ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.

መጠነኛ መግለጫ ላስቀድም፦

“አንተ” እያልሁ የምጽፍባቸው ምክንያቶቼ፦

• እኔ አገሬን በግዙፍ አካል ስለይ፦ ዐቢይ ገና መልካሚቱና ነቢይቱ እናት ማህፀን ውስጥ ነበር፦
•የጠቅላይ ሚኒስትርነቱም ምርጫ በብዙሐኑ ሳይኾን የብዙሐኑን ድምጽ ቀምቶ “ተመረጥሁ” ባለ ግም ባር ነው፦
•ታሪካዊዋን በ“አጥንትና በደም” ተከብራ አስከብራ የኖረችዋን ሰንደቅ-ዓላማዬን በተገፋችበትና “መተት” የተለጠፈበትን (ወድዶም ኾነ ሳይወድድ) ይዟል
•በእነዚህ ዓበይት ምክንያቶች የአንቱታን ክብር መስጠት የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም።

ጠ/ሚ. ዶ/ር ዐቢይ አህመድንና አቶ ለማ መገርሳን በተመልከተ ያለኝ አቅዋምና ምክንያቴ(ቶቼ) ሁለቱም በግም ባሩ አባልነት ለረጅም ጊዜ የሠሩ/ያገለገሉ መኾናቸውን የሚክድ የለም ከራሳቸው ጀምሮ። በዚህም ረጅም ጊዜ ግም ባሩ በሠራው ተጠያቂነታቸውን እነርሱም አይክዱም። ግን በአኹኑ ጊዜ የያዙት አገር-አድን፦

የተቅደሰ አገልግሎት ዘመናቸው ነቅተውና ቆርጠው በተመለሱብት ወቅት ግም ባራቸው የተሰማራበትን ታሪክ ክህደትና በይባስም በጥላቻ የተለውሰ ታሪክን መሠረት ባማድረግ ውዲቱ አገራችንን እኛ ካልገዛን “የመከፋፈያ “ አልያም “የማቃጠያ” ዕቅዳቸውን በሚያሾሩበት ወቅት “ ከቀንዶኞቹ ውስጥ ሁለቱ ፦ – ለማ መገርሳና ዐቢይ አህመድ፦ “ እንዴት “ እኛ ሰዎች አይደለንምን? ብሎስ “ኢትዮጵያውያን” አይደለንምን? ታዲያስ አገር ወገን ምን እስቲኾኑ ነው የምንጠብቀው ብለው፦ በጠላት መሣሪያነት የተነደፈውንና እስካሁንም ለ፳፯ ረጅም የስቃይ ዘመናት የተገበረውን ወገንን የመለያያ ዕኩይ ተግባር ወደባሰ ደረጃ ሲያሳድጉት አናይም ብለው፦ የኢትዮጵያን ልጆች አንድንደነትና በታሪካዊነት ነጻነቷን ጠብቀው ያቆዮአትም በአንድነት መኾኑን አምነው እነሆ! ለ፳፯ ዓመታት የተለያዩትን አባት-እናት ልጆች ወንደም እህትማማቾች መልሰው በማስተባበር ለነጻነትዋና ለልጆችዋ አቻ ዕድገት መነሳታቸውን ተቀብያለሁ።

ለክርስቲያንና ለሙስሊም ወገኖቼ የጋራ ከኾነው ቅዱስ መጽሐፍ የሉቃስ ወንጌል ፩፭/፯ “ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከ፺፱ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል ፡” ይለናል፡” እና! ወገኖቼ በምድራችንም “ደስታ ኾኖ” የጀመሩትን የተቀደሰ አገር ማዳንንና ዘመድ አዝማድን ማዋሃድን ይቅናችሁ ብለን እንተባበር፤ ንስሐ የሚገባውም ያጠፋ – የበደለ – ሆኖም በድርጊቱ (ቶቹ) የተፀፀተ መኾኑን አንርሳ። “ ሰማያት የተደሰቱበትን “ እኛ እንዳያመልጠን።

