May 9, 2018
በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡን ለቁጣ ያስነሳው የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ማስታወቁን ፋና ዘገበ:: ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ሚድሮክ ጎልድ በለገደምቢ በሚያካሂደው የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ ቅሬታ ማንሳቱን ተከትሎ ነው ፍቃዱን ያገደው ብሏል ፋና::
በገለልተኛ አካል ጥልቀት ያለው ጥናት እስከሚጠና ድረስ የኩባንያው ወርቅ የማምረት ስራው የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ሜድሮክ ታግዷል::
የሜድሮክ የለገደምቢ ወርቅ ማምረት ፈቃድ መራዘምን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የሰው ሕይወትን ያስቀጠፈ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሲደረግ እንደሰነበተ ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም::
የሜድሮክ ጎልድ ‘ባለቤት’ ሼህ መሐመድ አላሙዲ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ አረቢያ ባልታወቀ ሥፍራ በ እስር እየማቀቁ ይገኛሉ::