‹‹የዱሮ ሰዎች ውሃ ዋና

ላይ ላዩን ነበር በጤና

የዛሬ ልጆች ይበልጣሉ

ውስጥ ለውስጥም ይሄዳሉ፡፡››

{1} የመንግሥትና የከፍተኛ ትምህርትን ተቆማት መለያየት፣

የደርግ/ኢሠፓና  የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ተቆማት ሥራ ጣልቃ መግባት የዮኒቨርሲቲ ተቆማት የእውቀት ማማነትን አጨለመው፡፡  የመለስ ዜናዊ መንግሥት 40 ምሁራንን ከዩኒቨርሲቲ ማባረሩ፣ ቀጥሎም ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ መባረር፣ የወያኔ የፖለቲካ በዮኒቨርሲቲው ጣልቃ ገብነት ያሳያል፣ የወያኔ ጣልቃ ገብነት የትምህርት ስርዓቱ እንዲወድቅ አድርጎል፣ መምህራን ዕውቀት ያላቸው ተማሪዎች መቅረፅ ተስኖቸዋል፣ የመምህራኑ ችሎታ አጠያያቂ ሆኖል፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ አስተዳደር በሙስናና ሌብነት መፈልፈያ ሆነዋል፡፡ በ2010 ዓ/ም ዮኒቨርሲቲዎች አስተዳደር ውስጥ በብዙ  ቢሊዩን ብር እንዳልተወራረደ ዋናው የኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ለተወካዮች ምክር ቤት አሳውቆል፡፡ የህገመንግሥቱ አንቀፅ 101 ‹‹ዋናው ኦዲተር የፌዴራሉን የሚኒስትርና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ሂሳቦች በመቆጣጠር በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የተመደበው ዓመታዊ በጀት፣ በበጀት ዓመቱ ለተሠሩት ሥራዎች በሚገባ መዋሉን መርምሮ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡›› የወያኔ መንግሥት የዋናው ኦዲተር ሥልጣን ከተጣሰ ዓመታት ተቆጥሮል፡፡ ስለዚህ መንግሥት ከትምህርት ተቆማት ላይ እጅና እግሩን ማንሳት ይኖርበታል፡፡

{2} የመንግሥት የፖለቲካ ሥራና የሙያተኞች ጥናት መለያየት፣

በኢትዮጵያ ስታተተስቲክስ ኤጀንሲ፣ በዓለም ባንክ፣ በዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ወዘተ በጥናታዊ መረጃ በቀረበን ሥራ ለፕሮፓጋንዳ የፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም በህግ እንዲያስጠይቅ ማድረግ፣ በሹሞች የተጋነኑ መረጃዎች ሲቀርቡ በኢትዮጵያ ስታተተስቲክስ ኤጀንሲ ፅህፈት ቤት ስህተቱን መጠበቅ፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪዎች ፣ አክቲቪስቶች በየጋዜጣዎቹ፣ ድረ-ገፆቹ፣ ኢንተርኔት፣ ወዘተ መልስ መስጠት ይጠበቃል፡፡ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ አጥኝዎች ምሁራን ሥራ ማበረታታትና  ለውይይት በመገናኛ ብዙሃን ማሰራጨት እውቅና ድጋፍ መስጠት እንዲሁም መንግሥት ለምሁራን ጥናት ዓመታዊ በጀት መመደብ ያስፈልጋል፡፡ ቀጥሎም የሚቀርበው በኢትዮጳያ የወጣት ሥራ አጦች ችግርና መፍትሄ ከኢንዱስትሪያል ዞን ግንባታ ጋር በማያያዝ የቀረበ ሲሆን በቀጣይ በዶክተር አርከበ እቁባይ መፅሃፍ ላይ ያተኩራል፡፡

{3} የመንግሥትና የቢሮክራሲ ሥራ መለያየት፣

የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የቢሮክራሲ መንግሥታዊ መዋቅር ማሽን ፕሮፌሽናል ሰራተኞች፣ ሙያዊ ክህሎታቸውን እንዳይወጡ የወያኔ መንግሥት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ምክንያት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያለ ሙያ ክህሎት በአንድ ዘር አድሎዊ መዋቅራዊ ሰንሰለት ተሰግስገው ይስተዋላሉ ለምሳሌ የደህንነት መሥሪያ ቤት፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጰያ አየር መንገድ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዚንና ሬዲዩ ድርጅት፣ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ ከላይ እስከ ወረዳና ቀበሌ ያሉ መዋቅሮች በህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬዎች የአንድ ለአምስት የተደራጅ ቢሮክራሲዊ ሠንሰለት የተዋቀረ በመሆኑ በሃገራችን ሥራና ሠራተኛ ተለያይተዋል፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የሠለጠነ አስተዳደራዊ የዘመነ ሥርዓት የደደቢት ጠርናፊ ቢሮክራሲ ወንዝ አያሻግርም፣ የሙያ ክህሎት አይኖርም፣ ፍትሃዊ አሰራርና ግልጽነት አይኖርም፡፡ ሃገራችን በዘመናዊ አስተዳደር እንድትሰለጥን ከተፈለገ የመንግሥትና ቢሮክራሲ ዘርፍ መለያየት ይገባቸዋል፡፡

