‹‹ እናት ኢትዮጵያ ሞኝነሽ፣ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ፣የገደለሽ በላ!!! ››
በኢትዮጵያ በቀ.ኃ.ሥ ዘመንና በደርግ አገዛዝ የማዕድን ኃብት የህዝብ ኃብት ነበር!!!
የሚበላው የሌለው ህዝብ፣ መሪዎቹን ይበላል!!!›› ትንቢተ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
‹‹ ይሄ የኔ ሰው ነው፤አትንካው!!!” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው፡፡››ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
- ትዕይንት አንድ፤ የኢፌዲሪ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበረ ብሄራዊ ቤተ መንግሥት ለአባ ገዳዎች፣ ለሽማግሌዎችና አርቲስቶችና አትሌቶች ወዘተ የእራት ግባዣ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር …ለምርጫው 5 ቀናት ሲቀረው የማሰሪ ትዕዛዝ ወጣ አሉ፡፡ ይህም እኛን ለማሸማቀቅ አንደኛ በለማ መገርሳ እንዲሁም በእኔና በሌሎች ሦስት ጎዶች ላይ ነበር፡፡ እኛ የሚያስፈራን ነገር ስለሌለና ህዝብ ከእኛ ጋር በመሆኑ ማዘዣ ያወጡት ሰዎች ደረስንባቸው እነማን እንደሆኑ ያውቁታል ሲሉ ሁሉ በግርምት እርስ በእርስ ይተያይ ነበር፡፡ ብዙ ውጣ ውረዶች አልፈን ዛሬ ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ችለናል እንዳለመታደል ሆኖ ምነው ለዚህ ነፃነት የወደቁ ሌሎች ወገኞች ዛሬ ብያዮ ምነኛ መታደል ነበር፡፡›› ገዳዮቹን የአጋዚ ጦር ለፍርድ ማቅረብና ለሞች ወላጆች የደም ካሳ ማሰጠት ከትያትር ሥራዎ ትወና ይልቅ በተግባር ያሳዩ እንላለን፡፡
- ትዕይንት ሁለት፤ በውጭ ሃገር የሚገኙ የሬዲዬና ቴሌቨዥን ጣቢያዎች የኦሮሞ ሚዲ ኔትወርክ፣ ኢሳት ወዘተ የመሳሰሉት አዲስ አበባ ውስጥ ሆነው ዝግጅታቸውን እንዲያቀርቡ ዶክተር አቢይ አህመድ ለቤኒሻንጉል ህዝብ ንግግር መድረካዊ ትወና አድርገዎል፡፡ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት ያልቻለ መሪ ኃላ ከጥላው ሌላ የሚከተለው እንደማይኖር መገንዘብ ህሊና ላለው ግልፅ ነው፡፡ በዓለማችን በፕሬስ ነፃነት ከ180 ሃገራት 150 የሆነችው ሃገራችን፣ በፀረ ሽብር ህግ ሰለባ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ለሞት፣ ለእስራት፣ ለስደት መዳረጋቸውን ሳያውቁት ቀርተው አይመስለንም፡፡ ከበረቱ ከወሬ ይልቅ የአስቸኮይ ጊዜ አዋጁን ማስነሳት፣ እስረኞች መፍታት፣ የጸረ ሽብር ህግ፣ ማስነሳት ላይ ይበርቱ፡፡
- ትዕይንት ሦስት፤ ሰሞኑን ሜድሮክ ኩባንያ በለገደንቢ የወርቅ ፋለጋና ቁፋሮ ሥራ እንዲሠራ የወያኔ መንግሥት የ10 ዓመት ፍቃድ ሠጥቶታል፡፡ ይህም የኢትዮጵያን ህዝብና የኦሮሞ ቄሮ አስቆጥቶል፡፡ ‹‹ ለአለፈው 20 ዓመታት ኩባንው በህዝባችን ላይ፣ በአካባቢው እና በቤት ውስጥና በዱር እንሰሳት ላይ ያደረሰውንና አሁንም እያደረሰ ያለውን ጉዳት (የሰው ሞት፣ የአካል መጉደል፣ የፅንስ ማስወረድ፣ሁለ ገብ የጤና መቃወስ፣የዓየር፣ የውሃ፣ እና የአፈር መበከል፣ የእንሰሳት ማለቅ፣ የአዋፋት መሰደድ ወዘተ) እንዳላዮ በማለፍ መንግሥት የፈቃድ እድሳት መፍቀዱ ለህዝባችን ስቃይ ቅንታት ታህል ግድ እንደሌለው አስረግጦል፡፡››
ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች፡- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ከታወጀ በኃላ በሃገሪቱ 31 ያህል ሰዎች ተገድለዋል እንዲሁም 1077 ሽህ ሰዎች ታስረዋል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለማንሳት ህብረ-ብሄራዊ የሦስት ቀን የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ለማድረግ ዝግጅት ይደረግ ቀን ይቆረጥ !!! ከኦሮሞ ወገኞቻችን የትግል ጥሪ፣ ከሱማሌ ወገኞቻችን የትግል ጥሪ በመስማት ህዝባዊውን እንቢተኛነትና ተጋድሎ ማቀናጀት ይጠበቅብናል፡፡ ነፃነት በትግል እንጅ በስጦታ አይገኝም!!! ወያኔ ታግሎ እንጅ ለምኖ ሥልጣን ላይ አልወጣምና!!! ዶክተር አብይ አህመድ ወይ ከህዝብ ጋር ወግን ወይ ከወያኔ ጋር ህዝቡ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ ብሎልና፣ ልጆቻችን አይገደሉም፣ መሬታችን አይመራም፣ ወርቃችንን አይዛቅም፣ ከብታችን አይነዳም፣ እህላችን አይጫንም፣ ድል በትግል ብለን ቆርጠን ተነስተናል፡፡
‹‹አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ እንዳሉት ሰላም ባለ ድምፅ ተራራ ላይ ወጥቶ በመጥራት አይመጣም፡፡ ሰላም እንዳይኖር ያደረገው የኢህአዴግ አገዛዝ ነው፡፡ ህዝቡማ ምንጊዜም ሰላም ወዳድና ሁሌም ሰላማዊ ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለሰላሙ ዘብ ይቁም ብሌ ጥሪ ማድረግ እምብዛም ቦታ የለውም፡፡በመሆኑም እውነተኛ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ፅህፈት ቤቱ ተመልሶ፣ ካቢኔውን ሰብስቦ በአራት ነገሮች ላይ ውሳኔ መስጠት ነው፡፡››
- ‹‹የሰላም ጠንቅ የሆነውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማንሳት፣ (ዶክተር አብይ ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ›› 1- እሁድ ሚያዝያ 7 ቀን 2010 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል፣ በቡሌ ሆራ ከተማ ጉጂ ዞንና ገርባ ከተማ፣ ውስጥ የአጋዚ ወታደሮች አራት ሰዎችን መግደላቸውታውቆል፡፡ አምስት ሰዎች አቁስለዋል፡፡የሃረማያ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬም በአጋዚ ጦር ሠራዊት ይደበደባሉ፣አጋዚ ከግቢያችን ይውጣ ነው ጥያቄቸው፡፡ አጋዚ ልዮ ሃይል በሞያሌ ሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ቦንብ ወርውረው ከባድ ጥቃት አደረሱ 3 ሰዎች ገደሉ፣ 64 ሰዎች አቆሰሉ የሚል በድረገፆችና ቪኦኤ ተገልፆል፡፡) ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ከታወጀ በኃላ በሃገሪቱ 31 ያህል ሰዎች መገደላቸውንና 1077 ሽህ ሰዎች መታሰራቸውን ይታወቃል፡፡ ከሁሉ በፊት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማንሳት ጦሩን ወደ ካንፑ ማስገባት፣ ግድያ ማቆምና እስራት ያብቃ፡፡
