“ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንደሚባለው ወያኔ  በደንቆሮ ዋሻ መሽጎ ከነበረበት ከ1970ዎቹ ዓመታት አንስቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በደበኛ ጠላትነት ፈርጆ እየገዘገዛትና እያደማት ይገኛል። ወያኔ በተለይም የስልጣን ማማ ላይ ከተቆናጠጠበት ካለፉት 27 ዓመታት አንስቶ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በተጠናከረ ሁኔታ በመዝመት መነኮሳትን ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ሳይቀር በጥይት እየቆላ (ባሕታዊ ፈቃደሥላሴ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን  ውስጥ በአባ ገብረመድህን ‘አቡነ ጳውሎስ’ ትዕዛዝ የተገደሉት) ገዳማትን እያፈረሰና እያጋየ የጥፋትና የውድመት እኩይ አላማውን ቀጥሎበታል። ከዚህም በተጨማሪም ህጋዊውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው በጉልበት በማውረድና የአገር ቤቱን ሲኖዶስ በመቆጣጠር ለአላማው መጠቀሚያ አድርጎታል። ይህንን የተቃወሙ አባቶች በስደት ህጋዊውን ፓትርያርክ ይዘው ሲኖዶስ አቋቋመው በውጭ የሚገኘውን ህዝብ እያገለገሉ ይገኛሉ።

ይህ በአገዛዙ ምክንያት የተፈጠረው መከፋፈል ለአንዳንድ ወስላቶች አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ከተጠያቂነት እንዲያመልጡና “ለያዥ ለገራዥ” እንዲያስቸግሩ ረድቷቸዋል። ለምሳሌ በዝሙት ምክንያት ስልጣነ ክህነቱን የተገፈፈው አቶ ታደሰ ሲሳይ ተጠሪነት ያለው ሲኖዶስ ከበላዩ ስሌለ በዝሙት ተጨማልቆ ቤተክርስቲያንን እያረከሰ ይገኛል። ታደሰ ሲሳይን የመሰሉ ወንበዴዎች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዴት በሲኖዶሶች መካከል የሚካሄድ እርቅን እንደሚያደናቅፉ ቀሲስ አስተርዓየ ሁኔታውን ተንትነው የሰጡትን ትምህርት አቅርበንላቸኋል።