April 30, 2018
ታህሳስ 25/2010 ዓም የኢሃዴግ ለረጅም ጊዜ አደረግሁ ባለው ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ባወጣው ኑዛዜ በሀገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ ማለትም ለጠፋው የሠው ህይወት ፣ ለደረሰው አካል መጉደል ፣ ለወደመው ንብረት ፣ በግፍ ታስረን ለተሰቃየነው እራሱን ተጠያቂ አድርጎ በማቅረብ በግፍ ታስረን የነበርነውን የፓለቲካ እስረኞች እንደሚፈታ ለተበደሉ ካሳ እንደሚከፍሉ በአደባባይ ደሰኮሩ በአራቱ የድርጅት መሪዎች በደብረጽዮን ፣ በለማ መገርሳ ፣ በሀይለማሪያም እና በደመቀ መኮንን በተለይ ለማ መገርሳ የማዕከላዊን መዘጋት አስመልክቶ የተናገረው ድንቅ ነበር ” ላለፉት 26 ዓመታት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የወንድሞቻችን አካል የጎደለበት ዘራቸው የተኮላሸበት …..” ይህንን ስንሰማ ከነዚህ በላይ ባለስልጣን የለም ሀገሪቱን የሚዘውሩት እነ ደብረፅዮን ስለሆኑ በእርግጠኝነት ከእስር እንፈታለን ብለን አምነን ነበር የማይታየውን ስውሩን መንግሥት መኖሩን እረስተ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሪው ፈችው የማይታወቅበት ሀገር መሆኑን ልብ ሳንለው ቀርተን መሠለኝ ፡፡
በሌላ በኩል የነዚህ ሠዎች በአደባባይ ስለ በማዕከላዊ ይህንን መናገራቸው እየተደበደብን እንደ ቋንጣ ተንጠልጥለን ያልሰጠነው የኛ ያልሆነውን ግን በዱላ ብዛት እነሱ አዘጋጅተው ተገደን የፈረምንላቸው የዕምነት ቃል ቂቂቂቂቂ ቃል 27/2 መሠረት ዋጋ አጣች አልን ደግሞ አገዛዙ በዘመኑ እንዲህ አይነት ንስሃ አውርዶ አይተን ሰምተን ስለማናውቅ ጥርጣሬው እንዳለ ሆኖ የእውነት መሠለን ምንም እንኳን ከእስር ቤት ውጭ የነበረውን የህዝብ ስሜት ባናውቅም በእስር ላይ የነበርነው አገዛዙ በሚዲያ ባወጣው መግለጫ መሠረት አድርገን በግዞት እስር ቤት ውስጥ ሰፊ ክርክሮችን አድርገን ነበር አብዛኞቻችን ኢህአዴግ አሁን ከደረሰበት ከባድ ህዝባዊ ነውጥ በመነሳት የሚወስዳቸው የለውጥ እርምጃዎች እንደሚኖሩ በዚህ ምክንያት በመላሀገሪቱ የተስፋፋው ህዝባዊ አቢዮት / አመጽ / ሊቀዘቅዝ እንደሚችል እና በኛ በኩል የምናስበው መሠረታዊ ለውጥ ማለትም አንባገነኑ አገዛዝ ፈርሶ በአዲስ የፓለቲካ ስርዓት ተገንብቶ ለውጥ እንዲመጣ የምንመኘው ለውጥ ሊዘገይ እንደሚችል ህዝቡን ለማረጋጋት እራሱ ጥገናዊ ለውጥ ያደርጋል የኛ ፍላጎት መሠረታዊ ለውጥ ሊዘገይ ይችላል የሚል እምነት ነበረን በዚህ መሠረት ሊወስዳቸው ይችላል ያልናቸው እርምጃዎች
1. ሙሉ በሙሉ በፓለቲካ የታሰሩ ዜጎችን ከእስር እንደሚፈታ
2.ብሄራዊ መግባባት ለማምጣት ብሄራው እርቅ ሊያደርግ ይችላል
3.በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ካሉ የፓለቲካ ሀይሎች ጋር ሠፋ ውይይት እንደሚደረግና እስከ ሽግግር መንግሥት ምስረታ ወዘተ እንደሚኬድ ግምት ነበረን ፡፡
