በገብረ ክርስቶስ ዓባይ                                      መጋቢት 21ቀን 2010 ዓ/ም

ሕወሃት ኢሕአዴግ ከእኩዩ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ሕይወት በኋላ ጠንካራ መሪ ለማግኘት ድንጋይ ሲፈነቅል፤ ተራራ ሲቧጥጥ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ሊሳካለት አልቻለም። ምክንያቱም እኩዩ መሪ ሥልጣኑን ለብቻው ጠቅልሎ ለማያዝ እንዲያመቸው ችሎታና አቅም የነበራቸውን ሰዎች ጥርግ አድርጎ በማጥፋት በዙሪያው ሲያሰባስባቸው የቆዩት ሰዎች ደካሞችና ምንም ራዕይ የሌላቸውን በመሆኑ ሕወሃትን ብቻ ሳይሆን ኢሕአዴግን ጭምር አጋልጦ ለአለፉት ዓመታት ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ከቶ ሲያተራምስና ዓባላትን በሚያቀርቡት የሀሳብ ልዩነት  እርስ በእርስ ሲያጋጭና ሲያነታርክ መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው።

 

 

 

 

 

 

 

ከዚህም የተነሳ ሕወሃት በእጁ ያስገባቸውን የበላይነቶች እንዳስጠበቀ ለመቀጠል ሲል በሚወስዳቸው ፍፁም አረመኔያዊ የኃይል እርምጃና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካካል እያደረ እየጠነከረ የመጣውን አልገዛም ባይነት፤ በኃይል ለመጨፍለቅና በተለይም ታላላቆቹን ብሔሮች ማለትም አማራን ከኦሮሞ፤ እንዲሁም ኦሮሞን ከሶማሊያ ጋር በማጋጨት የፖለቲካ አጀንዳ ለማስቀየር ሙከራ ቢያደርግም፤ ምስኪን ሕዝቦችን ከመጨረስ ባለፈ እንዲያውም ይባስ ብሎ ያልታሰበ ሕዝባዊ ስሜት በመጎተቱ ሕወሃት ባልጠበቀው መንገድ የኔ በሚላቸው በድርጅቱ ዓባላት መካከል ሳይቀር መነቃቃት በመፈጠሩ፤ ይህንን አረመኔያዊ ስልትና ዘዴ በማውገዝ ችግሩን በድፍረት አስከ መጋፈጥ በመሄዳቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ለወራት ሲታምስ፤ ሲታሽና ሲጎሽ ቆይቷል።

ጎፍላው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም የሙት መንፈስ ተላብሰው ለተወሰነ ጊዜ ቢያገልለግሉም ሕወሃትን ግን ከገባበት የፖለቲካ ቀውስ ሊታደጉት አልቻሉም። እንዲያውም ሕወሃት የባሰውን ግልጽ የሆነ ጸረ ሕዝባዊ አቋም እንዳለው የተመሰከረበት ወቅት ሆኖ አልፏል። ይህ ብቻም አይደለም ሕወሃት የአገር ሉዓላዊነት የማይገደው ምንም ዓይነት ራዕይ የሌለው እንደሆነ በግልጽ የተረጋገጠበት ወቅት ሆኖ ይዘከራል። ወያኔ ሃይ ባይ የሌለበት እንዳሻው የአፈናና የጸረ ዴሞክራሲና ጸረ ሕዝብ ድርጅት ሆኖ ልጓሙን እንደበጠሰ ፈረስ አገሪቱን ከሰሜን አስከ ደቡብ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ እንደፈለገ ሲጋልብና ንጹሐን ዜጎችን ሲዘርፍ፤ ሲያፈናቅል፤ ሲያስር ሲያሰቃይ ደም ሲያፈስ፤ እያዩ ጎፍላው ጠቅላይ ሚንስትር ተው የማለት ሥልጣን አልነበራቸውም።

ይህም መረን የለቀቀ አፈናና እመቃ ሕዝቡ በራሡ ጊዜ ቆም ብሎ ወደ እራሱ እንዲመለከት አደረገው። በተለይ ሕወሃት የብሔር ግጭቶችን እንደስልት ሲያራግብ የነበረበትን ሁኔታ በደንብ በመገንዘብ አማራና ኦሮሞ ደምህ ደሜ ነው ተባብለው ቁጭ አሉ። አማራና ኦሮሞ እሳትና ጭድ ናቸው እያለ ሕወሃት ሲለፍ “ይህ የተበላ ዕቁብ ነው ሌላ አምጣ” ተባለ። ግፍና አሣር የበዛበት ትውልድ የሚታደገው መሪ ቢያጣም ችግሩን እራሡ ሊጋፈጠው በቁርጠኝነት በመወሰኑ መስዋዕትነት ከፍሏል።

ምንም ሳይዙ ይህንን መሰል የማንነት ጥያቄ ባነሱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በሕወሃት አጋዚ አልሞ ታኳሽ ሠራዊት የተቀጠፉት ሰላማዊ ሰዎች ደም፤ ዓባላትን ዕንቅልፍ ከመከልከሉም በላይ እልህና ቁጭትን አሳደረ። ሁሌም ዘራፊ፤ አሳሪ፤ ገራፊ ገዳይና አስገዳይ ሕወሃት፤ ሲሆን በአንጻሩም ተዘራፊ፤ ታሳሪ፤ ተገራፊና ተገዳይ ደግሞ ሌላው ብሔር መሆኑ በስሙ ቆመንለታል  የሚሉትን ኅሊና ያላቸው የኦሕዴድና የብአዴን መሪዎችን ከወደቀባቸው አዚም ድንገት እንዲባንኑ ምክንያት ሆነ።