እዚህ ላይ የአንዳንዶች ፅጉር እንድሚቆም ይሰማኛል። ግን የሚሉትን- የሚመኙትን ( የምንመኘውን) ለማግኘት ተዘግተናል!? አኹንም የተለመደውን አነብናቢዎች …እንድሚሉ ይገባኛል። ባጭሩ ዝንጀሮዋ እንኳን አለችው ከሚባለው እንማር፤፡ አገራችን ትዳን። እጅግ ከባድ አደጋ ላይ መኾንዋን እንረዳ። ስለዚህ እምነቴንና መፍትሄ የምለውን በቅርቡ አካፍላለሁ። ይህን ካልሁ በኋላ፦ ዶ/ር ዐቢይ!- ባለፉት ፪ – ፫ ወራት ውስጥ በተለያዩ መድረኮች የተናገርሃቸውን አድምጬ በጥልቀትህ፦ በአርቆ አስተዋይነትህ፦ ለአገር ለወገን መልካም መመኘትህን ተረድቼ እንዳከብርህ አድርገኸኛል፤አኹን በተወዳደርህበት ማሸነፍህን በሙሉ ልብና ደስታ መቀበሌንም ልገልጽልህ እውድዳለሁ። የሚገባህ ነህ። ይኽን ስል ያለህበትን “ ግም ባርም በለው ሌላ “ እንኳን ልወድደው ስለርሱ የማልሰማበትን ጊዜ በጸሎት እየጠብቅሁ መኾኔን እንድታውቅ ይገባል።” ሌላ የምወድደውና የማከብረው ለዚህ ውድድር በማመቻቸቱ አቶ ለማ መገርሳን ነው። የሱን ዐቢይ አገራዊ አስተዋጽኦ እዚህ ከመጥቀስ ማለፍ አያስፈልግም። እርሱና ድርጅቱ እንዲሁም አገሬው በሙሉ በእናት አገራችን ላይ የተገመዱትን ሴራ ኹሉ አክሽፈው የጎንደር ሠልፈኛ “ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው፦ በቀለ ገርባ መሪዬ ነው !”ያለውን የአዳማ ሠልፈኛም አስተጋብቶት በለማ መገርሳ አምበልነት እሳትና ጭድ አደርገናል ብለው ለ፳፯ እጅግ አሰቃቂ ዘመናት፦ የተንደላቀቁብትን ትምክህተኛነት ባዶነት አሳየ። ስለዚህ ለአንተ የገለጽኋቸው ለርሱም ይኾናሉ። ምርጫውን በተመለከተ አቶ ደመቀ መኮንንንም ላመሰግነው እውድዳለሁ። በኹለት ምክንያቶች
 አንደኛው ራሱን ከተወዳዳሪነት ማውጣቱ ኹለተኛው በግሉም ኾነ በምክር መውጣቱን የገለጸበት ጊዜ፦ አስቀድሞ ተናግሮ ቢኾን …እንለፈው ከዚህ በኋላ ወደ ስያሜህ የመቀብያ ንግግርህ ስገባ፦

እምዬ ኢትዮጵያችንን ፦ በፍቅር – በኩራት – በአድናቆትና በተስፋ – ባለፉት እጅግ ረጅም ፳፯ ዐመታት ውስጥ ሰንኳን ሊነገሩ ሊታሰቡም መቻላቸው አጠራጣሪ በኾነበት/ ከኹናቴ አውጥተህ አንተ በሙሉ ልብና ስሜት ስታነሳት ለእኔ “ አብዮታዊ!” አዎ! አኩሪ አቢዮታዊ!! ሆንህ። ደግሞስ ከመወለድህ በፊት ጀምሮ በዚያ ምክር ቤት ውስጥ ስሙ ተነስቶ የማያውቀውን የእናታችንንና ልጆችዋን ሲያጠፉ የሚቀጣ እንጂ የማያጠፋትን እንዲያውም በፍቅር የሚጠብቃትን አምላኳን አምላካችንን ማንሳትህና መማጸንህ፦ ቅዱስ ፈጣሪያችን አገእራችንን የፍቅሩ መለኪያ አድርጓት የለምን? “ የእስራኤል ልጆች ሆይ!- እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?” አሞጽ ፱ -፦ ቁ ፯ ይህ ተማጽኖህ የብዙዎቻችንን፡ ምናልባት የኹላችንንም ልብ ነክቷል። አኹንም “ ተባረክ!”