- የህዝቡን የልብ ትርታ ለማየት የፖለቲካ እስረኞችን በችርቻሮ መፍታትን አቁሞ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ትእዛዝ ማስተላለፍ፣ ከሃያ ሰባት ዓመታት ጀምረው በጨለማ ቤቶች ውስጥ ታጉረው የሚሰቃዩ በኦነግ ስም የታሰሩትን ጨምሮ፡፡›› ከዲያስፖራ ወገኖቻችን ወያኔ በእስራት ለሚያሰቃያቸው ዜጎችና የአገር ቤት ዜጎች እንዲፈቱ እንታገል!!! ከየመን ታፍኖ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ፣አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ በአስቸኮይ እንዲፈታ ህዝብ ይጠይቃል፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ዲያስፖራ ተቃዋሚ የህዝብ ልጆችን እያደኑ በመግደል ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔዊ ተግባር ፈፅመዋል፡፡ ለስብሰባ ከመጡት ዲያስፖራ ወገኖቻችን አቶ አበራ የማነአብ ለአስራ አምስት ዓመታት በግፍ በመለስ ዜናዊ ሴራ ታስሮ መፈታቱን ልብ ይበሉ፡፡ ወ/ሮ ገነት ግርማና ሌሎቹም ታሪክ ያስታውሳቸዋል፡፡ ዲያስፖራው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የልብ ህክምና ሆስፒታል ገንብተው ወገኛቸውን በማገልገል ላይ እያሉ እስካሁን በወህኒ ቤት በግፍ ይሰቃያሉ፡፡ ከጋምቤላ ቱወት ፖል ቢፈቱም ሌሎችም የጋምቤላ እሰረኛች አልተፈቱም፣ ይፈቱ!!! ከኦጋዴን አብዲከሪም ሼህ ሙሴ ሌሎችም ይፈቱ!!! በኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እስረኞች በአስቸኮይ ይለቀቁ!!! (ለአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኛ ፂዮን ግርማ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች የዘገብሽውን በእስረኞች ሥም የከበረ ምስጋናና የጋዜጠኛ ሙያሽን ቀጥይበት እያልን፣ በጉዲፈቻ ስለተሸጡ 25 ሽህ ህጻናት፣ ውስጥ የ7000 ህፃናቶች አድራሻቸው የማይታወቅ እናቶች ስቃይ በመዘገብ የእናቶቹን እንባ ብታብሽ አደራ እንላለን!!!)
- በየመንደሩና በከፍተኛ የትምህርት ተቆማት ውስጥ ተበትነው ሰላም የሚነሱትን የመከላከያና አጋዚ ጦር ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ማስተላለፍ፡፡››
- ከእውነተኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እውነተኛ ድርድር ለማድረግ ለሁሉም በግልፅ ይፋዊ ጥሪ ማድረግ፡፡ እነዚህ አራት መሰረታዊ ጉዳች ትክክለኛ መልስ ካገኙ ህዝቡ ለሌሎች ጥያቄዎች መልስ ጊዜ ሊስጥ ይችላል፡፡ ሰላም የሚመጣው ያኔ ብቻ ነው፡፡ ህዝብ ሰላም የሚያጣው ጦርነት ሰላለ ብቻ አይደለም፡፡›› አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ለዶ/ር አብይ ያስተላለፉት መልዕክት! የተወሰደ ነው፡፡
የማዕድን ኃብታችን ሁኔታ
የሃገሬ ህዝብ የማዕድንህን ኃብት ለወያኔ አታስበዝብዝ፣የጥይት መግዣ ይሆናቸዋልና!!! የሃገሪቱ የተፈጥሮ የማዕድን ኃብቶች ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ሃገሪቱ ያልተጠቀመችባቸውን እምቅ የማእድን ኃብቶች በጂኦሎጂካል ሰርቬይ ጥናት አቅምና ችሎታ በማሳደግ ትችላለች፡፡ የዓለም ባንክ ለታዳጊ አገራት በማእድን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከሚያደርገው ድጋፍ ውስጥ የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት፣ ተወዳዳሪ፣ ራዕይ ያለው፣ ኃላፊነት የሚሰማው ስትራቴጂ በመንደፍ፣ በህግ ፍህታዊ የሆነና ማህበራዊ ኃላፊነት የሚወጣ የማዕድን ኃብት ማለትም የአልማዝ፣ ወርቅ፣ የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ እንዲኖራቸው ያማክራል፡፡በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ በጮርቃ የዕድገት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በሚያነጥሩ አንጥረኞች ከክርስትና ሃይማኖት በኃላ ጀምሮ የማዕድን ቁፋሮ እንደተጀመረ ይገመታል፡፡ ሆኖም ያልተዛቀ ብዙ እምቅ የማዕድን ኃብት እንዳለ ይታመናል፡፡ በኢትዮጵያ ጥንታዊ መንግስታት ዘመን ጀምሮ ባህላዊ የወርቅ ምርት፤ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ከአክሱም እስከ አዶሊስ የመሬት ስር የውስጥ ለውስጥ የዋሻ መንገድ ነበረ ይባላል፣ በዛ የጨለማ ዋሻ ጎዳና የተጎዙ ሰዎች ከዋሻው ያገኙትን በእጃቸው እየዘገኑ አልፈው ከዋሻው መውጫ በር ሲደርሱ በእፍኛቸው የጨበጡትን ሲያዩት ወርቅ ሆነና ‹‹የዘገነም፣ ያልዘገነም እኩል አዘነ›› እየተባለ ይተረታል፣የዘገነው ጨመር አድርጌ አፍሼው በነበረ ብሎ!!!፣ ያልዘገነው ምነው አፍሼው በነበረ ብሎ!!! አሉኝ የአክሱምን ቅርስ ያስጎበኑኝ ቄስ፡፡ ኢትዮጵያ ስፊና የተለየ ባህላዊ የማዕድን ዘርፍ ወርቅ የማንጠር ብልኃትና ጥበብ የተካኑ ከ1 ሚሊዮን አስከ 1.5 ሚሊዩን (2009 ዓ/ም) የወርቅ አንጥረኛ ጠበብት ያላት ሃገር ናት፡፡ የወርቅ አንጥረኞቹ ለዜጎች ጠቃሚ የሆነ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ለሃገሪቱ የውጪ ንግድ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግና የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት ከወያኔ መንግሥት ኃላፊነት በላይ የሰሩ የኢትዮጵያኖች ባህላዊ ወርቅ አንጣሪዎች ታሪክ አይረሳቸውም፡፡ በ2012 እኤአ የማዕድን ዘርፍ 19 በመቶ የአጠቃላይ የውጪ ንግድ ሸፍኖል፣10 በመቶ የውጭ ምንዛሪ አስገኝቶል፡፡ ከማዕድን የውጪ ንግድ በወርቅ ምርት የተገኘው ከ100 መቶ የሚጠጋ ሲሆን ከዚሁም ውስጥ በአመዛኙ ሁለት ሦስተኛው ገቢ የተገኘው ከባህላዊ የወርቅ አምራቾች መሆኑን የዓለም ባንክ ግሩፕ በጥናት በድረ-ገፁ አረጋግጦል፡፡ ‘‘Ethiopia also has an extensive and unique artisanal mining sector; the government estimates there are around 1 million miners, making it an important source of job creation, and an important source of foreign currency. Although the industry is in its infancy stage, the contribution to the country’s exports is already significant. In 2012, mining was responsible more than 19% of the total value of exports, and up to 10% of foreign exchange earnings. Gold makes close to 100% of mining exports and most of it, about 2/3, comes from artisanal mining, according to a recent World Bank Group (WBG) partner study, Strategic Assessment of the Ethiopian Mineral Sector”
የሃገሪቱ ካላት የማዕድን ኃብቶች ዘርፍ መሪውን ስፍራ የያዘው ወርቅና ላይም ስቶን ምርቶች ሲሆን በአነስተኛ ምርቶች ደረጃ የሚመረቱት ውስጥ ታንታለም፣ ጨውና፣ፑሚስ ይገኛሉ፡፡ የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣ ዋና ዓላማ በማዕድን ኃብት ዘርፉ ሃገሪቱ ጥሩ ገቢ እንድታገኝ ለማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ካለው እምቅ የማእድን ኃብቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆንና በተግባር ድህነትን እንዲቀንስ ለማበረታታትና መንግሥት በዘርፉ ለውጥ ጉልህ ሚና እንዲጫወት ማማከር ነው፡፡ በኢትዮጵያ የማዕድን ኃብት ዘርፍ 14 በመቶ ለውጪ ንግድ፣ 1 በመቶ ለአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ)፣ 2 በመቶ ለመንግሥት ገቢ ሲያስገኝ እንዲሁም ሪፖርት ባደረጉት ካንፓኒዎች መረጃ መሠረት ለ11,000 ሰዎች የሥራ እድል ፈጥሮል፡፡ “The country is a leading producer of gold and limestone, but also produces smaller quantities of tantalum, salt and pumice. Ethiopia EITI aims at helping the government reform the mining sector to ensure a good return on Ethiopia’s significant untapped mineral resources. Extractive Industries contribution 14 % to exports 1 % to GDP 2 % to government revenue 11 thousand jobs (reporting companies only) ” Website EITI Ethiopia
