(ፍርዱ ዘገዬ)

(To read the article in PDF, click here)

“እግዚእብሔር ያሳያችሁ፤ ክርስቶስ ያመላክታችሁ” – ከነዚህ ወያኔ ትግሬዎች ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል ከወልቃይት ደረገጽ ቀድቼ ከዚህ በታች ያስቀመጥኩትን ምሥል በማየት ለመረዳት ሞክሩ፡፡ ከሺህ የቃላት ድርደራ አንድ ሥዕል ብዙ እንደሚናገር ዘወትር የሚጠቀሰውን የዘመን ርዝማኔ የማያደበዝዘው እውነት ይህ ከዚህ በታች የምናየው ዘግናኝ ምስል በተጨባጭ ያስረዳል፡፡ ከዘረኝነት የፀዳን ነን የምትሉ ተጋሩ ይህን ጽሑፍ ስታነቡ መናደድ አይገባችሁም፡፡ እውነት መራራ ናት፡፡ ወያኔዎች እያደረጉት ያለው ነገር ከአማራ ጋር ጭራሽ የሚያቀባብር አይደለም፡፡ ከፍለው የማይጨርሱትን ግፍ እያስቀመጡ እንደሆነ በመረዳት ጦስ ጥምቡሱ ለሌሎች ንጹሐን ዜጎችም እንዳይደርስ በጸሎት ጭምር አማሮችን ዕርዱ፡፡

ይህ ምስል የአማራ እስረኞች ምስል ነው፡፡ በዚህ ምስል ውስጥ ስድስት ያህል እስረኞች በግልጽ ይታያሉ፡፡ ሁሉንም እዩዋቸው – ሁሉም ምርኩዝ ይዘዋል፤ አንካሣ አማሮች ብቻ እየታደኑ እስር የገቡ እንዳይመስላችሁ፡፡ ይህ ምርኩዝ የወያኔ ዴሞክራሲ ለአማራው ሕዝብ ያመጣለት “ጣፋጭ ሸንኮራ አገዳ” መሆኑ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ከጎሣቸው ውጪ ማለትም ሳይወዱ በግዳቸው አማራ ሆነው ከመፈጠራቸው ውጪ የሠሩት ምንም ዓይነት ጥፋት የሌለባቸው መሆኑ በታሳቢነት ተይዞልኝ አጠፉ እንኳን ቢባል በጅምላ እንደዐይጥ እየተቀጠቀጡ ሁሉም አካለ ጎዶሎ እንዲሆኑ መደረጋቸው የሥርዓቱን ምንነት በገሃድ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህን የወያኔ ትግሬዎች ጥጋብና ዕብሪት እንዲሁም አማራ ላይ ያላቸውን ለከት የለሽ ጥላቻ እነሱው የመለመሉት ዶክተር አቢይ ቀርቶ እግዚአብሔር ራሱም የሚያለዝበው አይመስልም፡፡ አምላክም ፈርቷቸው ሳይሆን አይቀርም ይህን ሁሉ ግፍና በደል እያዬ ዝም ብሏቸዋል – ለነገሩ አንዱ ደንቆሮ የወያኔ ኮሎኔል ሶሎሞን ክፍሌ ቃለ ምልልስ እያደረገለት ያለው ከአሜሪካ መሆኑን ሲነግረው “እንኳን ከአመሪካ ከመንግሥተ ሰማይም ቢሆን አምጥቼ አስርሃሎሁ!” ብሎ ባሳቀን ጊዜ የነዚህን ጉግማንጉጎች ከፈጣሪም በላይ ለመሆን የመፈለግ አባዜ ታዝበናል፡፡ ከሁሉም በላይ የመሆን ፍላጎት የሚያሰቃየው ሰው  ሥነ ልቦናዊ የዝቅተኝነት ስሜት የሚያንገላታው ድውይ ፍጡር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬውም በፀረ-አማራነትና በፀረ-ኢትዮጵያነት በመቆሙ እንጂ ይህን ምስል በማየት ብቻ ሕወሓትን ከመኮነን አልፎ በጣልቃ ገብ ጦር ባስወገደውና ባለሥልጣናቱንም ዘሄግ ፍርድ ቤት ወስዶ በገተራቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ወያኔ ትግሬዎች ልክ እንደቀደሙት ባንዳ አባቶቻቸው የማን ወይም የነማን ተላላኪዎች መሆናቸውን እናውቅ ዘንድ እንዲህ እንዲሆን ግድ ሆነ፡፡ ፎቶውን ደግማችሁ ተመልከቱት – ሁሉም ተሰባብረዋል፡፡ ሁሉም አካላቸው ጎድሏል፡፡ ሁሉም ደቀዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነ ከፊታቸው ሌሎች እስረኞች እንዳሉ ደግሞ መገመት አይከብድም፡፡ እነሱም እንደነዚህኞቹ የተሰባበሩና የተጎሰቋቆሉ እንደሆኑ መረዳት አይከብድም፡፡ ዜጎችን በህግ ታራሚነት ስም አስሮ በአንድ ጎሣ አባላት ቀጥቃጭነትና ገራፊነት እንዲህ ያለ ጭካኔ በአንድ ነገድ ላይ መፈጸም ነገ የሚያስከትለውን ጣጣ ወያኔዎች አላወቁትም፡፡ ሰውን በግልጽ የጦርነት ሜዳ ተዋግቶ ማሸነፍ ሲገባ በህግ ስም አስሮ እልህን መወጣት ወንድነት አይደለም – ለነሱም ፈጣሪ አላቸውና በዚህ ዘግናኝ ታሪክ ውስጥ የተሳተፉና የሚሳተፉ ወያኔ ትግሬዎች ፍርዱን ለመቀበል  መዘጋጀት አለባቸው፡፡ ለማንኛውም ወያኔ የሚኮራበት የአማራ መሰቃየትና ወደታሪክ ትቢያነት መለወጥ በዚህ መልክ ለትውልድ ቀርቧል፡፡ አሁን ነገር ዓለሙን ትቶት ከመንበሩ የተሠወረ የሚመስለው እግዚአብሔር ፍርዱን በቶሎ እንዲሰጥ ከመማጸን ውጪ ለጊዜው ሌላ አማራጭ የለም፡፡ እርግጥ ነው – ፈጣሪ ግፈኛን ሊቀጣ ሲፈልግ ሰውን ያስነሳል እንጂ ራሱ ልምጭ አይቆርጥም፡፡