ቀጠል ሳደርግ፦ ግን “… ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ለተከሰተው ፖለቲካ አለመረጋጋት የመፍትሄ አካል ለመኾን የአገር ክብርና ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ሁኔታ በአዲስ አመራር ሊጠበቅ ይችላል ብለው በማሰብ፦ ለአህጉራችን ምሳሌ በኾነ መልኩ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ላሸጋገሩት…”

ይህን ካንተ ስሰማ “ አይ ፖለቲከኛነት!!!” አልሁ። ይህ ነገር ሲደጋገም ቆይቷል። እንዲያውም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንደዬም ኹለተዬ ተብሏል፦ ግም ባርህን ለማወደስ። ውሸት የሠርክ ልብሱ ለኾነ፦ እህ አያስደነቅም። አንተ ግን አላልህም። ከውሸታሞቹ በዚህ እንኳን ባለመደባለቅህ ደስ ብሎኛል። እስቲ እባክህ ‘ምንሥልጣን’ ይኾን የተላለፈልህ? ከየትስ መጥቶ? ስለማስታውሰው ‘ሥልጣን ስለተባለው’ ልንገርህ? ብታውቀውም! ፩- መለስ የሞተ ጊዜ እርሱ በም/ጠ.ሚኒስትርነት እያለ ለርሱ ሳይነገር ስንኳንስ በርሱ አቅራቢነት ሊኾን “ዕውንተኛዎቹ ባለሥልጣኖች” እንደተለመደው ኹለት ወንዛ-ወንዜዎቻአቸውን ጄነራል አሳስደረጉም? እንደማስታውሰው፦ ሕጉ የሚለው “ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት “ አይደለም? ጠ. ሚኒስትሩ በሌለበትስ በምክትሉ መኾን አልነበረበትም? ታዲያ ሕጉ እንዲያውም “ሕገ-መንግግሥቱን” የዚች ያልታደለች አገር ከፍተኛዎቹ ባለሥልጣኖች (ሿሚውም አሿሚውም) ሲሽሩት “ አይ አንቺ አገር! እምን ዓይነት አዘቅት ውስጥ ገባሽ? አያስብልም? በዚህ አግራሞት እንለፈውና… በባለሥልጣኖች ሕገ-መንግሥት ተብዬው የተደፈረው- የተርገጠው ተቆጥሮ አያልቅምና ወደ “ሥልጣን በፈቃድ “ አሸጋገሪ ተብዬው እንመለስ። “በሥራዬ ገባችሁ! ስልጣኔንና መብቴን ተጋፋችሁ!” አለ? ሲባል ሰምተሃል? አይመስለኝም። ብቻህንም አይደለህ። ያልተባለውን? ይህን ባለማድረጉስ “ በሃሞቱ እግራቸውን አልታጠቡም? ቀመሱት ለዚህ አይገባም። ፪- የአውሮፓ ሕብረት መማክርት ስለ ሰብአዊ መብት አነጋግረውት የፖለቲካ እስረኞቹን ለማየት አስፈቅደውት ቃሊቲ ሲደርሱ “ ይህን ትእዛዝ አናውቅም/አንቀበለም” ብለው እንደመለሷቸው አልሰማሁም እንዳትለኝ ይህስ ከኾነ በኋላ የውኅኒ ቤቶችን ባለሥልጣናት ስንኳንስ “ቀጣ!” ጠየቀ ሲባል ሰምተሃል? አለመስማትህ አይደነቅም፤አልተደረገማ!! በሌሎቹስ አገር የውኅኒ ቤቶችን ዋና አዛዥ ነበር። ፫- ኳስ ተጫዋቾቻችን አሥመራ ሄደው ለመጫወት ይችላሉን? ብላ የአልጄዚራዋ ጋዜጠኛ ስትጠይቀው “ እንዴታ!” ብሎ ሌላ ሌላም ከጨመረ በኋላ ጋዜጠኛዋ ሊሎቹ እኮ “አይቻልም!” ብለዋል ስትለው ያለው ትዝ አለህ? እንዴትስ ትዝ አይልም? በሃፍረት ለመደምሰስ ካልተሞከረ… “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኔ! እኔ ያልኩሽን ተቀብዪ!” ይሄዳሉን።” ይኾን የሰማኸው? እኔ የሰማሁት ለዓለምዐቀፍ ዜና አቅራቢ “ለኔ እኮ ምንም አይነግሩኝምን፡” ነው ታዲያ ዶ/ር ዐቢይ የቱን ሥልጣን ነው የተረከብኸው? “ሥልጣን “በሰላም!” ተላለፈ” ማለትህ ግን ግራ አጋብቶኛል። በቃሉ “ በሰላም” ትርጉም ላይ የማላውቀው መጣን? ብዬ ባስብ፦ የሰማሁትም – ያነበብሁትትም የለ። ታዲያ ክቡር ጠ/ሚ. ከስንት አስቸኳይ ጊዜ አዋጆች፡ ( በይፋ ከታወጀኡት ማለቴ ነው) በኋላ እንዴት በሰላም ተባለ? አስተማሪ ሳያሻኝ አልቀረም፤፡ ቢረሳ – ቢረሳ አጋዚዎቻችሁ እናትን ልጅዋን ገድለው እሬሳው ላይ እንድትቀመጥ ያደረጓት ይረሳ? ወይስ ይህም የሰላም ተግባር ነው???

