አንዳንዴ አንዳንድ አድሀሪ የብአዴን አባላት ለብአዴን እንደ ድርጅት ያልፈጠረበትን ዝና እና ስዕብና ሲሠጡት ይገርመኛል፡፡ ብአዴን የተኮላሸ፤ ማነንት የሌለውና በማንነት ውስጥ የሚዋዥቅ ድርጅት ነው።
ማንም ንጹህ ህሊና ያለው ሰው እንደሚመሰክረው፣ የብአዴን ማንነት የተመሰረተው #በአማራ_ክልል_ውስጥ_የህውሀትን_ፍላጎት_ለማስፈጸም ነበር፤ አማራ በህውሀት ላይ እንዳያምጽ አስሮ እንዲይዝ ታስቦ ነው ብአዴን ተፈጠረው፡፡
እንዲሁም ሌላ አማራዊ ድርጀት በአማራ ክልል ውስጥ እንዳይፈጠር ታስቦ ነው ብአዴን የተፈጠረው፡፡ ለዚህ ደግሞ ብአዴን መአህድን በማጥፋት የተጫዎተው ሚና ዋነኛው ማሳያ ነው፡፡ እውነቱ እሄ ሁኖ እያለ ብአዴንን የአማራ ህዝብ ወኪል አድርጎና ” የአማራ ህዝብ ምርጥ ስጦታ” ነው ብሎ ያለ ሀፍረት መናገር፤ወይም አስመስሎ ለመሳል የሚደረገውን ሙከራ የአማራ ወጣቶች በፍጥነት ሊያስወግዱት ይገባል፤ ብአዴን አማራን አይወክልም ፤ ብአዴን የአማራ ህዝብ ጠላት በሆነው ህውሀት ተፈጥሮ አማራን እንዲያስገዛ የተፈጠረ፤አማራን ያስደፈረና ያዋረደ፤ አማራን ያስጠቃ፤ ምንደኛ ድርጅት ነው፡፡
እውነተኛው ብአዴን እሄ ነው፡፡ ብአዴንን የአማራን ህዝብ አይወክልም የሚሉ ወገኖች ደግሞ ለብአዴን ሌላ ስም ሲሰጡት ይስተዋለል፡፡ እንደነዚህ ወገኖች እምነት ብአዴን የህውሀት የትግርኛ ክንፍ ነው፡፡
ብአዴን-የአማራ ህዝብ ምርጥ ስጦታ ወይስ የህውሓት የአማርኛ ክንፍ?
ከላይ እንዳነሳሁት በአሁኑ ወቅት ብአዴንን ከአማራ ህዝብ ጋር ስላለው መስተጋብር የተለያዩ ሃሳቦች ይሰነዘራሉ፡፡ በተለያዩ የብአዴን መድረኮች አንዳንድ የብአዴን ካድሬዎች ( ያውም የድል አጥቢያዎቹ) “ብአዴን ማለት የአማራ ህዝብ ምርጥ (ወርቃማ ) ስጦታ ነው” ብለው በድፍረት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው ፡፡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ብአዴንን “የ ሕውሀት የአማርኛ ተናጋሪ ክንፍ” ነው ይሉታል (ተመስገን ደሳለኝ፣ 2008 ዓ.ም፤ ገጽ 22 )፡፡
እነዚህን ሁለት ሃሳቦች ትክክል ናቸው ወይም ስህተት ናቸው ለማለት ቅድሚያ የሃሳቦቹን መነሻና ይዘት መመርመር ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ ሁለቱም ሃሳቦች የያዟቸውን ጭብጦች ከተመለከትን በኃላ የአባባሎቹን ተገቢነት መበየን ያስችለናልና፡፡ ስለሆነም ሁለቱን ሃሳቦች በየራሳቸው እንደሚከተለው እንመርምራቸው፡፡
እውን ብአዴን የአማራ ህዝብ ወርቃማ ስጦታ ነው?
