May 9, 2018

ለገሠ ወ/ሃና

Masresha Sete
በጠም ዘግይቶ የተጀመረው የነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ የ38 ተከሳሾችን ጉዳይ የተመለከተው 4ኛ ችሎት በቅሊንጦ ቃጠሎ የተከሰሱት 38 ተከሳሾች ብይን ሰጥቷል
ከ38ቱ ተከሳሾች መካከል
31ኛ ተከሳሽ ጌታቸር እሼቴ
32ኛ ተከሳሽ ቶፊቅ ሽኩር
33ኛ ተከሳሽ ሸምሱ ሰኢድ
34ኛ ተከሳሽ ፍፁም ጌታቸው በቂሊንጦ ቃጠሎ ሰበብ
በተገደሉት ሰዎች ነፍስ እንዲከላከሉ ሲበየንባቸው
6ኛ ተከሳሽ አብዱሉሂ አልዩ
7ኛ ተከሳሽ እስማኤል በቀለ
11ኛ ተከሳሽ ቃሲም ገንቦ
18ኛ ተከሳሽ አንጋው ተገኘ
21ኛ ተከሳሽ ሰይፈ ግርማ
27ኛ ተከሳሽ ዲንሳ ፉፉ
28ኛ ተከሳሽ ናስር ደጉ
29ኛ ተከሳሽ ናኦል ሻሜሮ በነፃ እንዲሰናበቱ ተበይኗል።
መቶ አለቃ ማስረሻ፣ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ፣ አግባው ሰጠኝ፣ ወልዴ ሞቱማ፣ ሚስባህ ከድር፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ደረጀ መርጋ፣ ከበደ ጨመዳ፣ ደሴ አንዳርገው፣ ፍፁም ቸርነት ጨምሮ 28 ተከሳሾች እስር ቤት ውስጥ አመፅ በማደራጀት፣ በመምራት፣ በመሳተፍ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አንቀፅ 464/2/ሀ፣ ለ፣ 461/ሀ እና 494 /2 ስር እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።

ይህ ብይን እየተነበበ ባለበት ጊዜ አንድ ተከሳሽ በሃመል ገብቶ እንድት እናንተ በገደላችሁት ነፍስ እንዴት ተከላከል እባላለሁ ገድለኸዋል ተከላከል የተባልኩት ሰው አብሮ አደጌ ጓደኛን ነው በዚህ ሠው ሞት አባቴ ደንግጦ ህይወቱ አልፏል በማለት ድምጽን አሰምቷል የችሎቱ ሁኔታ ያስፈራቸው የቅሊንጦ ባለጠመንጃዎች ገና ችሎቱ ሳይጠናቀቅ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነበር ችሎቱ እንደተጠናቀቀ ተከሳሾች እኛ ወንጀል አልፈፀምንም ወንጀለኞች እናንተ ናችሁ የሚል የምሬት ቃል ሲያሰሙ ዳኞች ከወንበራቸው ተፈናጥረው ከመጋረጃው ጀርባ ገብተዋል መሽገዋል ፡፡
እጅግ በርካታ በለ ጠመንጃዎች መሣሪያቸውን በማቀባበል ወደ ህዝቡና ወደ ተከሳሾች በማዞር በተለይ ተከሳሾችን ዙሪያቸውን ከበው በማነጣጠር ዝም ለማሰኘት ቢሞክሩም አልተሳካም ችሎቱን ለመከታተል የመጣውን ህዝብ ፣ የተከሳሽ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ባሰሙት ጩኸት ፓሊስ የችሎቱን ታዳሚ በመገፈታተር እና በመምታት ጭር ህዝቡን አሰወጥተውታል ህዝቡ ከችሎት ብቻ በማስወጣት ሳይወሰኑ እየገፈታተሩ ከፍርድ ቤት ግቢ አስወጥተውናል በዝምታ የተጀመረው ችሎት በጩኸትና በለቅሶ ተጠናቋል ፡፡