በአጠቃላይ በ2009 ዓ/ም መረጃ መሠረት በባህላዊ የወርቅ አምራቾች ለአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በላይ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረና ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው የውጪ ንግድ ገቢ የሚያስገኘውና የውጪ ምንዛሪ ገቢ የሚገኘው ከባህላዊ የወርቅ አምራቾች ዘንድ ነው፡፡ በአንፃሩ በዘመናዊ የወርቅ አምራቾች በአል-አሙዲን ሚድሮክ ጎልድና በህወኃት/ኢፈርት ኢዛና ወርቅ ካንፓኒዎች ከዚሁ የማዕድን ዘርፍ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የውጪ ንግድ ገቢና የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኙ ሲሆን ለአስራ አንድ ሽህ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በሁሉም የሀገሪቱ ሥፍራዎች የተገኙ የወርቅ ማዕድን ቦታዎችን በአግአዚ ጠራዊት እያስጠበቁ በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ድንበር ዘለል የወርቅ ማዕድን ኮንትሮባንድ ንግድ ከወርቅ ማዕድን ኃብት ዘርፍ በውጪ ንግድ ገቢ ከ2003 እስከ 2009 ዓ/ም ማሽቆልቆል፤ የኢትዮጵያ የንግድ ሚኒስቴር ከወርቅ ማዕድን ኃብት ዘርፍ በውጪ ንግድ ገቢ ያገኘችው ውጪ ምንዛሪ ገቢ ሪፖርት መረጃ እንደሚያሳየው፡-
- በ2003 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 430 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 16.1%፣ድርሻ ነበረው፡፡
- በ2004 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 620 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 19.1%፣ድርሻ ነበረው፡፡
- በ2006ዓ/ም የወርቅ ውጪ ንግድ 456.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 13.8% ድርሻ ነበረው፡፡
- በ2007 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 318.7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ –% ድርሻ ነበረው፡፡
- በ2008 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 219 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 30.1% ድርሻ ነበረው፡፡
- በ2009ዓ/ም የወርቅ ውጪ ንግድ 209.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 10.1% ድርሻ ነበረው፡፡
ከወርቅ ማዕድን ኃብት ከውጪ ንግድ የተገኘው 620 ሚሊዮን ዶላር ወደ 209 ሚሊዮን ዶላር መውረድ ዋነኛ ምክንያት የወርቅ ማዕድኑ በኮንትሮባንድ በተለያዩ አጎራባቾች ሃገራት በኩል መውጣት፣ ሚድሮክ፣ ኢዛናና የቻይና ኩባንያዎች የሚላከውን የወርቅ ምርት በመቀነስ የውጭ ምንዛሪውን ገቢ ውጪ በማስቀረት፣ራሳቸውን ተጠቃሚ በማድረግ የሃገርና የህዝብ ጥቅምን አስቀርተዋል፡፡ በብሄራዊ ባንክ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የወርቅ ምርት በ2006ዓ/ም 12350 ኪሎ ግራም የነበረ ሲሆን፣ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ በመሄድ በ2007ዓ/ም 9000ኪ/ግ፣ በ2009ዓ/ም 8580ኪ/ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ ተሸጦል፡፡ የወርቅ ማዕድን ኃብታችን የመቀነስ ሚስጢሩ የኮንትሮባንድ ንግድ ነው!!! መፍትሄው፣ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን የክልል መንግሥታትና ህዝብ መታገልና መጠየቅ አለበት፡፡ “በህይወቴ በዓለም ላይ ለሕዝብ ተጨንቆ ሲሰራ ያየሁት ሁለት መንግስት ብቻ ናቸው ፡እነሱም የኢትዮጵያና የሳኡዲ ዓረቢያ መንግስት ናቸው” ሸህ አላሙዲን ከሚሉ “በህይወቴ በዓለም ላይ በሙስና ተጨማልቆ ሲሰራ ያየሁት ሁለት መንግስት ብቻ ናቸው፣እነሱም የኢትዮጵያና የሳኡዲ ዓረቢያ መንግስት ናቸው”ቢሉ ይሻላቸው ነበር።
‹‹ የወርቅ ባህላዊ አምራቾች፣ ለሃገሪቱ የወርቅ ወጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፆኦ ካላቸው መካከል ባህላዊ አምራቾች ሰፊውን ድርሻ በመያዝ በዘርፉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡በየዓመቱ ለውጪ ገበያ ከሚቀርበው የወርቅ ምርት ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ ድርሻ የሚይዘው በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ወርቅ ሲሆን፣ ከ1.5 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች በባህላዊ ወርቅ የማውጣት ሥራ ውስጥ በመሰማራት የህልውናቸው መሠረት ለመሆን ችሎል፡፡›› በባህላዊ መንገድ የሚመረተው የወርቅ ምርት በ2004ዓ/ም 8327.7 ኪሎ ግራም ወርቅ በባህላዊ መንገድ ተመርቶ ለብሄራዊ ባንክ ቀርቦ ነበር፡፡በመሆኑም 439.3 ሚሊን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ተገኝቶበታል፡፡ ይህም በ2004ዓ/ም ከወርቅ ከተገኘው 620 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ገቢ አኮያ ሲመዘን፣ በባህላዊ መንገድ ከሚመረተው የተገኘው ምርት የአብላጫውን ድርሻ ለመያዙ አመላካች ነው፡፡ ለወርቅ የውጪ ንግድ መቀነስ የኮንትሮባንድ ንግድ ነው፡፡ የብሄራዊ ባንክ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ የሚያቀርቡ ማህበራት ምርቱን ባቀረቡበት ዕለት ካለው የዓለም የወርቅ ዋጋ አምስት በመቶ ጭማሪ በማድረግ ግዥ ይፈፅማል፡፡ ይሁንና የኮንትሮባንድ ንግድ ሊገታ ባለመቻሉ፣ ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚመጣው የወርቅ መጠን በየጊዜው እንዲቀንስ አድርጎል፡፡ ከ2004 ዓ/ም ወዲህ የወርቅ ምርት እየቀነሰ ለመምጣቱ ከዓለም የወርቅ ዋጋ መውደቅ አንዱ ቢሆንም የወርቅ ምርቱን በመጨመር የውቺ ምንዛሪ ገቢን ከፍ ማድረግ ሲቻል፣ በአሁኑ ወቅት በባህላዊ መንገድ የሚመረተውም ሆነ በኩባንዎች በኩል ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የወርቅ ምርት በአቅርቦት ደረጃ በእጅጉ ቅናሽ ማስመዝገቡን ቀጥሎል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ጀነራል መኮንኖች በህገወጥ የድንበር ንግድ ዋነኛዎቹ አይነኬ ተዋናዮች በመሆናቸው እነሱን ከሥልጣን መንበራቸው መንቀል ግድ ይላል፣ ብሎም ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል አይደለችም!!!
