
የሚድሮክ ጎልድ የሳውዲው ቢሊዮነርና፣ የህወሓት/ኢፈርት የትግራዋይ ኢዛና ወርቅና፤ቴዎድሮስ አሸናፊ
በኢትዮጵያ በቀ.ኃ.ሥ ዘመንና በደርግ አገዛዝ የማዕድን ኃብት የህዝብ ኃብት ነበር!!!
የሚበላው የሌለው ህዝብ፣ መሪዎቹን ይበላል!!!›› ትንቢተ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
‹‹ ይሄ የኔ ሰው ነው፤አትንካው!!!” የሚባልበት የአይነኬዎች ስርአት ነው፡፡››ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
የትግራይ ወጣት የኢዛና የወርቅ ኃብትህን ከወያኔ ኢፈርት አስመልስ!!! የአማራ ፋኖ፣ከኦሮሞ ቄሮ ጋር የትግል አጋርነትህን አሣይ!!!
{2} ኢዛና ማዕድን ልማት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር(Ezana Mineral Development Private Limited Company (EFFORT)፣በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢዛና ማዕድን ልማት በህወሃት/ ኢፈርት ባለቤትነት የተቆቆመ ካንፓኒ ሲሆን ዋና የበላይ ተቆጣጣሪዋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ስትሆን አታክልቲ አርዓያ ጀነራል ማናጀር ናቸው፡፡ የኢትዬጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ስንቅነሽ እጅጉ እና ኢዛና ማዕድን ልማት ካንፓኒ ጀነራል ማናጀር አታክልቲ አርዓያ የወርቅ ማዕድን የማውጣት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ በሃገሪቱ ኢዛና ካንፓኒ የወርቅ ማእድን ፍቃድ በማግኘት ከሜድሮክ ቀጥሎ ሁለተኛው ሆኖል፡፡ ኢዛና ካንፓኒ በትግራይ ክልል በ393.7 ሚሊዩን ብር ወይም (17.8 ሚሊን ዶላር) የፕሮጀክት ወጭ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፣ኢዛና በመዐድን ዘርፍ ለ106 ሠራተኞች የስራ እድል ፈጥሮል፡፡ በትግራይ ክልል ውስጥ የተገኘውን 13 ቶን ወይም ፣13,000 ሸህ ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት የካናዳዊያን የወርቅ ማዕድን ካንፖኒ ጋር ህወሃት/ኢፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘረፈው የወርቅ ሃብት ሲሆን ሲሆን ስለ ካንፓኒው ብዙ መረጃ አይገኝም፡፡ ኢዛና ካንፓኒ 393.7 ሚሊዩን ብር የፕሮጀክት ወጪ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፡፡በዚህ መሠረት 2017 ኪሎ ግራም ወርቅ 2,017,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 69,552 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1218.80 ዶላር ስናባዛ 84,769,977.6 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ በ20.34 ሲባዛ 1,724,221,344.384 ቢሊዩን ብር የህወሃት ጦር አበጋዞች በውጪ ሃገር ባንኮች አከማችተዋል፡፡ ለሙሰኛው ህወሃት/ ኢፈርት የኢዛና የወርቅ ማዕድን ሃብትን የትግራይ ህዝብ በህዝባዊ እንቢተኝነት ከህወኃት ገዥዎች በማስመለስ የሃገራችን ኢትዩጵያ ሃብት የማድረግ ታሪካዊ ሃላፊነት አለበት፡፡ የኦሮሚያው ለገደንቢና የአማራው የመተከል የወርቅ ማዕድን ኃብት በህዝብ አመፅ የህዝብ ሃብት ይሆናል፡፡ የወያኔ አልጠግብ ባይነት ውሎ አድሮ እንኮን በኢትዬጵያ በትግራይ ህዝብና በህወሃት አባላቶች ጭምር አንቅረው ይተፉታል፡፡ ኢዛና ወርቅ ከሜድሮክ ወርቅ ካንፖኒ የጠበቀ ሸርክና እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ኢዛና ወርቅ ከሜድሮክ ወርቅ ካንፖኒ የጠበቀ ሸርክና አላቸው፡፡ የህወሃት መንግስት በትግራይ ህዝብ ጭምር አንቅሮ ተፍቶታል፡፡ ኢዛና የማዕድን ኃብት በ1993እኤአ ሲመሠረት በ1.4 ቢሊዩን ብር መነሻ ካፒታል ነበር፡፡ ካንፓኒው በ17.8 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ በቱርክ ማንሃተን ኮርፖሬሽን ተገነባ፡፡ ኢዛና የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ ሲገነባ ለአራት ዓለም ዓቀፍ ኮንትራክተሮች ጨረታ ወጥቶ የተሠጠ ሲሆን የአዶላና የለገደንቢ በዓለም ዓቀፍ ጨረታ ሳይወጣ ያለጨረታ ለሼክ አላሙዲ መሸጡ ምን ያባላል!!!
የማዕድን ኃብት(Mineral resource) የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በትግራይ ክልላዊ መንግስት የገንዘብና ፕላን ቢሮ በነደፈው የእድገትና ትራንስፎርሜድን ፕላን (2010/11-2014/15) በገፅ 17 መሠረት፤ ከ1999 እኤአ ጀምሮ፤በትግራይ ክልል አጠቃላይ፤የስነ-ምድር ካርታ ጥናት መሠረት፤በዓይነት፣ በሚሸፍነውና በመጠኑ የክልሉን የማዕድን ኃብቶች መለየት ተችሎል፡፡ እስካሁን የስነ-ምድር ካርታ ጥናት እንቅስቃሴ መረጃ መሠረት 24,780 ሜትር ስኮይር የስነ-ምድር ጥናት ተጠንቶና ተጠናቅሮ ሪፖረቱ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ በትግራይ ክልል የስነ-ምድር ካርታ ጥናት ስብስብ መረጃ 46.2% ደርሶል፤እናም ክልሉ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀማጭ አድርጎል፡፡ በዚህም ረገድ፤ የተወሰኑ ድክመቶች ስላሉ አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግላቸው ከሚገቡት መኃል፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት፣ የመመርመሪያ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ አገልግሎቶች ማሞላትና ሌሎቹም ነጥቦች ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ መሠረት 850 ኪሎ ግራም ወርቅ 850,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 29,310 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1,218.80 ዶላር ስናባዛ 35,773,448 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ በ20.34 ሲባዛ 726,768,548.7 የህወሃት ጦር አበጋዞች በብሄራዊ ባንክ አከማችተዋል ማለት ነው፡፡ ዝርዝሩን ከድረ-ገፁ ያንብቡ፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ5 ስብሃት ነጋ፣የኢዛና ወርቅ ማዕድን ዋና ዘራፊና አቃቢ ንዋይና ወርቅ አስቀማጪ ጌታ መሆናቸው ይታወቃል!!!
{3} ከፊ ሚንራልስ ፒአልሲ፣ KEFI Minerals plc
ኬኢኤፍአይ ሚንራልስ ኢትዩጵያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የእንግዚዝ ካንፓኒ የሆነው ኬኢኤፍአይ በኢትዩጵያ ጥልቅ የወርቅና መዳብ መዕድን ከአዲስ አበባ 510 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በኦሮሚያ ክልል፣ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ጂንጂ ወረዳ፣ቱሉ ካፒ አካባቢ በተለይ ካፒ ጉራቾና ቢቂልቱ አንኮሬ ቀበሌ የወርቅ ማዓድን ለማውጣት ተፈራርማFል፡፡ ኬኢኤፍአይ ሚንራልስ ቱሉ ካፒ ፕሮጀክት፣ ግዙፍ የወርቅና መዳብ መዕድን ክምችት ለማልማት የሃያ ዓመታት ፍቃድ ከማዕድን ሚኒስቴር አግኝቶል፡፡ በዚህ የመዓድን ኢንቨስትመንት፣ሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ታገኛለች፣ የስራ እድል ይፈጠራል እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር በመቅስም ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፆኦ ያበረክታል፡፡ የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ሰባት ስኩየር ኪሎሜትር ኩታ ገጠም መሬት ያጠቃልላል፡፡ ኬኢኤፍአይ ሚንራልስ ኢትዩጵያ ካንፓኒ 31 ቶን ወርቅ የወርቅ ክምችት ውስጥ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ 28,875 ኪሎ ግራም ወርቅና መዳብ (በዓመት 2,887.5 ኪሎ ግራም) እንደሚያመርት አስታዉቆል፡፡ በዚህም 1.2 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር እንደሚያገኝና ለ700 ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር የካንፓኒው ሊቀመንበር፣ሃሪ አናግኖስታር አዳምስ አስታውቀዋል፡፡6
{4} በቤኒሻንጉል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስካም ማይኒንግ (ቤኒሻንጉል) ክልል የወርቅ ፍለጋ ያደርጋል፡፡
ከማዕድን ዘርፍ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶል ‹‹በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ማጠናቀቂያ፣ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ ከማዕድንና ከጋዝ ወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለመሰብሰብ ታቅዶል፡፡ ከማዕድን ዘርፍ መኃል ከወርቅ፣ ከፖታሽ፣ ከታንታለምና ከተፈጥሮ ጋዝ ኤክስፖርት እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ቶሎሳ ሻጊ አስታውቀዋል፡፡ከማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ፍኖተ ካርታ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከኩባንያዎች ባለቤቶችና ተጠቃሚዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መግለፅ አስገዳጅ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በቅርብ የወቱ ሪፖርቶች እንደሚያሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ170 የሚበልጡ ከኩባንያዎች በማዕድን ፍለጋ ተሰማርተዋል፡፡ ከ2003 ዓ/ም እስከ 2004 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ አገሪቱ 618 ሚሊዮን ዶላር ከዘርፉ ያገኘች ሲሆን፣በ2016 ዓ/ም ገቢውን ወደ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ አቅዳለች፡፡››6 የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ በማዕድን ዘርፍ ተሰማሩ ኩባንያዎች፤ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ ገንዘብ ልውውጦችን ይፋ እንዲያደርጉ የሚያስችል ረቂቅ የሕግ ማእቀፍ አዘጋጅቶ አጠናቀቀ፡፡ ለዝግጅት ብቻ አንድ ኣመት የፈጀው የሕግ ማእቀፍ ወደ ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ ፅሕፈት ቤት የሚላክ ሲሆን፣አስተያየት ከተሰጠበት በኃላ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችምከር ቤት ይላካል፡፡ የሕግ ማእቀፍ በአዋጅ ወይም በመመር ይሁን የሚለው ገና እንዳልተወሰነ፣ የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ ዋና ፀሃፊ አቶ መርጋ ቀናአ ይገልጻሉ፡፡ የሕግ ማእቀፍ ኩባንያዎች ገቢያቸውንና የከፈሉትን ግብር እንዲገልጹ ያስገድዳል፡፡ በተጨማሪም መንግስት ከእነዚህ ኩባንያዎች የሰበሰበውን ገቢ ግብር፣ ሮያሊቲ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ እንዲሁም ኤክሳይዝ ታክስ እንዲገልፅ ይገደዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህ የህግ ማዕቀፍ በማዕድን ኢንዱስትሪው ግልፅነት እንዲኖር ይረዳል፡፡
የደም ገንዘብ!!! ‹‹የወርቅ ፍለጋ የአዋጭነት ጥናት ቁፋሮ እየተካሄደ ነው፡፡››7 ብሄራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን የ530 ሺ ኪሎ ግራም የወርቅ ፍለጋ የአዋጭነት ጥናት ቁፋሮ ከሁለት ድርጅቶች ጋር ማለትም ከኢትዩጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ እና ሲንቱላ ከተባለ የሞሪሽየስ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ውል ተፈራርሞ ተደርጎ ቁፋሮ ተጀምሮል፡፡ የኮርፖሬሽኑ የወርቅና ቤዝ ሜታል ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ደምሴ በኦሮሚያ ክልል ያቤሎ ዞን፣ በአሬሮ ወረዳ በዳዋሌ ጋቴ ፕሮጀክት አካቴ በተባለ ቦታ ከአሁን ቀደም በተደረጉ ምርምሮች እስከ 530 ሺ ኪሎ ግራም የወርቅ ክምችት እንዳለ ተረጋግጦል፤ ይህን ወደ ምርት ለማስገባት የአዋጭነት ጥናት ቆፋሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የወርቅ ፍለጋ የአዋጭነት ጥናት ቁፋሮ እየተካሄደበት ያለው ቦታ እስካሁን በኢትዮጵያ ከተገኙት የወርቅ ክምችቶች ከፍተኛው እንደሆነ ገልፀዋል፤ መመረት ሲጀምርም ደግሞ አገሪቱ ከማዕድን የምታገኘውን ገቢ ከፍ እንደሚያደርግ ታውቆል፡፡ የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን ከ3 እስከ 5 ሺ ሜትር የተለያ ጥልቀት ያላቸው ጉድጎዶችን ቁፋሮ ይካሄዳል፡፡ የኢትዩጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ቁፋሮውን ለማከናወን በ13 ሚሊዩን ብር እና ሲንቱላ ጋር በሜትር 70 ዶላር አካባቢ ቁፋሮ ለማድረግ ስምምነት ውል ተፈራርሞ ቁፋሮ ተጀምሮል፡፡ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን በማዕድን ዘርፍ የተሠማሩትን መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመደገፍ የዘርፉን እድገት ለማፋጠን በየዓመቱ በአማካይ 34 ሚሊዩን ብር የሚጠጋ የአገልግሎት ገቢ ለመሰብስብና በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይም 170 ሚሊዩን ብር የአገልግሎት ገቢ ለመሰብሰብ ግብ አስቀምጦል፡፡ ግቡን ለማሳካት በየዓመቱ በአማካይ በሜትር 26 ሺ የኮር ድሪሊንግ፣ የውሃ ጉድጎድ እና የጂኦተርማል ቁፋሮ እና በአማካይ ከ66 ሺ በላይ የተለያዩ የጂኦሳይንስ የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ አገልግሎት ለውስጥና ለውጭ ደንበኞች ይሰጣል፡፡ የማዕድን አለኝታ ቦታዎችን ከነበሩበት 162 ወደ 32 ለማሳደግ ራዕይ አስቀምጦ እየሰራ እንደሚገኝ ታውቆል፡፡የማዕድናት ዘርፍ ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኮንስትራክሽንና ለግብርና ዘርፎች ግብዓት በማምረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ በሃገሪቱ የወርቅ ምርት በከፍተኛ መጠን እንደጨመረ መምጣቱ ቢታወቅም፣ አዳዲስ የወርቅ ማውጫ ተቆቁመው፣ ከፊ ሚራልስ (ወለጋ ውስጥ) ሚድሮክ ጉልድ (መተከል)፤ አስካም ማይኒንግ (ቤኒሻንጉል) እና ኢዛና ማይኒንግ (ትግራይ ውስጥ) በውጪ ምንዛሪ የተገኘው ገቢ ባህር ማዶ እንደሚያሸሹ ይታወቃል፡፡ ህገወጥ የማዕድን ንግድ ባይኖር ኖሮ ኢትዩጵያ በየዓመቱ ከማዕድን ኤክስፖርት 3 ቢሊዩን ዶላር ማግኘት ትችል ነበር፡፡ በዓለም ዓቀፍ ገበያ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የወርቅ፣ የከበሩ ድንጋዮችና ጌጣ ጌጥ ኤክስፖርት መጨመር፣ የታንታለም ምርት መጨመርና የፖታሽ ምርት መጀመር ኤክፖርት የውጭ ምንዛሪ ገቢ መጨመሩ እርግጠኛ ቢሆንም ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ አይደለም፡፡ በመንግስተና በግል ዘርፎች የተሰማሩ የማእድን ኩባንያዎች፣ በተለይ በወርቅ፣ ፖታሽ፣ የተፈጥሮ ጋዝና የሚኒራል ኃብት ግልፅነት ያለው አጠቃቀም ገቢያቸውን ማሳወቅ፣ ተጠያቂነትና ታማኝነታቸውን የሚያሳይ፣ የህዝብ ተጠቃሚነትንና ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት ያለውን አስተዋፅኦና እንዲሁም ከሙስናና ከሌብነት፣ ግልጽ ካልሆነ አሰራር፣ አድሎ ወዘተ ማህበራዊ ኃላፊነት በሃቅና በገለልተኛ ተቆም ማስረጃ መረጋገጥ እንዲችል ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ የማዕድን ኃብት ዘርፍ የተሰማሩ ሃገራቶች ስምምነት ከፈረሙበት፣የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል ካልሆነች የማዕድን ኃብታችን ተቀብሮ ለሚቀጥለው ትውልድ ቢተላለፍ የተሸለ ይሆናል፡፡