ወደ ሥራህ ስመለከት ተስፋዬ፦ ቢያንስ እሱ የመለስን የቅርብ ሠራተኞች እንደወረስ አንተም በዚያው ዓይነት እንዳልቀጠልህ ነው። በርክክቡ ጊዜ ያየናቸው ከቀጠሉ…የአንተን ሥልጣን ምን ያህል እንደሚሸረሽረው፦ ሳስብ “ ወይ ለፍቶ መና!” ያስብለኛል። እዚህ ላይ ምን ያህል እንደምትጠነክር አላውቅም”” ዝምብለህ ከወርስህ ግን በሃዘን “ ለፍቶ መና! ! እንዳይኾንብህ ከመመኘት ሌላ ምን አደርጋለሁ? የመቀብያ ንግግርህ ላይ፦ በምናውቀው የምዕራባውያን የምርጫ ውድድር አሸናፊ የሚናገረው ዓይነት ስለነበር ብዙሃን እንደነሱ የሥራ አጋሮችህን ( ሚኒስትሮችን) አንተ የምትመርጥ የመሰላቸው ጥቂት አይደሉም።፤፡ ለእኔ ግን አይመስለኝም። ማብራራትም አያስፈልገኘም። የግም ባርህን ሥራ ከምፈልገው ጊዜ በላይ አያቻለሁና/ሰምቻለሁና። ግን አንድ ነገር ላይ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ዓይነት ምክር ልለግስ፦ ይኸውም በአንተ ምርጫ አካባቢ ጀምሮ የ “ አጋር ድርጅቶች “ መደመር ወሬ ደምቆ ይነሳል። አኹን ሚኒስትሮች ሹመት ላይ “አጋር ድርጅቶችን” ከጨመርህ – እስዬው – አብዮት ለመቀስቀስ ትመቻላችሁና! የምን አዋጅ – የምን አዋጅ ብትሉ አይቆምም። አጋር ድርጅቶቻችሁ ከእናንተ እንደእናንተ ኾነው ምርጫ ገብተው ነበር? እናንተ የሕዝብ ድምጽ ቀምታችሁ … አኹን ደግም እዚያ ቅሚያ ውስጥ በእናተነት በሌሉ እናስገዛችሁ ብትሉ “ አንገዛም!!’( የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብት መኾኑን ብንቀበልም) ሳይመረጥ አይገዛንም!! ቢል ከልካዩ ጥይት ብቻ ነው። ግን ይህ ጥይት የመጨረሻውን እንደምትፈልጉት እንደማይወስንላችሁ ይሰማኛል። ሕዝቡን አትፍጁት – መርሮታል – በቅቶታል! አትሞክሩት። ሌላው፦ ይህን ክፍል ለመደምደም “…ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ለተከሰተው ፖለቲካ አለመረጋጋት የመፍትሄ አካል ለመኾን…” ያልከውን በቀና መንፈስ ልቀበል። ግን “ ሥልጣናቸውን ( ይህን ክፍል ተነጋግረንበታል) ‘ በፈቃዳቸው ላሸጋገሩት” ያልከው ግን የሚያነጋግር አይመስልህም?። እኔ ለተሻለ ሥራ መሰለኝ፦ እንዲያውም “ነው” ለማለት እደፍራለሁ። “የተሻለ” ያልሁት ያነጋግር ይኾናል። “ከኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትርነት!?” ኾኖም፦እኔ ግን ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማ. እንደ…ሄደበት/ እንደተወሰደበት – – ይህኛው ግን ለተደላደለ ሥራ መኾኑ ይሰማኝል። ካልኾነ የለቀቀልህን የቀድሞ “ባለሥልጣን” በአደባባይ ይቅርታ እጠይቃለሁ። አንድ ሦስት ወራት እንስጠው። ለማንኛውም መልቀቁ ልርሱም ኾነ ለአገር መልካም ነው። ለ – ቀድምትነት ሊሠጠው የሚገባቸው ግዳጆች ( እንደእኔ!) ፩- በምክር ቤት የወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንተ ልታነሳው እንደማትችል ይገባኛል። ሊነሳ የማይፈልግ ወገን እንዳለም ይሰማኛል – እስከነ ምክንያቱ። ይህ ኹሉ ግን የወገንን ሥቃይ አይቀንሰውም። እዚህ ላይ አንድኹለት አባብሎች ትዝ አሉኝ፡ “ ያዲያቆነ ሰይጣን ሳያቅስስ” አይለቅም!” ይባል የለ? እንዲሁም ” አብሮ-አደግ በሽታ ካልገደለ አይለቅም፤፡” የሚባለውስ? ግም ባርህ ለምንም ይኹን ስንኳንስ ለሥልጣን ሳጥን ሳይገለብጥ፦ ድምጽ ሳይሰርቅ ቀረ ተብሎ ሲታማ ተሰምቶም አይታወቅም። ይህ ኹሉ በ”ምሥጢር” ዓይነት ነው። የዐዋጁ ድምጽ ቆጠራ ግን ዓይን አወጣ! ሕዝብን መናቅ አይደለም! “ ምናባትህ ትኾናለህ” አለው። ሕዝብን!!
