረጉትን የሽብር አዋጅ ስብሰባው ዛሬ ቢደረግ ከወያኔና ጥቂት ደቡብ አባላት በቅር በሰፊ ልዩነት እንደሚወድቅ አትጠራጠሩ፡፡ ሰሞኑን ኦሕዴዶች እግራቸው እየተቆረጠ ነው፣ ሁሉም ነገር በወያኔ እጅ እየገባ ነው ምናምን ወሬ በዝቶ ነበር፡፡ ይህ እሳቤ ግን ከአለመረዳት ይሁን ሆን ብሎ ውዥንብር ለመፍጠር ባይገባኝም ለእነደኔ ያለው ግን በተቃራኒው ያለው እውነት ግልጽ ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ሁሉ የወያኔን ወሮበላነት ለማሳየት የተደረገ ትዕግስት እንጂ አንድም ቦታ የመሸነፍ አዝማሚያ አላየሁም፡፡ ለማና ቡድኑ እየሄደበት ያለው ስልትና ፍጥነት 27 ዓመት በወሮበላነት ለኖረ ባዶ የወያኔ ቡድን ሊያስተውለው አይችልም፡፡ ወያኔዎች እኮ ዝም 27 ዓመት አረመኔያዊ ድርጊትን በሕዝብ ላይ በመፈጸምና በማሸበር የተፈሩ መስሏቸው ባዶነታቸውን ማስተዋል ትንሽ እንኳን አጥተው ጉድጓዳቸውን እየቆፈሩ ነው አሁንም ያሉት፡፡ ሰሞኑን ትግሬን አንበሳ ኦሮሞን ዝሆን አድርገው የወያኔ ጀሌዎች ሲያሰራጩ ነበር፡፡ ይሉኝታ ያላችሁ ትግሬዎች ከቀራችሁ እናንትን አይመለከትም፡፡ ግን አብዛኛው ትግሬ እንደዛ እየሆነ ተቸግራናል፡፡ ባዶነት እኮ ነው እንዲሕ የሚያደርገው፡፡ አንድ ነገር ግን እናውቃለን፡፡ የኦሮሞ ባንዳ የለም፡፡ ባንዳዎች ግን ይፈሩታል ይጠሉታል፡፡ ወያኔ ትግሬ ከወሬና፣ እንደ ሴት ውሻ አንዱን ከአንዱ በማናከስ ስኬታማ እንሆኑ እናውቃለን፡፡ ጀግኖች እንዲሀ በተዋረደ መልኩ የሚመጣን ጠላት ባለማስተዋል ብዙ ጥፋት ጠፍቷል፡፡ አሮሞን ከአባቶች ታሪክና የአገር በአለደራነት አምክነው ለዘመናት አገሪቱ የወሮበሎች መፈንጫ ሆነች፡፡ ግን እግዚአብሔር ቀን ቆጥሮ ወደልቦናችን እንድንመለስ አደረገ፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያዊነት የተነሳውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተለይ ኦሮሞ ማን ሊያቆመው ይችላል፡፡

