መነበብ ያለበት የትህነግ/ህወሓት ሴራ!

የትህነግ/ህወሓት ተከፋይ ፌስቡከኞች በቅማንት ስም እንዴት እየነገዱ እንደሚገኙ የሚያሳይ ጥናት ነው! ይህን መረጃ አንብባችሁ፣ ለሌላው አድርሱ! ቢቻል ለገበሬውም ፕሪንት ተደርጎ መድረስ ነበረበት! ……ይህ ጥናት ከደረሰን መረጃ ትንሹ ሲሆን በቀጣይም በተከታታይ እናደርሳለን)

በ”ቅማንት ጥያቄ” ስም የሚነግደው የሕወሓት ሴራ ሲጋለጥ

ዶ/ር አብይ አህመድ መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት ካደረገው ንግግር በኋላ የወልቃይት ጉዳይ እንደገና መነጋገሪያ ሆኗል። በአማራ ሕዝብ ላይ በሚፈፀመው በደል ጩኸቱ ገዥዎችንም እስከ ማስደንገጥ ደርሷል። ከመጀመርያውም የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ የተነሳው ህወሓት የአማራን ሕዝብ እርስ በእርሱና ከሌላ ሕዝብ ጋር በማጋጨት የስልጣን ጊዜውን ሲያራዝም ኖሯል። ሰሞኑን የወልቃይት ጥያቄ እንደገና በአዲስ መልክ መነሳቱ ያሰጋው ህወሓት የተለመደ ሴራውን ጀምሯል። ዶ/ር አብይ ጎንደር በሄደበት ወቅት የቅማንት ጥያቄን የሚያነሱ ሰዎች ባነር አስልፈው እስከመግባት ደርሰዋል። ምን ምን ጥያቄ ማንሳት እንዳለባቸው ጎንደር ላይ በገዥዎቹ ድጋፍ መወያየታቸውም ተሰምቷል። ከትናንት ጀምሮ ደግሞ በቅማንት ጥያቄ ሰበብ የአማራን ሕዝብ ለማጫረስ ወደ ተግባር መገባቱ ታውቋል።

በቅርብ አመታት በደሉ የወልቃይት ጥያቄ፣ እንዲሁም የአማራ አርሶ አደሮችን እያፈናቀለ ለሱዳን የሰጠው መሬት ላይ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማዳፈን የአማራን ሕዝብ እርስ በእርስ ለማጋጨት ያስችለኛል ያለውን የቅማንትን ጥያቄ አንስቷል። የቅማንት ጥያቄ እንዲነሳ የተደረገው የወልቃይትና የሱዳን መሬት የተሰጠባቸው አካባቢዎች ድንበር ላይ መሆኑ ጥያቄ የሚያነሳውን ሕዝብ በመከፋፈልና በመወጠር ላይ የተሰመረተ ፖሊሲ ስለመሆኑ በግልፅ የሚያስረዳ ነው። የአማራን ሕዝብ እርስ በእርስ በማፋጀት የወልቃይትና ለሱዳን የተሰጠውን መሬት ጉዳይ ለማዳፈን የቅማንትን ጉዳይ በደህንነት መስርያ ቤቱ በኩል ሲያራግብ ቆይቷል። የደሕንነት መስርያ ቤቱ ጥያቄውን ከሚያራግብባቸው መንገዶች አንዱ ፌስቡክ ነው። የትግራይ ተወላጅ ደህንነቶች “ቅማንት ነኝ” በማለት በሚከፍቷቸው የሀሰት የፌስቡክ ገፆች ከደሕንነት መስርያ ቤቱ የሚሰጣቸውን የተቀነባበረ መረጃ ለሕዝብ እየለቀቁ ሲያወናብዱና ሲያጋጩ ቆይተዋል። ለዚህ እንደማሳያ “ቅማንት ኢትዮጵያዊ” በሚል የፌስቡክ ገፅ ከደሕንነት ተቋሙ የሚሰራውን ሴራ እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል። በዚህ የፌስቡክ ገፅ የሚጠቀም ግለሰብ ነዋሪነቱ መቀሌ ስለመሆኑ በፃፈበት ወቅት የት እንደነበር ፌስቡኩም ጭምር ያስረዳል።