እስቲ በፈጠረህ፦ ሕግ የለም እንዴ? ለእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ። እንደእማውቀው፦ እንደራሴዎቹ ባሉበት ቁጥሩ ተስተካክሎ አልያም እንደጋና ድምጽ ተሰጥቶ ነብር እንጂ በማታ ቴ.ቪኢዥን! አይ ድፍረት… አይ የሕዝብ ንቀት፡ ሕግ የለ! አስፈጻሚ የለ!! በዋናነት ዐምሐራ ላይ “ ትጥቅ ማስፈታት!” ተብሎ የሚፈጸመው ወንጀል፦ አዎን ወንጀል ዐዋጁን እንኳን የሚመለክት አይደለም። አርፎ እቤቱ የተቀመጠውን ገበሬ! ይህን የማስቆሚያ ሥልጣን ያለህ ይመስለኛል። ኾኖም “ ባለቤት ካልጮኸ…” እንደሚባለው የዐምሓራው ገዥዎች አቤት! ይቁም ማለት አለባቸው። ይህን ለማለት እንኳን ካልፈሩ! ! ! ዐምሐራው ትጥቅ እንዲፈታ የተፈለገብትና በዚህ ሰበብም የሚሰቃየው፦ ሕወሃት “ የትግራይን ሬፐብሊክ የምንመሠርተው በዐምሐራው መቃብር ላይ ነው።” ያለውን ዕውን ለማድረግ ጥርጊያውን ለማሳማር ነው። ይህን ዕኩይ ተግባር በአስቸኳይ ለማደናቀፍ አንተና የዐምሐራው ገዢ ካልፈጠናችሁ በወንጀሉ የቅድሚያ ተጠያቂነት አይቀርም። ይህን ዐኩይ ተግባር የኢትዮጵያ ልጆች ዝም ብለው የሚያሳልፉት ይመስልሃል? ፪- በሌሎቹ ያገራችን ክፍሎች ኢሕጋዊውን ዐዋጅ ለማንሳት ከየአካባቢ አስተዳደሮች ጋር በመነጋገር ክፍሎቻቸው አሸባሪ ስለሌለባቸው ኣዋጁ እንዲነሳላቸው እንዲጠይቁ በማድረግ መገላልገል ነው። ይበልጥም ህዝቡን መገላገል ይገባል። ፫- ዐዋቂዎቹ አባት/እናቶቻችን ብዙ ትምህርቶችን በአጫጭር ዐረፍተ – 0ነገሮች ትተውልናል፤፡ ከነዚህ አንዱን ላስታውስ፦ “ሺህ አውል ከሚሞት – ሺህ ይሙት !” ትርጉም አያሻውም። አኹን ያመጣሁት አንድ ዕውቅ የልብ ሐኪም ሳይፈረድብት ለረጅም ጊዜ መታሰሩን ያልሰማ የለም። “ አንድ ጥርስ ያላት በዘነዘና ልወቀር!” እንዳለችውስ አይኾንም? ስንት የልብ በሽተኞች እየተርመሰመሡ?! ይህ ዕውቅ ሐኪም በስደት ከሚኖርበት አገረ! ወገኔ ብሎ እንደመጣ እሰማለሁ፤፡ ካስፈለገ እንኳን – ካገር እንዳይወጣ በዋስ ተለቅቆ ወገገኑን ቢረዳና ከስቃይ ቢያድን – ምናልባትም ከሞት ቢያተርፍ ምን ይጎዳል? በጥብቅ እንዲታሰብበት አደራ!!! ፬ – የአንዲት አገር ዕድገትና ብልጽግና በሰላም ሊረጋገጥ የሚችችለው ፦ ሕዝብ በሚያምነውና በመረጠው ሲተዳደር መኾኑን በሚጥሙ ቃላት ደጋግመህ አስረድተሃል። ይህንኑም ዕውን ለማድረግ እስከዛሬ በተቃዋሚነት የሚታወቁትን ፖለቲከኞች በ” ተፎካካካሪነት ‘ እንዲታወቁ ኾኖ ለአገራቸው የበለጠና