አሁንም ይቀራል፡፡ እንድ እርምጃ ወደፊት ከመጣ ወያኔ በፍርሀት ትተናለች፡፡ ሰሞኑን ከእስር የተለቀቁ ቤታችሁ ለምን ደግሳችሁ ትገባበዛለችሁ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ለምን ሰቀላችሁ ብለው ይሄው የወሮበላ ነገር መቼም ነገር ፍለጋ ነውና እንደገና አስረዋቸዋል፡፡ የዚች ባንዲራ ጉዳይ ወያኔን ለምን እንደሚያስደነብራት ብዙዎች አልገባቸውም፡፡ ልብ በሉ ሲናገሩን ቀልድ ይመስላል ግን ወያኔ ኮከቡን አስጠንቁላ ለሰይጣን ተስላ ነው የለጠፈችበት፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ወያኔን እጅግ ያስበረግጋታል፡፡ እዚህ ላይ ገና አልደረስንም፡፡ ብዙውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ደግሞ በዚህች አገር ከፍተኛ የደምና የአጥንት ዋጋ በመክፈል አገርን አንድ ከማድረግ እስከ ዛሬም ከውጭ ጥላት በመሪነት ሲጠብቅ ከኖረው ሕዝብ ዋነኛው ኦሮሞ ከራሱ ታሪክ በመጣላቱ ለወያኔ እድል ገጠማት፡፡ በአማራ ክልል ብዙም ሰላማዊ ሰልፍ አልተካሄደም ከኦሮሚያ አንጻር  ማለቴ ነው፡፡ ወያኔን ድምጥማጧን ከአጥፋት ሰልፎች በታሪክም ወደፊት ሊዘከር የሚችለው የጎንደሩ ሰልፍ አርንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ነበር ወያኔን መረት ከቀላቀላት አንዱ፡፡ ይሄ ሰንደቅ አላማ በኦሮሚያ እንደዚሁ ተነስቶ ቢሆን ወያኔ እስከዛሬም እድሜ ባልኖራት፡፡ ዛሬ በኦሮሚያ ሁሉ የኢትዮጵያ ባንዲራ ቢነሳ ብታምኑም በአታምኑም የወያኔ ግብዓተ መሬቷ ይሆናል፡፡ ይህ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድነት ምልክት ነው፡፡ የባንዳዎቹ ልጆች የሚፈሩትም ለዚህ ነው፡፡ ከአደዋ ጀምሮ ስለዚች ባንዲራ (የአገር ምልክት) ታላላቅ ጀግኖች ተዋድቀዋል፡፡ እኛ ብንተወውም ዛሬም መንፈሳቸው ስለሚያስፈራት ወያኔ ይህን እጅግ ትፈራዋለች ትጠላዋለች፡፡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በነገሮች አንባዝን፡፡ እንድ እንሁን፣ ከኢትዮጵያዊነት በታች ያለው ማንነታች ለውበት ከአልሆን አያኖረንም፡፡ ወደድንም ጠላንም አገሪቱ ስለቀደሙ አባቶች ደምና አጥንት እንዲሁም ስለታላላቅ አባቶች ጸሎት የኢትዮጵያውያን ነች፡፡ ይህን ንቅን የወራዶችን ሀሳብ ስለተከተልን ነው ብዙ ውርደት የመጣብን፡፡

ወያኔ በቤታችንም ለመብላትና ለመጠጣት የእኔን ፍቃድ ከአላገኛችሁ ስትል ስለኖረች አሁንም መስሏታል፡፡ ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቃድ እንጂ በወሮበሎች ፍቃድ የሚደነገግ ሕግ፣ የምትመራ አገር አይኖረንም፡፡ ለተራ ትግሬዎች ጫጫታ ብዙም ጊዜ አታባክኑ፡፡ አትጥሏቸውም፡፡ ወያኔ አእምሯቸውን ባዶ አድርጋ እንዲያመልኳት ስላደረገቻቸው ዛሬ ብዙም አይገባቸውም፡፡ እየሆነ ያለውንም ለማስተዋል አይችሉም፡፡ ለእነሱ ጀግኖች ወሮበሎቹ ሽፍቶች ናቸው፡፡ ሰማዕት እያሉ ሲሞሏቸው የኖሩት እኮ ወሮበሎቹን ነው፡፡ ወያኔ እግዚአብሔርን አስጥላ እራሷን እንዲያመልክ ያደረገችው ትግሬ ሁሉ ማስተዋሉን እንዲሰጠው ጸልዩ፡፡ ምን ትግሬን ብቻ ሌላውንም እኮ እንደዛው አድርጋው ነበር፡፡ መቼም መለስ ሞተ ተብሎ የመለስን ራዕይ ከአላልክ እዚህች ምድር መኖር አትችልም እሰከማለት እኮ ነው የቀራቸው ነበር፡፡ በየሰፈሩ መለስ የሚመለክበት ፓርክ እየተባለ፣ የታላቁ መሪያችን ምናምን……ኧረ ይቅርብኝ በቃ ሁሉንም እኮ አደንዝዛው ነበር፡፡ አዚም ለቃበት፡፡

