A German airport management company bought 45 percent of Athens International Airport on May 31. Greece’s primary railway company, TrainOSE, was sold to an Italian railway company last year. TrainOSE, A ship docked at Piraeus port in Athens, 51 percent of which was acquired by the Chinese company COSCO. Ethiopia International Airport, Ethiopia railway company and EthioTelecom.

ኢትዮጵያ ከሃገረ ግሪክ የብድር ጫና ትማር!!!‹‹ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት ደሞዝ ለመክፈል አይበደርም›› ዶክተር ደምስ ጫንያለው(ሜይ 11 ቀን 2018እኤአ/ ቢቢሲ አማርኛ)‹‹ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገቶ የምትጠቀሰው ኢትዮጵያ በቅርቡ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቆም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት ምጣኔ ሃብታዊ ዘገባ ላይ የእዳ መጠኖ ከፍተኛ እንደሆነ አትቶል፡፡ ኢትዮጵያ የእዳ ጫናዋ መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቶ 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሆነ ተጠቅሶ ከአገራቱ ተርታ ተመድባለች፡፡ ምንም እንኮን ተቆሙ ብድሩ አስጊ ደረጃ ላይ እንደሆነ ቢገልፅም በተቃራኒው ብድር እንደ ችግር ሊታይ አይገባም የሚሉት የግብርናና ምጣኔ ሐብት ባለሙያ ዶክተር ደምስ ጫንያለው እንደ ምሳሌነት የሚጠቅሱትም በብድር የምትመራውን አሜሪካ መሆኖን ይጠቅሳሉ፡፡ ‹ብድር መውስድ የሚያስገርም ነገር አይደለም፡፡ ማንኛውም እድገት ከመበደር በነፃ እንቅስቃሴ አይደለም፡፡ ዋናው ጥያቄ ለምን ተግባር ይውላል›› ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ ብድር የምትበደረው ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት እንደሆነና አይ ኤም ኤፍና የዓለም ባንክ የመሳሰሉት ተቆማት ለአገሪቱ የተለያዮ መሰረተ ልማቶች ብድር እንደማይሠጡም ይገልፃሉ፡፡ ‹‹የመንገድ ሥራዎች ለመስራት፣ ግድቦችን ለመገንባት፣ ለመብራት መስፋፋት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ፣ ለባቡር ዝርጋታ እና ለመሳሰሉት ኢትዮጵያ ብድር የምትወስደው ከቻይናና ከህንድ ነው ይላሉ፡፡ አንድ የብድር መጠን ሊነፃፀር የሚገባው ከመክፈል አቅም ጋር ነው፡፡ ብድሩን ተጠቅሞ ገቢ ማግኘትና በወቅቱ መክፈል እስከተቻለ ድረስ ሪፖርቱ እንደሚለው የሚረብሽ ነገር የለውም፡፡ በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ለምን ተበደረ የሚል አቆም የላቸውም፡፡›› ይላሉ  ዶክተር ደምስ ጫንያለው፡፡ ከድረገጽ መረብ በርብረው የእዳ ጫና የተለያዩ ሃገራትን አዘቅት እንደሚከት ማስተዋልና ህዝብ ማስተማር ይመረጣል፣ ማስረጃ ሳይጠቅሱ መናገርና መፃፍ በዚህ ዘመን ያስተዛዝባል ለፖለቲካ እንጀራ ተብሎ ምንጩን ሳይጠቅሱ ወጣቶችን ማሳሳት ከተማረ ሰው አይጠበቅም፡፡ ብድር እንደ ችግር አይታይም ይላሉ ለምን አይታይም! የአሜሪካ አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት $15 ትሪሊን ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያ ጂዲፒ 69 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ነው ምኑን ከምኑ ነው የሚያወዳድሩት ሰማይና ምድር ነው የኢኮኖሚያቸው ልዮነት፡፡ ኢትዮጵያን ከአሜሪካ ጋር ማወዳደር አሁን ምን ይባላል!!! እይ ኤም ኤፍና የዓለም ባንክ ለመሠረተ ልማት ብድር አይሰጡም ያሉት ማስረጃ ይጥቀሱ፡፡ በአጠቃላይ ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን ለይተው ሙያዎን በሃቅና በማስረጃ ያቅርቡ እንላለን፡፡ ማሳሰቢያ ለሁሉም፡- የዶክተሬት መነሳነሶዎን ቢሰቅሉት የተሻለ ይሆናል!!! ለምን የዶክተሬት፣ የፕሮፌሰር፣ ሜጀር ጀነራል፣ ሌፍተናት ጀነራል፣ የቀድሞ አንባሳደር፣ የቀድሞ ህወኃት፣ ኢህአፓ፣ መኢሶን… አመራር ወዘተ የአበሻ የስልጣን ኮተት መቼ ይሆን ከዚህ ደሃ ያልተመረ ህዝብ ላይ ሸክሙ የሚወርድለት!!! ደብተራ ምሁራን ዘመኑ የአዕምሮ እንጅ የዲግሪና በሹመት ማሳያ መሆን የለበትም፣ እኔ ‹ሜጀር ጀነራል፣ አንባሳደር፣ ዶክተር› ነኝ! ሃሳቤን ተቀበል ለማለት ነው፣ በህብረተሰቡ ላይ ሽጉጥ እንደመምዘዝ ያስቆጥራል፣ ቤተሰቦዎ ያወጡሎት ደምስ ጫንያለው ምን አሎት፣ ይሄ መጥፎ ባህል መቀየር አለበት፣ ፈረንጆቹ ይሄን ማዕረግ አይጠቀሙበትም፡፡ አሁን ደግሞ ‹ዶክተር ኢንጅነር›፣‹ፕሮፌሰር ኢንጅነር›፣ ‹አንባሳደር ዶክተር› ወዘተ

ኢትዮጵያ ከሃገረ ግሪክ የዕዳ ጫና ትማር ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት፣ለማዓት!!!  በ2017 እኤአ የግሪክ መንግሥት በተዘፈቀበት 354 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ምክንያት የባህር ወደቦቹን፣ ኤርፖርቶቹንና ሜጋ ፕሮጀክቶቹን በዕዳ ጫና ምክንያት ለውጪ ኢንቨሰተሮች በፕራይቬታይዝ ተሸጠዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ስምምነት ባንክ፣ Bank for international Settlemets (BIS) በዓለም አቀፍ ስምምነት የግሪክ አበዳሪዎች የባህር ማዶና የሃገር ቤት አበዳሪዎች አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጅም፣ ካናዳ፣ ቺሊ፣ ቻይና፣ ቴፒ፣ ፊንላንድ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ኒዘርላንድ፣ ኖርዌ፣ ፖርቱጋል፣ ሲንጋፖር፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ስፔን፣ ሲዊድን፣ ሲዊዘርላንድ፣ ቱርክ፣ እንግሊዝ፣ እና አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ስምምነት ባንክ ለግሪክ መንግሥት ያበደሩትን ሪፖርት አደረጉ፡፡ የዓለም አቀፍ ስምምነት ባንክ ግሪክን ለእርድ አቅርቦ ቅርጫውን ለመቃረጥ ፊሽካ ነፋ፡፡  በሃገረ ግሪክ የህዝብ ኃብቶች የነበሩ የአውሮፕላን ማኮብኮቢያና ማረፍያዎች፣ የፍጥነት መንገዶች፣ የውሃ አገልግሎት፣ የኤሌትሪክ አገልግሎት፣ መንግሥታዊ ሪል እስቴቶች ወዘተ ለግሪክ አበዳሪ አገራቶች ፕራይቬታይዝ ተደረጉ፡፡ የኢትዮጵያ ሃገራችን የህዝብ ሃብትም ዕጣ ፈንታችን  ለቻይና መንግሥት በእዳ ጫና ምክንያት መሸጡ አይቀሬ መሆኑ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ቻይና ቻይና የሸተተ ልማት፣ ለቅኝ ተገዥነት!!!

