አገርን የበዘበዘ፡ ህዝቡን ያጭበረበረው የመንግስት ኮንትሮባንዲስቶች ናቸው፡፡ በተላይ በአፋር ክልል የመንግስት አመራሮች በንግዱ አለም በህብረት ገብተው በህጋዊ መንገድ የሚነግደው አካል ከጨዋታ ውጭ የተደረገበት የብዝበዛ መድረክ ሆኖዋል አፋር ክልል፡፡ ህጋዊ ነጋዴ በግብር እያስለቀሱ ከመድረኩ እንዲወገድ ሲያደርጉ አመራሩ ግን ካለምንም ርህራሄ በሁሉም የንግድ አይነቶች ውስጥ ገብቶ ማህበረሰቡ ከሚሸከመው በላይ በኑሮው እንዲጨነቅ አድርጎታል፡፡

በተላይ በጠረፍ ንግድ ላይ የተሠማሩት የመንግሥት ባለስልጣናት ሸቀጡን እንደፈለጉ ለመአካላዊ ገበያ በማቅረብ ሚስኪኑ የአፋር ማህበረሰብ ሱኳር፡ዘይት፡ነጭ ዱቄትና ሌሎች ሸቀጦች ድሮ ከነበረው ዋጋ እንዲጨምር በማድረግ እነሱ ዶላሩን ሲያግበሰብሱ ሚስኪኑ ድሃ ግን እንባውን እንዲያነበ አድርጎታል፡፡ አሁን አሁን ነገሩ እየከፋ መጣ፡፡ አስማጭው ባለስልጣን፡ ጠረፍ ነጋዴው ባለስልጣን፡ኮንትራክተሩ ባለስልጣን፡ የጨው ማህበር አመራሮች ባለስልጣን ጊዜው በሙሉ የባለስልጣን ብዝበዛ ዘመን ሆኗዋል፡፡

የዋጋ ንረቱ ከከተሞች አልፎ ገጠር ገብተዋል፡፡ ሠው ኑሮውን በአግባቡ መኖር ከብዶት በሳምንት አንድ እንስሳን ወደ ገበያ ማቅረብ ጀምረዋል፡፡ መንግሥት ገበያ ለማረጋጋት ብሎ ያመጣው የጠረፍ ጀምላ ንግድ መስመሩን ስቶ የባለስልጣናቱ መጠቀሚያ ሆናዋል፡፡ ህዝቡም ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ አልሆነም፡፡ የፌዴራል መንግስት በጉዳዩ ላይ ጠልቃ ገብቶ አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት አለበት፡፡ በዝበዛ ሁሉ ህዝቡን የመንግሥት ካባ ለብሰው በዘበዙት ኮ:: ህዝቡ ተስፋ ቆርጦ ዝም ዝም ሆነ ነገሩ አጃኢባ፡፡