ራያ!
ወደ ትግሬ በግድ የተካተተው የአንጎት(ራያ) ህዝብ ብዛት በ አሀዛዊ መረጃ፤
አላማጣ፤ 286,118
ኮረም/ወፍላ፤ 262,114
ራያ አዘቦ፤ 162,106
ድምር፤ 710,338
ከፊል የራያ አካባቢዎች
እንዳ መኾኒ/ማይጨው፤ 116,262
አምባላጌ፤ 152,174
ድምር፤ 268,436
አጠቃላይ ድምር፤ 978,774
የተሰረቀው “ወያኔ” የሚለው ስያሜ፡፡
“ወያኔ” የሚለው ቃል ዐማርኛ ሲኾን፣ ትርጉሙም፡- ራስን ከውጫዊ ጥቃት ለመከላከል እና መለሶ ለማጥቃት ጦርነት የሚገጥም ሰው ማለት ነው፡፡ “ወያን” ሲል ቡድኑን የሚያመለክት ሲኾን፣ “ወያኔ” ግን የቡድኑ አባል ነው፡፡ ይኽ ቃል፣ ከደብረ ሲና ጫፍ እሰከ ራያ ሰሜናዊ ጫፍ ድረስ ያለው የምስራቅ ዐማራ ህዝብ የሚጠቀምበት ቃል ነው፡፡ በተለይም በራያ አካባቢ የተለየ ትርጉም፣ ማኅበረ-ፖለቲካዊ ፋይዳ/ቦታ አለው፡፡ በራያ ህዝብ ዘንድ፣ “ወያኔ” እንደባሕላዊ ፍልሚያ እና የራስን ወታደራዊ ብቃት መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይኽም ማለት፣ አንድ የራያ ወጣት ከ18 ዓመት በላይ ሲኾነው ጉልበቱን፣ ድፍረቱን እና የመዋጋት ብቃቱን ለመፈተሸ የሚያከናውነው ባሕላዊ ፍልሚያ ነው፡፡ ፍልሚያው በዱላ፣ በጎራዴ፣ መጥረቢያ ወዘተ ይካሄዳል፡፡ በዚኽም ልምምድ፣ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት ይከሰታል፡፡ የራያ ህዝብ ይኽን ወታደራዊ ልምምድ (ወያኔ) እንደ ጅራፍ ግርፊያ ነው የሚመለከት፡፡ ይኽም ባሕላዊ ፍልሚያ እስከ 1938 ዓ/ም ቀጥሏል፡፡
የወያኔ እንቅስቃሴ አጀማመር
ከጣልያንን መውጣት በኋላ፣ ጥር 3 ቀን 1934 ዓ/ም በነፊት አውራሪ ገበየሁ አፍለኝ እና ፊት አውራሪ ፈንታ ኩቢ መሪነት የራያ አካባቢ ህዝብ በማዕከላዊ መንግሥት ላይ አመጸ፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት አማጺዎቹን “ወያኔ” ብሎ ጠራቸው፡፡ ማዕከላዊው መንግሥት “ወያኔ” ብሎ መጥራቱ፣ የራያ ህዝብ ከነበረው ባሕላዊ “ወያኔ” ከሚለው የወታደራዊ እንቅስቃሴ አንጻር ነው፡፡ በዚኹ እለት በተፈጠረው ግጭት፣ ከመንግሥት 9 ወታደሮች እና 3 የእንግሊዝ የጦር መኮነኖች ሲሞቱ፣ በአጸፋ ቆቦ በጦር አውሮፕላን ተደበደበ፡፡ በአዲስ አበባ – አስመራ መንገድ መኖርና በሌሎች ምክንያቶች ቆቦ ለሽፍትነት ስላላመቻቸው፣ አማጺ ቡድኑ (ወያኔው) ወደ ጨርጨር ተዛወረ፡፡ ይኽን የአመጽ እንቅስቃሴ (ወያኔን) ለመጨፍለቅ 30/ሠላሳ ሽህ የሚገመት የትግሬ ሠራዊት በትግሬው ራስ ስዩም እየተመራ ከአድዋ በመንቀሳቀስ ራያን ወረረ፣ ዘረፈ፣ አጠፋ፡፡ የራያን አካባቢ እንቅስቃሴ በማየትና በተፈጠረው የአመጸኝነት ሙቀት፣ በራያ አጎራባች የትግሬ ቦታዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ ትግሬዎችም እንቅስቃሴቸውን “አረና” ብለው ሰየሙት፡፡ መሪያቸውም ብላታ ኃይለ ማርያም ረዳ ነበር፡፡ ብላታ ኃይለ ማርያም ረዳ የጣልያን ሹም የነበረ ባንዳ እንደርታዊ ሲኾን፣ የአመጹ መሠረታዊ ምክንያትም የነጻነትና የእኩልነት ጥያቄ ሳይኾን ጣልያን የሰጠውን ሹመት የትግሬው ጠቅላይ ገዥ ራስ ስዩም አላጸድቅለት ስላላው ብቻ ነው፡፡ በአጭሩ፣ የራያ አማጺ ቡድን “ወያኔ” ሲባል፣ ጥያቄውም የእኩልነት/ፍትሃዊነት/የግብር በዛብን ጥያቄ ነው፤ ያመጸውም በማእከላዊው መንግሥት ላይ ነው፡፡ የትግሬው አማጺ ቡድን “አረና” ሲባለ፣ ጥያቄውም የብላታ ኃይለ ማርያም ረዳ ጣልያን የሰጠኝ ሹመት ይከበርልኝ ነው፤ ያመጸውም በትግሬው ጠቅላይ ገዥ በራስ ስዩም ላይ ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በሰኔ 1936 ዓ/ም የአረናው ብላታ ኃይለ ማርያም ረዳ ለራያው የወያኔ ቡድን የበጋራ እንሥራ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ነገር ግን፣ ሁለቱም በነበራቸው የተለያዬ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ስነ-ልቡና፣ ለትግሉ የነበራቸው እሳቤ/መነሻ አመክንዮ እና አጠቃላይ ማንነት ሳቢያ ባለመግባባት ተቋጨ፡፡ በወቅቱም፣ የራያው ወያኔ ከ10000/አሥር ሽህ በላይ ሠራዊት ሲኖረው፣ የትግሬው አረና ግን 500/አምስት መቶ አካባቢ ብቻ ነበረው፡፡
አድዋን መነሻው ያደረገው የራስ ስዩም 30/ሠላሳ ሽህ የትግሬ ሠራዊት ሁለቱን አማጺ ቡድኖች እንዲቀጣ ተላከ፡፡ የራስ ስዩም ሠራዊት ያደረገው ግን የራሱ ወገን የኾኑትን የአረና አማጸዎችን በምክርና በተግሳጽ እንቅስቃሴያቸውን እንዲያቆሙ ብቻ ሲያደርግ፤ በራያ የወያኔ አማጺ ላይ ግን ዘግናኝ ጭፍጨፋ አድርጓል፡፡ ይኽም፣ በጥይት መግደል የሰለቸው የራስ ስዩም ሠራዊት የራያን ወያኔዎች በሳር ጎጆ እያስገባ በጅምላ በእሳት እዲቃጠሉ አርጓል፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ሰላማዊ ህዝብም አልቋል፣ ከብት ንብረቱ ተዘርፏል፣ መሬቱንም በመቀማት ጭሰኛ እንዲኾን ተደርጓል፡፡
“ተሀህት” ወደ “ወያኔ” መለወጥ ለምን አስፈለገው?