ለተፈጥሮ ጥቅም የሚከፈል ካሣ፣(Royality) ሁለተኛው የወርቅ ማዕድን ምርት የሚመረተው በባህላዊ መንገድ ወርቅ በሚያነጥሩ አንጥረኞች ሲሆን ከክርስትና ሃይማኖት በኃላ ጀምሮ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከ2000 እኤአ ባህላዊ የወርቅ አንጥረኞች 1000 (እስከ 3000) ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት አምርተዉ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በመሸጥ የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ ሲቻል የወርቅ ምርት አምርተዉ፣በተለያዩ ክልሎች በህወሓት የጦር አበጋዞችና የክልል ሹሞች በሽርክና በድንበር በኩል ወደ፣ሱዳን፣ሱማሊያ፣ ኬንያና፣ጅቡቲ በኩል ከአገር እንደሚወጡና በከፍተኛ ዋጋ በውጪ ምንዛሪ ይሸጣሉ፡፡ ‘‘የፌዴራል መንግስቱ፣ ለተፈጥሮ ጥቅም የሚከፈል ካሣ 48.5 ሚሊዩን ብር በየአመቱ ላለፈው ሦስት አመታት በተከታታይ ገንዘብ ከከፍተኛ ደረጃ የወርቅ ማዕድን አምራቾች መሰብስብ ችሎል፡፡ የክልል መስተዳድሮችም (ዘጠኝ ክልላዊ መንግስቶችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች) ለተፈጥሮ ጥቅም የሚከፈል ካሣ (Royality) በጥቂት አስር ሚሊዩን ብር (ሦስት ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር) የሚገመት ገንዘብ ከአነስተኛ ደረጃ ባህላዊ ማዕድን አምራቾች( የተከበሩ ድንጋዬች፣የኢንደስትሪና የግንባታ መስሪያ ማዕድናት ከሚያመርቱ ይሰበስባሉ፡፡ ሃገሪቱ ከተለዩ የማዕድን ሃብቶች ከወርቅ፣ ከታንታሊት ውህድ ፕላቲንም፣ጌጥ ያላቸው ድንጋችና ከከበረ ድንጋይ 135 ሚሊዩን ዶላር የውጭ ምንዛሪ በየዓመቱ ታገኛለች፡፡ ሃገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልከው ምርቶች፤የማዕድን ሃብቶች ከ7 እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል፡፡ ፣እንደ የኢትዬጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር መረጃ መሠረት በ1990 እኤአ የማዕድን ሃብት ዘርፍ ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት ከአንድ(1) በመቶ ድርሻ ነበረው፡፡ የማዕድን ሃብት ዘርፍ ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት በ2007/8 እኤአ 5.8 በመቶ እንዲሁም 2008/9 እኤአ 5.5 በመቶ ለማደግ ችሎል፡፡ ’’ ሜድሮክ ለተፈጥሮ ጥቅም በሚከፈል ካሣ በአመት 100 ሚሊዩን ብር ቢከፍልም ይማርራል፡፡ በፊዴራል ኦዲት ሪፖርት ሜድሮክ ለተፈጥሮ ጥቅም በሚከፈል ካሣ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን በፓርላማ ሪፖርት አድርገዋል፡፡
{5} የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ፣ በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ‹‹ በቀ.ኃ.ሥ ዘመነ መንግስት በኢትዩጵያ ነዳጅ ፍለጋ እኤአ በ1940ዎቹ አጋማሽ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ በአሜሪካውያን ኩባንያዎች ነበር፡፡ በደርግ ወታደራዊ መንግስት ዘመን፣ከሩሲያ ኩባንያዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በካሉብ ዘጠኝ እንዲሁም በኢላላ አካባቢ ሦስት ጉድጎዶች ላይ ስራ ተጀምሮ ነበር፡፡ በህወኃት/ ኢህአዴግ ዘምን በ1999ዓ/ም የማሌዥያ ፔትሮናስ ኩባንያ ካሉብን ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችን ለማጥናት ፍቃድ ወስዶ ሥራ ጀምሮ የነበር ቢሆንም ኩባንያው በእራሱ ፍላጎት ፍለጋውን አቆርጦ ወጥቶል፡፡ ሃንስ ኦይል እንዲሁም ማክሰስ ኢነርጂ የተሰኑ ኩባንያዎች ፍለጋቸው ተስፋ ባለማሳየቱ ጥለው ወጥተዋል፡፡››
የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ፔትራም ትራንስ የተሰኘ የሆንግ ኮንግ ኩባንያ ሲሆን ሥራውን በአግባቡ አልተወጣም ተብሎ ፍቃዱ ተሠረዘ፡፡ ቀጥሎም ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ ተሠጠ፡፡ የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በአራት ቢሊዩን ዶላር ወጪ የግንባታ ሥራ ጀምሮል፡፡ ኦጋዴን ክልል ውስጥ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማት ጥረት እየተደረገ እንደሆነና በ2010 ዓ/ም ወደ ምርት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በኢትዩጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማትና ነዳጅ ለመፈለግ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ ከማእድን ሚኒስቴር ጋር በ2013 እኤአ የፔትሮሊየም ፍለጋና ልማት ስምምነት መፈራረሙ ይታወቃል፡፡ ኩባንያው በካሉብና በሒላላ አካባቢዎች በቆፈረው ጉድጎዶች መልካም ውጤት ማግኘቱን አስታውቆል፡፡