በወያኔ እስር ቤቶች የሚማቅቁ እነዚህን መሰል አማሮች የጠቅላላው አማራ ወካይ ናቸው፡፡ ወያኔዎች እነዚህን ሰዎች በአማራነታቸውና መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ እንዲህ ከሰውነት በታች እያደረጓቸው የሚገኙት በ20 እና በ30 ሚሊዮን የሚገመተውን የአማራ ሕዝብ በነዚህ ምስኪኖች ውስጥ ያገኙ እየመሰላቸው ነው፡፡ ወያኔዎች ለበቀላቸው ድንበር የለውም፡፡ አማራን ለማጥፋት የተጓዙት ርቀት የሚያሳየን በበቀል ጥማት የሚሰቃዩና  በሕይወት እያሉ አማራ የሚባል ዘር በምድር ሊኖር የማይችል መሆኑን ነው፡፡ ይህንን እምነታቸውን ታላላቅ የዓለም ኃይላት በሚገባ ያውቃሉ!

እናም በኔ ግንዛቤ ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢሉ ወያኔ ትግሬዎች ከአማራ ጋር በአንድ ሀገር ይቅርና በጉርብትናም መኖር የሚያስችል አንድም ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መደላድል አይታየኝም፡፡ አማራጩ ምን ይሁን ለሚለው ጥያቄም ለጊዜው የምለው የለም፡፡ የሚታየኝ ግልጽ እውነት ግና ወያኔ-ትግሬዎችና አማሮች በተቻለ ፍጥነት ፍቺ መፈጸም ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ እንደዚህ እንደማርያም ጠላት ባልተወለደ አንጀት እየተቀጠቀጡ፣ ዘር እንዳያፈሩ እየተኮላሹ፣ በመድሓኒት ስም የማምከኛ መርዝ በመርፌ እየተወጉ፣ ማን ያውቃል – ውኃቻውና እህላቸው እየተመረዙ፣ ቀደምት መንገዶቻቸውና የልማት አውታሮቻቸው እየተዘረፉና እየፈራረሱ፣ መሀላቸውን ሰንጥቆ የሚያልፈው መብራት እንዳይደርሳቸው ተደርጎ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እየኖሩ፣ ትምህርት ቤቶቻቸው በጥራትም ሆነ በአስተዳደርና በታህታይ መዋቅር ረገድ ቁልቁል ወርደው እየተፈጠፈጡ፣ ላዕላዊ አስተዳደራዊ መዋቅሮቻቸው አማርኛ በሚችሉ ትግሬዎችና በሆዳም አሽከሮች ተሞልተው ሕዝ ለከፋ ድህነት እየተዳረገ፣ ቀጭን ሰበብ እየተፈለገ በእስር ቤቶች እየታጎሩና ሂትለርና ሙሶሊኒ እንኳን ያልፈጸሙት የግፍና የስቃይ ዶፍ እየዘነበባቸው፣ ከተናጋሪ እንስሳነትም ባነሰ እጅግ ተጎሳቁለውና ተዋርደው መኖርን ካልመረጡ በስተቀር አማሮች በዚህ መልክ ከወያኔ ትግሬዎች ጋር በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ መቀጠል አለባቸው ብሎ መፍረድ ፍርደ ገምድልነት ይመስለኛል፡፡ እንደሰው የማይቻል የሚመስልን እንደ አምላክነቱ ፈጣሪ ያስተካክለው እንደሆነ እንጂ ትግሬና አማራ በአንድ ሀገር ውስጥ የመኖር ወርቃማ ዕድላቸውን ወያኔዎች ከሥሩ መንግለው የጣሉት ይመስለኛል፤ ሥሩም ዳግም እንዳያቆጠቁጥ አድርገው በጣጥሰውታል፡፡ የዚህ ጭፍግ (ትራጄዲ) ትያትር ዋና ደራሲ የሆነውን የመለስ ዜናዊን ፎቶ ነው እንግዲህ ደብረ ጽዮን ለአቢይ የሸለመው – ማንን ለማናደድ? መልእክቱስ ምንድን ነው? መልሱን ሁሉም አማሮች ያውቁታል፡፡

የትግሬ ወያኔ መሪዎች ስለ አማራ ሕዝብ ከተናገሩት በከፊል የተወሰደ

