“እኔ የምሰራው የፊፋን ህግ ተከትዬ ነው። ከመልበሻ ክፍል ጀምሮ ችግር ነበር። እኔ ግን በሕጉ ብቻ እንደምሰራ ተናግሬያለሁ። እስከ 84ኛ ደቂቃ የጥላቻ ስድብ ስሰደብ ነበር። እንዲያውም እኔ ታግሼ ነው። ሲደረግ እንደነበረው ቀይ ካርድ ብሰጥ ጨዋታው በ3ኛ ደቂቃ ይፈርስ ነበር። ብዙ ታግሻለሁ። ፊሽካ በተነፋ ቁጥር ተጫዋቾቹ በአንድነት ወደ እኔ ይመጡ ነበር። የቡድን መሪውን እያዩ ነበር ወደ እኔ የሚመጡት። ……ወደ ኢቲቪ ስቲድዮ የሄድኩት ለይቅርታ አይደለም። እሱን ከመጋረጃ በስተጀርባ አስቀምጠው ቀረፃ ላይ እግሬ ላይ መጥቶ እንዲደፋ አድርገዋል። ‘እኔን አይደለም ይቅርታ የምትጠይቀው፣ የተሰደበውን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቅ’ ብየ ገፍቼ ወጥቻለሁ። ሲደበድበኝ ‘በለው ይህን ቆሻሻ አማራ’ እያለ ነው። የተሰደበው ሕዝብ ስለሆነ ህዝብን ይቅርታ ጠይቅ ብየ ጥየው ወጥቻለሁ። የተጠራሁትም ለይቅርታ ፕሮግራም አልነበረም።”

ዳኛ እያሱ ፈንቴ በስልክ የነገረኝ እንደወረደ ፅፌው ነው!!