ለምሳሌ ያህልም ረዕቡ ሕዳር 2/2016 አክሱም፣ ሰኞ ሕዳር 7/2016 መቀሌ ነበር። አርብ ሕዳር 11/2016 አዲ አብጋሄ (ትግራይ?) ነበር፣ ሕዳር 11/2016 ውቅሮ ነበር፣ጥቅምት 10/2010 መቀሌ ነበር፣ ሰኞ የካቲት 6/2017 መቀሌ ነበር፣ ረቡዕ የካቲት 8 መቀሌ ነበር፣ ሰኞ የካቲት 13/2017 ዓም መቀሌ ነበር።

ይህ ግለሰብ የደሕንነት መስርያ ቤቱ ሰው ምን አልባትም ከኃላፊዎች መካከል ሊሆን እንደሚችል የሚያስረዳው ሌላኛው ማስረጃ ከአራት በላይ ፅሁፎቹን የፃፈው አዲስ አበባ የሚገኘው የደሕንነቱ መስርያ ቤት መቀመጫ አካባቢ ስለመሆኑ ፌስቡኩ ያመለክታል። ለምሳሌ ያህል ረቡዕ መጋቢት 22/2017 ወደ INSA መጥቷል። አርብ መጋቢት 24/2017 ኢንሳ ውስጥ ነበር። ሰኞ መጋቢት 27/2017 ኢንሳ ነበር፣ አርብ መጋቢት 31/2017 ከኢንሳ ወደ መቀሌ ተመልሷል። ማክሰኞ ሚያዝያ 18 እንደገና ወደ ኢንሳ ተመልሷል። ይህም የሚያመለክተው በቅማንት ስም የተቋቋመና የሚያራግብ የፌስቡክ ገፅ ላይ በደሕንነት መስርያ ቤቱ ሰራተኛ ምን አልባትም ኃላፊ የሚፃፍ መሆኑን ነው።

በዚህ የደሕንነት መስርያ ቤቱ የቅማንትን ጥያቄ በሚያነሳበት ገፅ ላይ የሚፅፈው ሰው ውቅሮና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ድረስ የሚንቀሳቀስ (ምን አልባት ቤተሰብ ለመጠየቅ ይሆናል) መቀሌ የሚኖር፣ ወደ ደህንነት መስርያ ቤቱ የሚመላለስ ሰው ነው። ይህን ፌስቡክ የሚያንቀሳቅሰው አካል የቅማንት መሰረት ነው የሚባለው አካባቢ ብዙ እንቅስቃሴ የለውም። ከዚህ ይልቅ ለስራም ይሁን ቤተሰብ ለመጠየቅ በሚመስል ሁኔታ ወደገጠሩ የትግራይ ክፍል እንደሚንቀሳቀስ ከፌስቡክ ገፁ የተገኘው መረጃ አመላካች ነው። በአንፃሩ የቅማንት ከተማ ወደሚሏት አይከል አንድ ጊዜ የመጣ ሲሆን በነጋታው ወደ ጎንደር ሄዷል።አይከል ሀሙስ ታህሳስ 3/2016 ገብቶ፣ ቅዳሜ ታህሳስ 6/2016 ጎንደር ስቴዲዬም ገብቶ የፋሲልን ኳስ ጨዋታ አይቷል። ይህም የሚያሳየው “ቅማንት ነኝ” የሚለው ጎንደርም ሆነ አይከል የሚቆይበት፣ የሚሰራበት አጋጣሚ ሳይኖረው፣ ከመቀሌ ሆኖ ጥያቄውን እንደሚያጮህ ነው። ይህ ሰው ታህሳስ 1/2010 ጎሃ ፅዮን የነበር ሲሆን ከአዲስ አበባ ምን አልባትም ከኢንሳ ወደ አይከል እየሄደ እንደሆነ መገመት ይቻላል።

በዚህ የፌስቡክ ገፅ የቅማንትን ጥያቄ የሚያራግበው ሰው ጉዞው በአውሮፕላን ነው። ለምሳሌ ሀሙስ ሕዳር 24/2010 ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ አርብ መጋቢት 10/2017 ከቦሌ አውሮፕላን ወደ ባህርዳር እየሄደ ነበር፣ በነጋታው ቅዳሜ መጋቢት 11/2017 ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ረዕቡ መጋቢት መጋቢት 15 ከቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ባህርዳር ሄዷል። ከዚህ ጊዜ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ የቆየው ኢንሳ ነው።