The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI)
የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣ በዓለም ደረጃ የማዕድን ኃብት ዘርፍ የተሰማሩ ሃገራቶች፣በመንግስተና በግል ዘርፎች የተሰማሩ የማእድን ኩባንያዎች፣ በአልማዝ፣ ወርቅ፣ ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝና የሚኒራል ኃብት ግልፅነት ያለው አጠቃቀም ማለትም በተፈጥሮ ኃብት የተሰማሩ የማእድን ኩባንያዎች፣ ገቢያቸውን ማሳወቅ፣ ተጠያቂነትና ታማኝነታቸውን የሚያሳይ፣ ከማዕድን ኃብቱ የህዝብ ተጠቃሚነትንና ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት ያለውን አስተዋፅኦና ለሃገሪቱ ለውጭ ምንዛሪ ገቢ የሚያበረክተውን ድርሻ እንዲሁም ከሙስናና ከሌብነት፣ ግልጽ ካልሆነ አሰራር፣ አድሎ ወዘተ ማህበራዊ ኃላፊነት በሃቅና በገለልተኛ ተቆም ማስረጃ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ያልሆነበት ልማትና ጥቂቶች ብቻ ተጠቃሚ የሆኑበት የደም ገንዘብ (Blood Money) በኮንጎ የዶይመንድ ንግድ እንዲሁም በናይጀሪያ የነዳጅ ኃብት ወዘተ በናሙናነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በኢትዩጵያችንም የማዕድን ኃብት የለገደንቢ ወርቅ ግልፅነት በሌለው አሰራር ይመዘበራል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ሹማምንቶችና የጦር መኮንኞች፣ ካድሬዎች፣ ጥቂት የአገር ቤትና ቦህር ማዶ ምላሳዊ ጋዜጠኞች፣ ጥቂት የድረ-ገፅ፣ የሬዲዬ፣ የቴሌቪዝን ድቤ መችዎች የአል-ሢሦ መንግስት ደም-ሞዝተኞች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንዳትሆንና የሌብነት ሥርዓት እንዲቀጥል የሚያደርጉ የአል-ድቤ መችዎቹ ቪላ ቤቶች፣ መኪኖችና ረብጣ ብር ከሽህ አል ተበርክቶላቸዋል፡፡
የማዕድን ኃብት ባለሃብቶች ለመንግሥት የገቢ ግብርና ሮያሊቲ ወዘተ በግልጽነት የሚከፍሉበትን ማስረጃ በዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣ የሕግ ማእቀፍ ህግና ደንብ ተከትለው መስራታቸውን የሚመሠክር ገለልተኛ የሆነ ተቆም ነው፡፡ በማእድን ማውጣት የተሰማሩ ኩባንያዎች፣የከፈሉትን ግብር ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላቸዋል፡፡ ለዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ዋና ማረጋገጫው፣ መንግሥትም ከማዕድን ኃብት ያገኘውን የግብር ገቢ፣ ሮያሊቲ ወዘተ ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃንና በጋዜጦች መረጃውን እንደወረደ በየሩብ፣ መንፈቅና ዓመታዊ ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም የኩባንያዎቹና የመንግሥት ሪፖርቶችን የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣ የማዕድን ዘርፍ ሪፖርት በገለልተኛ አካል ኦዲት ተደርጎ የማዕድኑ ገቢ ለሁሉም የአገሪቱ ዜጋ በፍትሃዊነት የሚውል መሆኑን ሃብቱ ያለጥርጥር የአገሪቱን ኢኮኖሚ በመቀየር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ያሻሽላል፡፡ የማዕድን ኃብት የባለቤትነት ሰሜት በህዝቡ ዘንድ እየሠረፀ ይመጣል፡፡ በዓለም አቀፍ ተቆማት የማእድን ዘርፉን አሰራርና ግልፅነት ያላቸውና የሌላቸው ሃገራቶች ማስረጃ በይፋ ወጥቶ ይገለፃል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል ባለመሆኖ ሃገሪቱ በሚድሮክ ወያኔና በቻይና፣ የማዕድን ኃብቶች በግልፅና በድብቅ ዝርፌያ ላይ ትገኛለጭ፡፡ “The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) is an international standard for openness around the management of revenues from natural resources. It is designed to improve accountability and public trust for the revenues paid and received for a country’s oil, gas and mineral resources. It asks:
- companies to publish what they pay for oil, gas, quarrying and mining
- governments to disclose what they receive from oil, gas, quarrying and mining. These figures are audited by an independent administrator and published along with contextual information in the EITI report.”1
‹‹የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ ከስምንት ዓመታት በፊት የተጀመረ ሲሆን፣ከአራት ዓመታት በፊት በ2000ዓ/ም የመጀመሪያውን ሪፖርት አቅርቦ ነበር፡፡ 35 የሚሆኑ በማእድን ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንዎች በሪፖርቱ ተካተው ነበር፡፡ ከነዚህም ውስጥ 26 ያህሉ ዝርዝር የሆኑ ኩባንያዎቹን በማን ባለቤትነት እንደተያዙ ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ‹‹ዕጩ አባል›› መሆን ችላለች፡፡ ‹‹ሕጉ ገለልተኛ በሆነ አካል መውጣት ሳላለበት በእኛ አማካይነት ወጥቶል፤›› ሲሉ አቶ መርጋ ይናገራሉ፡፡ የሕግ ማእቀፉ በማእድን፣ ነዳጅና የተፈትሮ ጋዝ ሚኒስቴር ስር ሆኖ አፀፋዊ ፍተሸ እንዲደረግ ይረዳዋል፡፡››1 ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንዳትሆን ህጉ በገለልተኛ በሆነ አካል እንዳይወጣ የሚያደርጉ ሹማምንቶች ከመጋረጃው በስተጀርባ በመተወን አስር አመታት አስቆጥረዋል፡፡ በማዕድን ኃብታችን በሙስናና ሌብነት የተጨማለቀ ሥርዓት እስካልወደቀና እ..ተመነገለ ድረስ ሃገሪቱ መቼም አባል አትሆንም!!!