የተሻለ ዕቅድ ይዘው እንዲገኙ በሌሎች ተመሳሳይ (ዴሞክራቲክ) አገሮች ያለውን ኹሉ ለማሟላት ቃል ገብተሃል። ይህ ቀላል እንደማይኾንልህ እረዳለሁ። የግምባርህን ተንኮል እንኳን እኔ በዚህ እድሜ ወጣቱም ያውቀዋልና። ለዚህ ይጠቅም እንደኾን አንዳንድ አሳቦችን ልወራውር፦ -ሀ- በግም ባርህ እየተከፈሉ በርሱ ፈቃድ ፈጻሚነት በስመ-ተቅዋሚነት የተሰለፉ ብዙሃን መኖራቸው በግልጥ ይነገራል። በቀደምት ክፍያውን ማቆም ምን ይመስልሃል? ዐቅዋምህን ባሳወቅህባቸው ንግግሮች ትጸና እንደኾን፦ሃሞትህን እግር መታጠቢያ ለማድረግ ካልፈቀድህ!!!
ለ- አያሌ የሕግ ዐዋቂዎች ከማንም ያልወገኑ አሉ ( ከውስጥም ከውጪም) እነዚህ የእምዬ ልጆች፦
•የምርጫ ቦርድ ተብዬውን ክስያሜው እስከ ማስፈጸሚያው በዓለም ዐቀፍ ደረጃ መሠረት ማዋቀሪያውን እንዲያዘጋጁ፦ •ያዘጋጁትን ተውዳዳሪዎች ኹሉ ተነጋግረውበት፤- የማይስማሙበት ቢኖሩ አንድ የሽማግሌ ዐቅዋም እንዲሸምግላቸው ማረግ •በሕገእ-መንግሥት ጥላ ሊወሸቅ የሚፈልግ ቢኖር ሕገ-መንግሥት ተብዬውን እንደይረጋገጡት በመዘርዘር የሚያፍር ካለ ዓፍሪዎችን ኹሉ እንደሚዘርዘር ይወቅ። ሕዝብን አታሰቅቁት! ሐ- ተፎካካሪዎችን በተመልከተ ራሱን አስችዬ አቀርባለሁ። ፭- ወልቃይትንና ጠገዴን በተመለከተ” የተብለውን የተሸረበውን፦ በግፍ የተፈጸሙትን ኹሉ ወደጎን አድርጌ መፍትሄ የተባለው “ በሕገመንግሥቱና በሕግ መሠረት..” የተባለው ሕጋዊ ሊኾን እንደማይችል ለማስረዳት ልሞከር፤፡ ሀ- የአሜሪካን ሕገ-መንግሥት በሚረቀቅበት ጊዜ አንዳንድ ክፍሎችን ተወት ሲያደርጓቸው፡ ያሉትን ከ.ጠ.ሚኒስትር ታውቅ የለ? “ባልተሳተፍሁበት ሕግ አልገብርም፡!” አይደለም ለ- የበርሊኑ ስብሰባ ካለቀ በኋላ አሕጉራችንን ሊቀራመቱ መኾኑን እምዬ ምኒልክ ሲሰሙ “ ያልተሳተፍሁበትን ስብሰባ ውሳኔ አልቀበልም”” ካሉ በኋላ የዘመኑን ቁጥር በውል አላስታውስም፡ “ እኔ የ….ዘመን የክርስቲያን አገር ንጉስ ኾኜ እጎረቤተ ድረስ መጥታችሁ…ዝም ብሎ ለማየት ሕሊንናዬ አይፈቀድልኝም። ጥቅሱን ቃል-በቃል ባለማስተካክሌ ይቅርታ። መልዕክቱ ግን ግልጽ ነው። ሐ- እንግሊዞች ግብጽንና ሱዳንን በሚገዙበት ጊዜ የአባይን ድርሻ የወሰነውላቸውን ስምምነት ግብጾች ኢትዪኦጵያ እንድትቀበል ቢጥሩም ፡ አሻፈረኝ ማለቷንና ምክንያቷን የማያውቅ አለ? ታዲያ አማራ ሕገ-መንግሥት ተብዬው ሲረቀቅና ሲጽድቅ ያልተወክለችብተን አኹን በርሱ ተገዥ ስትባል 
 ይኾናል? !/ ! የአማራ ልሂቃን ምን ትላላች???