የወያኔ ትርጉም፣ ታሪካዊ አመጣጥ እና የስያሜው ተጠቃሚዎች ከላይ እንደተገለጸው የአንጎት/የራያ ዐማራዎች ኾኖ ሳለ፣ አሁን በመንግሥት ስልጣን ያለው የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን/ተሀህት/ “ወያኔ” የሚውን ስያሜ ለምን ወሰደ? በሰፊው ሲታይም፣ የትግሬ ተገነጣይ ቡድኖች ለምን በቋንቋቸው/በመዝገበ ቃላታቸው፣ በባሕላቸው፣ በማኅበረ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴቸው፣ በጥቅሉ በማንነታቸው ፈጽሞ የማይወክላቸውን “ወያኔ” የሚለውን ስያሜ ለምን ለመጠቀም ፈለጉ? ሲብስም፣ አባቶቻቸው የደፈጠጡትን “ወያኔ” የሚለውን የእኩልነት እንቅስቃሴ ለምን ለራሳቸው መጠሪያነት (ህወሓት/ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ወሰዱት? ይኽን ስያሜ የወሰዱበት መሠረታዊ ምክንያቶችም፡-
1. በ1968 ዓ/ም ፍኖተ መርሐቸውን/ማኒፌስቶ/ ሲያዘጋጁ ለመገንጠል ከሚያስፈልጓቸው ለም መሬትና የተፈጥሮ ሀብታት የሚያገኙበት አንዱ የራያ ለም መሬት ነው ብለው በማመናቸው፣ የራያን ህዝብ ታሪክ የተጋሩ በመምሰል የህዝቡን ስነ-ልቡና ማርኮ በሂደት መሬታቸውን መንጠቅ፤
2. ዐማራ መሬቱን በቀላሉ ላይሰጥ ይችላል በማለት፣ የራያን አካባቢ እንደ የጦር ቀጠና (War Buffer Zone) ለመጠቀም በማሰብ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ስዬ አብርሃ “ታንኮቻችን ማይጨው ላይ እናጥራቸዋለን” ያለውን ንግግር ያስታውሷል፡፡
3. በራያና አካባቢው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነትና ግርማ ሞገስ ለማግኘት ሲባል፤
4. አባቶቻቸው ያጨናገፉትን የራያ የፍትህ እንቅስቃሴ (ወያኔን) ታሪክ በማድበስበስ ከጥፋተኝነት ለመዳን በማሰብ፤
5. ትግሬዎች “አብዮት” የሚለውን የተለመደ የዐማርኛ ቃል ለመተካት ሌላ “ያልተለመደ”ና የራሳቸው ማስመሰል የሚችሉትን የዐማርኛ ቃል ለመጠቀም በማሰብ ነው፡፡
በአጠቃላይ የአሁኑ የትግሬ ገዥ ቡድን ራሱን እንደ “ዳግማዊ ወያኔ” የሚጠራበት እና ወጣት ትግሬዎችን “ለሳልሳዊ ወያኔነት” የሚያዘጋጅበት ምንም ዓይነት የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የባህልና የማንነት መሠረት የለውም፡፡ በተቃራኒው፣ “ወያኔ” የሚለው ቃልና አመጽ የዐማራ ቃልና ባህል ነው፡፡ ይልቁንም፣ የራያን የወያኔ የፍትህ እንቅስቃሴ በማጨናገፍና በማኮላሸት ብቸኛ ሚና የተጫወቱት ትግሬዎች ናቸው፡፡ የታሪክ እውነታው ይኽ ኹኖ ሳለ፣ ትግሬዎች በአባቶቻቸው የተጀመረ የወያኔ አመጽ እንደነበረ በማስመሰል የሚናገሩት ከሃቅ የራቀ መኾኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከአሁን በኋላ፣ ይኽ ቡድን በተገጣይ ስሙ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት/ተሀህት” ተብሎ መጠራት አለበት፡፡
ለ. በራያ ላይ የአጼ ዮሐንስ 4ኛ ወረራ እና ጭፍጨፋ፡ የራያ ሀዝብ ለንጉስ ቴዎድሮስ ታማኝነቱ በባላንባራስ ካሳ ምርጫ (የኋላው አጼ ዮሐንስ) እርዳታ አጼ ቴድሮስን ለመዋጋት የመጣውን የእንግሊዝ ጦር ከትግሬ ወደ መቅደላ ሲጓዝ የራያ ህዝብ አላሳፍ በማለት የናፒርን ሰራዊት ወግቶበታል፤ ብዙ ሰውም ገድሎበታል፡፡ በዚህም የራያ ህዝብ አርበኝነቱን እና ለአገሩና ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝነቱን አሳይቷል፡፡ ከመቅደላው ጦርነት በኋላ ቀይቶ ባላንባራስ ካሳ ምርጫ አጼ ዮሐንስ 4ኛ ተብሎ በነገሠ ማግስት፣ የእንግሊዝን ጦር የራያ ህዝብ ያደረሰበትን ጉዳት በማስታወስ የራያን ህዝብ ለመበቀል ቆርጦ ተነሳ፡፡
አድዋ ላይ ኾኖም “ራያ ይጥፋ ዱር ይገፋ” በማለት አዋጅ አስነገረ፡፡ እንግዲህ የራያ ህዝብ እልቂት የታወጀበት ሌላ ምክንያት ሳይኖር ለምን ለአጼ ቴዎድሮስ ወግናችሁ የእንግሊዝን ጦር ወጋችሁ በማለት ብቻ ነበር፡፡ ይኽም ባንዳዎች በአርበኞች ላይ ያስተላለፉት የሞት ጥሪ ነበር፡፡
በ1872 ዓ/ም፣ ባንዳው ዮሐንስ በአርበኛው የራያ ህዝብ ላይ በሁለት አቅጣጫ የእልቂት ጦር አዘመተበት፡፡
1. በራሱ በዮሐንስ የሚመራው ከኮረም ጀምሮ ገባቲ፣ ወረባየ፣ ኩፍኩፍቶ፣ መኾኒ እና መቻሬ ድረስ አጠፋው፤