{1} የአቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ ሄለኒክ ሪፓብሊክ አሴት ዲቨሎፕመንት ፈንድ አቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ለአቪአልያንስ የጀርመን ኤርፖርት ማኔጅመንት ካንፓኒ በ45 በመቶ ድርሻ  በ672 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጦል፡፡ በ2016እኤአ ጀርመን ካንፓኒ ሆነው  ፍራፖርት ስሌንቴል 14 የግሪክ የአይሮፕላኖች ማኮብኮቢያና ማረፍያዎች፣ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር ገዝተዋል፡፡ ስምምነቱ የዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ፍላጎት የመንግሥታዊ ኃብቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ብሎም የ86 ቢሊዩን ፓውንድ እዳ ለመክፈል የተደረሰ የአቴንስ ስምምነት ነበር፡፡ የፍራንክ ፈርት ኤርፖርት ኦፕሬተር ፍራፖርት በ1.23 ቢሊዮን ፓውንድ የ40 ዓመታት ሊዝ ኮንትራት ፈፅመዋል፡፡(On May 31, the Hellenic Republic Asset Developent Fund(HRADF), negotiated the extension of a contract giving control of 45 percent of Athens International Airport to AviAlliance, a German airport management company.  The bid was worth $ 672 million. In November 2016, another German company, Fraport-Slentel, gained control of 14 regional airports in Greece for $ 1.3 billion, including the country’s second largest facility in Thessaloniki.  That licence agreement expires in 40 years, according to the HRADF website.)

{2} የግሪክ የባቡር ካንፓኒ፣ የግሪክ የህዝብ ሃብት የነበረው ትሬን ኦኤስኢ ሙሉ እጅ ድርሻ ለጣሊያን መንግስታዊ ዘርፍ ለሆነው ባቡር ካንፓኒ በ50 ሚሊዮን ዶላር ተሰሸል፡፡ (The primary railway company, TrainOSE, was 100 percent acquired by an Italian government-owned railway company for $50 million in 2016.)

{3} የግሪክ ፒራኢዮስ የባህር ወደብ5 ለቻይና ኮስኮ የመርከብ ኮርፖሬሽን በ313 ሚሊዮን ዶላር ለሰላሳ ስድስት ዓመታት ሊዝ ኮንትራት  ተሸጠ፡፡(In 2016, Piraeus, the largest port in Greece, located in Athens, was sold to COSCO, a Chinese company, for $313 million in a deal that expires in 2052.)

{4} የግሪክ ቴሳሎኒኪ ወደብ፣ ፔኒዙላና የሮድስ ደሴት፣ ለጀርመን፣ ፈረንሳይና ግሪክ የግል ኢንቨሰተሮች በጋር ጥምረት በ67 በመቶ ድርሻ ወይም 259 ሚሊዮን ዶላር ኮንትራት ሽያጭ፣ ቴሳሎኒኪ ወደብን እስከ 2051 እኤአ ድረስ ሰምምነት አደረጉ፡፡ በ2014 እኤአ አስታየር ቮሊያግመንቲስ ፔኒዙላ ለአረብ ቱርኮች በ440 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ፡፡ የአሜሪካው ኮንስትራክሽን ካንፓኒ ኤም ኤ አንጄሊዲስ በ30 ሚሊዮን ዶላር የሮድስ ደሴትን ገዛ፡፡ የሮድስ ደሴት  ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ለግሪክ ካንፓኒ ቲኤን ኤጅን ስን ኢንቨስትመንት ሊሚትድ በ17 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ፡፡

{5} የግሪክ የውኃና ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ በሃገረ ግሪክ የህዝብ ኃብቶች የነበሩ፣ ቴሳሎኒኪ የውኃ አቅቦት ማከፋፈያ/ የውሃ አገልግሎት፣ እና የቁሻሻን በቱቦ የማስወገጃ አገልግሎት፣  የኤሌትሪክ አገልግሎት 17 በመቶ ድርሻ፣ ሄለኒክ ፒትሮሊም የ35 በመቶ ድርሻ ወዘተ ለግሪክ አበዳሪ አገራቶች ፕራይቬታይዝ ተደርገዋል፡፡ (Major utilities will privatized such as 23 percent of the Thessaloniki water supply and sewerage, and 11 percent of Athens’ water supply and sewerage. A bidder for 17 % of the Public Power Corporation, the electricity supply company in Greece. The fund is also exploring options to privatize 35 % of Hellenc Petroleum, the leading oil refiner and distributor in the country.)

{6} የግሪክ ፖስታ አገልግሎት፣ በሃገረ ግሪክ የህዝብ ኃብቶች የነበሩ፣ የፖስታ አገልግሎት መስሪያ ቤቶች፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ማሪናስና ኢግናቲያ ኦዶስ የተባሉ ለፈጣን መኪኖች አገልግሎት የሚውል 416 ማይልስ መንገድ 33 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ የሚያስተናግድና 54 በመቶ የግብርና እርሻ መሬትን የሚያስተናግድ ጎዳና ነው፣ ለግሪክ አበዳሪ አገራቶች ፕራይቬታይዝ ተደርገዋል፡፡ (Greece is now looking to privatize its postal system, dozens of major marinas and the Egnatia Odos Motorway, a 416- mile highway serving 33% of the Greece population and reaching 54 % of agricultural land.) (Source:-Desperate to escape debt, Greece is forced to sell off its major infrastructure, mortimerd / June 12, 2017 ) የግሪክ የእዳ ጫና ውድቀት የዓለም አቀፍ ፋይናንሻል ማርኬት አናግቶ ነበር፡፡  በ2016 እኤአ ግሪክን ለመጎብኘት 30 ሚሊዮን አገር ጎብኝዎች ገብተው ነበር፣ ከዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮኑ በአይሮፕላን የመጡ ነበር፡፡ በግሪክ የእዳ ጫና የተነሳ የስራ አጥ ቁጥር ከፍተኛ ሆኖል፡፡የግሪክ መንግሥት ድጋሚ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች መሳብ ግን እሰካሁን አልቻለም፡፡

የቻይና መንግስት ለታዳጊ አገሮች የሚሰጡት የመሠረተ ልማትና ሌሎች ብድሮችየቻይና መንግስት ለታዳጊ አገሮች የሚሰጡት ሁለት የብድር ዓይነቶች ሲኖሮቸው አንደኛው ኮንሴሽናል የባህር ማዶ የብድር እርዳታ (Concessionary loans) ይባላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተሻለ ምርጫ ለተበዳሪው (Preferential buyer’s credits) በመባል ይታወቃል፡፡