የተፈጥሩ ማዕድን ብሄራዊ ሪፖርት
ለተባበሩት መንግስታት ኮሚሸን ለዘለቄታዊ እድገት THE UNITED NATION COMISSION ON SUSTAINABLE DEVELOPMENT (UNCSD) ኒው ዬርክ
የኢትዬጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር
አዲስ አበባ ፣ህዳር 2009 እኤአ
‹‹ከ1974 እስከ 1991 እኤአ በሃረሪቱ የግል ኢንቨስትመንት በማዕድን ሃብት ዘርፍ ላይ አልነበረም፡፡ እንዲያውም የመንግስት ዘርፍ የሆኑ ኢንስቲትውሸንስ የሃረሪቱን ማዕድን ሃብት የመፈለግና የማውጣት መብት ሙሉ መብት ነበራቸው፡፡ በ1991 እኤአ የፖለቲካ ለውጥ ምክንያት፤ አዲስ በገበያ መር የተቃኘ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በሃገሪቱ ተዋወቀና ወጣ፡፡ በማዕድን ሃብት ዘርፍ፤መንግስት አዲስ የማዕድን ሃብት አዋጅ፣ የማዕድን ሃብት ታክስ አዋጅ በማውጣት የግል ዘርፉን ባለሃብቶች በማዕድን ሃብት ዘርፍ የማዕድን አሰሳ፣ ፍለጋና፣ ልማት የስራ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ፈቀደ፡፡ የማዕድን ሃብት አዋጅ ቁጥር 52/1993፣ የማዕድን ሃብት ደንብ ቁጥር 182/1994 እዲሁም የገቢ ታክስ አዋጅ ቁጥር 53/1993 አዋጅ በማውጣት የግል ዘርፉን ባለሃብቶች መዕዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱና ለመሳብ ታቀደ፡፡ አዋጆቹ በየግዜው እየተሻሻሉና በዓለም ዓቀፍ ደረጀ ተፎካካሪና ለኢንቨስተሮች ተስማሚ እንዲሆን ተደረገ፡፡ እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ የወርቅ ማዕድን ምርት የለማበት የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ነው፡፡ ለገደንቢ በደቡብ አረንጎዴ ድንጋይ የቀለበት ክልል ሥፍራ ውስጥ የሚገኘ ሲሆን 82 ቶን ወይም 82,000 ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ክምችት ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ አማካይ አመታዊ ምርቱ ደግሞ 3.6 ቶን ወይም 3,600 ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ይሆናል፡፡›› ይላል የኢትዬጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ለተባበሩት መንግስታት ኮሚሸን ለዘለቄታዊ እድገት (UNCSD) በፃፈው ደብዳቤ፡፡ በሌላ በኩል የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን የወርቁ ክምችት መጠኑ 37,215 ኪሎግራም ነው ይላል፡፡ 44,785 ኪሎግራም የወርቅ ማዕድን ክምችት ልዩነት በሁለቱ ሪፖርቶች መኃል ይገኛል፡፡ አንባቢ ከዚህ ጥናታዊ ፁሁፍ በመነሳት ሁለቱንም ከድረ ገፆቹ እንዲያነቡ እንጋብዛለን፡፡
- (http://www UNCSD _National report_November 2009.doc)
- (http://www MIDROC Gold Mine Pvt Ltd. Co. (MGOLD)
የሚድሮክ ጎልድ ኩባንያና የወያኔ መንግሥት የኢትዬጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ሪፖርት በሌብነትና በሙስና ሰንሰለት የተሳሰሩ በመሆኑ የህዝብ ኃብት በዚህ መልክ ይዘረፋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የማዕድን ዘርፍ ሪፖርት በገለልተኛ አካል ኦዲት እንዳይደረግና አባል እንዳትሆን ሚድሮክ፣ ኢዛና ወዘተ የመሳሰሉ ቢሊነር/ሚሊዮነር ቱጃሮች በማከላከል የሃገር ኃብት ይዘርፋሉ፡፡
የኮንትሮባንድ የደም ገንዘብ!!!
‹‹የንግድ ሚኒስቴር የ2009 ዓ/ም የውጪ ንግድ አፈጻፀም የሚያሳየው ሪፖርት፣ወርቅ ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ የማዕድን ዘርፍ የተገኘው ወጪ ንግድ ገቢ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ በ2009 በጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፎች አንደሚገኝ ታቅዶ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ገቢ መጠን 718.6 ሚሊዮን ዶላር ቢሆነም፣ በተጨባጭ የተገኘው ግን 231 ሚሊዩን ዶላር ብቻ እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት አስፍሮል፡፡›› የቀድሞው የማእድን ሚኒስቴር የአሁኑ የማእድን፣የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር አቶ ሞቱማ መቃሳ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለቀረባላው ጥያቄ ‹‹ የወርቅ ኮንትሮንድ ንግድ እና በድንበር አካባቢ የሚወጣ ሕገወጥ የማዕድናት ዝውውር መስፋፋት አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ከፍተና ጥቅም እያሳጣት መሆኑን በቅርቡ ተገልፆል፤ ይሄን ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄዎች እተወሰዱ ነው›› ሲመልሱ ‹‹አገሪቱ ከምታመርተው አጠቃላይ የወርቅ ሀብት 60 በመቶ የሚመረተው በባህላዊ አምራቾች በኩል ነው፡፡ ሕሁንና በባህላዊ መንገድ የተመረተወ ወርቅ በአግባቡ ወደ ብሄራዊ ባንክ እየቀረበ አይደለም፡፡ ምርቱ ቢኖርም በኮንትሮባንድ ንግድ እየወጣ ነው፡፡የባህላዊ ምርቱ የሚከናወንባቸው አምስት ክልሎች ኦሮሚ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ እና ጋምቤላ ናቸው፡፡ ወርቅ በብዛት የሚገኘውና የሚመረተው ጠረፍ በሆኑ አካባቢዎች ነው፡፡ ከእዚህ ጋር ተያይዞ የተመረተውን ምርት ወደ ባንክ ከማቅረብ ይልቅ ወደ ውጪ በኮንትሮባንድ የመሸጥ ሁኔታ ይታያል፡፡ ይሄንን ችግር ለመግታት አገራዊ ንቅናቄ ተጀምሮል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ተቆቁሞ እየሰራ ነው፡፡ የሁሉንም ትኩረትና ርብርብ ይጠይቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአካቢዎቹ አስተዳዳሪዎች መሰጠት የሚገባቸው ትኩረት ከፍተኛ መሆን ይገባዋል፡፡ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጪ ምንዛሪ ሳታገኝ በህገወት መንገድ ወደ ውጭ የሚሄድበት ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ችግሩ በሚፈለገው ደረጃ እየተገታ አይደለም፡፡›› የብሄራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው ከዓለም አቀፍ ዋጋ አምስት በመቶ ጭማሪ በማድረግ ሆኖ እያለ እንኮን ወርቁ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቆርጦ መሸጡ ነጋዴዎቹ በጎረቤት ሃገራት ዶላር ለማሸሽና ማስቀመጥ ሲረዳቸው የሃገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ገቢን በመቀነስ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በማደናቀፍና የህዝቡን ጉሮሮ በመዝጋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በሰሜን ከኤርትር፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምስራቅ ጅቡቲና ሶማሊያ፣ በሰሜን ምዕራብ ሱዳንና በስተ ደቡብ ምዕራብ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ያዋሰኖታል፡፡ የህወሃት ጦር አበጋዞች መንግሥት፣ መከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች በዚህ ህገወጥ የድንበር የወርቅ ማዕድን ንግድ ግንባር ቀደሙን ሥራ በመስራት ወርቁን በዶላር በመሸጥ ዘረፋ ያከናውናሉ፡፡ የማእድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር ድኤታ አቶ ቴውድሮስ ገብረመድህን ከስር ሆነው በመዘወር ህወኃትን ድንበር ዘለል የወርቅ ንግድ ያመቻቻሉ አሊያም ያስቆማሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው፣ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን ማድረግ ብቻ ነው፡፡
