* የፋብሪካው የድጋፍ ግንብ ስድስት መቶ ሜትር ያህል ተሰንጥቋል ።
* የኩሊንግታወሩ እየሰመጠ መሆኑንና
* ግንባታው በተመረጠበት አካባቢ ረዥም የመሬት መሰንጠቅ መኖሩን በስፍራው ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል ።
( የተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት )
ልናወራ ያሰብነው ስለ ያዬ ቁጥር አንድ የማዳበሪያ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ነው ። ይህን ፋብሪካ ለመገንባት በመንግስት በኩል እንደታሰበ አንድ የቻይና ኩባንያ ፨.ነገርግን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የማዳበሪያ ፋብሪካውን በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያጠናቅቅ ለዚህም 11 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልገው በመግለፁ ፕሮጀክቱ በዚህ ብር በዚህ ቀን አጠናቅቄ አስረክባለሁ ካለው የቻይና ኩባንያ ተነጥቆ ተሰጠው ።
ሆኖም ሜቴክ ይህን የማዳበሪያ ፋብሪካ በሁለት አመታት ሰርቼ አጠናቅቃለሁ ቢልም በስድስት አመትም ሊያልቅ አልቻለም ። በነዚህ ስድስት አመታት ውስጥም የፋብሪካው ግንባታ ከ44 % በላይ ሊሄድ ካለመቻሉም በላይ ይህ ይህን የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ሲዋዋል የጠየቀው 11 ቢሊየን ብር ሆኖ ሳለ አሁን ላይ ግን ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ዘጠኝ ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልገው ገልፇል ።
ይህም ማለት የፋብሪካውን ወጪ ወደ ሃያ ቢሊየን ብር ያደርሰዋል ። የዚህ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ ቢሆንም ሜቴክ እስካሁን 60 % የሚሆነው ገንዘብ ተከፍሎታል ።
የያዪ ማዳበሪያ ፋብሪካ ጣጣ ይህ ብቻ አይደለም ። ለዚህ ፋብሪካ መስሪያ የሚሆን ገንዘብ ላበደሩ ባንኮች በቀን ወደ ሶስትሚለየን ብር ወለድ የሚከፈል ሲሆን በዚህም መሰረት በወር ዘጠና ሚሊየን ብር እየተከፈለ ይገኛል ።የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነገር በዚህ አያበቃም ፡
በማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ቦታ ላይ የሚገኙ ማናቸውም ጥሬ ሀብቶች ባለቤታቸው የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሆኑ በውል ላይ የተገለጸና የሜቴክ ስራ በውሉ መሰረት የፋብሪካውን ግንባታ አጠናቆ ማስረከብ ብቻ ሆኖ ሳለ ሜቴክ ከማዕድን ሚኒስቴር ፍቃድ አውጥቶ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሚገነባበት ቦታ ያለውን የድንጋይ ከሰል እያወጣ ካለኤጀንሲው ፈቃድ በመሸጥ ከውሉ አላማ ውጭ መንቀሳቀሱ በቋሚ ኮሚቴ አባላት ጉብኝት ቢረጋገጥም ምንም አይነት የእርምት እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል ።
ሜቴክ በሁለት አመት አጠናቅቃለሁ ብሎ እስካሁን 44% ብቻ በሰራው ይህ ማዳበሪያ ፋብሪካ እስካሁን ካለመጠናቀቁም በተጨማሪ የተሰራው ስራም ጥራቱ የወረደ መሆኑን የተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በመስክ ጉብኝታቸው ያዩትን ሲገልፁ
* የፋብሪካው የድጋፍ ግንብ ስድስት መቶ ሜትር ያህል ተሰንጥቋል ።
* የኩሊንግታወሩ እየሰመጠ መሆኑንና
* ግንባታው በተመረጠበት አካባቢ ረዥም የመሬት መሰንጠቅ መኖሩን በስፍራው ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል በማለት ለምክር ቤቱ አስታውቀው ቢሆንም ከሳሽና ወቃሽ የሌለው ሜቴክ ለችግሩ ምንም የእርምት እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል ።