ለሁለት ሳምንት ሙሉ አስቀድምቻሁ እንደሰማችሁት ከመተከል-ቤንሻንጉል-ጉሙዝ-ኦሮሞያ ቡኖ በደሌ ወዘተ ወዘተ..የተፈናቀሉ አማራዎች ባጠቃላይ ትላልቆቹ 503 ሲሆኑ ከነ ህጻናት በጠቅላላ ከ1100 በላይ እንደሚሆኑ ተዘግቧል። ቤቶቻቸው እየተቃጠለ፤ ከብቶቻቸው እና የያዙት ገንዘብ እየተዘረፉ ሰላም አጥተው፤ ሸሽተው በመምጣት፤ለመፍተሄ ፍለጋ ወደ ወያኔዎቹ አሽከሮች “ብአዴን’ ብሎ ራሱን ወደ እሚጠራ ጸረ አማራ “የባንዳ ስብስብ” አቤት ቢሉም ያገኙት ምላሽ ፤ ወደ ነበራችሁበት ተመለሱ ወይንም “እንደ ማንም ዜጋ (መቋቋሚያ ሳይሰጣቸው) ወደ ፈለጋችሁት ተበትናችሁ ሂዳችሁ ኑሮኣችሁን ‘ሀ’ ብላችሁ ጀምሩ። ተብለው ለተሰጣቸው “የሞት ፍርድ ውሳኔ” ለማስለወጥ በተቃውሞ ሊያነጋግሯቸው ቢሞክሩም “ውሳኔው ጸድቋል፤ አማራጭ የላችሁም” ተብለው ከታገቱበት ሥፍራ እየተጎተቱ ግማሾቹ ወድየት እንደገቡ (ምናልባትም ወደ አዲስ አባባ የጎስታፖዎቹ ‘ማዕከላዊ’ ሊሆን ይችል ይሆናል ማን ያውቃል!) ሳይታወቅ ይኼው “በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ” ፍዳ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ከታች አያይዤ የምሰጣችሁን ቪዲዮ ተመልከቱ እና ፍረዱ። ከላይ የምታዩት ፎቶግራፍ “ከአለምነው መኮንን” ቀጥሎ የተከሰተው ሌላው “አሳፋሪ ሰው ነው” ስሙ “አማረ ክንዱ” ይባላል፤ “የአማራ አደጋ መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሐላፊ ነው”። ተፈናቃዮችን በሚመለከት ‘የአማራ ክልል ዜና ማዕከል” እያለ ራሱን የሚጠራ የዜና ማሰራጫ ጣቢያ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለት ከገጽታው የሚነበበው የዚህ ሰው ‘ጭካኔ’ የሚያስታውሰኝ ‘የድሮ የደርግ ገራፊ የሚመስል’ ፤ ለወገኖቹ ከቶ ምንም የራራ አንጀት የማይታየው እዛው “ሰብአዊ ዕርዳታ በሚደረግበት ጽ/ቤት” ውስጥ “መቀመጥ ያልነበረበት እርከኩስ ጨካኝ ንግግሩን አድምጡልኝ። እሱ የሚወነጅላቸው ተፈናቃዮቹ ውሳኔውን አንቀበልም ብለው ከታገቱበት “በር “እየገፈተሩ” እምቢ ብለው ወጥተዋል (ኮንሰንትረሽን/የናዚዎቹ የማጎርያ ካምፕ ማለት ነው)። መውጣት መግባት እንኳ አይችሉም፤ የተዘጋ በር እየገፈተሩ ሲል በተከበበ ስፍራ ውስጥ ነው እየተጠበቁ የነበሩት ማለት ነው።) ተፈናቃዮቹ የሚሉት ደግሞ “ከተጠለሉበት ቦታ እየታፈኑ” ‘የት አንደደረሱ’ አይታወቅም’ ሲሉ ለጋዜጠኛው ተናግረዋል። ለማንኛውም እስኪ ይህንን የተሰራጨው የቃለ መጠይቅ የቪዲዮ ዘገባ አድምጡና እና የራሳችሁን ትዝብት ጨምሩበት። እንዲህ ያሉ ሰዎች አማራውን ይረዳሉ ተብሎ ከቶ የማይታሰብ ነው። ገዱ አንዳርጋቸው ለአማራ ያስባል፤አዲስ ተራማጅ ነው፤ ወያኔ ሊገድለው እየፈለገ ነው፤/… ቁልቓል ጅኒ ጃካ የምትሉ ሰዎች ብአዴን የሚባለው ከገዱ ጀምሮ ‘እስር ቤት መግባት ይገባቸዋል (ፍትህ ቢኖር ኖሮ)። ተፈናቃዮች ዛሬም ትኩረት ይሻሉ፡