- የካሉብ የጋዝ ክምችት ከአዲስ አበባ ደቡብ ምሥራቅ 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ1972 እኤአ ቴኔካ የተሰኘ የአሜሪካን ኩባንያ ካሉብ አንድ ጉድጎድ በመቆፈር ፣የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱን ማግኘቱ እንዲሁም ቴኔካ ኩባንያ በሂላላ አነስተኛ መጠን ያለው ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
- እኤአ በ1980ዎቹ የቀድሞው የሶብት ኅብረት ኩባንያ የሆነው ስፒ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጎዶች በመቆፈር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱን መጠን ያረጋገጠ ሲሆን በሂላላ ተጨማሪ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አግኝቶ ነበር፡፡ በጥናቶቹ መሠረት በካሉብና በሂላላ ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መጠን 118 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ እንደሆነ በተለያዩ ኩባንያዎች የተካሄዱ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
- በ2013 እኤአ ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ ከማእድን ሚኒስቴር ጋር የፔትሮሊየም ፍለጋና ልማት በመስማማት በኦጋዴን 117151 ካሬ ኪሎ ሜትር የነዳጅ ፍለጋ ይዞታ ባለቤት ሆኖል፡፡ ኩባንያው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቶን ለማልማት ጂቡቲ ወደብ ድረስ 830 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ አራት ቢሊዩን ዶላር ይገመታል፡፡ የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በመጋቢት ወር 2008 ዓ/ም ተቀምጦል፡፡የጋዝ ማስተላለፍያ ባንባ ዝርጋታ ሥራ በነሐሴ 2008 ተጀምሮል፡፡ ፖሊ ጂሲኤል ኩባንያው በዓመት አራት ቢሊዩን ሜትር ኪብ ጋዝ በማምረት አብዛኛውን ምርት ወደ ቻይና ለመላክ አቅዶል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያው የፔትሮ ኬሚካል ምርቶች ማምረቻ ሊያቆቁም በጥናት ላይ ነው፡፡ ኩባንያው የተፈጥሮ ጋዝ ምርቱን በ2019 እኤአ ይጀምራል፡፡ በሪፖርተር ጋዜጣ መረጃ መሠረት የተጠናቀረ ነው፡፡
ሃገራችን ኢትዩጵያ ከዚህ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትና የፔትሮ ኬሚካል ምርቶች ማምረቻ የምታገኘው ጥቅም፣ የፕሮጀክቱ ጥናት በድብቅ እንደ ማፍያ ሥራ መረጃው ይፋ ባለመሆኑና ሊጠይቁ የሚችሉ ህዝብና ጋዜጠኞችን በማፈን በሚስጢር የሚከናወን ሴራ እንዳለ እሙን ነው፡፡ የኦጋዴን መሬት ለቻይና ኩባንያ ካልተሸጠ በቀር የሃገሪቱ ኃብት ድርሻ ከፕሮጀክቱ ምን ያህል እንደሆነና ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን በግልፅ ማሳወቅ የአንድ መንግስት ሥራና ኃላፊነት ነው፡፡ የኢትዩጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት 17.5 ቢሊዩን ዶላር ብድር እንዳለበት የዓለም ባንክ በቅርቡ አስታውቆል፡፡ የኢትዩጵያ መንግስት ከውጭ ሃገራት የተበደረውን ብድር ለህዝብና ለምጣኔ ኃብት ጠበብት፣ ለአጥኝዎች፣ ለፓርላማና ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡ በመረጃው አሰጣጥ የተዛቡና የመዘበራረቀ የአሀዞች ማቅረብ ለምን ይሆን፡፡ ቀጥሎ አስተውሉት፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ዶክተር ቴዎድሮስ አዳኖም በኢትጵያ ሄራልድ ጋዜጣ፣ ኢትዩጵያ፣ ጅቡቲና ቻይና በህብረት የአራት ቢሊዩን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ፕሮጀክት፣የድፍድፍ ማጣሪያ ፕልንትና፣ 700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል እስከ 12 ሚሊዩን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ምርት በአመት፡፡ ከዚህ ውስጥ ኢትዩጵያ፣ 10 ሚሊዩን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ለቻይና በአመት ኤክስፖርት እንደምታደርግ ተገልፆል፡፡ ፖሊ-ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ የፕሮጀክቱን ግንባታ ውጪ እንደሚሸፍንና በሦስት አመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚያልቅ አናዶሉ ኤጀንሲ አስታውቆል፡፡ የማእድን፣የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር አቶ ሞቱማ መቃሳ የነዳጅ ፍለጋውን በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ‹‹ስምንት የሚሆኑ ድርጅቶች ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ አንደኛው የቻይና ኩባንያ የሆነው ፖሊ ጂሲኤል የሚባል ኩባንያ ተፈጥሮ ጋዙን አግኝቶል፡፡ አሁን የተገኘውን ጋዝ ከኦጋዴን ተፋሰስ ወደ ውጪ ለመላክ እስከ ጂቡቲ ወደብ የ700 ኪሎ ሜትር የቦንቦ መስመር ዘርጋታ ድርድር ተጠናቆል፡፡ በቅርቡም ወደ ዝርጋታ ይገባል፡፡ የቦንቦ ዝርጋታው አንድ ኩባንያ ብቻ ሳይሆን ኦጋዴን ተፋሰስ ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ የሚያገለግል ነው፡፡ነዳጁን በተመለከተ ግን ፍለጋው እንደቀጠለ ቢሆንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ሆኖም ይገኛል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው፡፡››2 ብለዋል፡፡