{4} የመንግሥትና የሃይማኖት መለያየት፣

በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 መሰረት፣ አንቀፅ አንድ ‹‹መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዮ ናቸው፡፡›› አንቀፅ ሁለት ‹‹ መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም፡፡›› አንቀፅ ሦስት ‹‹ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡ ሃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡›› ተግባራዊ ማድረግና ለህዝብና ለተማሪዎች ማስተማር፡፡

{5} የመዘዋወር ነፃነት

በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 32 መሰረት፣ አንቀፅ አንድ ‹‹ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና መኖሪያ ቦታ የመመስረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነፃነት አለው፡፡ ››

አንቀጽ ሁለት ‹‹ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር የመመለስ መብት አለው፡፡›› ተግባራዊ ማድረግና ለህዝብና ለተማሪዎች ማስተማር፡፡

{6} የመንግሥትና የመከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ተቆማት መለያየት፣

የመንግሥትና የመከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ተቆማት ከሀገሪቱ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር መለያየት አለባቸው፡፡ ከማንኛውም ፖለቲካ ነፃ ሆነው ለህዝብ ታማኝ ሆነው ህገመንግሥቱን አክብረው መኖር ለሃገር ቃለማህላ ያደረጉበት ቃልኪዳነቸውን መጠበቅ አለባቸው፡፡ የሀገር ፖለቲካ መሪዎች ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ፡፡ ህዝብና ሃገር ግን ቀጣዬች ናቸው፡፡  የመከላከያ ሠራዊትና የደህንነት ተቆማት የወታደራዊ ሳይንስ እውቀትና ክህሎት ራሱን የቻለ ሙያ በመሆኑ እንደማንኛውም ህዝባዊ ተቆም በዘለቄታ በቀጣይነት ይሰራል፣ የመንግሥት ፖለቲካ ቢቀያየር እንኮ ይህ ተቆም ቀጣይ ነው፡፡

ህወሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት ስምንት ሚሊዮን አባላቶች ያሉት ድርጅት የመቶ ሚሊዮን ህዝብን የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ችግሮችን ሊፈታ አይችልም፡፡  ህወሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት የፊዴራልና የክልል መንግሥታት መደበኛ በጀታቸው ከህዝብ ከሚሰበስቡት ግብርና ታክስ አኮያ የሲቨልና አስተዳደር የሙያ ክህሎት ያላቸው ሠራተኞች መቅጠር የሚችሉት፡፡ ከየዮኒቨርሲቲዎቹ በዲግሪና ዲፕሎማ የተመረቁ ወጣት ዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ወጣቶች በሳይንስና በሶሻል ሳይንስ የትምህርት እውቀታቸው የፌዴራልና የክልሎች ቢሮክራሲን በዘመናዊ መልክ ማንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የፖለቲካ ካድሬና ኮሚሳር ዘመን ተስካሩ ሊወጣለት ይገባል እንላለን፡፡ ዛሬ አገር የሚቀናው እውቀት ባላቸው ሙያተኞች፣ ልምድና ክህሎት ባላቸው ምሁራን  እንጂ እንደ ደርግ ወታደራዊው መንግሥትና  እንደ ወያኔ መንግስት በፖለቲካ ታማኝነት ዘበኛም ቢሆን ሥልጣን የሚይዝበት ዘመን ማክተም ይኖርበታል፡፡ የወያኔ ጀነራል መኮንኖች ወታደራዊ ሳይንስ እውቀት የሌላቸው ከእውቀት ጋር የተጣሉ ተገዳዳላይ የዘመኑን ወታደራዊ ሳይንስ ሳያውቁ እድሜቸውን ገፉት፣ በሹመት ላይ ሹመት አራት ጀነራሎች፣ እልፍ ብርጌዴር ጀነራሎች፣ ሚሊዮን ሌፍተናል ጀነራሎች፣ ከጋንታ መሪነት ተነስተው ያለዕውቀትና ችሎታ ጀነራል ሳይሆኑ፣ ጀነራል አልናቸው! ኮነሬል ሳይሆኑ ኮነሬል አልናቸው! ይሄ የመለስ ዜናዊ ዘመን ማብቃት አለበት፡፡ ተገቢው ሰው፣ በተገቢው ቦታና ሰዓት ሃገሪቱን መምራት አለበት፡፡ ይህንንም ለማድረግ የወታደራዊ ሳይንስን መመዘኛ ያደረገ ማዕረግ መስጠትና በህገመንግሥቱ መሠረት ወታደሩ ከፖለቲካ  ጣልቃ ገብነት ውጪ ሆኖ ሃገር አሌንታ የህዝብ መከታ የሚሆንበትን መንገድ ማዘጋጀት ያሻል፡፡ በተመሳሳይ የመንግሥት ቢሮክራሲ ዘመናዊ ማሽንም ከፖለቲካ ድቤ መችዎች ካድሬና ኮሚሳር ተላቆ በሠለጠነ ዘመናዊ እውቀትና የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመናዊ እውቀት የታጠቀ፣ የአካዳሚካል እውቀቱ የመጠቀ፣ ከሌሎች ጋር ተወዳድሮ በእውቀቱና ቸሎታው ለሥልታን የታጨ መሆን ይኖርበታል፡፡ የፖለቲካ ብዱን ድጋፍ፣ ተሳትፎ በአድሎና በዘመድ ሥራ፣ በካድሬና ኮሚሳር በዘርና በፖለቲካ ድርጅቶች በአጋር ድርጅቶች እውቀት አልባ ምላስ አደሮች የተዋቀረው የወያኔ ቢሮክራሲ  ለዘለቄታው መለወጥና ዘመናዊ አስተዳደር በኢትዮጵያ ካልተጀመረ  ሃገሪቱ ልትወጣ በማትችለው ችግር በተለይ የስራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ከአመት አመት መጨመር ምክንያት አብዩት መፈንዳቱ አይቀሬ ነው፡፡ በዘመናዊ መንገድ የተዋቀረው በመልካም አስተዳዳር የዘመነው ቢሮክራሲ ማሽነሪና ዮኒቨርሲቲዎች በጥናትና የቢዝነስ ፕሮፖዛል በማቅረብ ዋነኛ ሥራዎች  በዓመት ለአንድ ሚሊዩን አምስት መቶ ሽህ ወጣቶች ሥራ የሚያስገኝ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በማድረግ ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠርና የገቢ ምንጫቸውን በማሳደግ፣ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ሃገራቸውን የሚወዱ ሙስና የተጠየፉ በሥራ ባህል ብቻ ማደግ እንደሚቻል ለቀጣዮ ትውልድ የሚያስተምሩ ዜጎች መፍጠር መቻል ይኖርብናል፡፡