፮- ከሱዳን ያለንን ወሰን በተመለከት፦ ሟቹ ጠ/ሚ አንደዬ አፄ ምኒልክ ፈርመዋል፡ ሌላ ጊዜ አፄ ኃይለሥላሴ ፈርመዋል ቢል ፊርማውን ከየት ያምጣው? የመንግሥቱንም ስም ቢያነሳ “ ፊርማዬን ያምጣ!” አለው ሲባል ሰምቻለሁ። እምዬ ምኒልክ ዓባይን እንዳይገድቡ ውል ይገቡ ዘንድ እንግሊዞች ቢወተውቷቸው፦ “ ኢትዮጵያ የክርስቲያን አገር ነች፤፡ ማንም በውኃ ጥም እንዲሞት አትፈልግም። ስለዚህ አላቋአርጠውም!” ብለው ዘጉ። ጭል-ጭል ይበል ወይም ይንፏፏ የእኛ ፈንታ ነው ማለት ነው ። ድንበሩንም በተመለከተ ጉዌይን የተባለው የእንግሊዝ መኮንን እንደፈለገው ገብቶ ካርታ ላይ አስምሮ ቢያሳዩአቸው። የእኔ ድንበር ጁባ ነው፤፡ ከመሬቴ አንድ ጫማ እንኳን አሳልፌ አልሰጥም ነበር መልሳቸው፡፤ ይህም እንደ ብዙ አገሮች ደንበር ወንዝን- ሸንተረርን ትከትሎ ይሄድ እንደነበር ማስታወሱ አይከፋም። ሕወሃት ግን የሱዳንን ርዳታ በመፈለግ የአገስራችንን መሬት ለመስጠት በገባው ቃል መሠረት እስካኡሁንም ሰፊ መሬታንን እንዳሳለፈ ይነገራል፤፡ በወዳጅነት ብትመክራቸውና ቢሰሙህ የሚጠቅመን ከ፹፫ ዓ.ም በፊት ከነበረው ላይ መርጋቱ ነው። ካልኾነ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲቋቋም “ የኮሎኒዎቹን ድንበር እንያዝ” በተባለው መሠረት የለቀነውን ኹሉ የማስመለስ መብት ሊኖረን እንደሚችል ማስገንዘቡ አደብ ያስገዛቸው ይኾናል። አለበለዚይ ከእሥሬላውያንና ከፍልስጠኢማውያን ይበሰ የወሰን ግጭት እንደሚጠብቀን ማሳሰቡ አይከፋም። የሚበጀው መልካም ጉርብትናን ይዞ መቆየቱ ነው፤፡ በመጨረሻ አንድ ጠቅለል ያለ ክር ልወርውር፦ ያለህበት አጣብቂኝ ኹኔታ እንደምታምንበት የሚያሠራህ አለመኾኑን እኔ እረዳለሁ። ይህንን በመጠኑም ቢኾን ማቃለያ ቢኾን ብዬ እነሆ! ክቡር ሊ/ጄኔ ( ያንዬ ይህ ማዕረግ ብርቅ ነበር! በሚያዝያ ፷፮ ( አጠር ባለ መልኩ)) ጠርተውኝ፦ የአገር መከላከያ ሚኒስትርነት ከተሾምሁ ፫ ወራት ኾኑ። በዚህ ኹሉ ጊዜ ስንኳን አንድ ቀን አንድ ሰዓትም ለመከላከያው ተግባር ላውል አልቻልኹም። በአስተዳደር – አንዱ – ያላግባብ ማዕረግ አልስፉኝ – ሌላው ለ…ዓመት በረሃ አንገላቱኝ ፤…” በሚል አቤቱታ መስማት ተውጥሬ ዋናውን ሥራ ልሠራ አልችልኩም። አሁን አንተ ብትፈልግ በሚሊቴሪው ብትፈልግ ብሲቪሉ በምትፈልግባት ማእረግ ደረጃ በልዩ ረዳትነት ላሹምሕና እርዳኝ። አሉ መልሴ ፤- ጌታዬ እኔባለሁበት ደረጃም ከክቡርነትዎ ጋር መሥራቱን እንደ ልዩ ዩኒቨርሲቲ ትምሕርት እቀበለው ነበር። ግን ክቡርነትዎ ክ. ጠ. ሚኒስትሩ ሃሳቤን እንዲቀበል ያድርጉልኝና!” ስላቸው ፤ ለረጅም ጊዜ በሚመስል ኹናቴ ተክዘው፡
