March 29, 2018

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጠቃሎ ወደ ድምፅ አሰጣጥ ከመኬዱ በፊት የምናገረው ነገር አለኝ በማለት የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል። “እኔን ሊተካ የሚሄደው ሰው እንደእኔ እንዳይሆን እውነቱን እናገራለሁ። ሊያሰሩኝ አልቻሉም፣ ያስፈራሩኛል። እስከቤተሰቦቼ ድረስ ያስፈራሩኝ ነበር ፣ እኔ ምንም ልሰራ ያልቻልኩት ለዛ ነው ” ብለዋል ። ከህወሃት ከተገኙ የምክር ቤት ተወካዮች መካከል አንዱ “ማነው ያስፈራራህ?” ብለው ጠይቀዋቸው ነበር ። አቶ ሃይለማርያም ሲመልሱ ” ይህንን ችግር ህወሃት ውስጥ አልገመገምንም? ነገር ግን እናንተ ይህንን ልትፈቱ አልቻላችሁም” ብለዋል፣ ይህንን ሲናገሩ ቤቱ እርስ በርስ ተያይቷል ። በዚህ የሃይለማርያም ንግግር የተነሳ የተወሰኑ የደህዴን ሰዎች ለዶር አብይ ድምፃቸውን እንዲሰጡ አስተዋእፃ አድርገዋል። “ይህንን ነገር የማነሳው አዲሱ ጠሚ harrase እንዳይደረግ ነው” ማለታቸው ታውቋል:: የራሳቸውን መጨረሻም አሳምረዋል ። ለህዝቡም ውለታ ውለዋል በማለት ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልፀዋል::