በዚህ ፌስቡክ የሚጠቀመው ሰው ከሚኖርበት መቀሌና ከትግራይ ከተሞች ቀጥሎ ምን አልባትም የአማራን ሕዝብ ለማጋጨት መሳርያ የሚያደርጋቸውን የብአዴን ካድሬዎች ለማግኘት ወደ አማራ ከተሞች ይንቀሰቀቀሳል። ባህርዳር ለሶስት ጊዜ ያህል፣ ደሴ አንድ ጊዜ፣ ደብረ ብርሃንና ጎንደር አንድ አንድ ጊዜ ሄዷል። በፌስቡክ ገፁ የሚጠቀመው ሰው ለገዥዎቹ አስፈላጊ በመሆኑ በየጊዜው በሀገር ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ ከተሞች ይዞራል። ስብሰባ እና ስልጠና የሚሳተፍ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ መቱ፣ ክብረ መንግስት ላይ ሆኖ የፃፈባቸው ጊዜያት አለ። አንድ ጊዜ ማለትም ሰኞ መሰከረም 4/2017 እየሩሳሌም ሆኖ ፅፏል። እስራኤል የህወሃት ደህንነቶች ስልጠና የሚወስዱበት ሀገር ነው።

ከፃፋቸው ፅሁፎች መካከል አምስቱ ስለ ኢህአዴግ መልካም ነገር፣ ሶስቱ ስለ ህወሓት መልካምነት የተፃፉ ናቸው። ስለ ቅማንነት የሚያራግበው ይህ ፌስቡክ ፀረ አማራ፣ ከዚህም አልፎ አንድ አንድ ጊዜ በተለይ በሕዝባዊ ንቅናቄው ወቅት ብአዴንን የሚኮንን አቋም የያዘ ነው። ስለ ህወሓት አንድም አሉታዊ አቋም ያላሳየው በዚህ ፌስቡክ ገፅ የሚፅፈው ሰው (ቡድን) ትስስር በወር እስከ 40 ሽህ ብር ተከፍቷቸው የሚፅፉት የህወሓት ፌስቡከኞች የሚደርስ ነው።

ይህ እንግዲህ ፌስቡክ ላይ በተደረገ መጠነኛ ጥናት ነው። ህወሓት መቀሌና ባህርዳር ካሰለጠናቸው የፌስቡክ ካድሬዎቹ በተጨማሪ የደሕንነት ተቋሙ የመደባቸው ግለሰቦች ቅማንት መስለው የቅማንትን ጥያቄ እያራገቡ፣ ሕዝብን ከሕዝብ እያፋጁ ይገኛሉ። ይህን አንድ የፈፀስቡክ ገፅ እንደምሳሌ ተወሰደ እንጅ በርካታ በህወሓት ካድሬዎችና የደሕንነት ተቋሙ ባሰማራቸው ሰዎች የሚመሩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች አሉ። እነዚህ ገፆች ላይ የሚልፉት ግለሰቦች ከደሕንነት መስርያ ቤቱ ባሻገር ህወሓት በሚከፍላቸው ፌስቡከኞች የሚደገፉ፣ ትስስርም ያላቸው ናቸው።

የወልቃይት ተወላጆችን በሽብር የሚከሰው ህወሓት የቅማንት ማንነት ጠያቂ ናቸው በሚል መቀሌ ቢሮ ከፍቶላቸዋል። በየ ዩኒቨርሲቲው በህወሓት ካድሬዎች ተቆጣጣሪነት ሴል እያደራጀ ይገኛል። ይህ ፌስቡክ ላይ የተደረገ መጠነኛ ጥናት የሚያመለክተው “የቅማንት ጥያቄ” ለህወሓት ትልቅ መሳርያ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በፌስቡክ ይህን ያህል እያሴረ ያለው ህወሓት በተቆጣጠረው የደሕንነት ተቋም፣ መከላከያና ካድሬው በኩል የሚጎነጉነው ሴራ የተዋለደን ሕዝብ እስገማጋደል ደርሷል። ይህ መጠነኛ ጥናት የተዘጋጀው የህወሓት ሴራ ከማጋለጥ ባሻገር ሴራው ሳይገለጥላቸው “ቅማንት ነን” የሚሉ አካላት ሴራውን አውቀው መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ ግንዛቤ ለመስጠት ነው!

(ቀጥሎ ያሉት ሰንጠረዦች ግለሰቡ የት የት ቦታ ላይ ሆኖ ሲጽፍ እንደነበር የሚገልጽ ማጠቃለያዎች ናቸው።)

Muluken Tesfaw

በ”ቅማንት ጥያቄ” ስም የሚነግደው የሕወሓት ሴራ ሲጋለጥ

በ”ቅማንት ጥያቄ” ስም የሚነግደው የሕወሓት ሴራ ሲጋለጥ