የገዳም መነኩሴን አሸባሪ ብላ ስታስር ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ስለእውነት ወያኔን ለመፈታተን አልተነሳም፡፡ ለመሆኑ ግን ሀይማኖት እንሰብካለን የምትሉ እውን በህዝብና አገር እንዲህ ያለ ግፍ ሲፈጸም ትንፍሽ ለማለት እንኳን ያላስቻላችሁ እምነታችሁ ከልክሎ ነው? ብዙ አልልም ግን የእኛው አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ ታላላቅ ሰማዕታት ከሕዝብና አገር ጋር በመቆም ስለእውነት ግፈኞችን በማውገዛቸው ነው ታላቅነታቸው የተመሰከረው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ዛሬ ወያኔ እያደረገች ያለችው በተለይ በኦርቶዶክስና እስልምና ላይ ሕዝቡን ከመሠረታዊ እሴቶቹ ማስወጣትና ምንም ሥርዓት የሌለው በማድረግ እንደልቧ የምትነዳው ማሕበረሰብ ለመፍጠር ነው፡፡ በሥርዓትና ህግ የሚኖር ሕዝብ እንደ እሷ ያለውን ወሮበላ ቀን ቆጥሮ እንደሚጥላት ታውቃለች፡፡ በቃ ሕዝብ ከመሠረታዊ እሴቶች ከጠፋ ምንም የሚይዘው የለም፡፡ ከእሴቶቻችን አንዱ ኢትዮጵያውያን የምንመገባቸው ነገሮች ነው፡፡ የአህያ ቄራ ስትከፍትልን መቼም ለሙከራ ነበር፡፡ የሀይማኖት መሪዎች ብዙም አላሉም፡፡ ግን ህዝብ አሁንም እሷ በፈለገቸው ደረጃ ስላልወረደ አልተሳካላትም፡፡ በተከበሩ የእምነት ቦታዎች የምታደርገው ድፍረትና ወሮበላነት ሕዝብን ከእንዲህ ያለ ድርጊት ጋር ማለማመድ ነው፡፡ ጴጥሮስ በሀይማኖትህ የመጣ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ለዚህ ወራሪ አትገዛ ምድሪቱም አትገዛው ያሉት እኮ እንዲህ ያለ እርኩሰት ወደ አገሪቱ እንዳይመጣ ነው፡፡ የባንዳዎቹ ልጆች ቆይተው የጌቶቻቸውን እርኩሰት በአገር ላይ በማለማመድ ሕዝቡን ከማንነቱ ከአስጣሉት በኋላ እነሱን እንዲያመልክ ነው እቅዳቸው፡፡ በምድር ላይ ያለ አስነዋሪ አረመኔያዊ ግፍ በታሳሪዎችም የሚያደርሱት ለዚህ ነው፡፡

ሁሉን መናገር አልችልም፡፡ ግን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እለምናችኋለሁ፡፡ ንቁ! ለማና ቡድኑ (እነገዱን ጨምሮ)ማድረግ ከሚገባው በላይ አድርጓል አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ዛሬም እናግዛቸው፡፡ ብዙ ጋሬጣዎችን ብቻቸውን ነው እየተጋፈጡ አገር እያጠሩ ያሉት፡፡ እውነት ከሆነ ደመቀ መኮንን ከውድድሩ ወጥቷል  ነው የሚባለው፡፡ ይህን ከአደረገ ትልቅ ሥራ እንደሰራ ነው የምቆጥረው፡፡ ለክብሩ ይቆይ፡፡ ቀጥሎም ምን አልባት በምክትልነት ከቀጠለ፣ አብይ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ከቀጠለና ሁለቱም ለኢትዮጵያዊነት በአንድ መስመር ከተሰለፉ ነገሮች ከአሁኑም በፈጠነ ሁኔታ ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ የወያኔን ደህንነት ብትፈልግ ይዛው ሲኦል ትግባ፡፡ እሱን በታትነንዋለ፡፡ መከላከያውና ፖሊስ እንዲሁም ፍትህ ግን ሙሉ በሙሉ ከትግሬ ወያኔ የጸዳ መሆን አለበት፡፡ በዚህ አብይን እንፈትነዋለን፡፡ የሽብር አዋጁ መሰረዝ ብቻም ሳይሆን ይህ የሽብር አዋጅ በወሮበልነት ያጸደቁና ያስፈጸሙ ሁሉ በሕግ እንዲጠየቁ መደረግ አለበት፡፡ አካሂዳችን እንደዛ ነው፡፡ ግንቦት 7 እና ኦነግን ወዳጃቸው ወያኔ እየወደቀ መሆኑን ተረድተው አደብ እንዲገዙ እንላለን፡፡ ኢትዮጰያዊ ሁሉ ጠላቶችህ ለይ፣ ባንዲራህን አንሳ! ሁሉም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ያነሳ ቀን ወያኔ ምን እንደሚሆን ታያላችሁ፡፡ ለወሮበላ ወያኔ ጥይትም አናባክንም፡፡ የለማና ገዱን ቡድን አበረታቱ ሁላችንም ትኩረታችን ወደእነዚህ በለራዕዮች ይሁን፡፡ የማንም ወሮበላና ነጋዴ አይጫወትብን፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ አሜን!

ሰርፀ ደስታ