05/05/2018

በደምሰው ይላቅ
በቅርቡ ከቤምሻንጉል ጉምዝ ተፈናቅለው በባህር ዳር ቅዱስ ጊዬርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተጠለሉትን የአማራ ብሄር ተፈናቃዮች የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርና የከተማው ነዋሪ እርዳታ እያደረገላቸው ቢሆንም በባህር ዳር የኮማንድ ፖስቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መሀመድ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ተፈናቃዮቹን አስወጡ ማለቱን ተከትሎ ብጹእ አቡነ አብርሀም “የእግዚአብሄር ቤት የድሆች መጠጊያ መጠለያ ነው ከዚህ አስወጥቼ ወዴትም ልሰዳቸው አልችልም የት ይወድቃሉ?” በማለታቸው የቤተክርስቲያኗን አስተዳዳሪ ጨምሮ ለጥያቄ ትፈለጋሉ ተብለው ከሰአታት በፊት በመከላከያ ኮማንድ ፖስት ተወስደዋል። ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልን የምናሳውቅ ይሆናል።