ሕወሃት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆኖ የሚሠራውን ፋሽስታዊ እኩይ ተግባር ለማሻሻልም ሆነ ከማረም ይልቅ የባሰውኑ ወደ በለጠ አረመኔያዊነት እያደገ መሄዱን መርጧል። ስለሆነም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅና ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ሕዝቡን አፍኖና እረግጦ መፈናፈኛ በማሳጣት በመሣሪያ አፈሙዝ ረግጦ ለመግዛት ከመሻት በስተቀር ሌላ አማራጭ አልተዋጠለትም። እንዲህ ያለው አጋጣሚም ሰላማዊውን ሕዝብ ለመዝረፍና በሕዝብ  መካካል መረጋጋት እንዳይፈጠር ሽብር ለመንዛት ተጠቅሞበታል። በዚህ አኳኋን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲታመስ የጥይት ድምፅ የማይሰማባት ሕዝብ ተረጋግቶ የሚኖርባት፤ ብትዘርፍ እንጂ የማትዘረፍ፤ብትገርፍ እንጂ የማትገረፍ፤ ብታሥር እንጂ የማትታሠር፤ ብትገድል እንጂ የማትገደል፤ ብታሰድድ እንጂ የማትሰደድ፤ ትግራይ ብቻ ሆና ቆይታለች።

ይህንን መሰል የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ የኑሮ ሁኔታ እያዩ አምኖ የመቀበል ኅሊና በሕወሃት ኢሕአዴግ ዘንድ ካልሆነ በስተቀር በየተኛውም የፖለቲካ መመዘኛ በቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። ለዚህም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በየጊዜው የሚነሱት ተቃውሞዎች ዋነኛ ማስረጃዎች ናቸው። ሕወሃት ዝርፊያውንና አፈናውን ለማስፈጸም የአጋዚን ቀሳፊ ኃይል ቢጠቀምም ሕዝቡ ያንንም ከምንም ባለመቁጠር ‘ወይ ተከብሮ መኖር! አልያም መሞት!’ በሚል ቁርጠኛ ውሳኔ ኅብረቱን እያጠናከረና አድማሱን እያሰፋ ሕወሃትን ሲፈታተን እንደቆየ በግልጽ ታይቷል።

የዚህ ዓይነቱ ፍጥጫ ሕወሃትን ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደጣለና በተለይ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ዓይናችሁ ላፈር እንዳሰኛቸው ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው። ሕወሃት እንዲህ ያለውን ቀውስ ለመመከት የሚያስችል የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ክህሎት አልታደለችም። በሁሉም መስፈርት ሕዝብ ቀድሞ የሄደ በመሆኑ ሕወሃት እንድቀድሞው በመሣሪያ አፈሙዝ ለመግዛት ብትጥርም ከትርፉ ይልቅ ኪሳራው እየጎላ በመምጣቱ በሁሉም ዘርፍ ተሸናፊ እንድትሆን አድርጓታል።

በተለይ ደግሞ በደንብ ተደራጅተው በተቃዋሚነት ከተመዘገቡት የፖለቲካ ድርጅቶች በላይ ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ የሕወሃትን ድብቅ ምስጢር ሳይቀር እየበረበሩ ወዲያውኑ ለሠፊው ሕዝብ ይፋ በማውጣት ከፍተኛ እራሥ ምታት በመሆንና በሕወሃት መካካል ሳይቀር እምነት እንዲላላና ጥርጣሬ እንዲነግሥ ያደረጉት በጣት የሚቆጠሩ የሐገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆች በፌስ ቡክ ጠንክረው በመሥራት ሕዝቡን ከሰላባነት አውጥተው በጋራ እንዲመክቱ ለማደረግ ችለዋል። እንግዲህ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው ኢሕአዴግ ለወራት ሲታመስና በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ሆኖ የሰነበተው። ከዚህም ፍርሃቱ መውጣት ባለመቻሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ማወጅና ኮማንድ ፖስት እስከ ማቋቋም የደረሰው። ነገር ግን ከብዙ ውይይትና ጥልቅ ግምገማ በኋላ ሕወሃት ከፍርሃት ቆፈን ለመውጣት እየተውተረተረ ይገኛል።

የፖለቲካ እሥረኛችንም ለመፈታት  የወሰደው የድፍረት እርምጃ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተደርጎ ሊወሰድ ይቻላል። እንግዲህ  ዶ/ር ዓቢይ አህመድ የተከሰቱት ይህንን በመሰለ አወንታዊ ተነሳሽነት በተፈጠረበት ወቅት ነው። የዶ/ር ዓቢህ አህመድ ታላቁ ተግዳሮት በምንም መመዘኛ ቢሆን እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ የማይቻልበት መሆኑን ሕወሃትም ቢሆን ሊገነዘብ ይገባል።

ዶ/ር ዓቢይ ማድረግ የሚገባቸው ዋና ዋና ነገሮች ብቃት ያላቸውን ምሁራንን በተለይ ከየዩኒበርስቲዎች በማሰባሰብ ኮሚቴ በመሰየም፤

የኢትዮጵያ ሕዝብም ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። ውጤታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እመኝላቸዋለሁ።