ሀ/ የቻይና መንግስት ኮንሴሽናል የባህር ማዶ የብድር እርዳታ (Concessionary loans) የቻይና መንግስት አስመጭና ላኪ ባንክ (Eximbank) (Chinese Export and Import Bank) በኩል ሁለት ዓይነት ብድሮች ለታዳጊ አገሮች ያበድራሉ፡፡ የኮንሴሽናል የባህር ማዶ የብድር እርዳታ ዋንኛ ገፅታዎች (1) ብድሩ በቻይና የገንዘብ ምንዛሪ renminbi (RMB) የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን በትንሹ የቻይና 20 ሚሊዬን አርኤምቢ (3 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር) ነው፡፡(2) ብድሩ የመካከለኛና የረጅም ግዜ ብድሮችን ሲያካትት፣ የብድሩ ግዜ ለሃያ ዓመታት ሲሆን የእፎይታ ግዜውም (grace period)  አምስት ዓመታት ነው፡፡ በእፎያታ ግዜት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ (principal) መክፈል አይችልም፡፡ (3) ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ (4) በቻይና መንግስትና በተበዳሪው መንግስት መካከል በብድሩ የሚሰራው ፕሮጀክት ይመረጥና ይፀድቃል፡፡ከቻይና ካንፓኒዎች መኃል የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር እንዲሰራ ይመረጣል፡፡ የብድሩ 50 እጅ ከመቶ የቻይና እቃዎች (Equipment,materials technology)ና አገልግሎቶችን ተበዳሪው መንግስት መግዛት ይገደዳል፡፡ በፊት ይሄ አሃዝ 70 በመቶ ነበር፡፡ (5) የብድሩ ስምምነት የሚከናወነው በሁለት መንግስታቶች መካከል ሲሆን በቻይና የንግድ ሚንስትር በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የገንዘብ ሚኒስትር ጋር በመሆን ከተበዳሪው አገር አቻ ሹማምንቶች ጋር የብድር ስምምነት ያደርጉና ይፈራረማሉ፡፡ የቻይና የባህር ማዶ እርዳታ ዲፓርትመንት የብድሩን  ስምምነት ሁኔታ፣ይደራደራል፣  ያመቻቻል፣ ይቆጣጠራል፡፡ ኤክስኢም ባንክ የብድሩን ስምምነት ያስፈፅማል፡፡

ለ/ የተሻለ ምርጫ ለተበዳሪው (Preferential buyer’s credits) ዋንኛ ዓላማው የቻይናን ኢኮኖሚ ማሳደግና የንግድ ግንኙነቶችን በቻይና መንግስትና በታዳጊ አገሮች መኃል ማጠናከር ነው፡፡ የብድሩን ዓይነት ዋነወኛ መገለጫዎች (1)ፕሪፈረንሻል የብድር ዓይነት ሁሌ የሚከናወነው በዩኤስ ዶላር ወይም በሌላ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ነው፡፡(2) የፕሪፈረንሻል ብድር ከኮንሴሽናል የብድር የገንዘብ አቅርቦት መጠኑ የላቀ ሲሆን ይህውም ከ200 እሰከ 500 ሚሊዬን ዩኤስ ዶላር ይሆናል፡፡(3) ብድሩ የመካከለኛና የረጅም ግዜ ብድሮችን ሲያካትት፣ የብድሩ ግዜ ለአስራ አምስት ዓመታት ገደብ አለው፡፡ (4) ተበዳሪው የተበደረውን ሁሉንም ገንዘብ ከቻይና መንግስት  እቃዎችና አገልግሎቶችን መግዛት ይገደዳል፡፡ እንዲሁም ተበዳሪው 15 በመቶ የሚሆነውን ወጭ በቅድሚያ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ኤክስኢም ባንክ የብድር የፕሮጀክት ወጭ 85 በመቶ ያበድራል፡፡ ከእነዚህ የፕሮጀክት ዓይነቶች መኃል የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙትን በጥናትና ምርምር በመምረጥ ከነዚህ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ኢነርጂ፣ትራንስፖርት፤ቴሌኮምንኬሽን፣ ማኑፋክቸሪንግ/የምርት ሂደት እና የግብርናው ዘርፎች ይካተታሉ፡፡(5) ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በተዋዋለው  ወለድ መጠን ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ በእፎይታ ግዜያት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ መክፈል አይችልም፡፡   (6) የብድሩ ስምምነት የሚከናወነው በቻይና መንግስት አስመጭና ላኪ ባንክ (Eximbank) ( Chinese Export and Import Bank) እና በተበዳሪው መንግስት ሚንስትር ባለስልጣን መካከል ሲሆን የተበዳሪው አገር የንግድ ሚንስትር ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የገንዘብ ሚኒስትር ጋር ኤክስኢም ባንክ የብድር ስምምነት ያደርጉና ይፈራረማሉ፡፡ ቻይና ለኢትዬጵያ ከምትሰጠው እርዳታ በአመዛኙ በእርዳት ሰጭው ፈቃድ ላይ የተመሠረተ (ብድሩ 25 በመቶ እርዳታ ለኢትዬጵያ የተሰጠ ሲሆን) ስራው ሙሉ በሙሉ የሚሰራው በቻይና መንግስታዊ የግንባታ ድርጅቶችነው፡፡  ለምሳሌ ያህል በ2003 የተገነባው የአዲስ አበባ ቀለበት መንገዶች ልብ ይላሉ፡፡