መጥፎነቱ የወያኔዎች ሰይጣናዊ አስተሳሰብ በጣም ተዛማጅ መሆኑ ነው – The viral disease of TPLF is highly contagious and so many of its culprits are from the ethnic group it proudly claims to represent. Nowadays, it is becoming a rare lottery-like prize to have Samaritan Tigrian who, at least, opposes what their devil incarnate brethren are doing especially against the Amharas. It is enigmatically mindboggling that a plethora of Tigrians is behind this nihilist East African ISIS, namely TPLF. Of course, I absolutely understand that TPLF is a highly pampered in vitro son of anti-Ethiopian global forces without the staunch economic and intelligence assistance and moral support of whom these crooked creatures wouldn’t come out of their initial den, namely Dedebit. “ስምሰ ይቀድሞ ለነገር” – መነሻቸውም ደደቢት እነሱም ደደቦች! የሚገርም የነገሮች መመሳሰል፡፡  They, the anti-Ethiopian forces, must be, for example, the composers of the following anti-Amhara slongas which were and still are reiterated by the top leadership of TPLF. እነዚህ የወያኔ አባባሎች ብቻቸውን ለአማራና ትግሬ አብሮ አለመኖር በቂ የፍቺ ምክንያቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ንግግሮች በተግባር ለማሳየት ነው እንግዲህ በሚሊዮን የሚቆጠረው የትግራይ ወጣትና ጎልማሣ በመላዋ ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ አማራን በገባበት እየገባ ዘሩን እየመተረው የሚገኘው፤ በኔ ላይ ጣት ከመቀሰር ኢትዮጵያን ተዘዋወሩና ራሳችሁ ፍረዱ፡፡ አዲስ አበባ ራሷ ኅያው ምሥክር ናት፡፡ “የደንቆሮ ልቅሶ…” ካላላችሁኝ ካለ ትግሬ ሌላው የሚኖርባት፣ ሌላው የሚነግድባት፣ ሌላው ሀብት የሚያፈራባት፣ ሌላው ሕንፃና ቤት የሚገነባባት፣ ሌላው የሚሾምባት…. አትመስልም፡፡ ይህን ፀረ-ወያኔ ትግሬ ምሬት የምናገረው ተመሳሳይ የአማራ ወይም የሌላ ተበደልኩ ባይ ዕብሪት ተፈጥሮ ትግሬ እንደ አማራ ሲጠፋ ለማየት አይደለም – በጭራሽ! ለጋንግሪንና ለካንሠር ግን መላ እንዲፈለግና ንጹሓን ዜጎች ዕረፍትና ጤና እንዲያገኙ ጽኑ ምኞቴና ፍላጎቴም ነው፡፡ በመሠረቱ ወያኔዎች ባይኖሩ ኖሮ በአምባቸውና በግደይ መካከል የሚያገዳድል ቀርቶ የሚያኮራርፍ  እንኳን አንዳችም ምክንያት አልነበረም፡፡ በቋንቋ በል፣ በዘር ግንድ በል፣ በሃይማኖትና ባህል በል፣ የዛሬውን አያድርገውና በምጣኔ ሀብታዊ ደረጃ በል፣  በሥነ ልቦና በል፣ በሰውነት ቅርጽ በል፣… ትግሬና አማራ አንድ ነበሩ፡፡ “ናቸው” ማለት ፈልጌ አፌን ዳባ ዳባ አለው፡፡ ይገርማል – አለያዩን፡፡ ጥቁር ውሻ ይውለዱ!!