ከማዕድን ዘርፍ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶል2
በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ማጠናቀቂያ፣ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ ከማዕድንና ከጋዝ ወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለመሰብሰብ ታቅዶል፡፡ ከማዕድን ዘርፍ መኃል ከወርቅ፣ ከፖታሽ፣ ከታንታለምና ከተፈጥሮ ጋዝ ኤክስፖርት እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ አስታውቀዋል፡፡
ከማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ፍኖተ ካርታ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከኩባንያዎች ባለቤቶችና ተጠቃሚዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መግለፅ አስገዳጅ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በቅርብ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ170 የሚበልጡ ከኩባንያዎች በማዕድን ፍለጋ ተሰማርተዋል፡፡ ከ2003 ዓ/ም እስከ 2004 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ አገሪቱ 618 ሚሊዮን ዶላር ከዘርፉ ያገኘች ሲሆን፣በ2016 ዓ/ም ገቢውን ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ አቅዳለች፡፡
የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ በማዕድን ዘርፍ ተሰማሩ ኩባንያዎች፤ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ገንዘብ ልውውጦችን ይፋ እንዲያደርጉ የሚያስችል ረቂቅ የሕግ ማእቀፍ አዘጋጅቶ አጠናቀቀ፡፡ ለዝግጅት ብቻ አንድ አመት የፈጀው የሕግ ማእቀፍ ወደ ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ ፅሕፈት ቤት የሚላክ ሲሆን፣አስተያየት ከተሰጠበት በኃላ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ይላካል፡፡ የሕግ ማእቀፍ በአዋጅ ወይም በመመርያ ይሁን የሚለው ገና እንዳልተወሰነ፣ የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ዋና ፀሃፊ አቶ መርጋ ቀናአ ይገልጻሉ፡፡ የሕግ ማእቀፍ ኩባንያዎች ገቢያቸውንና የከፈሉትን ግብር እንዲገልጹ ያስገድዳል፡፡ በተጨማሪም መንግስት ከእነዚህ ኩባንያዎች የሰበሰበውን ገቢ ግብር፣ ሮያሊቲ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ እንዲሁም ኤክሳይዝ ታክስ እንዲገልፅ ይገደዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህ የህግ ማዕቀፍ በማዕድን ኢንዱስትሪው ግልፅነት እንዲኖር ይረዳል፡፡ ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንዳትሆን የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የኢዛና ወርቅ ማዕድንና የለገደንቢ ሜድሮክ ጎልድ የሌብነት ሥርዓት እንዲቀጥል ያደረጉ የአል-ድቤ መችዎች ግብረ አበሮች በሽህ መሃመድ አላሙዲን በሙስና የሌብነት ወንጀል በሃገረ ሳውዲ አረቢያ መታሰር ለቅሶ ተቀምጠዋል፡፡ አል-ኃይለማርያም ደሣለኝ አላሙዲንን ለማስፈታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እናደርጋለን በማለት በቴሌቪዚን መግለጫ ሰጥጦል፡፡ ላንባው ተነቃነቀ!!! ‹‹የፀሃዩ›› አል-ሢሦ መንግሥትም ጠለቀ!!! ንቡም ቀፎውን ለቀቀ!!! የወያኔ መንግሥት ወደቀ!!! የኢትዮጵያ ህዝብ ይላችኃል፡፡
{1} ሚድሮክ ጉልድ፤MIDROC Gold
‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ከዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ እስከ ዴሬክተር ጀነራል በየነ ገብረመስቀል የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ወያኔ ‹‹በልማታዊ መንግሥት ስም›› የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት በሞኖፖል ተቆጣጥረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊና የሼህ አላሙዲን ስውር የወርቅ ማዕድን ኃብት የሽርክና ሚስጢር ታሪክ ያወጣዋል፣የወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላና ተከላ ጥናታዊ ዘገባ ሚስጢር ዋነኛው፣ የመለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ወፍጮ ስራውን የጀመረው ከመንግስታዊ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ ኃብትን በማዘዋወሩ ፕራይቬታይዜሽን ስም የተከናወነ ድራማ! የደደቢቶች ትያትር! በሃገሪቱ ታሪክ ወደር አይገኝለትም፡፡
{ሀ} የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን፣ ሜድሮክ ኢትዩጵያ፣ ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ የወርቅ ማዕደናት እንዳሎት የዳሰሳ ጥናቶች ቢያመላክቱም፣በደርግ ወታደራዊ መንግሥት ዘመን፣ በ1972 ዓ/ም ተገኝጦ በ1982 ዓ/ም ተመርቆ ሥራ የጀመረው የለገበንቢ የወርቅ ማዕድን፣በፕራይቬታይዜሽን የመንግሥት ልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በ172 ሚሊዮነረ ዶለር ለሚድርክ ወርቅ ባለቤት ሼክ መሃመድ ሁሴን አላ-አሙዲ የባለቤትነት ድርሻ 98 በመቶ ሲሆን የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ድረሻ 2 በመቶ በንግድ ሽርክና ላይ የተመሠረተ ካንፓኒ ተመሠረተ፡፡ ተሸጠ፡፡ ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር (MIDROC Gold Mine Pvt Ltd. Co. (MGOLD) የሜድሮክ ኢትዬጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አካል ነው፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በ1990 እኤአ (6/19/97) በሼክ መሃመድ ሁሴን አላ-አሙዲና በሚስታቸው ሶፊያ ሳላህ አላ-አሙዲና በኢትዬጵያ መንግስት 51.6 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር መነሻ ካፒታል የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡ ከብሄራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ( National