2. በደጃች/ራስ አርኣያ የሚመራው ከአላማጣ ጀምሮ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ሮቢት እና ጎብየ ድረስ አጠፋው፤ እልቂቱን ውጤታማ ለማድረግ፣ ወደ ራያ የሚፈሱትን ወንዞች በመገደብ የራያን ህዝብ በውኃ ጥም ፈጀው፣ እንስሳትም እንዲያልቁ አደረገ፡፡ የዮሐንስ ሠራዊትም አገሩን ፈጽሞ ዘረፈው፣ አቃጠለው፣ አወደመው፡፡ አያሌ ቁጥር ያለው ህዝብም ወደ በረሃ ተሰደደ፡፡ የሚገርመው ግን “ወርቅ ለሰጠ ጠጠር መልስለት” ኾኖ፣ አጼ ዮሐንስ ባላንባራስ ካሳ ይባል በነበረበት ጊዜ፣ ከትግሬ ተቀናቃኞቹ ሳይቀር ደብቆ ነፍሱን ያተረፉለት ራያዎች ነበሩ፡፡ የእንጎዬ ሜዳ ጭፍጨፋ፤ በራያ ላይ ሁለተኛ እልቂት!!!
አትመነው ትግሬን፣ ቢምል ቢገዘት፤
ክርስትና አግብተው፣ ኪቢን አረዱት፡፡
ያበሉታል እንጂ፣ ያጠጡታል እንጂ፤
እንዴት ይገደላል፣ ለኾነለት ልጅ፡፡
ወደ ደጃች ገ/ኪዳን ዘሞ የተላከው የአጼ ዮሐንስ መልክተኛ ከቆቦ ከተማ ወደ ዞብል ሲያመራ አርቋቴ በተባለ ቦታ ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ፡፡ በራያ ህዝብ ላይ የማርሽር ጥላቻ የነበረው አጼ ዮሐንስ ይኽን አጋጣሚ ቂሙን ለመወጣት ተጠቀመበት፡፡ በዚኽም፣ በአካባቢው ተሰሚነት የነበራቸውን እና ራሱ ዮሐንስ የክርስትና አባት የኾናቸውን ኩቢ አባ ቦናን ለተባሉት ሰው ለአቅመ አዳም የደረሰ የራያ ሰው ኹሉ እንጎዮ ሜዳ ላይ ሰብስበው እንዲጠብቋቸው አዘዘ፡፡ በዚኽም፣ 3000/ሦስት ሽህ የራያ ሰው በረባዳው የእንጎዬ ሜዳ ተሰበሰበ፡፡ ነገር ግን፣ ቀድሞ የአጼ ዮሐንስ ሠራዊት ዙሪያውን ቦታ ቦታ ይዞ ይጠብቅ ነበር፡፡ የተሰበሰበው ገበሬ የተለመደ ስብሰባ እንጂ፣ የተደገሰለትን የሞት ድግስ አላወቀም ነበር፡፡ የዮሐንስ ሠራዊትም የተሰበሰበውን ሰው አንገት አንገቱን በመቅላት አንድም ሳይቀር ፈጀው፡፡ ሌላው ቀርቶ፣ የክርስትና ልጁን እና ታማኙን ኩቢንም አርዶታል፡፡ ይኽ ኹሉ የኾነው አንድ መልክተና ተገደለ ተብሎ ብቻ ሲኾን፣ የዮሐንስን የራያ ህዝብ ፍጹም ጥላቻ ከማሳየት ያለፈ ጉዳይ የለውም፡፡
ማንም ሰው ከላይ የኾነውን እና ሌሎች ድርጊቶችን በማገናዘብ አጼ ዮሐንስ የክርስትና ባሕሪ ኾነ ሰባዊ ርህራሄ ያልነበረው ሰው መኾኑን ይረዳል፡፡ ይልቁንም ከአገረ-ፖለቲካዊ ተክለ-ሰውነት ይልቅ የራሱን ፍላጎት/Ego የሚከተል ሰው ነበር፡፡ ለነገሩ መተማ ሄዶ የሞተውስ የጠንቋይ ምክር ተቀብሎ አይደል፡፡ ጠንቋዩም ያለው፡- መተማ ብትሄድ አንገትክን ተቀልተህ ትሞታለህ፤ መንግሥተ ሰማያት ግን ትወርሳለህ፤ ወደ ሸዋ ብትዘምት ድል ታደርጋለህ፣ አገርህንም አስፍተህና አንድ አድርገህ ትገዛለህ፤ ነገር ግን መንግሥተ ሰማያትን አትወርስም፣ የሚል ነበር፡፡ የትግሬዎች የአገራዊ ርዕይ ድርቀት ይሉሃል ይኽ ነው፡፡
መ. በራያ መሬት ላይ የትግሬ ሰፈራ
በአጼ ዮሐንስ ዘመን
ባላምባራስ ካሳ (የኋላው አጼ ዮሐንስ) ራያ ውስጥ በጥገኝነት በነበረበት ጊዜ የነበረውን የመሬት ለምነት፣ የከብት ሀብት፣ ይቀርብለት የነበረውን ስጋ፣ ማርና ወተት በማየት ውስጥ ውስጡን ይቀናና ይጎመጅ ነበር፡፡ ይኽን ለማረጋገጥ በኋላ የወሰደውን እርምጃ ማየቱ በቂ ነው፡፡ አጼ ዮሐንስ 4ኛ ተብሎ በነገሠ ማግስት፣ እያበላ እያጠጣ ከወደረኞቹ የከለለውን የራያ ህዝብ በማያባራ ጦርነት፣ ጭፍጨፋና ዘረፋ ከአዳከመ፣ የትግሬ ገዥዎችን በላዩ ላይ ከጫነ እንዲሁም ወሳኝ/ስትራተጂክ ቦታዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ምርታማና ለም በኾነው የራያ መሬት ላይ ትግሬን ማስፈር ጀመረ፡፡ ይኽም በታሪክ የመጀመርያው ነባር ህዝብን በመንቀል ትግሬዎችን የማስፈር ተግባር ኾኖ ተመዝግቧል፡፡ ነገር ግን፣ ይኽ ዘግናኝ ስህተት የዮሐንስ የአጭር ጊዜ ቆይታ መጠናቀቅ ተከትሎ በራያ ህዝብ ተውጠው ከቀሩ ውስን ትግሬዎች በስተቀር፣ ኹሉም የትግሬ ሰፋሪዎች ራያን/ዞብልን ለቀው ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡
“ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” እንዲሉ፣ በአጼ ዪሐንስ የተጀመረው የመሬት ወረራ ከመቶ አመት በኋላ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን/ተስፋፊዎች ተተግብሯል፡፡ ይኽም እንደ የሥጋና የመንፈስ አባታቸው የራያ ህዝብን በመግደል እና ማንነቱን በማውደም የተከናወነ ነው፡፡
በትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት ዘመን (ከ1968 ዓ/ም ጀምሮ)
የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በአጼ ዮሐንስ የተተለመለትን የመሬት ወረራ ተግባራዊ ለማድረግ በፍኖተ መርሁ ካካተተበት ከ1968 ዓ/ም ጀምሮ እስከዚህ ሰዓት ድረስ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይኼን ለማሳካት የሚከተሉት እርምጃዎች ወስዷል፡፡
1. በበረሃ ሽፍትነት ወቅት፣ ይቆጣጠራቸው በነበረው የራያ አካባቢዎች ተሰሚነት የነበራቸውን ባላባቶች እና ወደፊት የራያ ወደ ትግሬ መካለልን ይቃወማሉ ብሎ ያሰባቸውን ግለሰቦች በስውርና በግልጽ ገሏል፤
2. የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን በተቆጣጠረው የራያ መሬት በሚኖሩትን ተወላጆች “እኛ ነጻ ባወጣነው መሬት መኖር አትችሉም” በማለት አካባቢያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል፤
3. በ1985 ዓ/ም ከትግሬ ጋር በታሪክ፣ በማንነት እና በአስተደደራዊ አከላለል የማይገናኘው ህዝብ የሚኖርበትን ገሚሱን የራያ መሬት (ኮረም፣ አላማጣ፣ ጨርጨር ወረዳዎች) በግድ ወደ ትግሬ እንዲካተት ተደርጓል፤
4. የራያን መሬት (ኮረም፣ አላማጣ፣ ጨርጨር) ወደ ትግሬ መካተትን በመቃወም እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩትን የህዝብ ተወካዮች እንዲረሸኑ ተደርጓል፡፡ የኮረም ተወካዮች ኮረም ገበያ ላይ በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ፤ የአላማጣን ተወካዮች በወንጅል ከሶ በማሰርና በማንገላታት እንዲሞቱ፣ እንዲሰደዱ እና በስጋት እንዲኖሩ ተደርጓል፡፡ በዚኽ የተቀነባበረ ክስ ከ1985 አስከ 1990 ዓ/ም ድረስ ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲመጣ፤ “ስትፈለጉ ትመጣላችሁ” በማለት ክሱን በእንጥልጥል በመተው፣ ተከሳሾች በስጋት እንዲኖሩ ተደርጓል፡፡
5. “ወደ ትግሬ አንካለልም፣ ወሎየዎች ነን እንጂ ትግሬ አይደለንም፣ መካለል ያለብን ወደ ዐማራ ክልል ነው” ላሉት የራያ ህዝብ፣ የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን በግልጽ የመለሰው መልስ “ይኽ መሬት ደማችንን ያፈሰስንበት፣ አጥንታችንን የከሰከስንበት መሬት ስለኾነ፣ ትግሬ መኾን ካልፈለጋችሁ ተጠራርጋችሁ ከዚኽ ሂዱ፤ እና የምንፈልገው መሬቱን ብቻ ነው” ነበር፡፡
6. ከ1985 እስከ 1987 ዓ/ም የራያን ወደ ትግሬ መከለል በመቃወም የራያ ጎበዛዝት በተናጠልና በቡድን በመኾን ሸፈቱ/አመጹ፡፡ (ለምሳሌ፣ በአርብሴ ነጋ የሚመራ፣ በሞገስ አራጌ የሚመራ፣ በጌታሁን አርብሴ የሚመራ፣ በሞገስ አባተ የሚመራ፣ በተበጀ የሚመራ ወዘተ.. ይገኙበታል፡፡) ከሁለት ዓመት ትግል በኋላ፣ የትግሬ ነጻ አውጪ የአመጹትን የራያ ተወላጆች “ሽፍታ ማጥራት” በሚል ዘመቻ ሁሉንም ገደላቸው፣ አስከሬናቸውንም እንዳይቀበር በማድረግ ገበያ ላይ በማስጣት በ“እኔን ያየህ ተቀጣ” ሁኔታ የአራዊት ቀለብ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህም፣ የራያ ህዝብ ስሜት እንዲኮላሽ ተገርጓል፡፡
7. ከላይ የተጠቀሱት እና መሰል ቡድኖች/ግልሰቦች ከተመተሩ በኋላ፣ የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በፈለገው መንገድ የራያ ህዝብ ሊሄድለት ባለመቻሉ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወኔውን ለመስለብ የጅምላ እስራትና ውንጀላ አካሂዷል፡፡ በ1988 ዓ/ም 20000/ሃያ ሽህ የሚሆን ገበሬ በጅምላ የአውጫጭኝ ግምገማ ያለውን መሳሪያ አስረክብ በማለት ታስሯል፡፡ እስር ቤቶች አልበቁ ብለው በየቀበሌ ገበሬ ማኅበራት እንዲታሰሩ ተገርጓል፡፡ በእስር ቤት መጣበብና መጨናነቅ ምክንያት፣ ብዙ ሰዎች ሞተዋል፣ በሽተኛም ኾነዋል፡፡
8. የራያ ነጋዴዎችን ኮንትሮባንድ ትነግዳላችሁ በማለት ተዘርፈዋል፣ ተከሰው ተቀጥተዋል፣ አገር ለቀው እንዲሰደዱ ተገርገዋል፡፡
የራያን ህዝብ አደህይቶ የመግዛት እና ማንነቱን የማስጣል ትግሬያዊ ሴራ!