ለመሆኑ ብአዴን የአማራ ህዝብ ምርጥ ስጦታ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ከየት ነውስ የተሰጠው? ማንስ ነው የሰጠው? ወርቃማ ስጦታ ለመባልስ የሚያበቁት ቁምነገሮች ምንድን ናቸው? እንግዲህ ምርጥ ስጦታ አለ ከተባለ ቢያንስ ሦስት ነገሮች መኖር ሊኖርባቸው ነው፡፡ ስጦታውን አቅራቢ፤ ስጦታውን ተቀባይና ለስጦታ የሚቀርበው ቁስ፡፡ በዚህም መሰረት ስጦታ አቅራቢው ፈጣሪ፤ድርጅት ወይም ሰው ሊሆን ይችላል፤የስጦታው አይነት ደግሞ ቁስ ወይም እቃ፤ ሰው፤ ወይም ድርጅት ሊሆን ይችላል፡፡ ስጦታ ተቀባዩ ደግሞ ህዝብ ወይም ግለሰብ ሊሆን ይችላል፡፡
የብአዴንን ምርጥ የአማራ ህዝብ ስጦታነት ጉዳይ በዚህ መልኩ ካየነው ፈጣሪ ወይም ሌላ ሰው ወይም ድርጅት ብአዴንን ለአማራ ህዝብ ፈቅዶ ላከለት ወይም ሰጠው ማለት ነው፡፡ መቸም ፈጣሪ ብአዴንን ለአማራ ህዝብ ሰጠው በሚለው አባባል የሚስማማ አይኖርምና ቢያንስ ብአዴን ከፈጣሪ ለአማራ ህዝብ ተሠጠ ስጦታ አይደለም ብለን እንለፈው፡፡ ሌላኛው ስጦታ አቅራቢ ሊሆን ሚችለው ሰው ወይም ድርጅት ነው፡፡ በዚህ በኩል የብአዴንን ስጦታነት ከተመለከትነው ፤ ብአዴን የተባለ ድርጅት ( ሰው) በሌሎች በጎ ቃድ ተፈጥሮ ለሌሎች በስጦታ መልክ የቀረበ አካል መሆኑ ነው፡፡ በዚህ በኩል የሚገለጸው የብአዴን ለአማራ ህዝብ ስጦታነት የሚለው አባባል ነጥብ ያለው ይመስላል፡፡ ይህም ማለት ስጦታ አቅራቢው ሕውሀት፤ የስጦታው አይነት ወይም ቁስ ድርጅት( ብአዴን) ፤ ስጦታ ተቀባዩ የአማራ ህዝብ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ በኩል የብአዴንን ስጦታነት ከተመለከትነው ፤ ብአዴን የተባለ ድርጅት( ሰው) በሌሎች በጎ ቃድ ተፈጥሮ ለአማራ ህዝብ በስጦታ መልክ የተበረከተ ድርጅት መሆኑን ነው፡፡
የብአዴንንና አማራ ህዝብ መስተጋብር በዚህ መልኩ በሚገለጽ ስጦታነት ከገለጽነው፤ ቀጥለን ደግሞ ስጦታውን ወርቃማነት እንመርምር፡፡ ብአዴንን የአማራ ህዝብ ወርቃማ ስጦታ ነው በሚል መልኩ መግለጽ የተፈለገው ወይም ትርጉሙ፤ ብአዴን ለአማራ ህዝብ በጭንቅ ቀን የተገኘ( የተወለደ) ፤አማራን ህዝብ ከመቅሰፍት የታደገ፤ ለአማራ ህዝብ ወደርና ተኪ የለሽ ድርጅት ነው ለማለት ተፈልጎ መሆኑ ነው፡፡ በአጭሩ ብአዴን ለአማራ ህዝብ ወደር የለሽ ጋሻና መከታ ነው መባሉ ነው፡፡ እንግዲህ እሄንን የብአዴን ለአማራ ህዝብ ወርቃማነት የአማራህዝብ ቢያንስ ላለፉት 27 ዓመታት ጥሩ አድርጎ ስላየው፤ የአማራ ህዝብ ብአዴንን እንደ ወርቅ ወይስ እንደ ያልተጣራ ብረት ነው የሚመለከተው የሚለውን መላ የአማራ ህዝብ በሂዎቱ የተመለከተው ስለሆነ ፍርዱን ህዝብ ይስጥ፡፡ እኔ እምነት ግን ብአዴንን የአማራ ህዝብ ወርቃማ ስጠታ የሚያስብለው ነገር የለም፤ ከሆነም ያልተጣራ ብረትነት ነው የሚለው የሚገልጸው ይመስለኛል ፡፡
አውን ብአዴን “የሕውሀት የአማርኛ ተናጋሪ ክንፍ” ነው?