እግዚአብሔር ያሳያችሁ ክርስቶስ ያመላክታችሁ! ከዚህ በላይ የምትመለከቷቸው ምስሎች በአማራው አካባቢ ከሚገኙና ሻል ያለ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአንደኛው ተገኝቼ ራሴው የቀረጽኩት አንድ የመማሪያ ክፍል ነው፡፡ ክፍሉ የዓሣማ ጋጣ ይመስላል፡፡ መስኮትም ሆነ በር የለውም፡፡ የተማሪ መቀመጫ አግዳሚ ወንበሮቹም ተሰባብረዋል፡፡ የክፍሉ ጽዳት እንደምታዩት ነው – እንዲያውም የፈረንጅ ዓሣሞች ጋጣ ሳይሻል አይቀርም – (ስላላየሁ እርግጠኛ አልሆንኩም)፡፡ በዚያ ላይ ክፍሉን ምሥጥ ሊጥለው እየታገለው ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ዜሮ መምህራን ዜሮ ተማሪዎችን አስተምረውበት “ምርጥ ዜጎች” ሀገር ሊረከቡ እየተሰናዱ ነው፡፡ ወያኔ ትግሬ አማራን እንደዚህ ክፉኛ እየተጫወተበት ነው፡፡ ወደ ትግራይ ሄጄ የታዘብኩት ግን ሌላ ነው፡፡ አውሮፓ ያላችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ የትምህርት ጥራቱም ሆነ አስተዳደራዊ ድጋፉ ለአንደኛ ደረጃ ዜጎች ከሚጠበቀውም በላይ ነው፡፡ በፎቶ ባለማስደገፌ ይቅርታ፡፡ ግን እውነቴን ነው፡፡ አሁንም ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ!! (መውለዳቸውን አውቃለሁ! አንዳቸውም ልጅ አልወጣላቸውምና፡፡ እንደነሱ ክፉ መሆን አልነበረብኝም፡፡ ምርጫ አጥቼ በገባበት የእርግማን ኃጢኣት እግዜር ይቅር ይበለኝ፡፡ ‹ክፉን በክፉ አትቃወሙ› ይላልና፡፡)

