አብራሃም ግዛው

ዛሬ በቤተ- መንግስት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙዎች ያስገረመ ንግግር አደረጉ ልንታሰር ነበር አሉ።

ዛሬ ምሽት 12:00 ጥሪ ወደ ተደረገልኝ ፍልዉሃ የሚገኘዉ ብሔራዊ ቤተመንግስ አመራሁ ልክ ስደርስ 12:30 ሆኗል ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ወደ ዉስጥ ለመግባት መኪናችን እያስፈተሽ ሞባይልእና ካሜራ ባልተፈቀደበት ልዮ የእራት ምሽት መጥሪያዉ የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በብሔራዊ ቤተ- መንግስት ለአባ ገዳዎች ለኃይማኖት መሪዎች ለሀገር ሽማግሌዎች ለታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ለአርቲስቶች እና አትሌቶች በሚያቀርቡት የምስጋና ኘሮግራምና የእራት ግብዣ ላይ ሰኞ ሚያዚያ 22ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00ሰዓት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ማህተም ይህ ካርድ ወደ ሌላ አይተላለፍም። እባክዎ የጥሪዉ ካርድ እንዳይለይዎ አለባበስ:- ጥቁር ሙሉ ልብስ /የባህል ልብስ

በዚህን ልዮ ምሽት ለመታደም አርቲስቶች የክብርዶ/ር አሊ ቢራ ዮናስ ጅ አለሙ( ቤጋስ) ቀመር የሱፍ ታደለ ገመቹ ከባለቤቱ አይዳ ጋር ታደለ ሮባ ጌቻቸዉ ሃይለማርያም ደመረ ፅጌ አስቴር በዳኔ አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለ ከባለቤቱ ዳናዊት ጋር ስለሺ ስህን ጥሩነሽ ዲባባ ገዛኸኝ አበራ እልፍነሽ አለሙ ድቤ ጅሎ ሌሎችም 400እንግዶች ባሉበት ክብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ 1:15ወደ ተዘጋጀላቸዉ ስፍራ ሲያመሩ ሁሉም ከመቀመጫው በመነሳት በአክብሮት ተቀበላቸዉ። እሳቸዉ በአፀፋዉ እያቀፍ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ያላደረገዉ እያቀፍ የመጣዉ ታዳሚ ስላምታ ሰጡ እና ወደ ቦታቸዉ ተቀመጡ።

በመቀጠል ኘሮግራም መሪዉ የሃይማኖት መሪዎች ቡራኬ አደረጉ በመቀጠል አባ ገዳዎች እንዲሁም ቄሮ ወጣቶችም በተመሳሳይ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እና አቦ ለማ መገርሣ የከፈሉትን መሰዎትነት እና ፅናት ያደነቁት እያንዳንድ ተናጋሪዎች ልናግዛቸዉ ከጎናቸዉ ልንቆም ይገባል። ሲሉ አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ ንግግራቸዉ ጨርሰዉ ሲወርድ።

አንደበቱ እርቱ ጠቅላይ እንግዲ ብዙ ክፍላሀገር ሲሄድ ያሉት ይደግሙታል ወይም ያመሰግኑና ይወርዳሉ ሲባል ረዘም ያለ ንግግራቸዉ በምስጋና በመጀመር ዛሬ እንዲህ ከፊታችሁ እንድቆም ቄሮ ወጣቶች እንዲሁም ኦሮሞ ብቻዉ ሳይሆን አማራ ደብቡ ሌሎችም ብሔሮች አርቲስቶች አትሌቶች የማይናቅ ሚና ተጫዉተዋል የብዙዎች ቀልብ የሳበዉ ንግግራቸዉ… ለምርጫዉ 5ቀናት ሲቀረዉ የማሰሪያ ትእዛዝ ወጣ አሉ::

ይህም እኛ ለማሸማቀቅ አንደኛ በለማ መገርሳ እንዲሁም በእኔና በሌሎች ሦስት ጎዶች ላይ ነበር:: እኛ የሚያስፈራን ነገር ስለ ሌለና ህዝብ ከእኛ ጋር በመሆኑ ማዘዥ ያወጡት ሰዎች ደረስንባቸዉ: እነማን እንደሆኑ ያዉቁጣል ሲሉ ሁሉ በግርምት እርስ በእርሱ ይተያይ ነበር:: ብዙ ዉጣዉረዶች አልፈን ዛሬ ከእናንተጋር ለመገናኘት ችለናል እንዳለመጣደል ሆኖ ምነዉ ለዚህ ነፃነት የተዎደቁ ቄሮና ሌሎች ወገኖች ዛሬ ብያዮ ምነኛ መታደል ነበር::

ባለሥልጣን ብቻዉን ምንም ሊያደርግ አይችልም። ስለ ብሔር ከማሰብ ስለ አንዲት ኢትዮጲያ ማሰብ ይበልጣል። ትዉልድ ዉስጥ የዘራኸዉን ታጭዳለህ የኦሮሚያ ኘሬዘዳንት የተከበሩ አቶ ለማ መገርሳ የከፈለዉ መሰዎትነት ብዙ ነዉ ሊመሰገን ይገባል። ካሉ በሏላ በጋራ ማስተካከል ያለብን አስተካክለን ልንጎዝ ይገባል። ሲሉ አዳራሹ በጭብጨባና በእልልታ ሞላ::

በመቀጠል ዶ/ር አሊ ቢራ ታደለ ገመቹ ቀመር የሱፍ በተከታታይ ስራቸዉን አቅርበዎል ።

ልክ 4:30 ዝግጅቱ ሲያልቅ ብዙዎች መነጋገሪያ የነበረዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ ነገሮች ተዶልቶብናል ብዙ ሴራዎች ነበሩ ማለቻዉ አሁን አሁን ደፈር እያሉና እዉነትም ስልጣናቸዉ ማንም ሳይፈሩ እየተጠቀሙ ነዉ። በማለት ዛሬ ምሽት መወያያ ተደርጎ አምሽቷል።