ብአዴን የህውሀት አማርኛ ተናጋሪ ክንፍ ነው (ተመስገን ደሳለኝ፤2008 ዓ.ም
በርግጥ በአንጻራዊነት አሁን ያለውን ብአዴንና አዲሱን የአማራ ትውልድ ስንመለከት፤ክሱን እንዳለ ለመቀበል ያስቸግር ይሆናል፡፡ ይህም በተወሰነ መለኩ አማራዊ ሽታ ያላቸው አመራዎች በብአዴን ውስጥ ስለሚገኙ ነው፡፡
ስለሆነም ብአዴንን የሚገልጸው ስያሜ፣ ብአዴን የአማራ ህዝብ ሳይፈልገው በአጋጣሚ የተገኘ ድርጅት ፤የህውሀትን ዓላማ በአማራ ክልል ለማሳካት የተጋ፤በሂደት ደግሞ ከሕውሀት ጫና በመላቀቅ ወደ እውነተኛ አማራዊ ድርጅትነት ለመሆን በመውተርተር ያለ ድርጅት ተብሎ ቢፈረጅ ቡዙውን ሰው ሊያስማማ ይችላል፡፡ከዚህ ውጭ ብአዴን የአማራ ህዝብ ወርቃማ ስጦታም አይደለም፤ ይህን ስያሜ ለብአዴን ከመስጠት ይልቅ፣ ብአዴንን የህውሀት የአማራኛ ክንፍ ነው ብሎ መደምደም የሚቀል ያመስለኛል፡፡
ማጠቃለያ
አማራ ንቃ፤ ሙህራን አማራን እናንቃ፤ብአዴን የአማራ ህዝብ ድርጅት አይደለም፡፡ብአዴን ሲፈጠር ጀምሮ የእኛ እንዳልሆነ ብናውቅም ፤ከነገ ዛሬ አማራዊ ድርጅት ይሆናል ብለን 27 አመት ጠበቅነው፤ ዛሬም ግን የብአዴን ነገር ውሀ ቢወግጡት እምቦጭ ሁኗል፡፡ ብአዴን ዛሬም እውነተኛ የአማራን ወኪል መሆን አልፈለገም፤
ለዚህ ጥሩ ማሳያው ደግሞ በአማራ ስም በፌደራልና በክልሉ ቁልፍ ቦታዎች የሚመደቡትን ሰዎች ልብ በሉ፡፡በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ በቁልፍ ቦታዎች በአማራ ስም የሚመደቡት በአማራ ጠልነታቸው የታወቁ ወይም ከህውሀት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው፤ አንዳንዶች ደግሞ የክልሉ ተዎላጆች ያልሆኑትን ነው
በፌደራል ደረጃ፤ በመለስ አካዳሚ በሚኒስትርና በሚኒስትር ድኤታ ደረጃ አማራን የወከሉት እነማን ናቸው? ለገሰ ቱሉ እና ጥላሁን አይደሉም? እነዚህ ሰዎች አማራ ናቸው?.
ከአማራ ክልል ውጭ ያለውን አመራ ለማስተባበር ኃላፊነት ተሰጥቶት አዲስ አበባ ላይ የተመደበው ማን ነው?
አማራን ወክሎ አማራዎች ሲፈናቀሉና ፤ከትግራይ ጋር የሚካሄደውን ድርድር የያስተባብሩት እነማን ናቸው? እነ ሰማ ጥሩነህ አይደሉንም? ሰማ ማን ነው ?
በክልል ደረጃ የክልለ ዋና አፈ ጉባኤ ማን ናት? ወርቅ ሰሙ አይደለችንም? ወርቅ ሰሙ ማን ናት ?የሰቆጣ ህዝብ እንባ የሚያነባው በማን ሆነና?
የፌደራል ጉዳዮች እነ ከበደ ጫኔ እውቅ አማራ ጠል የህወሃት ጉዳይ አስፈፃሚ አይደሉምን?
ሌላም ሌላ መዘርዘር ይቻላል፡፡ አማራ እንዲህ ይቀለድበታል፡፡ አንተ አማረ ጠል ከሆንክ፤ አንተ አማራን ወክለህ በብአዴን ጥሩ ቦታ ይሰጥሀል፡፡አንተ የአማራን ጉዳይ አጀንዳ የምታደረግ ከሆነ በካልቾ ትመታለህ፤ ምክንያቱም ትምክተመኛ ነህ፤ ምክንያቱም የጨቋኟ ብሄር ጠበቃ ሁነሀልና!!
ለሁሉም አማራ እራስክን ብትጠይቅ ጥሩ ነው፤ ይበቃል፡፡
የአማራ ህዝብ “ህገ መንግስቱን” የማክበር ግዴታ የለበትም… በክፍል ሁለት ከምክንያታዊ ማስረጃ ጋር ይቀጥላል።