የትግሬ ፋሽስታዊ ቡድን በግድ በተቆጣጠረው የራያ አካባቢ የተለየ የቅኝ ግዛት የኢኮኖሚ ስርዓት ዘርግቶ ከተሜውንና ገጠሬውን በከፋ ድህነት እንዲማቅቅ እያደረገ ነው፡፡ በዚህም ጭካኔ የተመላበት ተግባር፣ የራያ ህዝብ በችጋር ተቆራምዶ እንዲጠፋ፣ የትግሬ ሎሌ እንዲሆን፣ አገር ጥሎ እንዲሰደድ እና የነበረውን ኩሩ እሴት እንዲጥል ኾኗል፡፡ በትግሬ ፋሽስታዊ ቡድን በራያ ህዝብ ላይ የተሠራው ኢኮኖሚያዊ ደባ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡፡
—————————————————————————
በነጋዴና በከተማ ነዋሪው ላይ፤
1. ቆሎ እና ሎሚ ሻጮች ሳይቀሩ ቀረጥ እንዲከፍሉ ማድረግ፡፡ በዚህም፣ የወረዳዋ ከተማ አላማጣ በ“ትግሬ” ክልል መቀሌንና ሌሎችን በመብለጥ በገቢ ግብር አንደኛ ኾናለች፡፡
2. ከ1978 እስከ 1989 ዓ/ም ድረስ የራያዎች የንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት እና የራያ ወጣቶችም በጣም ሃብታም የኾኑበት ወቅት ነበር፡፡ የራያዎች አቅም በኢኮኖሚ መጎልበት፣ ለትግሬው ቡድን እረፍት ነሳው፤ ሴራም ማሴር ጀመረ፡፡ በዚህም፣ ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ መሰሪ ትግሬዎች ለራያ ወጣቶች የአብረን እንሥራ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የዋሆቹ የራያ ወጣቶችም የትግሬዎችን ጥያቄ በቀና ዐይቶ በመቀበል፣ በንግድ ቡድኖቻቸው ውስጥ አስገቧቸው፡፡ ሰርጎ ገብ ትግሬዎች የራያዎችን የንግድ መስመርና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ካጠኑ በኋላ፣ ህገ ወጥ በሚል ሰበብ ለትግሬ ገዥ ቡድን አሳልፎ በመስጠት እንዲወረሱ ተደርጓል፡፡
3. በ1986-1988 ዓ/ም በትግሬ ክልል በደርግ የተወረሱ ቤቶች ለባለቤቶቹ ሲመለሱ፣ በ1985 ዓ/ም በትግሬ ክልል ውስጥ የተካተተው የራያ ባላባቶች ውርስ ቤቶች አልተመለሱም፡፡ ይኽም፣ የአካባቢው ተወላጅ በኢኮኖሚ እንዳያገግም በማቀድ የተሠራ ሥራ ሲኾን፣ እነዚሁ የራያ ባላባት ቤቶች ለትግሬ ነጋዴዎች ተላልፈዋል፡፡
በገበሬውና በገጠር ነዋሪው ላይ፤
—————————————————————————-
1. በከርሰ-ምድር ውኃ ሃብታም የኾነውን የራያ ለም መሬት በመንጠቅ ለትግሬ መስጠት፤
2. የከርሰ-ምድር እና የገጸ-ምድርን ውኃ በማሸግ አካባቢውን በውኃ እጥረት እንዲልቅ ማድረግ፤
3. የከብቶቻቸውን ቁጥር እንዲቀንሱ ማስገደድ፤
4. ማዳበሪያ ለማያስፈልገው የራያ ለም መሬት የማይጠቀሙበትን ማዳበሪያ በግድ እንዲወስዱ በማድረግ፣ በማዳበሪያ እዳ ከብቶቻቸውን እንዲሸጡ እና መሬታቸውን ለትግሬ እንዲያከራዩ ማደረግ፤
5. በአጎራባች አካባቢዎች (ኣፋር) የከብት እርባታ (ጓደና) እንዳያካሂዱ፣ አፋሩን በማስታጠቅ እንዲወጋቸው ማድረግ፤
6. በኢንቨስትመንት ስም መሬቱን እየነጠቁ ለትግሬ ባለስልጣናት መስጠት፤ ለምሳሌ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ የዘረፈው መሬት ድሮ ገበሬው እንደሚያመርተው ያለምንም ማኅበራዊ ጠቀሜታና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጤፍ ያመርትበታል፡፡
7. በከተማ ማስፋፋት ስም ያለ ምንም ካሳ የገበሬውን መሬት መቀማት፤
(ለምሳሌ፤ በ2005 ዓ/ም አላማጣ ላይ ከከተማው ዳር የሚኖሩትን 3000/ሦስት ሽህ ራያዎች በከተማ ማስፋፋት ስም ተፈናቅለው ለትግሬዎች ተሰጥቷል፡፡ የሚያሳዝነው፣ ተፈናቃዮቹን ራቅ ወዳለ ገጠር እንዲባረሩ ተደርገዋል፡፡ ይኽ የሚኾነው፣ በሁሉም የራያ ወረዳዎች በከተማ ኾነ በገጠር አንድም የራያ ልጅ በአስተዳደራዊ ስልጣን ባለመኖሩ ነው፡፡ ኹሉም የራያ ካቢኔዎች የተያዙት እጅግ ጨካኝ በኾኑ የትግሬ ማህይሞች ነው፡፡ ፖሊሶችን ጨምሮ እነዚህ የካቢኔ አባላት የሚመረጡት ጭካኔያቸውን፣ ድንቁርናቸውንና ፍጹም ጥላቻቸውን በማጥናት ነው፡፡ የራያ ህዝብ ለምንድነው በራሳችን ልጆች የማንተዳደረው ብሎ ሲጠይቅ፣ የትግሬዎች ምልስ ራሳችሁን ማስተዳደር ስለማትችሉ ነው፣ ነወ፡፡)
8. በአካባቢው ትግሬን በማስፈር የመሬት ጥበት እንዲፈጠር ማድረግ፤ ወጣቱ ማሰደድ፡፡
(በዳሰሳ ጥናት እንደተገኘው፣ ወደ ዐረብ አገራት ከሚሰደዱት ውስጥ ራያ ቅድሚያውን ይወስደል፡፡ ከአላማጣ ወረዳ ብቻ በአንድ ዓመት ከ17000/አስራ ሰባት ሽህ በላይ ወጣቶች ተሰደዋል፡፡ በሚያሳዝን መልኩ፣ በአንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች ሽማግሌዎች ሲያርፉ፣ አስከሬን ተሸክሞ ወደ ቀብር የሚወስድ ወጣት እስከማጣት ተደርሷል፡፡ ይኽም በትግሬ ገዥዎች ስውር ውስጣው ግፊት/ደባ/ የተደረገ ነው፡፡)
የራያ ህዝብ የጸረ-ትግሬ ትግል
በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በባህል እና በአጠቃላይ ማንነት ፈጽሞ ከትግሬ ጋር የማይገናኘው የራያ ህዝብ ትግሬን በተደጋጋሚ ሲዋጋ ኑሯል፡፡ የራያ ህዝብ በተለያዩ ቦታዎች ከትግሬ ጋር ጦርነቶችን ቢያደርግም፣ አጼ ዮሐንስ በባንዳነቱ ከእንግሊዝ ባገኘው ዘመናዊ ጦር መሳሪያ በመታገዝ ተጨፍጭፎ ተሸነፈ፡፡ የአጼ ዮሐንስ ሞት በትግሬ ላይ ቂም ለያዘው የራያ ህዝብ ጊዜያዊ እፎይታ ቢፈጥርም፣ ትግሬው ደጃች አብርሃ የራያን ህዝብ መውጋቱንና ሀብቱን መዝረፉን ባለማቆሙ ወደ ሌላ ግጭት ተገባ፡፡ በ1900 ዓ/ም ደጃች አብርሃ ኃይሉን በማጠናከር ራያን ወሮ አጠፋ፡፡ በ1902 ዓ/ም በአጼ ምኒልክ ተሹመው የመጡትን የዋግና ራያ አስተዳዳሪ ደጃች አባተን ለመውጋት ደጃች አብርሃ ዝግጅት አደረገ፡፡ ይኽንን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ የቆጠረው የራያ ህዝብ ከወገኑ ከደጃች አባተ ጋር በመኾን ኮረም ላይ የደጃች አብርሃን የትግሬ ጦር ገጠመው፤ አንድም ሳያስቀር ፈጀው፡፡ ከዚህ በኋላ፣ አዲሱ የትግሬ ቡድን ስልጣን እስከያዘበት እስከ 1985 ዓ/ም ድረስ የትግሬ ህዝብ የራያን ህዝብ በጦር ገጥሞ አያውቅም፡፡ የራያም ህዝብ ማንነቱን አስከብሮ ቆይቷል፡፡ ከ1985 ዓ/ም ወዲህ የራያን በግድ ወደ ትግሬ መከለል በመቃወም የትጥቅ ትግል በተደራጀና በተናጠል ተካሂዷል፣ እየተካሄደም ነው፡፡
ለምሳሌ፤ የአርብሴ ነጋ ቡድን፣ የሞገስ አራጌ ቡድን፣ የጌታሁን አርብሴ ቡድን፣ የሞገስ አባተ ቡድን፣ የተበጀ ቡድን ወዘተ ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ቡድኖች፣ የትግሬን ጦር ፊት ለፊት በመግጠምና በመደምሰስ፣ ኮምቦይዮችን በማጥቃት፣ የትግሬ ሹማምንትን በመግደል ወዘተ ጸረ-ትግሬ አቋማቸውን አሳይተዋል፡፡ ምንም እንኳ ቡድኖቹ አጠቃላይ ለውጥ ባያመጡም፤ የህዝቡን የነጻነት ትግል እንዳይጠፋ በማቀጣጠል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ ለትግሬዎች የራስ ምታትና ቀጣይ ስጋትም ፈጥረዋል፡፡ ለነዚህ ቡድኖችም የራያ ህዝብ በግጥም አክብሮቱን ገልጦላቸዋል፡፡
ከቶ ምንያደርጋል፣ ያርሲ ኩርሲ ልጅ፤
እንደአርብሴ ነጋ፣ አንድ ይበቃል እንጀ፡፡
የራያ ወጣቶች ለትግሬው ቡድን የሚሰጡት ምላሽ
በ1998 ዓ/ም በተደረገው አገር አቀፍ የተማሪዎች ስብሰባ፣ መቀሌ ላይ በተደረገው ስብሰባ፤ አገራዊ ገዳዩ ካለቀ በኋላ የትግሬ ክልላዊ አጀንዳዎቸ ሲነሱ፤ የራያ ተወላጅ ተማሪዎቸ “ትግሬዎች ባለመኾናችን፣ የትግሬ ክልላዊ ጉዳይ አያገባንም፣ አሰናብቱን” ብለዋል፡፡ በዚህም፣ ራያዎች ጸረ-ትግሬ እሳቤያቸውን አሳይተዋል፡፡ በተቃራኒው፣ በዚሁ ስብሰባ ላይ ስለተ ቋረጠው “የራያ ሸለቆ ልማት” ጉዳይ ሲነሳ፣ ትግሬ ተማሪዎች “የራያ ጉዳይ ክልላዊ ጉዳይ ስላልኾነ አንወያይም” በማለት የአጸፋ መልስ ሰጥተዋል፡፡ አብሮ የማይኼድ ብቻ ሳይኾን፣ የማይታረቅ ማንነት ማለት ይኽ ነው!!!