{1} የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርጅት፣ አይሮፕላኖቹን እያስያዙ ከተለያዩ ባንኮች የሚያደርጎቸውን የውጭ ብድሮች ቀጥለን እንመልከት፡፡ በ2008 እኤአ ስምንት ቦንባርዲየር ኪው 400 አይሮፕላኖች 242 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር፣በ2010እኤአ አስር ቦይንግ 737-800 አይሮፕላኖች  767 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ዋጋ ለመግዛት ተስማምተዋል፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ1.6 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለአስር ቦይንግ ድሪም ላይነርስ አበድሮል፡፡ በ2011 እኤአ አራት ቦይንግ 777ኤፍ አይሮፕላኖች በ1.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለመግዛት ስምምነት ተፈፅሞል፡፡ በ2012 እኤአ አምስት ኪው 400 አይሮፕላኖች   160 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለርና ተጨማሪ አንድ ቦይንግ 777-200ኤልአር አይሮፕላን  276 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር  ለመግዛት ስምምነት ተደርጎል፡፡ በተለያየ ግዜትም የተገዙት አይሮፕላኖች ወደ አገር ውስጥ ገብተዋል፡፡በ2013 እኤአ ኤር ሊዝ ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ 777-300 ኢአር አይሮፕላኖች ለመከራየት  ተስማምተው፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ130 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ  ብድር አበደረ፡፡ በ2014 እኤአ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 20 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላኖች  የ2.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከዩኤስ አቪየሽን ጋር ስምምነት አደርገዋል፡፡ በተጨማሪም አስራአምስት 737 ማክስ 8 ነዳጅ ቆጣቢ አይሮፕላኖች ለመግዛት ስምምነት ፈፅመዋል፡፡በአጠቃላይ ከ 2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000, 000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (104,599,294,400 ቢሊዩን ብር) አይሮፕላኖች ለመግዛት የውጭ ብድር ተበድሮል፡፡ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ አይሮፕላኖቹን 1,730,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (32,267,614,000 ቢሊዩን ብር) በማበደር የአንበሳውን ድርሻ በመያዝ የኢትዬጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች በወለድ አግድ collatoral በመያዝ እንደሚያበድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርጅት የውጭ ብድር በተመለከተ ብቻ የቀረበ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ብድር ከተለያዩ ባንኮች የተበደሩትን እንደማይጨምር አንባቢ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ 2012እኤአ የኢትዩጰያ  የአገር ውስጥ ብድር 45.5 ፐርሰንት ከዓመታዊ አጠቃላይን ብሔራዊ ምርት የነበረ ሲሆን የውጭ ብድር 10 ፐርሰንት ከዓመታዊ አጠቃላይን ብሔራዊ ምርት የያዘ ነበር፡፡“Ethiopia has huge unsustainable internal and external debts strongly discourage opening up a business. It is unsettling to invest in a country that can not manage its finances, and has it’s economic potential stifled by the need to pay debts. …. As of 2012 Ethiopia’s internal debt was 45.5 percent of GDP, it’s external debt was 10 percent of it’s GDP. “McKEEVER INSTITUTE of ECONOMIC POLICY ANALYSIS, Web address: http://www.mkeever.com ይመልከቱ፡፡ለግንዛቤ እንዲረዳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2012 እኤአ Revenue (አጠቃላይ ትርፍ) 33.815 ቢሊዩን ብር(1,812,961,752 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር)፣Net income (የተጣራ ገቢ) 1.049 ቢሊዩን ብር(56, 241,221 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር)፣Profit (ትርፍ) 2.031 ቢሊዩን ብር(108,890,295 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር)፣Total assets (አጠቃላይ ንብረት) 26.368 ቢሊዩን ብር(1,413,697,338 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር)ና Total equity (አጠቃላይ ንብረት ሁሉም እዳ ከተከፈለ በኃላ የሚቀረው የድርጅቱ ንብረት) 2.772 ቢሊዩን ብር (148,618,364 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር)እንዳለው አስታዉቆል፡፡1 ዩኤስ ዶለር 18.6518 ኢትዮጵያ ብር የተሰላ ነው፡፡ የኢትዬጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት ለዚህ መልስ ቢሰጡበት ብቃታቸውን ያሳዩበታል ድርጅቱ የተበደረውን ብድር ለህዝብና ‹ለፓርላማ እንደራሴዎች› ማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

{2} የኢትዬጵያ ንግድ ባንክ፣ ዲሴንበር 6/2011እኤአ  የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ( Chinese Export and Import Bank)ለኢትዬጵያ ዩኤስ 400 ሚሊዩን ዶለር (6.9 ቢሊዬን ብር) ሁለት  የብድር ስምምነቶች አድርገዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የባንኩ ምክትል ፕሬዜዳንት ዘሁ ሆንጃይ( Zhu Hongjie) እንደገለጹት ባንኩ 1.81ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(31ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡አንዱ ስምምነት ባንኩ 100 ሚሊዩን ዶለር ለአዲስ አበባ የውሃ ሥራዎች አቅርቦት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ጋር 300 ሚሊዩን ዶለር የባንኩን የብድር አቅርቦት ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ተዘግቦል፡፡ ዘሁ ሆንጃይ እንደገለፁት ከሆነ ባንኩ እስካሁን 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር አበድሮል ብለዋል፡፡

{3} ኢትዮቴሌኮም፣ በአጠቃላይ፣ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ጋር የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም ከኢትዩጵያ የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ እንደሚወራረድ ይታወቃል፡፡

{4} የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል፣ 5 ቢሊዩን 490 ሚሊዬን ዶላር ብድር እንዳለበት ጥናቱ ያሳያል፡፡ የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል1.2 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከኢትዬጵያ መንግስት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር IFIs/Government to Sector Institutions on-lending የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሹማምንት ጋር ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቆማቶች መኃል (የዓለም ባንክ ዓለም ዓቀፍ ልማት ትብብር( International Development Association (IDA)፣ የአፍሪካ የልማት ባንክ African Development Bank(AfDB)፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ  European Investment Bank (EIB) etc.) ኮንሴሽናል ብድር (Concessionary loans) ለኤሌትሪክ አገልግሎት ዘርፉ አበድረዋል፡፡ኮንሴሽናል ብድር ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ ብድሩ የመካከለኛና የረጅም ግዜ ብድሮችን ሲያካትት፣ የብድሩ ግዜ ለሃያ ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ የብድሩ የእፎይታ ግዜ (grace period)  አምስት ዓመታት መሆኑና፡፡ በእፎይታ ግዜት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ (principal) መክፈል አይችልም፡፡ ሦስተኛ ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ ከ3 እስከ 6 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡

በ2002 እኤአ በሲኖ ሃይድሮ ኮርፖሬሽን (Sino Hydro Corporation) በ224 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር  የተከዜ ሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ፖሮጀክት/ ግድብ በተከዜ ወንዝ ላይ  በ2007 ዓ/ም ለማጠናቀቅ ታቅዶ በመሬት መንሸራተት ችግር ምክንያት ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው በ2009 ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ስራው(ፕሮጀክቱ ወጭ) 365 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲደርስ 300 ሜጋ ዋት ያመነጫል ቢባልም 75 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭ ይታወቃል፡፡ በጁላይ 2009 እኤአ ኢትዬጵያ ከቻይና  በሲኖ ሃይድሮ ኮርፖሬሽን ተጨማሪ የስምምነት ፊርማዋን በማኖር 2150 ሜጋ ዋት ሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ፖሮጀክት በጊቤ አራት (በኦሞ ወንዝ)ና ሃሌሌ ወራቤሳ ግድብ ለመስራት 2.67 ቢሊየን  ዩኤስ ዶለር  ተስማማች፡፡ ቻይና 85 በመቶ ፕሮጀክቱ ወጭ የምትሸፍነው (through preferential buyer’s credit and concessionary loans) በመስጠት ነው፡፡ ቻይና ለኢትዬጵያ ዩኤስ 1 ቢሊዩን ዶለር(18,180,000,000 ቢሊዩን ብር) ብድር በአፕሪል 27/2013 ሰጠች፡፡ ብድሩም ከአዲስ አበባ ወደ ህዳሴ ግድብ የኤሊትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማገናኘት  እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የህዳሴው ግድብ  ዩኤስ 4.1 ቢሊዩን ዶለር( 74,538,000,000  ቢሊዩን ብር) በምዕራብ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገነባ ግድብ ሲሆን 6000 ሜጋዋት የሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ያመነጫል ተብሎ ይገመታል፡፡ በአጠቃላይ ቻይና በአፍሪካ አህጉር ላይ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት በማድረግ የቻይና ካንፖኒዎችም የግንባታውን ሥራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ዋናው ትኩረታቸውም የታዳጊ አገሮች ጥሬ እቃዎች ማዕድናቶች፣(ብረት፣ወርቅ አልማዝ)፣ቤንዚን፣የግብርና ዘርፍ ምርቶች(ቡና፣ሰሊጥ፣ካካዎ ወዘተ)፣መያዣ ለአበደሩት ገንዘብ እዳ ዋስትና( Collateral) በመያዝ አዲስ ዓይነት የረቀቀ ዘረፋ ከአንባገነን የአፍሪካ መሪዎች ጋር በመመሳጠር የስብአዊና ዴሞክራሲያዊ  መብቶች ረገጣን እዕያዩ እንዳላዩ በመሆን አሰቃቂ ምዝበራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ቻይና በህዝቦ ላይ የስብአዊና ዴሞክራሲያዊ  መብቶች በመርገጥ ከስልሳ አምስት አመታቶች በላይ የቻይና ካምኒስት ፓርቲ በብቸኝነት በስዩመ እግዚአብሄር መንግስትነት የሚገዛበት አገር ነው፡፡ ኢትዬጵያ በህወሃት/ ኢህአዲግ መንግስት ከ1991 እኤአ እስከ 2013 እኤአ ባለ 22 ዓመታት ውስጥ 1,550 ሜጋዋት የሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ብቻ ማመንጨ~ ይታወቃል፡፡ በደርግ ዘመን 750 ሜጋዋት ጋር ሰደመር  2,300 ሜጋዋት ደርሶል፡፡ የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ( Chinese Export and Import Bank)ለኢትዬጵያ ዩኤስ 500 ሚሊዩን ዶለር(9,090,000,000   ቢሊዩን ብር) የብድር ስምምነት አድርጋለች ገንዘቡም ለ15 የልማት ፖሮጀክቶች  ግንባታ  ላይ ለማዋል ታቅዶል፡፡ ኢትዬጵያ የአምስት አመት  ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት ለሃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ግንባታ፣ ለፈርትላይዘር(ማዳበሪያ) ፋብሪካዎች፣ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታ፣ለ2000ሽህ ኪሎሜትር የባቡር መሥመር ዝርጋታና ለመንገድ ሥራ ግንባታ እንደሚውል ታውቆል፡፡ ይህ ስምምነት የተፈፀመው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ቻይናን በጎበኙበት ግዜ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ቻይና ለኢትዬጵያ ዩኤስ 4 ቢሊዩን ዶለር (72,720,000,000 ቢሊዩን ብር) ብድር በቴሌኮምኒኬሽንና ለመንገዶች መሰረተ ልማት ፖሮጀክቶች ግንባታ ብድሩ እንደሚውል ተገልፆል፡፡ በኢትዬጵያ ውስጥ ከ20000 በላይ የሚሆኑ ቻይናውያንም በተለያዩ የግንባታ ዘርፎች ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ  ታዉቆል፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀን አራት ሽህ ቻይናውያን ይስተናገዳሉ፣ ዶላር ይዞ በመውጣት የተካኑ ናቸው፡፡

{5} የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣ የወንጂ ሸዋ ፣የመተሃና የፊንጫ ስ£ር ፋብሪካዎችን ጠቅልሎ በመያዝ በበላይነት እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ኮርፖሬሽኩ በደቡብ ክልል ሰባት፣ በአማራ ክልል ሦስት፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል አንድ (የአፋር ክልልን መሬት) ፋብሪካን ጨምሮ በድምሩ 12 አዳዲስ ስኮር ፋብሪካዎችን የክልሎችን መሬት በፌዴራል መንግስት ስም በመንጠቅ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን 500 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከቻይና ልማታ ባንክ (China Development Bank Corp.)  ጋር ተፈራረመ፡፡ ባንኩ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ መንግስታዊ ንብረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን በብድሩ ሁለት ትልልቅ የስኮር ድፍድፍ ማጣሪያዎች ፋብሪካዎች ይገነባል፡፡  አንዱ ፋብሪካ በደቡብ ኢትዮጵያ ኦሞ ዞን ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ሁለተኛው ፋብሪካ በሰሜን ምዕራብ አፋር ክልል ውስጥ በሜታል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያዊ መንግስታዊ ድርጁትና በቻይና ኮምፕላንት ግሩፖ ኢንክ (China Complant Group Inc) የሚገነባ ሲሆን ምርቱን በ2025 እኤአ አስር እጥፍ ለማድረግ ታቅዶል፡፡ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን የወንጂ ሸዋ ፣የመተሃና የፊንጫ ስካóY ፋብሪካዎችን ጠቅልሎ በመያዝ በበላይነት እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ኮርፖሬሽኩ በደቡብ ክልል ሰባት፣ በአማራ ክልል ሦስት፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል አንድ(የአፋር ክልልን መሬት ወደ ትግራይ ክልል በመከለል የተወሰደ መሆኑን ልብ ይሎል)  ፋብሪካን ጨምሮ በድምሩ 12 አዳዲስ ስካóY ፋብሪካዎችን የክልሎችን መሬት በፌዴራል መንግስት ስም በመንጠቅ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡አስራ ሁለት  የሸንካራ አገዳ እርሻና ፋብሪካዎች በመገንባት የስካóY ምርትን አሁን ካለው ምርት 265000 ሽህ ሜትሪክ ቶን ወደ 2.3 ሚሊዩን ሜትሪክ ቶን ከፍ በማድረግ ወደ ውጭ ሃገራት በተለይ ለአፍሪካ ቀንድ አገራት ለመላክ ሲሆን አገሪቶን በ2025 በዓለም ካሉት አስር የስ£ር ላኪ አገሮች ጎራ ለማስገባት በሚል የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ተወጥኖል፡፡ የኢትዮጵያ ስ£ር  ኮርፖሬሽን አጠቃላይ የግንባታ ስራ ወጭ 100 ቢሊዩን ብር (5.5 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር) እንደሚሆን ሲገመት ማሽነሪዎች ለመግዛት ግማሹ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይሻል፡፡ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል ትንዳሆ 30 በመቶ ምርት በማምረት ላይ ሲገኝ በአሁኑ ግዜ በ394 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከህንድ አስመጭና ላኪ ባንክ(Export-Import Bank of India) በተገኘ ብድር የፋብሪካው ግንባታ ሥራ በህንድ(India’s Overseas Infrastructure Alliance) በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን በጥናት ላይ የተመሰረተ ሥራ እንደማይሰራ በምሁራኖች ዘንድ ይታወቃል፡፡ የምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ የንግድና ልማት ባንክ (ፒቲኤ ባንክ) ለኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን 25 ሚሊዮን ዩኤስ ዶለር ብድር ስምምነት አርጎ ፡፡