ኢትዮጵያ ወጣቶች የሃያ አንደኛውን የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ለመቀላቀል አባቶቻችሁ የፈፀሙትን ስህተት ባለመድገም፣ ሁሉን ነገር በሰለጠነ መንገድ ፣በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት አዲሱን የነፃነት ዘመን አብስሩ፡፡ የዳግማዊው ዓለም ዓቀፋዊ ትስስር/ግሎባላይዜሽን በ1997 ዓ/ም ለዘብተኛና የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ የተሳተፉ ተወዳዳሪ አገሮች ከ128 በመቶ ሲደርሱ እነሱም ወደ ውጭ ሃገር ድንበር አሻግረው በቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ያደረጉት 644 ቢሊዮን ዶላር አድጎ በዓለማችን ተስተውሎ ነበር፡፡ ለዚህ ነው ቀዳማዊው የዓለም ዓቀፋዊ ትስስር ዓለማችንን ከትልቅ መንደርነት ወደ መካከለኛ መንደርነት ሲያመጣት ዳግማዊው የዓለም ዓቀፋዊ ትስስር ደግሞ  ዓለማችንን ከመካከለኛ መንደርነት ወደ ትንሽ መንደርነት የቀየራት፡፡ ሃገራችን ወደዚህ የዓለም ዓቀፋዊ ሥርዓት ለመቀላቀል ማስወገድ የሚገባን የጠባብ ብሄርተኝነት አመለካከት በህብረ- ብሄራዊ አመለካከት ብሎም አህጉራዊ አመለካከት ልቆም ወደ ዓለም ዓቀፋዊ አመለካከት መሸጋገር የሰው ልጆች የእውቀት አድማስ ምጥቀት መገለጫ በመሆኑ ነው፡፡ የዓለም ዓቀፋዊ ትስስር የእራሱ የሆነ ቴክኖሎጅዎች አሉት ኮንፒውተራይዤሽን፣ ዲጅታላይዜሽን፣ ሳተላይት ኮሙኒኬሽን፣ ፋይበር ኦፕቲክስ፣ እና የኢንተርኔት ቴክኖሎጅ ውጤቶች ዓለም ዓቀፋዊ ውህደትና ትስስርን ለማምጣት አስችሎል፡፡ ማንኛውን አገር ወደ ዓለም ዓቀፋዊ ትስስርና ዝምድና ለመግባት ይሄን ዘመናዊውን ቴክኖሎጅ ለመቅሰም የየሃገራቱ ምሁራኖች ከአገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በዓለም ዓቀፋዊ ንግድ፣ የነጻ ገበያ ውድድርና የምሁራን የዓይምሮ የፈጠራ ችሎታ ውድድር መኃል አገራቸው በምን መንገድ መሳተፍ እንደምትችል በማጥናት ዓለም ዓቀፋዊ ትስስርና ግንኑነትን ለማጠናከር ብሩህ ተስፋ አላቸው፡፡ ኢትጵያጵያዊያን ምሁራን ወደ ሃያ አንደኛውን የዲጅታል ቴክኖሎጅ ዘመን ለመሸጋገር የ‹‹ዘር ቆጣሪ፣ አጥር አጣሪ!!!›› የህሊና ደዌችንን መላቀቅ፣ ከምናባዊ የክልሎች የወሰንና ድንበር አመለካከታችን እስካልወጣን ሃገሪቱ አታድግም እንላለን፡፡ የእውቀት አድማሳችንን በማስፋት በዴሞክራሲ ባህል በውይይትና ሰጥቶ በመቀበል ቀና መንገድ በመመራትና በስታትስቲክስ መረጃ ምንጭ እየጠቀሱ ጥናትና ምርምር አድራጊ ልሂቃን በመጋበዝ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሥልጣኔ  ተቆዳሽ ለመሆን አበክረን እንስራ፡፡  የወያኔን ሥርዓተ አገዛዝ ላለፈው 27 አመታት በከፋፍለህ ግዛ ዘርና የቆንቆ ክልላዊ አስተዳደር ሃገራችንን ህዝብ አለያይቶል ገዝቶል፡፡ ዛሬ በወርሃ ሚያዝያ ሁለት ሽህ አስር በኢትጵያ  ሶማሌ ክልል የአብዲ ኢሌን አስተዳደር ብዙ ወጣቶች በአሰረ ማግስት በተነሳው ህዝባዊ አመፅ በሽንሌ ከተማ እስር ቤት ሰብረው በመግባት እስረኖች አስለቅቀዋል፣ ህዝባዊው አመፅ ተቀጣጥሎል፡፡  ነገ ደግሞ የትግራይ ወጣቶች ህዝባዊ አመፅ አቀጣጥለው ህብረ ብሄራዊው ትግል ህዝባዊ እንቢተኛነትና ተጋድሎ በመሬት አንቀጥቅጥ ንጥነጣዊ ስጥመት (tectonic depression) የወያኔ አንባገነናዊ አገዛዝ ገሃነበ እስት መዶሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

{1} በዘር የተዋቀሩ በባንክና የፋይናንሻል ዘርፍች ባንኮችና ኢንሹራንሶች መለኪያቸው በሙያ ክህሎትና የትምህርት ዕውቀት ላይ ብቻ በውድድርና በፈተና ስራ የሚገባባቸው ህብረ- ብሄር ተቆማት እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

{2} የዘር መታወቂያ ካርድ ማስቀረት፣ በኦሮሚያ የአቶ ለማ መገርሳ ኢትዮጵያዊ የሚል ታወቂያ መሥጠት ከዘር ፍጅትና ከፖለቲካ ጥላቻ ይሰውራል፡፡

{3} የመኪና ታርጋ ካፔላ  በፊት እንደነበረው መቀየር ከውድመት ያድናል፡፡ ኦሮ፣ አማ፣ ትግ፣ደቡ፣ አፋ፣ሱማ የሚለውን በኢትዮ መቀየር

{4} በዘር የተዋቀረ የመከላከያ ሥራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የደህንነት ተቆማት ህብረ ብሄረ ስብጥሩንና ሹመቱን ማመጣጠን

{5} በክልልና ዘር የተዋቀረ የዩኒቨርሲቲ ተቆማትን ህብረ-ብሄራዊ ዩኒቨርሲቲዎች ማድረግ   እንደ በፊቱ ቀ.ኃ.ሥ ዮኒቨርሲቲ መምህራኑንና ተማሪዎቹን የተቀላቀሉ ማድረግ

የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን›› ይነሳ!!!

ያደግሁባትን መሬት

ማነው ሜዳ ነው ያላት

ልናገር እኔ የማውቃት

አገሬ ጋራ ናት፡፡