‘‘Ethiopia, Djibouti, China to launch 4 Bln. USD natural gas project’’ Addis Ababa- Ethiopia says physical work on a massive four billion USD joint natural gas project between Ethiopia, Diouti and China will soon be launched. The announcement was made Thursday by Foreign Minister Dr. Tedros Adhanom at the opening of the 4th Ethiopia- Djibouti Joint Ministerial Commttee Meeting in Addis. …The project is made up of a natural gas pipeline, a liquefaction plant, and an export terminal at Damerjog, Djibouti. The project, which includes a 700 kilometere pipeline capable of transporting up to 12 billion cubic meteres of natural gas per year, would enable Ethiopia to export 10 million cubic meters of liquefied natural gas (LNG) to China annually. Chines firm POLY-GCL Petroleum Group Holding Ltd. Will finnce the project, which is scheduled to take three years to complete, according to Anadolu Agency.3 በማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒሰቴር የፔትሮልየም ፋቃድና አስተዳደር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ቀፀላ ታደሰ የማዕድን ፍቃድ በመስጠት አድሎ፣ አድሎዊ አሠራርና በሙስና የዓለም ዓቀፍ የፍቃድ አሰጣጥ ይነቀፋሉ፡፡በሌላ በኩልም በኦጋዴን ኤልኩራን በተባለ አካባቢ የሚከናወን ፍለጋ መኖሩን ገልፀዋል፡፡ በዚሁ አካባቢም በእንግሊዙም ኢ አይ ጂ ኩባንያ ባለፍት ዓመታት የተለያዩ ጥናቶችን ሲያካሂድ ቆይቶል፡፡ዴሎኖክስ የሚሰኝ ኩባንያም በዚሁ ኦጋዴን አካባቢ ሦስት ብሎኮች እንዲሁም በተመሳሳይ አካባቢ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ የተባለ የሆንግ ኮንግ ኩባንያ በቅድመ ቁፋሮ ላይ ሲገኝ በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልልም ሥራ ጀምሮል፡፡ እንዲሁም ታሎ ኦይል በደቡብ ኦሞ፣ የካናዳው አፍሪካ ኦይል ኮርፖሬሽን በስምጥ ሸለቆ ከዝዋይ እስከ አርባ ምንጭ ባለው አካባቢ፣ የሩሲያው ጋስፕሮም በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ የፍለጋ ሥራ እያከናወኑ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ የተባለ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ቡድን መስራች የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ ይባላሉ፡፡ ባለሃብቱ በተለያዩ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ የህወኃት/ ኢፈርት የቢዝነስ ሽርካ ለመሆናቸው ‹‹የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ›› ከዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ የሃገሪቱን ምጣኔ ኃብት በማዕድን፣በሚኒራል ውኃና በሆቴል ዘርፍ አገልግሎት፣እንዲቆጣጠር አድርገዋል፡፡ ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በርካሽ ዋጋ ከተሸጠላቸው ድርጅቶች ውስጥ፡-
- ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ፣ በነዳጅ ፍለጋ ሥራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ሲሆን፣ በሶማሌ ክልል በኦጋዴንና በጋምቤላ ክልል የነዳጅ ፍለጋ ፕሮጀክቶች በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ ለነዳጅና ጋዝ ፍለጋ የተረከቡት ምሥራቃዊው የአገሪቱ ክፍል በሃገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅና ጋዝ ክምችት አለው ተብሎ ይታመናል፡፡
- የጋምቤላ ኢትዮጵያ ሆቴል፣ ሳውዝ ዌስት ፒኤልሲ ባለቤት አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በ3,750,000 ሚሊዮን ብር በ21/7/2005ዓ/ም ገዝተውታል፡፡
- በአምቦ ውኃ ማዕድን በ19,782,807 ሚሊዩን ዶላር ተሸጠ፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር አቶ በየነ ገብረ መስቀልና ሳውዝ ዌስት ዴቨሎፕመንት አቶ ቴዋድሮስ አሸናፊ ተፈራርመዋል፡፡ መንግሥት በአምቦ ማዕድን ውኃ አክሲዮን ማሕበር ያለውን የ33 በመቶ የአክሲዩን ድርሻ ለአምቦ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ሊሚትድ በሚል ስያሜ ለሚታወቅ ሳብ ሚለር ከተባለው የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ጋር ተጣምረው ገዝተዋል፡፡
- ሳውዝ ዌስት ሆልዲንግ ሁለት የኮካኮላ ፋብሪካዎች ከኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ፣ የተሸጠበት ዋጋ 64,030,000 ሚሊዩን ብር ጋር ተጣምረው በ5/15/95 ዓ/ም ገዝተዋል፡፡
- በኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፓል ሌሎች በርካታ ኩባንያዎች ላይ የአክሲዮን ባለድርሻ ናቸው፡፡ ዓመታወ ገቢያቸው ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መኃል አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ፣አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ ወ/ሮ አኪኮ ሥዩምና አቶ በላይነህ ክንዴ ይገኙበታል፡፡
{6} ዳሎል የፖታሽ ማዕድን፣በአፋር ብሄራዊ ክልል መንግስት ‹‹በአፋር ክልል በደናኪል ረባዳማ ሥፍራ በዳሎል የፖታሽ ማእድን ዓመታዊ ምርት 600,000 ሜትሪክ ቶን ሰልፌት ኦፍ ፖታሽ ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ የማእድን፣የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚንስቴር መሠረቱን ካናዳ ባደረገው ለሰርከም ሚኒራልስ ሊሚትድ የሃያ ዓመት የማዕድን ፍቃድ በማግኘት፣ በ2.7 ቢሊዮን ዶላር መዋለ ንዋይ በማፍሰስ የተመሠረተ መሆኑን በፊርማው ስነስርዓት ላይ ሚንስትሩ ሞቱማ መካሳ ገልፀዋል፡፡ የሰርከም ሚኒራልስ ዋና ስራ አስኪያጅ ብራድ ሚልስ በዓመት 2.75 ሚሊዮን ፖታሽ በውጪ ንግድ ወደ ባህር ማዶ የመላክ እቅድና 1700 ኢትዮጵውያን የሥራ እድል እንደሚፈጥር አረጋግጠዋል፡፡››4 ዳሎል አካባቢ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው የፖታሽ ማዕድን ለማልማት ጥናት ሲያካሂድ የቆየው ያራና ሰርኪውም ሪሶርስ የተሰኙ ኩባንያዎች ወደ ምርት ይሸጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አላና ፖታሽ የተሰኘው የካናዳ ኩባንያ በፖታሽ ምርት ለመሰማራት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ሰፊ የፍለጋና ምርምር ጥናት ካካሄደ በኃላ ኩባንያው ይዞታውን አሳልፎ ለእስራኤል ኬሚካልስ ኩባንያ የሸጠ መሆኑን አስታውቆል፡፡
አይሲኤል የእስራኤል ኩባንያ፡- አይሲኤል በዳሎል የፖታሽ ማዕድን ማውጫ፣ ሦስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ከአንድ ቢሊዩን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቆይቶል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአገሪቱ በአመት 300 ሚሊዩን ዶላር የውጪ ምንዛሪና ለ3000 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ታቅዶ ነበር፡፡ አይሲኤል ህዳር 1 ቀን 2009 ዓ/ም ለማዕድን፣ ፒትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር በፅፈው ደብዳቤ የፖታሽ ፕሮጀክቱን ሚኒስትሩ እንዲረከበው አመልክቶል፡፡ በመስክ የሚገኙ ማሽኖች፣መሣሪያዎችና ሌሎች የተለያዩ የኩባንያው ንብረቶች ለዝርፊያና ለስርቆት መዳረጋቸውን፣ የባንክ ሂሳቦቹ በመታገዳቸው ምክንያት ለሠራተኞችና ለኮንትራክተሮች ክፍያ መፈፀም ተስኖት እንደነበር ጠቁሞ፣ በዚህም ምክንያት የካሣ ጥያቄ ሊመጣበት እንደሚችልና ለዚህም ለጠፋ ንብረቶቹ ሙሉ በሙሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጎል ነበር፡፡ በኤሲኤል ደብዳቤ መሠረት ኩባንያው ወደ ዓለም ዐቀፍ ፍርድ ቤት ለመሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ፡፡በአፋር ክልል የፖታሽ ማእድን ልማት ላይ መሠረተ ልማት በማስፋፋት የአገሪቱ የመንገድ ደረጃ ከ58 ቶን በላይ መሸከም አቅም በ78 ቶን የመሸከም አቅም እንዲኖረው ተደርጎ እየተሠራ ይገኛል፡፡
{7} በርሃሌ የጨው ፋበሪካ፤ ከአዲስ አበባ 890 ኪሎ ሜትር ሰሜን ምሥራቅ በአፋር ብሄራዊ ክልል መንግስት የምትገኘው በርሃሌ ‹‹በማዕድን ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ኬሚካል ሶሳይቲ የተሠራ ጥናት በደናክል ዝቅተኛ ቦታ 100 ካሬ ሜትር መሬት በጨው የተሸፈነ እንደሆነ ያሳያል፡፡ የአሞሌ ጨው ክምችቱ አንድ ቢሊዮን ቶን እንደሚገመት፣ ይህም ከዓለም ትልቁ የጨው ክምችት እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ ጥናቱ የአሞሌ ጨው ጥራት ያለው መሆኑን ገልፆ፣ ለምግብነት ለማዋል ግን በፋብሪካ ሊቀነባበር እንደሚገባ ይጠቁማል፡፡››5 ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው የጨው ክምችት በአገር ውስጥ እያለ አገሪቱ አሁንም ጨው በውጭ ምንዛሪ እንደምታስገባ ይታወቃል፡፡ በበርሃሌ ሐመደላህ ሙቀቱ እስከ 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሚደርስ ቃጠሎ የአፋር ነዋሪዎች የእጅ መሣሪያዎች በመጠቀም ባህላዊ አሞሌ ጨው በማምረት ሥራ ተሰማርተው፣ ያመረቱትን አሞሌ ጨው በግመሎቻቸው ጭነው ከ60 እስከ 100 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ተጉዘው እየሸጡ በመጠቀም ህይወታቸውን ይመራሉ፡፡
{ሀ} የአፋር የጨው ማቀነባበሪና ማምረቻ ኃ/የ/ግ/ማ፣ ባለሃብቱ አቶ ሰኢድ ያሲን 51 በመቶና በካባዳ ጨው አምራቾች 49 በመቶ ለተቆቆመው የአፋር የጨው ማቀነባበሪና ማምረቻ ኃ/የ/ግ/ማ በቅርቡ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ፡፡ በመጋቢት 13 ቀን 2009 ዓ/ም የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፋብሪካውን ምንም ዓይነት ምርት ከማምረትም ሆነ ወደ ገበያ ከማሠራጨት አገደው፡፡ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድም ተከለከለ፡፡ በባለ ኃብቶቹ ማሃከልም አለመግባባት ተከተለ፡፡