{6} የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣  በዳግማዊ ሚኒሊክ ዘመነ መንግሥት፣በ1897 እና 1917 እኤአ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የባቡር ሃዲድ መስመር ዝርጋታ በፍራንኮ-ኢትዩጵያ የምድር ባቡር በኃላም (Chemin de Fer Djibouti (CDE) በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር በ1917 እኤአ ለትራፊክ ክፍት በመሆን የሃገሪቱን የወጪና የገቢ ንግድ 90 በመቶ፣ እቃዎች በማጎጎዝ ላለፉት 60 አመታት ያለ አንዳች ኪሳራ አገልግሎል፡፡ በመለስ ዜናዊ ዘመን፣ የባቡር ሃዲድ መስመር ዝርጋታ፣ በሃገሪቱ 2,395 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ማለትም ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስድ አዲስ የኤሌትሪክ የባቡር ሃዲድ መሥመር ዝርጋታ፣ ከመቐለ ታጁራ ወደብ የባቡርና  በአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞችን የሚያገናኝ ባቡር አገልግሎት፤ ለማስፋፋት ያለ ጥናት በእቅድ ተኮቶ ነበር፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 2006 እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር (በ2014 እኤአ) ‹‹የቻይና እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች  ሊ ኢቺያንግ ና ኃይለ ማርያም ደሣለኝ በተመራው የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ የመንግስትና የቢዝነስ አመራሮች ለኢትዩ-ጂቡቲ የባቡር መስመር ሐዲድ ዝርጋታ የሚውለውን ሦስት ቢሊዩን ዶላር ቻይና ብድሩን ለመልቀቅ ተስማማች፡፡ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቀላል የባቡር ሐዲድ መስመር ዝርጋታ፣ ከድሬዳዋ ወደ ደወሌ (ጂቡቲ ጠረፍ) ለሚገነባው መንገድ፣በአጠቃላይ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያለበት ብድር 5 ቢሊዩን 4 ሚሊዩን ዶላር ብድር ሥራው ተጠናቆል፡፡ “In 2012 China Civil Engineering Construction Corp.and China Railway Group Ltd. are working on sections of the 656 kilometer trade route connecting Addis Ababa to Djibouti at a cost of over 1 billion USD each.’’…“Until 2015 Ethiopia is building 4,744 kilometers of electrified railway lines at a cost of 5.9 billion USD 110.8 billion birr/ to satisfy transport demands in the country.”

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ ግንባታ በአራት አቅጣጫዎች እየተገነባ ሲሆን፤በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡ ለግንባታው ወጭ 475 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን፣ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በብድር የተገኘ ሲሆን 15 በመቶው በኢትዩጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ በባቡር መሰመሩ ላይ 39 መንገደኞች መሳፈርያና መውረጃ ጣቢያዎች፣እንዲሁም 27 የእግረኛ ማቆረጫዎች ይገናሉ፡፡ የአንዱ ባቡር ርዝመት 28 ነጥብ ስምንት ሜትር ሲሆን ጎን ስፋቱ 2 ነጥብ 65 ሜትር ነው፡፡ ባቡሩ በሰዓት 70 እስከ 80 ኪሎሜትር መጎዝ ይችላል፡፡ ባቡሩ በአንድ ግዜ 60 ሸህ መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚችል ታውቆል፡፡ በተመሳሳይ ከፈረንሣይ መንግሥት 35 ሚሊዩን ዩሮ ብድር፣ ለአዲስ አበባ ፈጣን የባቡር መስመር ግንባታና አውቶብሶችን ለማስገባት ተጨማሪ 35 ሚሊዩን ዩሮ ብድር ከፈረንሣይ መንግሥት ተገኘ፡፡ ከፈረንሣይ የልማት ኤጀንሲ 50 ሚሊዩን ዩሮ ባለፈው ዓመት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ተጨማሪ የ35 ሚሊዩን ዩሮ ብድር ስምምነት እንዲፀድቅ ለፓርላማ ቀርባFል፡፡ ፈጣን የአውቶብስ መስመር ግንባታ በዊንጌት-ጎፋ ገብርኤል አድርጎ እስከ ጀሞ የሚዘልቅ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ወጪ 101.6 ሚሊዩን ዩሮ ነው፡፡ ከፈረንሣይ የተገኙ ሁለቱ ብድሮች 85 ሚሊዩን ዩሮ የሚሆነውን ወጪ ይሸፍናሉ፡፡ የተቀረው 16.6 ሚሊዩን ዩሮ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚሸፍን ያመለክታል፡፡ ለአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት 34 ኪሎ ሜትር ሲሸፍን፤ ከአዲስ አበባ ምስራቅ ወደ ምዕራብ እንዲሁም ከሰሜን ወደ ደቡብ የባቡር ሐዲድ መስመር በመዘርጋት ነው፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ 475 ሚሊዩን ዶላር እንደሚሆን ይገመታል፤ከጠቅላላው የፕሮጀክቱ ወጪ 85 በመቶ የተገኘው ከቻይና መንግስት በብድር ነው፡፡

ከምድረ ደቡብ ሱዳን የዕዳ ጫና እንማርየቻይና መንግሥት 29 ቢሊዮን ዶላር ብድር የገነባው የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ምርት ማጣሪያ ፋብሪካ፣ ነዳጅ ማከፋፈያና ማሰራጨት በጀመረ ማግስት በነዳጅ ገንዘብ ገቢ የሰከሩት የጦር አበጋዞች ሳልቨኬርና የኑዌሩ ሬክ መቻል የጎሳ ተኮር ጦርነት ጫሩና ነዳጅ ላይ አርከፈከፉበት፣ ደሃው ህዝብ እንደ ትንኝ ረገፈ፣ ቆሰለ፣ ተሰደደ፡፡ የቻይና መንግሥት ቀልዱት ተውት በማለት አስር ሽህ በላይ የቻይና ሁለገብ ሠራዊት፣ የአየር ኃይል፣ የአየር ወለድ፣  የባህር ኃይል፣ ታንከኛ፣ መድፈኛ፣ ኮማንዶ ጦር በምድረ ሱዳን አፈሰሰ የነዳጅ ማጣሪ ፋብሪካና ማከፋፈያና ማሰራጫ እስከ ወደብ የተዘረጋውን የነዳጅ ቦንቦ የቻይና ሠራዊት በመቆጣጠር ነዳጅን በቻይና የነዳጅ መርከቦች እየጫኑ ወደ ቻይና እብስ እያሉ ምልስ፣ ማለት ጀመሩ፡፡ የቻይና ጦረኞች የነዳጅ ማስተላለፊ ቦንቦውን በቻይና የሲሲቲቪ የስለላ ካሜራ በመሰለልና ሥፍራው በኤሌትሪክ ጨረር በመታጠሩ ሥራውን ማስተጎጎል ከንቱ ዘበት መሆኑን የደቡብ ሱዳን የጦር አበጋዞች ተረዱ፡፡ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ውስጥ የቻይና መንግሥት በቀለ!!! በአፍሪካ አህጉር፣ በመንግሥት ውስጥ መንግስት እንደ ብቅል አበቀለ፡፡ በምድረ ሱዳን እስካሁን ጦርነት ይካሄዳል፣ ህዝብ ያልቃል፣ ይቆስላል፣ ይሰደዳል፣ የአፍሪካ ሰላም አሰከባሪ ጦር ሠፍሮል፣ ቻይናም በጦርነት መኃል የሱዳን ምድር ጡቶች የሚያመነጩትን ቤንዚን ይጠባሉ፡፡ የቻይና መንግሥት ሁለቱን ወገኞች ከማስታረቅ ይልቅ ተጨማሪ የጦር መሣሪያ ለሁለቱም በመሸጥ ተጨማሪ ጥቅም ያጋብሳል፡፡  ጦርነትና ወንጀል ባለበት ቦታ ሁሉ ትልቅ ሃብትና አዱኛ አለ የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ የቻይና መንግሥት በጅቡቲ ወደቡ ከፍተኛ የጦር ሠፈር በመገንባት የአየር ኃይል፣ የአየር ወለድ፣  የባህር ኃይል፣ ታንከኛ፣ መድፈኛ፣ ኮማንዶ ጦር ለአፍሪካ አህጉር የሚበቃ  ጦር ሰብቆል፣ ልብ ያለው ልብ ይበል እንላለን፡፡ ለደቡብ ሱዳን የደረሰ ኢትዮጵያ ላይ አይደርስም ብሎ ማሰብ ከንቱነት ነው በዘር ላይ የተመሠረተ ልዩነታችንን እናጥፋ፣ ኢትዮጵያውያን የጋራ አገራችን ናትና፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጅ  ዘመን   ወጣቶች ‹‹ ዘር ቆጣሪ! አጥር አጣሪ!››በሉ፣ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ እንዳሉት፡፡