በ2006 ዓ/ም ማይጨው ላይ በተካሄደው የመላው ትግሬ ክልል የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ ለፍጻሜ የቀረበው የኮረም ቡድን የአክሱምን ቡድን አሸነፈ፡፡ ነገር ግን፣ ዋንጫው ወደ ኮረም ሄደ ማለት ከትግሬ ወጣ ማለት ነው በማለት የትግሬው ገዥ ቡድን ዋንጫውን ለማስቀረት ሰበብ ፈለገ፡፡ እንደ ምክንያት የተወሰደውም፣ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተምራ የተመረቀች የኮረም ተወላጅ ኮረም የምትኖር ሴት በኮረም ቡድን ውስጥ መካተቷ ነበር፡፡ ትግሬዎችም አክሱም መማሯን በማስታወስ “የአክሱም ልጅ በኮረም ቡድን ተካታለች” ብለው ዋንጫውን በፎርፌ ለአክሱም ሰጡት፡፡ በዚህም፣ በ28 መኪናዎች ለድጋፍ የሄደው የራያ ህዝብ በመኪኖቹ በማይጨው ከተማ በመዘዋወር “ድሮም ከትግሬ ጋር ኅብረት የለንም፣ እኛ ዐማራ ነን” እያሉ ጨፈሩ፣ ቀውጢ አደረጉት፡፡ ከዚያም ቀጥለው፣ ወደ ኮረም በመምጣት “ድሮም ከትግሬ ጋር ኅብረት የለንም፣ እኛ ዐማራ ነን” እያሉ ከተማውን ዙረዋል፡፡ የኮረም ህዝብም በነቂስ ወጥቶ በሆታና በእልልታ ደግፏቸዋል፡፡
የራያ ሸለቆ ልማት
በ1988 ዓ/ም በወቅቱ የትግሬ ክልል ገዥ የነበረው በዘረኛው ገብሩ አስራት ቀጥታ ትእዛዝ እንዲቋቃም የተደረገው የራያ ሸለቆ ልማት፣ በራያ ምደር ላይ የገጸ ምድር እና የከረሰ ምድር የውኃ አቅም እንዲጠና ተደረገ፡፡ በጥናቱ መሠረትም፣ የተገኘውን እምቅ የውኃ ሃብት የእስራኤልን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ እንዳንዳቸው ከ350 ሄክታር በላይ የሚያለሙ ከ600/ስድሰት መቶ በላይ ጥልቅ የውኃ ጉድጓዶች ተቆፈሩ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ ትግሬዎችን በማስፈር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እና ራያዎችን ከመሬታቸው መንቀል ነው፡፡ ስልቱም፣ በሁለት ራያዎች መካከል አንድ ትግሬ በማስገባት የራያን ህዝቡ ተቆጣጥሮ በሂደት የራያን ማንነት ወደ ትግሬነት መለወጥ ነበር፡፡
ይኽ በእንዲህ እንዳለ፣ የትግሬ ገዥ ቡንድ በገጠመው ክፍፍል የመለስ አንጃ በማሸነፉ የገብሩ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሳይተገበር ቀረ፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ሚሊዮን ብር የወጣባቸውና ብዙ ሽህ ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉት የውኃ ጉድጓዶችም እንደገተዘጉ ቀሩ፡፡ እንዲህ የተደረገውም፤
1. የራያን ህዝብ ውኃ ከልክሎ በድርቅ ማሰቃየት እና ማደህየት፡፡ አሁንም ድረስ አካባቢው በከፍተኛ ድርቅ በተመታበትና ሰዎችና እንስሳት በውኃ ጥም በሚያልቁበት ወቅት ውኃዎቹ እንደታሸጉ ናቸው፡፡ ይኽ የሚያመለክተው ዘረኛው የትግሬ ቡድን የራያን ህዝብ በችጋርና በመከራ ለመጨረስ የቆረጠ እንደሆነ ነው፡፡
2. የውኃ ጉድጋዶቹ የተቆፈሩት ለትግሬዎች በመኾኑና ይኽን ለማድረግ ሁኔታዎች ስላልፈቀዱላቸው፤
3. በማንኛውም መልኩ የራያን ህዝብ ማንነት ከትግሬ ጋር ሊስማማ እንደማይችል በመገንዘብ፣ የራያን ህዝብ የመሬት ሃብት በመቆጣጠር በኢኮኖሚና በሰባዊ ልማት ማቀጨጭ፡፡
(የዚህም ማረጋገጫው ኢፈርት የተባለው የትግሬ ማፊያ ድርጅታቸው በ2002 ዓ/ም የአምስት ዓመት እቅዱን ሲያወጣ በሰነዱ በራያ እና በሁመራ ለሚከትሉት አምስት ዓመታት ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ እንደማያደርግ አስቀምጧል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጠው፣ የሁለቱ አካባቢ ህዝብ በትግሬ ክልል ውስጥ በግድ ቢካለልም ከህዝቡ መሠረታዊ ስሜትና ታሪክ አንጻር አብሮ ለመቀጠሉ ዋስትና ስለሌለ እና አካባቢው በፖለቲካ ውዝግብ የተመላ ስለሆነ ነው፡፡)