{ለ} የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሃብቱ ሐጎስን፣እስካሁን ከጨው አምራቾች የሚቀበለውን ጥሬ የጨው ምርት የሚያቀነባብረውና አዮዲን የሚረጨው በ1998 ዓ/ም 83 በመቶ የመንግሥት ልማት በሆነው ማዕድን ኮርፖሬሽንና 17 በመቶ ደግሞ የኢፈርት ድርጅት የሆነው ኢዛና በጋራ ያቆቆሙት የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲን ማህበር ማሽን በኮሚሽን በመከራየት መሆኑ ተገልጾል፡፡ በተመሳሳይ ለአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበር የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፋብሪካውን ምንም ዓይነት ምርት ከማምረትም ሆነ ወደ ገበያ ከማሠራጨት አገደው፡፡ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድም ተከለከለ፡፡ ወያኔ ኢፈርት የአፋር ጨውን ያለ አንዳች ተቀናቃኝ ኃብታቸውን ይዝቃል፣ የብዙ መቶ ሽህ ቶን የጨው ምርታቸውን የገንዘብ ክፍያ አይከፍልም፣ ለሠራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝ ይከፍልል፣ ለክልሉም አስፈላጊውን ግብርና ታክስ አይከፍልም፡፡ በቅርቡም በመገናኛ ብሁኃን ተገልፆ ነበር፡፡
{ሐ} ደናክል ኢንዱስትሪያል የግል ኩባንያ፣በበርሃሌ ከተማ አስተዳደር ሃያ ሽህ ካሬ ሜትር ቦታ የተረከበው የቲቲኬ ኢንዱስትሪያል ኩባንያ ባለቤት አቶ ሣሙኤል ካሣ ደናክል ኢንዱስትሪያል የጨው ፋብሪካን በ331 ሚሊዮን ብር ወጪ የጨው ማቀነባበሪያ ፋበሪካ በወር 500000 ኩንታል ጨው የማምረት አቅም እንደሚኖረው ከዚህ ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብዓት 20 በመቶ፣ የከብቶች መኖ 50 በመቶና ለገበታ ጨው 30 በመቶ ለማምረት የተገነባ ነው፡፡ የአፋር ነዋሪዎች የተመሠረቱ ሦስት የጨው አምራች ማህበራት ለፋብሪካው አሞሌ ጨው ለማቅረብ፣ ማሽነሪና የትራንስፖርት ድጋፍ ለማድረግ እንዲሁም ለ250 ስዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ባለቤቱ ገልፀዋል፡፡ ደናክል ኢንዱስትሪያል እህት ኩባንያ የሆነው ቲቲኬ ኢንዱስትሪያል በ2003 ዓ/ም በ35 ሚሊዩን ብር ካፒታል ተቆቁሞ በገላን ኢንዱስትሪ ዞን የዲተረጀንት ማምረቻ ማለትም የሳሙና፣ ሻምፑና ሌሎች የፅዳት ኬሚካሎች በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ ኩባንያው ካፒታሉን ወደ 120 ሚሊዩን ብር በማሳደግ በቅርቡ ለሳሙናና ሻምፑ ማሸጊያ የሚውል ፕላስቲክ ማምረቻ ገንብቶ የሙከራ ምርት ጀምሮል፡፡ የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማህበራት ያመረቱትን የብዙ መቶ ሽህ ቶን የጨው ምርታቸውን የገንዘብ ክፍያ አይከፍልም፣ ለሠራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝ ይከፍልል፣ ለክልሉም አስፈላጊውን ግብርና ታክስ አይከፍልም፡፡ በቅርቡም በመገናኛ ብሁኃን ተገልፆ ነበር፡፡
{8} የሞሮኮ ኦሲፒ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ በሞሮኮ ኦሲፒ ኩባንያ በ3.7 ቢሊዩን ዶላር በድሬዳዋ አስተዳደር ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተፈራርሞል፡፡ ኩባንያው ድሬዳዋን ምርጫው ማድረጉ፣ ለጅቡቲ ወደብ ይቀርባልF፣ ከባቡር መስመር አቅርቦትና ለማዳበሪያ ምርት በጥሬ ዕቃነት ለሚያገለግለው የፎስፌት አቅርቦት ጋር በተያያዘ መሆኑን ታውቆል፡፡ ፋብሪካው ሁለት የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻ አካላት ያሉተ ሲሆን፣ዩሪያ ዩኒት አንድ በተባለው ማምረጫ የአሞኒያ ዩኒትና የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ማብላያ ይኖረዋል፡፡ የሞሮኮ ኦሲፒ ኩባንያ፣ማምረቻ በዓመት አንድ ሚሊዩን ቶን ማዳበሪያ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም የማደባለቂያና የማሸጊያ ሥፍራው ሌላው የፋብሪካው ሁለተኛ አካል ነው ተብሎል፡፡ በዚህ ስፍራም 50 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ምርት የማሸጊያ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የሞሮኮ ኦሲፒ ኩባንያ፣ ሰማንያ በመቶ የዓለም ገበያን በማዳበሪያ ምርቶች እንደሚሸፍን ይነገርለታል፡፡
ስብሃት ነጋ፣የወርቅ ዘራፊ ጌታ!!! እድሜ አትገዛበት፣ተምሶል የመቃብርህ ቦታ!!!
የአስቸኮይ ጊዜ አዋጅ ይነሳ!!! የህዝብ ልጆች ገዳይ የአግአዚ ጦር ለፍርድ ይቅረቡ!!! የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም!!! ‹‹ዳውን ዳውን›› ወያኔ!!!፣ ‹‹ብለድ መኒ›› ማዕድኔ!!!
ምንጭ
{1} 1 For more information on EITI, visit: www.eiti.org. The Extractive Industries Transparency Initiative
Download: EITI_factsheet-1.jpg (55kb) EITI_factsheet-2.jpg (92kb)
{2} 2 መስከረም 23 ቀን 2008ዓ/ም(በማዕድን ዘርፍ አሠራር ላይ ግልፅነት ለማስፈን አዲስ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጀ ፖርተር ሚያዝያ 8ቀን 2009ዓ/ም)
{3} 3 ሳተናው October 29, 2017 10:07 {4} 4(ሪፖርተር ጋዜጣ ጥር 21 ቀን 2009ዓ/ም)
{5} 5(Tigray Regional State, Five Years 2010/11-2014/15, Growth & Transformation Plan, Bureau of Plan and Finance, September 2003 E.C, Mekelle, page 17)
{6} 6www.Kefi_granted_mining_licence, www. kefi-minerals.com, Email:info@kefi-minerals.com {7} 7 ጳጉሜ 4 ቀን 2007 ዓ/ም