ጅምሬን ላጠቃልል ነው ጥቂት ታገሱኝ፡፡

ወያኔ በባሕርይው በብዙ ነገሮች ይገለጣል፡፡ በቀዳሚነት የሚታየኝ ወያኔ ጅብ ነው – የማይጠግበው ጅብ ሊያውም፡፡ እርግጥ ነው – ጅብ ለብዙ ተምሣሌቶች ይውላል፡፡ ጅብ ሆዳም ነው፤ ጅብ ፈሪ ነው፤ ጅብ ጉልበተኛ ነው፤ ጅብ ከሰይጣን፣ ከቡዳና ከመተትም ጋር በተገናኘ ይነሣል – በሰፈር ውስጥ አንድ ጅብ ሲገደል ወይም ሞቶ ሲገኝ አንዱ ቅንድቡን ሌላው ግራ እግሩን፣ አንዱ ጉበቱን ሌላው ኩላሊቱን ለመቀራመት ሕዝበ ክርስቲያን ሲረባረብበት ስታዩ በየትኛው ዘመንና የትኛው ሀገር ውስጥ እንደምትኖሩ ባለመረዳት ትደነግጣላችሁ፡፡ ለማንኛውም እንደየማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ሌላ ሌላም ትዕምርታዊ ተጠቃሽነትና ባህላዊ አገልግሎት ሊኖረው ይችላል – አያ ጅቦ፡፡

 

ወያኔ በርግጥም ሆዳም ጅብ ነው፡፡ ይሄውና ከመጡ ጀምሮ በበሉና ባገኙ ቁጥር እየራባቸውና እየተስገበገቡ ሲሄዱ እንጂ በቃኝ ብለው ፈጣሪን ሲያመሰግኑ አልታዩም – ለነገሩ ፈጣሪንም አያውቁም፤ በባሕርይ አባታቸው በሰይጣን ከሆነ እንጂ በርሱ አያምኑምና፡፡ ስለዚህ በእምብርት የለሽነታቸው ከጅብና ከአህያ ጋር ቢመሳሰሉ በውክልናቸው እነዚህን ፍጥረታት ቢያስከነዱ እንጂ አይተናነሱም፡፡

ወያኔ በርግጥም ፈሪ ጅብ ነው፡፡ የፍርሀታቸው መጠን አንዱ መገለጫ አርቀን ቀብረነዋል የሚሉትንና ከሀገርም ከሀብትም ሙልጭ ያወጡትን አማራ በፈሪ ዱላቸው አሁንም ድረስ እያሳደዱ መቆሚያ መቀመጫ ማሳጣታቸው ነው፡፡ ወያኔዎችን በፍርሀት የሚስተካከል የለም፡፡ ጀግና መሐሪ ነው፤ ጀግና ይቅር ባይ ነው፤ ጀግና ሩህሩህ ነው፤ ጀግና ማሸነፉን ያውቃል፤ ያሸነፈውን ወገን ያከብራል፤ ይንከባከባል፤ ነግ በኔንም ይገነዘባል፡፡ ፈሪ ግን ማሸነፍ ብርቁ ስለሆነ፣ ያሸነፈው በአጋጣሚ እንጂ ታቅዶና ታስቦበት በጀግንነት ስላልሆነ የተሸነፈ አካልን ሞቶ እንኳን በድኑን ሲደበድብ ይገኛል፡፡ ጀግና ኮስታራ ነው – ሆዳምም አይደለም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወያኔዎች እጅግ ፈሪ በመሆናቸው ዐፅምን ከመቃብር አውጥተው ሳይቀር በምናባዊ ዱላቸው ይነርቱታል፡፡ ምሕረትና ይቅርታ የሚባል ነገር ሲያልፍም አይነካቸው – የፈሪ ባሕርይ አይደለምና፡፡ አሁን ያለው ሀገራዊ ምስል ሲለወጥ እንዴት እንደሚሆኑ ጥቂት ዕድሜ የሰጠው በርግጠኝነት የሚያየው ይሆናል – ደብቁኝ ደብቁኝ ለማለት ከነሱ የሚበልጥ የለም፡፡ የፈሪ ጠባይ እንደዚህ ነው፤ ሁለቱንም አይችሉም፡፡ ማግኘትንም አያውቁበትም፤ ማጣትንም አያውቁበትም፡፡ ማግኘት ናላቸውን እንደሚያናፍላቸው ሁሉ ማጣት የሚሆኑትን ያሳጣቸዋል፡፡ ጀግና ግን ለሁሉም ዝግጁ ነው፡፡ መሸነፍንም ማሸነፍንም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህም ፀጋ ነው፡፡ ቀንንም ማወቅ ጥሩ ነውና፡፡

