Wednesday, 28 March 2018 12:25
ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ
በይርጋ አበበ
ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ብሔራዊ ምክር ቤት በስድስተኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮችና በፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ባሳለፈው ውሳኔ በሶስት ነጥቦች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው በቀጣይ የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር በአስቸኳይ ሁሉን አቀፍ ድርድርና ውይይት አካሂዶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እውን እንዲሆን ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል ብሏል፡፡
በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ህዝቡ ካለው የስርዓት ለውጥ ፍላጎት የመነጨ መሆኑን የገለጸው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ይህም በፓርቲው አድናቆት እንደሚሰጠው አስታውቋል፡፡ በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት እንዲፈጠር እና የዜጎች እኩልነትና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን የሚሉት የህዝቡ ቀዳሚ ጥያቄዎች ናቸው ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ይህን የህዝብ ጥያቄ ለማፈን ኢህአዴግ የወሰደውን እርምጃ ኮንኗል፡፡