4. በመስኖ የሚጠቀሙትን የራያ ገበሬዎችን በሚገባ መሬቱን አላለመችሁም፣ በበቂ መጠን አላመረታችሁም፣ ከእናንተ በተሻለ መንገድ በማምረት ለገበያ ማቅረብ ለሚችሉ የትግሬ ባለሀብቶች እንዲያከራዩ ጫና እና ዛቻ እየተደረገባቸው ነው፡፡ በዚህም፣ የተወሰኑ ገበሬዎች ለትግሬዎች አከራይተዋል፡፡ ሌሎችም፣ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡ ይኽ በከፍተኛ ምርታማነት ሰበብ የራያን መሬት ለትግሬ ወራሪዎች ለመስጠት የሚደረግ የዝግጅት ምዕራፍ ነው፡፡
የራያዎች የኮንትሮባንድ ንግድና የትግሬዎች ሴራ
ከ1978 እስከ 1989 ዓ/ም ድረስ የራያዎች የንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት እና የራያ ወጣቶችም በጣም ሃብታም የኾኑበት ወቅት ነበር፡፡ የንግድ ሥራው ከጅቡቲ ወደ ዐማራ ክልል የሚገባውን የኮንትሮባንድ ንግድ ያካተተ ነበር፡፡ የራያዎች አቅም በኢኮኖሚ መጎልበት፣ ለትግሬው ቡድን እረፍት ነሳው፤ ሴራም ማሴር ጀመረ፡፡ በዚህም፣ ከ1988 ዓ/ም መሰሪ ትግሬዎች ለራያ ወጣቶች የአብረን እንሥራ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የዋሆቹ የራያ ወጣቶችም የትግሬዎችን ጥያቄ በቀና ዐይቶ በመቀበል፣ በንግድ ቡድኖቻቸው ውስጥ አስገቧቸው፡፡
በአካባቢው የሚኖሩትን የትግሬ ነጋዴዎች በኮንትሮባንድ ከሚሠሩ የራያ ነጋዴዎች ጋር በሽርክና እና በጓደኝነት አብረው እንዲሠሩ ተደረጉ፡፡ ይኽ በትግሬ ገዥ ቡድን የተቀነባባረ ሴራ እና በቀጥታ ትእዛዝና ቁጥጥ የተሠራ ነው፡፡ ይኽንን የትግሬ ገዥ ቡድኑን ሴራ ያልተረዱ፣ ዘረኝነትን የማያውዱ የራያ ነጋዴዎች ሙሉ ያላቸውን ጥሪት አሟጠው ከትግሬዎች ጋር አብረው መነገድ ጀመሩ፡፡ ትግሬዎች በንግዱ ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ስላላቸው ኮንትሮባንዱ በየትኛው አቅጣጫ እንደሚገባ፣ ስንት ሰዓት እንደሚገባ፣ በምን ያክል መጠን እንደሚገባ የተሟላ መረጃ ስላላቸው ለገዥው ቡድን እና ለጉምሩክ አከላት መረጃውን አሳልፎ በመስጠት ንብረቱ እንዲወረስ ያደርጋሉ፡፡ የትግሬ ነጋዴዎች የገንዘብ ምንጭ ግን ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚዘረፈው ነበር፡፡ በዚህም፣ የራያ ወጣቶች በሙሉ ወረታቸው እቃዎችን ስለሚገዙ፣ ሲወረሱ ያለምንም ቀሪ ሳንቲም ባዶ እጃቸውን ቀርተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት፣ የራያ ወጣቶች እና ነጋዴዎች በየገበያ መግቢው ድንኳን በመትከል ለእርጠባን እና ምጽዋት ተዳርገዋል፡፡ ተሰደዋል፣ ተገለዋል፣ በብስጭት ለበሽታና ለሞት ተዳርገዋል፡፡
ትግሬዎቹ ግን በገዥ ቡድናቸው ያስወረሱትን ንብረት በርካሽ የጨረታ ዋጋ መልሰው እንዲገዙ በመደረጋቸው እና ህጋዊነት በማላበስ በይፋ ጎንደር፣ ባህር ዳር እና ዋጋ በሚያስገኝላቸው የአገሪቱ ከተሞች እንዲሸጡ ይደረግ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ የራያ ሰዎች ወደ መቀመቅ ሲወርዱ፣ ትግሬዎች ግን በሃብት ተመንድገዋል፡፡ በዚህ ወቅት የራያ ህዝብ ያተረፈው ነገር ቢኖር፣ በአጼ ዮሐንስ ጊዜ የተገጠመውን ግጥም ማስታወስ ብቻ ነበር፡፡
አትመነው ትግሬን፣ ቢምል ቢገዘት፤
ክርስትና አግብተው፣ ኪቢን አረዱት፡፡
ያበሉታል እንጂ፣ ያጠጡታል እንጂ፤
እንዴት ይገደላል ለኾነለት ልጅ፡፡
ስለራያ ጠቃሚ ሰነድ፡፡
Yikuno Amlak እንደላከልኝ እንደወረደ አስቀመጥኩት እንጅ ለውጥ አላደረግኩበትም፡፡
ከሲሳይ መንግስቴ እና አለሙ ከሳ መጽሀፍ (2005) የተወሰደ፡፡
ስለቃላት አጠቃቀሙም ሆነ ይዘቱ ሀላፊነቱ የኔ አይደለም፡፡
____ስለራያ ጠቃሚ ሰነድ፡፡
Yikuno Amlak
ከሲሳይ መንግስቴ እና አለሙ ከሳ መጽሀፍ (2005) የተወሰደ።
____________________
#ልሣነ_ዐማራ