ወያኔ በርግጥም ጉልበተኛ ነው፡፡ ጉልበተኛ ማለት ግን በግድ ጀግና ነው ማለት እንዳልሆነ ከፍ ሲል ከተገለጸው የጀግንነት መለኪያ አኳያ  በመነሳት መረዳት ይገባል፡፡ ጉልበተኛ ዕድል ከገጠመው በኃይሉ ተቀናቃኙን አያሸንፍም ማለት እንዳልሆነም ልብ ይሏል – የተዋጊ ብዛትና የመሣሪያ ጥራት ከግምት ሳይገባ ብዙ ጀግኖች ቀን ጥሏቸው በፈሪዎች ተሸንፈዋል፡፡ ለማሸነፍ ለማሸነፍ አህያም ጅብን፣ ጅብም አንበሣን የሚረቱበት አጋጣሚ አለ፡፡ አያስደንቅም፡፡ የወያኔን ጉልበት በሚመለከት ግን ከጉንዳን ጋር በማወዳደር ትንሽ ንጽጽሮችን ማየት እንችላለን፡፡ ጉንዳን ከክብደቱ ስንትና ስንት የሚበልጥ ኮተት እየገፋ ወደጉድጓዱ ሲወስድ እናያለን፤ እናደንቃለንም፡፡ ወያኔም በተለይ ባለፉት 27 ዓመታት ከኢትዮጵያ ያጓጓዘው ሀብትና ንብረት ሲቃኝ በነዚህ ጥቂት ሰዎች በዚህን ያህል አጭር ጊዜ ውስጥ ይህ ሁሉ ጉድ እንዴት ተጋዘላቸው ብለን መገረማችን አይቀርም – ወያኔዎች ኢትዮጵያን በተቆጣጠሩ ሰሞን በሚዘረፍ ሀብትና ንብረት “ትግራይ ልትሰምጥ ነው!” የሚል ቀልድ መሰል እውነት ሲነገር እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ሆና ተዝቃ አለማለቋ በጄ እንጂ ወያኔዎች እኮ ዳሸንን የመሰለ  ተራራና ላሊበላን የመሰለ ታሪካዊ ሥፍራ “አጓጉዘው” ወደ ትግራይ ወስደዋል፡፡ እነሱ ምን ያልወሰዱት ነገር አለ! ሕንጻስ ዘርፈው ሲውስዱ ድንበር አካባቢ ተይዘዋል ተብሎ የለምን? እናም ወያኔዎች ምንም እንኳን ዱሮ ቀጫጭን ቢሆኑም በዚያችው ጉልበታቸው በዘረፋ ያከማቹት ሀብትና ንብረት ግቢያቸው አልበቃ ብሎ የጎረቤት ሀገር ካዝናም በውሰት ሳያጥለቀልቅ አይቀርም፡፡ የሚገርመው ነገር ወያኔዎች ኢትዮጵያን እንደሚያድሩባት ይቅርና እንደሚያመሹባት እንኳን ማመን ከብዷቸው በጥርጣሬ እንዳዩንና በጥርጣሬ እንደገዙን፣ የሀገራችንንም ስም ለመጥራት እንደተጠየፉና እኛንም እንደናቁን፣ በአካል ብቻም ሣይሆን በአእምሮና በሥነ ልቦናም እንደገደሉን፣ ገንዘባችንንና ሀብታችንን ግን እንዳፈቀሩና በሥልጣንና በንዋይ ፍቅር ሰክረውና ዐብደው እንደቀጠቀጡን ግማሽ ምዕተ ዓመት ሊዘልቁ ነው፤ ይህ ለዓለማችን እንግዳ የሆነ ክስተት በGuinness Book of Records እንዲመዘገብልንና እንዲመዘገብላቸው ቢደረግ ብዙ የዓለም ሕዝቦች ከተመሳሳይ ቅጣት ራሳቸውን ይጠብቁ ዘንድ አስተማሪ ይሆናቸዋል፡፡