ግምት የማይጣልበት አንባገነኑ ገዥ ቡድን ያሰብነውንም ጥገናዊ ለውጥ ሳያደርግ ሀይለማርያም ደሳለኝን በአቢይ አህመድ ብቻ በመለወጥ ለረጅም ዘመን በአገዛዙ ውስጥ ያረጁትን ሰዎች ቦታ በመቀያየር / ጉልቻ በመለዋወጥ / ምንም አይነት ለውጥ ሣያደርጉ በሁለት ወር ውስጥ እንፈታለን ያሉትን የፓለቲካ እስረኛ ከሶስት ወር በላይ ፈጅቶ እስረኞች ሳይፈቱ
ያደርጋል ብለን ያሰብነው ጥገናዊ ለውጥ ሣይደረግ እኔን ጨምሮ የተወሰንን እስረኞች ብቻ በመፍታት በድሮው አስተሳሰቡ በገዥነት ለመቀጠል አሁንም በመውተርተር ላይ ይገኛል ፡፡
በእኔ እምነት አገዛዙ እራሱን ጥፋተኛ ነኝ ካለ በኋላ መወሰድ የነበረባቸው ተግባራት
1.በፓለቲካ አመለካከታቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የታሰሩትን ይቅርታ አድርጌላችኋለሁ ፈርማችሁ ውጡ ሳይሆን የታሰራችሁት በኔ ጥፋት ስለሆነ እራሱ ይቅርታ በመጠየቅ እና የሞራል ካሳ በመክፈል ሁሉንም እስረኛ መፍታት
2 . ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩ እና ድርጅቱን ጥፋተኛ ነኝ እዲል ወይም በሀገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው ህይወት መጥፋት ፣ አካል መጉደል ፣ ንብረት መውደም ወዘተ ምክንያት ናቸው ያላቸውን ጥቂትም ቢሆኑ አመራሮች ለህግ በማቅረብ
3. በጉልበት የያዘውን ስልጣን መልሶ ለህዘብ በመስጠት እራሱን ማግለል ዋና ዋናዎቹ ተግባራት ሊሆኑ ይገባ ነበር ፡፡
አገዛዙ ከታህሳስ 25/2010 ዓም በኋላ ከላይ ሊተገበሩ ይገባቸው ነበር ብየ ካስቀመጥሷቸው ነጥቦች በተቃራኒው ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል ፡፡
ለምሳሌ
1. ባለፈው ዓመት ለ10 ወር ያክል ታውጆ የነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ2010 ዓም በድጋሚ ለ6 ወር ታውጇል
2. በአጭር ጊዜ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ላከናውን እቅድ ይዣለሁ እናንተም እወቁልኝ ብሎ በልሳኑ ኢቲቪ ካስተላለፈው መካከል የመጀመሪያው የፓለቲካ እስረኞችን መፍታት የነበረ ቢሆንም እሱ ፈታሁ ሊል ይችል ይሆናል ፡፡
እውነታው ግን ዛሬም በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓደኞቻችንን ቅሊንጦ ትተን መውጣታችንን ያደባባይ ሚስጥር ነው በአደባባይ አደርጋለሁ ብሎ ቃል የገባውን አንዱም ሳይተገበር ባለህበት እርገጥ እንደቀጠለ ነው ፡፡
በቀጣይስ ከኢህአዴግ ምን እንጠብቅ ?
የዚህ ፅሁፍ አንባቢ ለጥያቄው የሚሰጠው መልስ ከኔ የተለየ ይሆናል ብየ አላስብም ፡፡
እኔ ከዚህ ሥርዓት የምጠብቀው አንዳች ነገር ቢኖር በስብሻለሁ ፣ አርጂቻለሁ እየታደርኩ ስለሆነ ታገሱኝን ነው ቂቂቂቂቂቂ ፡፡