
ዶ/ር አብይም የፓርላማ አባል እንካን ሆኖ ፓርላማው በህውሓት እጅ ነው ያለው ብንል እንካን ከ170 በላዩ የኦህዴድ አባላት ይቃወማሉ ብቻ ሳይሆን ስብሰባውን እረግጠው ሁሉ ሊወጡ እንደሚችሉ መገመት እንዴት ያቅተናል ። በዛን ቀውጢ ወቅት እንካን በቀናት በሰዓታት ውስጥ ምን ይፈጠራል ሀገሪቱ ውስጥ እየተባለ በተሰጋበት ሁኔታ ለማና አብይን ህውሓት ብታስር ኪሳራው ሚዛን ይደፍ ነበር ብዬ አምናለው ህውሓቶችም የህፃን ጫወታ ጭራሽ አይጫወቱም ። እንካን እነዚህን ሁለት ሚሊየን ደጋፊ ያላቸውን ሰዎችን አይደለም አንድ ሚ/ዲኤታ እንኲን ለማሰር ሙስና በሚል ተጠርጥሮ ሊታሰር ሲፈለግ በፓርላማው ያለመከሰስ መብቱ እዛው ቁጭ ባለበት እንደተነሳ አይተናል ለዚህም አቶ አለማየሁ ጉላጆ ሕያው ምስክር ናቸው ። ሰዎቹ በጣም እንዲታመኑ ዶ/ር አብይም ከህውሓት/ኢህአዴግ በተፃራሪ አቋም የቆመ ሰው ነው እንዲባል እና ከበሮ እንደ ሰሞኑ መደለቅ ስላቆመ ሌላው ስብዕና መገንቢያ እምነት ማሳደርያ ስልት ናት እኛ ደግሞ እንዳናምን ምንም ያየነው የተለየ የተጨበጠ ነገር የለም ንፋስ ብቻ ነው ።