“ አሰፋ! አሉና “ አንተ እኮ እኛ ልናደርግ የሚገባንን ነበር ያሳሰብከው። አገር የሚያድን ነበር። ግን እንዳልኬ ( ( ጠ. ሚኒስትሩ) እምቢ አለ።” ብለው ትካዜያቸው ገቡ። “ ጌታዬ ይህን ሃሳብ ይህን ያህል ካመኑበት ወዳጅ ዘመድንም ጨምረው…” ስላቸው “ አይ አሰፋ ሳላደርግ – እኔ ብቻም አይደልሁ ሌሎቹስ ሳይሞክሩ ሳንሞክር የቀረን ይመስልሃል?” ብለው በዝምታ ከተዋጥን በኋላ “ መልስህ – ይህን ካላደርግህ…” ነው? አሉ? “ ‘ምን ላድርግ?’ ብዬ ወደ ሌላ ጉዳይ ሄድን። ይህን ያነሳሁት፦ አንተነም ከግራ-ከቀኝ – ከፊት – ከኋላ ይህን ይህን! እያሉ የሚያዋክቡህ እንደሚኖሩ በማመን ፡ ሕዝቡን ከግፍ ከውርደት ከሚያስተነፍሱት ውስጥ እነ ፦ •ፍርድና ፍትህን •በእስር የሚማቅቁትን • እምዬ ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ  የዳቦ ቅርጫት ትባል ነበር።  ድንግል መሬትዋ  በሙስና ከመቸርቸሩ በፊት፤ አኹንም ይህች ማስታወሻ በምትደርስብት ወቅት ተምሳሳይ ወንጀል ለመፈጸም እየተደራደሩባት ነው። በጊዜያዊ ችግር መፍቻ ሰበብ ትውልድን ለዘለቄታ ውርድት መዳረግ ምሕረት የማያሰጥ ወንጀል ስለኾነ በጥብቅ ይታሰብበት ! ! !
እንደኮሚቴ ዓይነት በማቋቋም ቢያቃልሉልህ – ምን ይመስልሃል ለማንም የማትወክለው ግን የታሪካዊዋን ሰንደቅ ዓላማችንን ጉዳይ ነው። ከላይ አማራ በሕገ-መንግስት ተብዬው ላይ እንዳልተወከለ የሰንደቅ ዓላማችንም መወርወር አስማትና መተት ያለበትን ለመያዝና ኢትዮጵያችንንም የ፻ ዓመት እድሜ ነው ያሉትን … ማዋረጃ ስለኾነ ሕዝብ አልወደደውም። እንደምታየው ሴቷም ወንዱም ወጣቱም መካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉትም ሰንደቅ ዓላማቸውን ከሻሽነት፤ ቆብ፤ የወገብ ማበቻ፤ እና የባት ማሳመሪያ እያደረገ ይዋብበታል። የነጠላና ይቀሚሱማ ማሸብረቅ አይነሳ!! ታዲያ ለምን በአባት እናትህ አያት ቅድመ- አያቶችህ ኮራህ ኮራሽ ነው? የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ልሙጡን አረንጓዴ፤ቢጫ፤ ቀዩን እንኳን ልጆችዋ ግመሎቻችንም ያቁታል። ይህ አያዋጣም! ስለዚህ ሌሎቹ የሚምሉ የሚገዘቱብት ሟቹ እንኳን ሕዝብ ካልፈለገው “ ለውጡት !!!” ብሏልና ለውጠው። አለበለዚያ ባላሳብኸው ፍጥነት እኛ እንለውጠዋለን፤ ኹሉን አትጨርሱ! የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላክ አገር ወገናችንን ይጠብቅልን፦

ከኮማንደር አሰፋ ሰይ