ከአያሌው መንበር
“ብርቱካንን_አገኘኋት ፤ ብር ምን ያደርግልናል፤ አገራችን ሄደን መኖር ነዉ እንጅ አለችኝ” ብርቱካን ለአንድ ወዳጀ ያለቸውን ሲነግረኝ ነው።
ከቤኒሻንጉል ከተፈናቀሉ ወገናቻችን ውስጥ ትምህርታቸውን አቋረጠው የትምህርት ያለህ? የሚሉ ህፃናት፣ንብረታቸው ወድሞባቸው የምግብ ያለህ የሚሉ ቤተሰቦች፣ ቤታቸው ተቃጥሎባቸው መጠጊያ ያጡ…በደፈናው ሰማይና ምድር የተደባለቀባቸው አማራ ወገኖቻችን ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምረው መጠለያ ፍለጋ ላይ ሁነው የወገን ያለህ በማለት ላይ ናቸው።ከሰሞኑ ወደ ባህር ዳር ሄደው ቢያንስ ወገን እንዳላቸው አሳይተዋቸው ትንሽ ደስታ የፈጠረላቸው ቢሆንም ዘላቂ ፍትህ፣ እና ዘላቂ መፍትሄ ባለማግኘታቸው አሁንም የሰው ያለህ? እያሉ ነው።ድንጋይ ፈልጦ ሀገር ያቆመ ህዝብ፣ ድንጋይ ፈልጦ መኖር የሚችል የስራ ሰው እንዴትስ አማራ እንዲህ ሊዋረድ ቻለ? እኛ ግን ወገን የሌለን ለምን ይሆን? ብለው ይጠይቃሉ።
እስካሁን ድረስ የአካባቢው አማራ ወገናችንና ሌሎች በውጭ የሚኖሩ አማራዎች ለጊዜያዊ መፍትሄ ጥረት እያደረጉ ቢያንስ ከርሃብ እያስታገሷቸው ነው።በዚህም ተፈናቃይዎቹ “ለካ ወገን አለን፤ አይዟችሁ የሚለን ህዝብ እያለን ነው እንደ ቁስ ሲያሰቃዩን የኖሩት?” በማለት ይገልፁታል።አሁንም ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየጮሁ ነው።የቤኒሻንጉል ክልል እኔ አላፈናቀልኩም ሲል ብአዴን ደግሞ ምላሽ ለመስጠት እንኳን ተቸግሮ አዳራሽ ውስጥ ይነታረካል።ተሰብሳቢዎች “አማራን እኛ የተዋረደ ህዝብ አድርገነዋል፤ እንዴትስ ቤኒሻንጉል ከግማሽ ያልተናነሰ አማራ የሚኖርበት ለዚያውም አማራ ያለማው ክልል ህዝባችን ሲይልፈናቅል ምላሽ መስጠት እንኳን አቃተን? ከዚህ በላይ ምን ውርደት አለ? ስለምንስ መሪ ነን እንላለን?” በማለት ጠይቀዋል።ወገኖቻችን ግን አሁንም መፍትሄ አላገኙም።ወልደው ከብደው ሀብት አፍርተው የኖሩበት አሁን ደግሞ የተፈናቀሉበት አካባቢ መሄድ ቢፈልጉም ከሶስት ጊዜ በላይ ተመሳሳይ አደጋ ስለደረሰ፤ ወገኖቻቸው አይናቸው እያየ ስለተገደሉ እና ጉድ ጓድ ውስጥ ስለተጣሉ ማንን አምነን እንሂድ? ይላሉ።እርግጥ መፍትሄ ማስተማመኛ ተሰጥቷቸው፤ ካሳ ተከፍሎ መመለስ ብቻ ነው።እነርሱም የሚጠይቁት ይህንን ነው።ህፃኗ ብርቱካን እንኳን የጠየቀችው ይህንን ፍትህ ነው።
የሆነው ሆኖ ግን ህዝባችን አሁንም እየጠየቃቸው ነው።ከእነዚህ ውስጥ አንድ ወዳጀ ይህንን መልዕክና ፎቶ ላከልኝ።
<<በቃሌ መሰረት ሄድኩ። ከደመወዜ 500 ብርም ሰጠሁ። ነገር ግን አልረካሁም፤ በጣም ተበሳጭቻለሁ። ትግል ዉስጥም ለመግባት ወስኛለሁ።ምን ብየ ልንገርክ አልቅሻለሁ።ብርቱካንን አገኘኀት ብር ምን ያደርግልናል አለችኝ አገራችን ሄደን መኖር ነዉ እንጅ አለችኝ።>>
እውነት ነው ያስለቅሳል።ያበሳጫል።ያ የተከበረ ህዝብ እንዲህ ሲደፈር ሲዋረድ ማንኛውንም መንገድ መከተል ሀጢያት አይደለም።የብአዴን ጉምቱ ባለስልጣናት ባህር ዳር መሽገው ቁርጥ በውስኪ እያወራረዱ ከዚያው ቤተክርስትያን የተጠለሉ ወገኖቻችን ለመጎብኘት እንኳን አላሰቡም።ብአዴን ማለት ቆሻሻ ድርጅት፤ ሰብአዊነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት፣ አማራዊ ስሜትን አሽቀንጥሮ ጥሎ ታዘዥና አፋኝ የሆነ፣ የጠላት ሀይል ጉዳይ አስፈፃሚ ነው።ብአዴን ውስጥ እንደእኔ ቆሽታቸው የሚያር ሰዎች ቢኖሩ እንኳን የአማራን ህዝብ ችግር መፍታት አይችሉም።ከአቅማቸው በላይ ነው።ብአዴን አዋርዶናል፤ አስገድሎናል፤ አንዳንዶች ገድለውናም ጭምር፣የህዝቡ ስነልቦና ተሰልቦ እንዳይናገር እንዳይጠይቅ ከማድረግ ባለፈ ተሸማቆ እንዲኖር ባልተቦረሸ አፋቸው ተፀዳድተውብናል፤ ሌሎችም እንዲሰድቡን ቃል አውጥተውልናል።ብአዴን ማለት ይህ ነው።
መፍትሄ፦
የእነ በረከት፣ ታደሰ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ከበደ ጫኔ ብአዴንን ማፍረስ ነው።ያስደፈረን፣ የደፈረን፣ ያዋረደን፣ያስገደለን፣ የገደለን፣ድሃ ያደረገን፣ ከሰው ተራ በታች እንድንሆን ያደረገን፣ በአለም የድህነት መዝገብ እንድንሰፍር ያደረገን/ያስደረገን ብአዴን ሲፈርስ የአማራ ህዝብ ክብር ይመለሳል፤ ጥቅሙ ይከበራል።ብአዴን ውስጥ ያሉ ተቆርቋሪ አማራዎች ካሉ ብአዴንን በማፍረስና የአማራ ህዝብን ሊወክል የሚችል ፓርቲ እንዲቋቋም በማድረግ ይተባበሩን።