Mining Corporation (NMC) ከተቆቆመ ጥቂት አመታት በኃላ ሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ተመሰረተ፡፡ በ1997 እኤአ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ለሜድሮክ የወርቅ ማዕድን (የወርቁ ክምችት መጠኑ 37,215 ኪሎግራም ነበር) 1,290,796,624 ብር (በ172 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር) የለገደንቢን የወርቅ ማዕድን ለሃያ አመታት ፈቃድ ተሸጠ፡፡ በ1997እኤአ እሰከ 2017እኤአ ሃያኛ ዓመቱ ውል ተጠናቀቀ፡፡ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ለሜድሮክ የወርቅ ማዕድን የለገደንቢን የወርቅ ማዕድን የ10 ዓመት ውል አደሰ፡፡ በሚያዝያ ወር የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ቀጥሎል፣ የአጋዚ ወታደሮች የአዶላ ወዮ መምህራን ኮሌጅ ሚያስተምሩ 6 መምህራኖችንጨምሮ 17 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸው ና ብዙ ወጣቶች መታሰራቸው ታውቆል፡፡ የወርቅ ማዕድኑ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን በአዶላ- ለገደንቢ የማዕድን አሰሳ ፍቃድ ሲኖረው አጠቃላይ አመታዊ ምርት 1.6 ሚሊዬን ቶን ያልነጠረ የብረታብረት አፈር ያመርታል፡፡ አመታዊ አማካኝ ምርት 4,500 ኪሎ ግራም የወርቅና ፣ብር ቅልቅል ተመርቶ በመጨረሻው 3,500 ኪሎ ግራም የነጠረ የወርቅ ምርት ያመረታል፡፡የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በ6/19/1997 እኢአ የተሸጠው ለሃያ አመት ኮንትራት ውል እስከ በ6/19/2017 ዓ/ም ድረስ የኮንትራት ውሉ አበቃ፡፡ አሁን ደግሞ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ለተጨማሪ ሃያ ዓመት ኮንትራት ውል ከሸክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ሜድሮክ ንብረትነት በሚስጥር ለመሸጥ ስምምነት ሰነድ በመፈራረም ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሄ ከህዝብ የተደበቀ የኢኮኖሚ ሻጥር በሃገሪቱን የሁለተኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 2008-2012 እኢአ የወርቅ ማዕድኑ ኃብታችን ጉዳይ እንደ ቀላል ነገር ተረስቶ መታለፉ ህወኃት ለሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና ለዜጎች ብልፅግና ግድ የሌለው በሙስና በጎቦ የሸክ መሃመድ ሁሴን እግር እየላሱ፣ የህዝብ ኃብት አሳልፈው በመስጠት ላይ መሆናቸውን ህዝቡ አውቆ በቃችሁ ማለት ይጠበቅበታል፡፡ እንዲሁም በ7/7/2000 ዓ/ም ቀንጢቻ ታንታለም በብሄራዊ ማዕድን ኃ/የ/ግ/ማ ስም ለሼህ አላሙዲን 215,800,000 ብር ተሸጠ፡፡
{ለ} ሳካሮ የወርቅ ማዕድን፣ ሁለተኛው የወርቅ ማዕድን ክምችት በተጨማሪ በዚሁ ጉጂ ዞን ሳካሮ አካባቢ ሁለተኛውን ወርቅ ማውጫ ፍቃድ አግኝቶ ወደ ግንባታ ገብቶል፡፡ በእምራብ ሳካሮ በ33.57 እስኩየር ኪሎሜትር ራዲየስ /ኩታገጠም ቦታ ውስጥ እስከ ለገደንቢ የሚገኝ ሲሆን የወርቁ ክምችት 17,250 ኪሎግራም ነው፡፡ በዓመት 2300 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምረት ይችላል፡፡ በዓመት ከዚህ የወርቅ ወጪ ንግድ 87.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንሚገኝ የሚድሮክ ወርቅ ጥናት መረጃ ያመለክታል፡፡
{ሐ} መተከል የወርቅ የማዕድን፣ ሦስተኛው የወርቅ ማዕድን ክምችት በሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት በመተከል የማዕድን አሰሳ ፍቃድ አለው፡፡የሜድሮክ የወርቅ ማዕድን ሃላፊነቱ፤ የግል ድርጅት 7, 2011 ሰብ ሰሃራ መረጃ በወጣው ዜና መሰረት 33,000 ኪሎግራም ያለው የወርቅ የማዕድን ክምችት መተከል የአማራ ክልል የነበረው በአሁኑ የመለስ ዜናዊ አከላለል በቤኒ ሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት ማግኘቱ ተገልፆል፡፡ በዛን ግዜ ባለው የዓለም ዓቀፍ ንግድ የወርቅ ገበያ መሠረት የተገኘው ወርቅ ዋጋው ሲሰላ 19 ቢሊዬን ብር እንደሚሆን ተገምቶል፡፡ የወርቅ ማዕድን ክምችቱ በኢትዩጵያውያን ኤክስፐርቶች ምርምር የተገኘ ሲሆን ቦታውም (በቀድሞው ጎጃም ክ/ሃ) በመተከል ዞን ጂላ በሚባል ቦታ በአሁኑ የኢህአዲግ አከላለል ቤኒ ሻንጉል ጉምዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ካንፓኒው የወርቅ ማዕድን ማሽን ተክሎ የወርቅ ምርቱን ማውጣት ጀምሮል፡፡ ካንፓኒው ከመንግስት 7,000 ሄክታር መሬት በመውስድና 46 ሚሊየን ብር መዋለ-ንዋይ/ኢንቨስት/ በማድረግ የወርቅ ማዕድን ምርት በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ በ1998 እኤአ ካንፓኒው ከማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ፍቃድ ተሰጥቶት ሥራውን ጀምሮል፡፡‹‹ ይህ ትልቁ የወርቅ ማዕድን ክምችት በመተከል ዞን ባገኘው የወርቅ ፍለጋ ፈቃድ በተባሉት ሦስት ቦታዎች በጀላይ፣ፌቲንና ቻሎ በሜድሮክ ካንፓኒ እንደተገኘ ጥናቱ ያስታውቃል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ባካሄደው ጥናት በአጠቃላይ 50.6 ቶን የወርቅ ክምችት መግኘቱን አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም 3066.67 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዶ 2754.93 ኪሎ ግራም ወርቅ መላክ ችሎል፡፡ ዕቅዱን 89.8 በመቶ ማሳካት የቻለ ቢሆንም፣ ይህም ተገኘው ከሚድሮክ ለገደንቢ ወርቅ ማውጫ እንደሆነ ተጠቁሞል፡፡››
የአማራ ፋኖ ከኦሮሞ ቄሮ ጋር የትግል አጋርነትህን አሣይ!!! የአማራ ፋኖ ለመተከል ወርቅ ታገል! የኦሮሞ ቄሮ ለገደንቢ ወርቅ ትግል ተቀላቀል!!!
‹‹መተከል ጎጃም ነበር፤ አማራ ግን «አገርህ አይደለም» ተብሎ እንደ ፋሲካ ዶሮ ይታረድበታል!3
ወያኔ ከጎጃምና ከወለጋ ወስዶ በፈጠረው «ቤንሻንጉል ጉሙዝ» በተባለው ክልል ውስጥ ከጎጃም የተወሰደው መተከል አውራጃ አዲስ የተፈጠረው ክልል ሰፊው ዞን ነው። በዚህ የወያኔ ክልል ውስጥ ዛሬም ድረስ አብዛኛው ባላገር አማራና ኦሮሞ ነው። እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ወያኔ ባካሄደው የቤትና የሕዝብ ቆጠራ ቤንሻንጉል ክልል የሚባለው ክልል ውስጥ 784,345 ኗሪዎች ነበሩ። ከነዚህ ውስጥ 170,132 የሚሆነው አማራ ሲሆን 106,275 የሚሆነው ደግሞ ኦሮሞ ነው። ክፍሌ ወዳጆ የሚባለው የወያኔ አገልጋይ በጻፈው ሕገ አራዊት ግን የክልሉ ሕገ መንግሥት በተባለው ሰነድ ውስጥ ጠቅላላ ድንጋጌዎች በቀረቡበት ምዕራፍ አንቀጽ 2 ስር ስለክልሉ ባለቤቶች እንዲህ ይላል፤ «በክልሉ [በቤንሻንጉል ክልል ለማለት ነው] ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች የሚታወቁ ቢሆንም፤ የክልሉ ባለቤት ብሄር፣ ብሄረሰቦች ግን በርታ፣ ጉሙዝ፣ ሽናሻ፣ ማኦና ኮሞ ናቸው። ልብ በሉ! የክልሉ ባለቤቶች የተባሉት ብሄርና ብሄረሰቦች ለምሳሌ ጉምዝ እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ወያኔ ባካሄደው የቤትና የሕዝብ ቆጠራ መሰረት ብዛቱ 163,781፤ ሺናሻ 60,687፤ ማኦ 15,384 ሲሆን ኮሞ ደግሞ 7,773 ነው። ከነዚህ የክልሉ ባለቤቶች ከተባሉት ብሄር፣ ብሄረሰቦች ቁጥር የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ትናንትና ጎጃምና ወለጋ የተወለዱ አማራና ኦሮሞዎች ግን ዛሬ ከጎጃምና ወለጋ ተወስዶ በተፈጠረው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ እትብታቸው በተቀበረበት ምድር ባለቤቶች አይደሉም። ባጭሩ ትናንትና ወለጋ የተወለዱ ኦሮሞዎችና ጎጃም የተወለዱ አማሮች እትብታቸው የተቀበረበት መሬት ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደሚል ስለተቀየረ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው «ኗሪዎች» እንጂ የተወለዱበት ምድር ባለቤቶች አይደሉም ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ እነዚህ ትናንትና ወለጋና ጎጃም የተወለዱ ኦሮሞና አማራዎች ዛሬ በፋሽስት ወያኔ ዘመን በተዘረጋው የከፋፍለህ ግዛ ዘይቤ አብረዋቸው የኖሩት ጎረቤቶቻቸው የክልሉ ባለቤት ሲሆኑ እነሱ ግን አማራና ኦሮሞ በመሆናቸው የተነሳ አገር አልባ ሆነዋል ማለት ነው።››››
በሜድሮክ ወርቅ ልማት ዘረፋ ላይ ጥቆማ ቀርቦል፡፡‹‹በማምረት ሙከራ ላይ መሆናቸውን ሚገልፁ የማዕድን ኩባንየዘዎች ላይ ክትትል እንዲደረግ ፓርላማው አሳሰበ›› በሚል ርእስ የሜድሮክ ወርቅ ልማት በማእድን ዘርፍ የተሠማሩ ኩባንያዎች የማምረት ፍቃድ ከወሰዱ በኃላ የማምረት ሙከራ ላይ መሆናቸውን በመግለፅ ለዓመታት እያጭበረበሩ እንደሚቆዩ እንደተደረሰበት በመግለፅ፣ ክትትል እንዲደረግ የፓርላማው ቆሚ ኮሚቴ አሳሰቦል፡፡ ተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ ጥር 17 ቀን 2009 ኣ/ም የማዕድንና ተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ሚኒስቴርን ሪፖርት መሰረት‹‹ ህገወጥ የማእድን ዝውውር እናንተ ከምትሉትና እኛም ከምንገምተው በላይ ነው›› የማእድን ፍቃድ ወስደው ለዓመታት የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጡ መኖራቸውን ወ/ሮ ጀንበርነሽ ብለዋል፡፡ የፓርላማው ቆሚ ኮሚቴ ከዚህ ቀደም ወደ ሻኪሶ አቅንቶ ሻኪሮ በሚባል ልማት በዚህ ያለው ሚድሮክ የወርቅ ልማት ገና በሙከራ ላይ ቢሆንም እውነቱ ከዚህ በተቃራኒ እንደሆነ ለሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ አሳስበው ነበር፡፡ በወርቅ ልማት ክልል ውስጥ ገብተው እንዳዩት ‹‹ እዚያ ያለ ባለሙያ ጭምር የገለፀው ከ21 ካራት በላይ የሆነ ጥራት ያለው ወርቅ እየተመረተ ከሻኪሮ ወደ ዋናው ሚድሮክ እየመጣ ነው፡፡›› በማለት አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ሚድሮክ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሙከራ ላይ መሆኑን ቢገልፅም፣በተጨባጭ ግን እየተመረተ ስለመሆኑ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በመከታተል የመንግሥትን ጥቅም እንዲያስከብር አሳስበዋል፡፡በሌሎች ማዕድናት ላይ ሙከራ ላይ መሆናቸውን እየገለፁ ለዓመታት የሚቆዩትን ኩባንያዎች መመርመር እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ በአጠቃላይ የማዕድን ዘርፍ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ በመሆኑ በጥልቅ ሊመረመር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በተለያዩ የማእድን ልማት አካባቢዎች ቱሪስት መስለው የሚንቀሳቀሱ የውጭ ዜጎች በህገወጥ መንገድ የከበሩ ማዕድናትን እያወጡ መሆኑን፣ በተለይም ኦፓል የተሰኘውን ማዕድን የራሳቸው አድርገው በድረ-ገፅ ጭምር የሚለቁ መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡ የመንግሥት የሥራ ኃላፋዎችና የግል ባለኃብቶች ከውጪ ዜጎች ጋር አቅደው የማጭበርበር ተግባር የሚፈጽሙ መኖራቸውን ኮሚቴው እንደደረሰበት በመጠቆም እርምጃ እዲወሰድ አሳስበዋል፡፡ ዘርፉ ግን ሙሉ ለሙሉ ለሙስና ተጋላጭ መሆኑን፣ ከፍተኛ ኃብት የሚያንቀሳቅሱ የውጪ ኩባንያዎች በቀላሉ ሁሉንም በገንዘባቸው እንደሚጠመዝዙ አክለዋል፡፡4 መፍትሄው ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን ማድረግ ብቻ ነው፡፡ለሙሰኛው ህወሃት/ ኢፈርት ‹‹የአዶላና የለገደንቢ ወርቅን የህወሃት መንግስት ለአላሙዲን ለጨረታ ሸጦል በ6/19/2017 እኤአ በኢትዩጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 12 ቀን 2009 ዓ/ም የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን የኮንትራት ውሉ ስምምነቱ አክትሞል፡፡ በአዶላና በለገደንቢ ወርቅ ማዕድን አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሚያና የአማራ ህዝብም የልጅ፣የልጅ ልጆቻችሁ ኃብት በግፍ እየተዘረፈ እያያችሁ ከመኖር፣ ለኃብታችሁና ለነፃነታችሁ ፈጣሪ የሠጣችሁን አዱኛ አስነጥቃችሁ በድህነት እየማቀቁ መኖር እጣ ፈንታችሁ አይደለም፡፡ ከወርቃችሁ ኃብት የመጀመሪያው ተጠቃሚ የመሆን መብት አላችሁ፡፡ ስብሃት ነጋ፣የወርቅ ዘራፊ ጌታ!!! እድሜ አትገዛበት፣ተምሶል የመቃብርህ ቦታ!!!
በኢትዮጵያ በቀ.ኃ.ሥ ዘመንና በደርግ አገዛዝ የማዕድን ኃብት የህዝብ ኃብት ነበር!!!
የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ ገዳዩ ‹‹ኮማንድ ፖስት›› የክልል መንግሥቶችን ለቆ ይውጣ!!! ወደ ጦር ካንፑ!!!
የህዝብ ልጆች ገዳይ የአግአዚ ጦር ለፍርድ ይቅረቡ!!!
የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
‹‹ዳውን ዳውን›› ወያኔ!!!፣ ‹‹ብለድ መኒ›› ማዕድኔ!!!
ላንባው ተነቃነቀ!!!
የወያኔ መንግሥት ወደቀ!!!
የአል-ሢሦ መንግሥትም አለቀ
ንቡም ቀፎውን ለቀቀ!!!
ጨለማ ደቀደቀ፣ፀኃይም ጠለቀ!!!
ምንጭ
{1} 1 For more information on EITI, visit: www.eiti.org. The Extractive Industries Transparency Initiative
Download: EITI_factsheet-1.jpg (55kb) EITI_factsheet-2.jpg (92kb)
{2} 2 መስከረም 23 ቀን 2008ዓ/ም እና (በማዕድን ዘርፍ አሠራር ላይ ግልፅነት ለማስፈን አዲስ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጀ ፖርተር ሚያዝያ 8ቀን 2009ዓ/ም)
{3} 3 ሳተናው October 29, 2017 10:07
{4} 4(ሪፖርተር ጋዜጣ ጥር 21 ቀን 2009ዓ/ም)
{5} 5(Tigray Regional State, Five Years 2010/11-2014/15, Growth & Transformation Plan, Bureau of Plan and Finance, September 2003 E.C, Mekelle, page 17)
{6} 6www.Kefi_granted_mining_licence, www. kefi-minerals.com, Email:info@kefi-minerals.com
{7} 7 ጳጉሜ 4 ቀን 2007 ዓ/ም