የቻይና መንግስት ለኢትጵያ ከ11.4 ወደ 17.6 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር አበድሮል፣ ዲሴንበር 6/2011እኤአ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት  የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ( Chinese Export and Import Bank) ለኢትዮጵያ ዩኤስ 400 ሚሊዩን ዶለር (6.9 ቢሊዬን ብር) ሁለት  የብድር ስምምነቶች አድርገዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የባንኩ ምክትል ፕሬዜዳንት ዘሁ ሆንጃይ( Zhu Hongjie) እንደገለጹት ባንኩ 1.81ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(31ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡አንዱ ስምምነት ባንኩ 100 ሚሊዩን ዶለር ለአዲስ አበባ የውሃ ሥራዎች አቅርቦት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር 300 ሚሊዩን ዶለር የባንኩን የብድር አቅርቦት ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ተዘግቦል፡፡ ዘሁ ሆንጃይ እንደገለፁት ከሆነ ባንኩ እስካሁን 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(272.2 ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግሥት ብቻ የተበደረችው ዕዳ 17 ቢሊዩን ዶላር በላይ መሆኑ ይታመናል፡፡ Meles on the occasion lauded the Chinese government and the banks for their contribution towards success of Ethiopia’s development endeavours. The Premier also said the relation between the two countries is laid on firm foundation and expressed Ethiopian government’s commitment to further work in collaboration with China. Zhu Hongjie on his part said the bank will further strengthen existing relation with Ethiopia as the country has registered sustainable growth during the last eight years. The bank has provided 11.4 billion USD loan for implementation of various development projects in Ethiopia, he said.

በ2007 እኢአ የኢትዬጵያ የፌዴራል መንግስት ባጀት 178.6 ቢሊዩን ብር ሆኖ በፓርላማ እንደፀደቀ ሲገለፅ ከዚህም ውስጥ የአመቱ የውጭ ዕዳ ክፍያ 8.2 ቢሊዩን ብር እንደሆነ ተገልፆል፡፡ኢትዩጵያ ዕዳውን ለመክፈል በዓመት 8.2 ቢሊዩን ብር እየከፈለችና ሌላ ገንዘብ ሳትበደር እዳዋን ለመጨረስ ከ45 ዓመታት እስከ 68 አመታት ይፈጅባታል፡፡ በ2008 እኢአ የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ባጀት 223.3 ቢሊዩን ብር ከዚህም ውስጥ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሃገሪቱ ባጀት ትልቁን ድርሻ የያዘው፣ የአመቱ የውጭ ዕዳ ክፍያ 11.903 ቢሊዩን ብር እንደሆነና  ተገልፆል፡፡ የውጪ እዳ ክፍያው ከ2007ዓ/ም በጀት በ3,703,000,000 ቢሊዩን ብር ከፍ ብሎል፡፡ ሀገራችን አንድ ቢሊዮን ዶላር በሶቨሪን ቦንድ መበደሮን ልብ ይበሉ!!!

ቀጣይና ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስቀጠል ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመንገድ ሥራዎች ለመስራት፣ ግድቦችን ለመገንባት፣ ለመብራት መስፋፋት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ፣ ለባቡር ዝርጋታ እቅድና አፈፃፀማቸውን በደንብ መከታተል፡፡ የውጭ ንግድ ገቢ ከፍ በማድረግ በየጊዜው የእዳና ወለድ ክፍያን መፈፀም፡፡ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ዘዴዎችን ዘዴ ምርታማነት፣ጥራትና ተወዳዳሪነትን ማሻሻለል፡፡ የውጭ ኢንቨስተሮችንና ቱሪስቶችን መሳብ፣ የውጭ ዲያስፖራ ወገኞችን ተሳትፎና ዜጋዊ ክብር መስጠት፡፡ የመልካም አስተዳደር መዘርጋት ሙስናን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን፣ ህገወት የድንበር ዘለል ንግድና ኮንትሮባንድ ሥራዎችን ማጥፋት ያስፈልጋል፡፡ የወያኔ መንግሥት፣ የመንግሥትን ወጪ መቀነስ፣ በአጠቃላይ የመደበኛ በጀት ወጪን መቀነስ፣ እልፍ ሚሚስቴር፣  ሚሊዮን ሚኒስትር ዴኤታ ሚኒስቴር፣ አንድ ሸህ አንድ ጀነራል መኮንኖች፣ ስንትና ስንት መቶ አንባሳደሮች መሾም ምን ሰርተው በየትኛው ኢኮኖሚያችን ትከሻ ይሸከመዋል!!! በሬ ጠምዶ በሚያርሰው ገበሬ ነው የውጭ ምንዛሪው የሚገኘው የመንግሥት ሹመኞች ደም የህዝብ ደም ከመምጠጥ ሌላ ምን ፈይደው ያውቃሉ!!! ለዚች አገር ምን አበርክተዋል እንደ መዥገር የደሃውን    የተለያዮ የኢኮኖሚ ዘርፎች ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን በጥናት አስደግፎ መተግበር  አንድ እርምጃ ነው፡፡ መንግሥት ለበትን ብድር በአግባቡ እየተከታተለ መክፈል፣ አንድ ፕሮጀክት ተጠናቆ ሲያልቅ ሌላ መጀመር፣ የባንኮችን ሙያተኞች ከፖለቲካ የካድሬነት ሥራ መለየት  ነገ በእዳ ጫና ምክንያት ለቻይና መንግሥት ፕራይቬታዝ የሚሆኑ የህዝብ ሃብቶችን በጊዜው ዕዳ በመክፈል መከላከል ይቻላል፡፡

{0}  በአጠቃላይ ከ1991 እሰከ 2010 እኤአ በህወሃግ/ኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ፤ በህገወጥ መንገድ ከሃገር ውስጥ የወጣ ካፒታልና የንዋይ ኩብለላ 15,903.2 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ከኢትዬጵያ ረሃብተኛ ህዝብ ተሰርቆ ወደ ተለያዩ ባህር ማዶ ባንኮች ተቀምጦል፣ ይህን ገንዘብ ማስመለስና ዕዳችንን ለመክፈል፣ አስመላሽ የህግ አስመላሽ ኮሚሽን አቆቁሞ በዓለም አቀፍ ሸንጎ መሞገት፣ የሌቦቹን በሃገር ውስጥ ያለ ንብረት ማምከን አስፈላጊ ነው፡፡

