በኮሎኝና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣

የታላቋ ኢትዮጵያዊት መቶኛ ሙትዓመት መታሰቢያ በኮሎኝና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ ነሐሴ 12 ቀን 1832 .ም በደብረ ታቦር ከተማ፣ በጌምድር/ጎንደር ተወልደው፣ እንጦጦ፣ የካቲት 4 ቀን1910 .ም እኩለ ሌሊት ላይ ዐረፉእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘኢትዮጵያ።

ለአዲሲቱ የኢትዮጵያ መዲና፣ «አዲስ አበባ» የሚል ሥያሜ በመስጠት፣ ዘመናዊ የሆቴል አገልግሎት እንዲጀመር በማድረግ ፣ ነጻ የኢትዮጵያ ባንክ እንዲቋቋም በማብቃት፣ እንዲሁም በሥርዓተ መስተዳድር ጥበብና በጀግንነት ይታወቃሉ።
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘኢትዮጵያ፣ በሕይወት ዘመናቸው የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፣ በአማካሪነት፣ በአስተባባሪነት፣ በተዋጊነትና በአዋጊነት፣ ከባለቤታቸው ከታላቁ ንጉሠ ነገሥት ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ጎን ለጎን የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገው ያለፉ፣ለዘመናችን ኢትዮጵያውያት ሁሉ አርአያነት ያላቸው፣ የአሁኑም የመጪውም ትውልድ ባለውለታ ናቸው።

በመሆኑም፣ በኮሎኝና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ማሕበር፣ ቅዳሜ ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2010 .(አፕሪል 28 ቀን 2018 ..) ከቀኑ ስምንት ሰዓት አስከ ቀኑ 12 ሰዓት ወይም በጀርመን ሰዓት ከቀኑ 14 ሰዓት አስክ ቀኑ 18 ሰዓት፣ ለእኝህ ታላቅ ኢትዮጵያዊት ታሪክ ሠሪ ንግሥት፣ መታሰቢያ አዘጋጅቷል።

የዕለቱ ዝግጅት፣

  1. ስለእቴጌ ጣይቱ ብጡልብርሃን ዘኢትዮጵያ ታሪካዊ ተግባራት በተመራማሪ ባለሙያ ጥናታዊ ገለጻ ይደረጋል።

    2. በየዘመናቱ ለእቴጌይቱ የቀረቡ የመወድስ ግጥሞች ይቀርባሉ።

    3. የጥያቄና መልስ፣ የአስተያየት ክፍለጊዜም ይኖራል።

    ማሳሰቢያ
    ለእንግዶች፣ ቡናና ሻይ፣ ምግብም በነጻ ተዘጋጅቷል።

    ! አኩሪ ታሪክ ሠርተው ያለፉ ባለውለታዎችን በሕብረት አብረን እንዘክር! ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ!

    የስብሰባ ቦታ——–ALLERWELTSHAUS, KÖRNER STR. 77, 50823 Köln(Ehrenfeld)

    ቀን—————-April 28, 2018

    ሰዓት————– 14 Uhr

    አዘጋጅ በኮሎኝና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ማሕበር