ይሄ ፌስቡክ የሚሉት ነገር ብዙ የማይረባ ነገር ያለውን ያህል መልካም ነገሮችም አያጣምና አንዳንድ ፎቶዎችን ተውሻለሁ፡፡ የሚከተለውን ምስል ተመልከቱልኝ፡፡ ጊዜ ሲጥል እንዲህ ነው፡፡ ለ27 ዓመታት በጅቦች ሲዘነጠል የባጀ ሕዝብ ከእንግዲህ እንደዚህ ኮበሌ የሜዳ አህያ የቁም ስቅሉን ሲያሳዩት የነበሩትን የፈረንጅ ተላላኪዎች የሚቆረጣጥምበት ዘመን በቅርብ መምጣቱ አይቀርም፡፡

እንጂ ኢትዮጵያ ሰፊ ሀገር ናት፡፡ ከተዛዘኑና ከተፋቀሩ እንኳንስ ለ100 ሚሊዮን ለ500 ሚሊዮን ሕዝብም ትበቃለች፡፡ የበሬ ግምባር በምታህል ቦታ ስንትና ስንት ሀገሮች ሕዝባቸውን አስማመምተውና አፋቅረው በጥሩ ሁኔታ እንደሚያኖሩ እናውቃለን፡፡ የሚከተለውን ምስል እንመልከትና ተቻችሎ መኖር ምን ሊመስል እንደሚችል መጠነኛ ግንዛቤ ለማግኘት እንሞክር፡፡ መቻቻል ሲባል ግን አንዱ ብልጥ ሌላው ሞኝ፣ አንዱ እሳት ሌላው ጭድ፣ አንዱ በይ ሌላው ተመልካች መሆን ማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል፡፡ ወያኔ የሚፈልገው ግን እኔ ስበላ እናንተ ተመልከቱ፤ እኔ ሳገሳ እናንተ አበስኑ፣ እኔ ስጠግብ እናንተ ተራቡ፤ እኔ ስወፍር እናንተ ክሱ… ዓይነት የጅሎች ፈሊጥ ነው፡፡

 

ወፍ ዘራሾቹ ወያኔዎች አባልተውንና አመናቅረውን ሊሄዱ የተቃረቡ ይመስላሉ፡፡ ስለመሄዳቸው ደግሞ በጭራሽ አትጠራጠሩ፡፡ ይሄ የዲያሌክቲክስም በሉት የሃይማኖት ወይም የተፈጥሮ ህግ በመሆኑ ከማርጀትና ከመሞት ሞቶም  ከመበስበስ፣ ከመለወጥና የእጅንም ከማግኘት የሚቀር አንድም ምድራዊ ክስተት የለም፤ አይግርመን፡፡ እምዬ ምንሊክም አልፈዋል፤ የተሻሉ ነበሩ የሚባልላቸው ጃንሆይና መንግሥቱም እንደየሥራቸው ማግገኘት አለማግኘታቸው በጥያቄ መልክ ተይዞ ያገኙትን አግኝተው አልፈዋል፡፡

በሰሞኑ የተሰማው የአንድ የእግር ኳስ አሰልጣኝ ወያኔ ዕብሪት ደግሞ ይሄውላችሁ – “ድንቁርና እስከ መቃብር” ይሏል እንዲህ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደገና ካልተፈጠሩ ከዚህ የጥላቻ አዙሪት የሚወጡ አይመስለኝም፡፡ የጥላቻቸው መንስኤ አሁን ግልጽ ነው፡፡ አማራ ካለ ኢትዮጵያን እንዳሻን አንዘርፍም ብለው ማመናቸው ለዚህ አማራን አምርሮ የመጥላትና በወንጀል ላይ ወንጀል የመደረብ ቅርቃር ሳይዳርጋቸው አልቀረም፡፡ አማራን በዋና ተቀናቃኝነት መዝግበዋል፡፡ ግን ግን አማሮች ኢትዮጵያን ትተውላቸው  በምትኩ እነሱ አማሮችን  ማሳደዳቸውን ባቆሙ፡፡ ለነገሩ እ እንዲህ ልበል እንጂ አማሮች ከኢትዮጵ ቢወጡም ወያኔዎች አይለቋቸውም – ልክፍት ነዋ!!

ምሥጋና – ቱባዎቹ ወያኔዎች ስለአማራ ሕዝብ የቀላመዱትንና በቻርት መልክ የተዘጋጀውን ምስል ወልቃይት ድረ ገፅ በጠየቅሁት መሠረት በቶሎ ስለላከልኝ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