{1}  በሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ የግብር ማጭበርበርና መደበቅ ሥራን መግታት፡፡ የተጀመረውን የሌብነትና የሙስና እንቅስቃሴና የታሰሩት ግለሰቦችና የተወረሰው ንብረት የህዝብ ሃብት ማድረግ፡፡ በፋይናንሻል ኢንቲግሪቲ ድርጅት፣ ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ  በሙስና ከዓለም 180 ሃገራት 107ኛ ደረጃ፣ እንዲሁም ከአፍሪካ ሃገራት 20ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሙስና ከመቶ 35 በመቶ ውጤት በማግኘት ወድቃለች፡፡ የውጭ እዳና ጫናን ሙስና እያለ የሀገር እዳና ብድር መክፈል አይቻልም፡፡ የጠቅላይ ኦዲተር ፅህፈት ቤት ሃላፊ፣ የጸረ- ሙስናውን ትግል በነጻነት እንዲመሩና በሃገሪቱ ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና፣ ኮንትሮባንድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገወጥ ግለሰቦችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ ኃላፊነት መስጠት፣ ከህግ በላይ ማንም ሰው መሆን እንደማይችል በተግባር መገለፅ አለበት፡፡ ሃላፊው በተደጋጋሚ ለፓርላማ ያቀረቡት የኦዲት ሪፖርት ድጋፍ ተሰጥቶት በፍርድ ቤት ፍትህ እንዲሰጥና የህግ ተፈፃሚነት ተግባራዊ ማድረግ፡፡ ሙስና፣ ኮንትሮባንድ ንግድና ኪራይ ሰብሳቢነት ህገውጥ ሥራ ከነሰንኮፉ ነቅሎ መጣልና የአይነኬ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ንብረታቸውና ሃብታቸው በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማስመዝገብና የሃብትና የንብረት ምንጫቸው ለህዝብ ማሳወቅ ግድ ይላል፡፡ የሹሞች የህክም ወጪ በውጭ ምንዛሪ ይቁም!!!

{2} በፕራይቬታይዜሽን የተሸጡ የህዝብ ሃብቶችና ንብረቶች የእርሻ ቦታዎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሆቶሎች፣ ወዘተ በጸረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ እንዲካሄድባቸው ማድረግ፣  የከተማና የገጠር የመሬት ቅርምት፣ የእርሻ መሬት፣ የሪል ስቴት መሬት፣ የአበባ መሬት፣ ወዘተ ህገወጥ የሙስና ተግባር፣ ህዝብ የተሳተፈበት የማጋለጥ ሥራ በመገናኛ ብዙሃን ሬዲዮ፣ ቴሌቪዝን፣ ጋዜጣ ፣ ኢንተርኔት ይፋ ማድረግ

{3} የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃብትና ንብርት የሆኑ ድርጅቶች የህወሓት ኢፈርት፣ የብአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ ዲንሾ እንዲሁም የደህዴን ወንዶ የንግድ ድርጅቶች ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ የአገልግሎት ሰጪ የንግድ ድርጅቶች፣ የመድሃኒት ፋብሪካ፣ የማዳበሪያ፣ የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ወዘተ የፓርቲ የንግድ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍና ተቆማት  ያለው የሙስና ተግባር ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን ተሸጠው የህዝብ ሃብት ማድገር፣በተለይ የማዕድን ሃብቶች የለገደንቢ፣ ሳካሮ፣መተከል፣ ኢዛና የወርቅ ማዕድኖችን የህዝብ ሃብት በማድረግ አልያም በአክሲዮን ለህዝብ 49 በመቶ ለመንግሥት 51 በመቶ በመሸጥ፣ በዓመት ከ3 እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር በውጪ ንግድ ሃነሪቱ ገቢ ማግኘት ትችልለች፡፡

{4} በግብርና እርሻ ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ የቡና፣ ሠሊጥ፣ ቦለቄ፣ ጫት ወዘተ የቀንድ ኃብት፣ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በማበረታታት አስፈላጊውን ለግሉ ዘርፍ እሴት ጨምረው ቡና ቆልቶ ፈጭቶ አሰሽጎ በመላክ፣ ሠልጥ ጨምቆ ዘይት አርጎ በመሸጥ በዓመት ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር እሴት በመጨመር ገቢ ማግኘት ይቻላል፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉንም በጨርቃጨርቅ በሃገር ልብስ፣ የሽመና ስራ፣ በቆዳ ሥራ ወዘተ እሴት ጨምሮ መሸጥ፡፡ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን አገር ጎብኝዎች በመሳብ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መሞከር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር በሠራተኛው የተጠላ፣ ሥራን ከወያኔ የፖለቲካ የካድሬ ሥራ ማላቀቅና ለሁሉም ዜጋ እኩል የሚያረግ ዘመናዊ ከዘር የፀዳ አስተዳደር መዘርጋት፡፡

{5} የፋይናንሻል ዘርፍና ተቆማት በመንግሥት ባንኮችና የግል ባንኮች፣ በማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ያለው የሙስና ተግባር ብድር በመስጠት፣ በመሰብሰብ፣ በውጭ ምንዛሪ፣ ለመንግሥት፣ ለክልሎች፣ ለግለሰቦች በአድሎ የተደረጉ ሥራዎች ተጋልጠው እንዲወጡ ማድረግ፤ የህወሓ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች ንብረት የሆኑት ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማት ተወርሰው ፣ ባንኮቹ ለህዝብ በአክሲዮን እንዲሸጡ ማድገር፣

{6} የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የመከላከያ ሠራዊት የብረታብረት ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ቁጥጥር ሥር ያሉ የሲቪል የግሉ ዘርፍ ሊሰሮቸው የሚችሉ ፋብሪካዎቸ ተወርሰው ለህዝብ በአክሲዮን እንዲሸጡ ማድረግ፡ ሜቴክ ከንግዱ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ መውጣት ይኖርበታል፡

{7} የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች ቤት እያከራዩ የመንግሥት ቤት ውስጥ የሚኖሩ በአስቸኮይ እንዲወጡ፣ እንዲሁም ቤት እያከራዩ በቀበሌና በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች ተጣርቶ እንዲለቁ ማድረግ፣ የመንግሥት ቤት ካርታን በስማቸው ያዞሩ ሹሞች ማጋለጥና ለፍርድ ማቅረብና ንብረቱን ማስመለስ፡፡ በተመሳሳይ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንትና የጦር መኮንኖች የመንግሥት መኪና ከአንድ መጠቀሚያ በስተቀር ሌሎቹን ማስመለስ ያስፈልጋል፡፡ የቅንጦት የመንግሥት መኪኖች ግዥ ማቆም ያሉትንም ለግሉ ዘርፍ እንዲሸጡ ማድረግ፣ የቅንቶት ዕቃዎች መኪናዎች፣ ሽቶ፣ ትንቦሆ፣ መጠጦች፣ ምግቦች ወዘተ ከውጪ በውጪ ምንዛሪ የሚገቡትን እገዳ ማድረግ ለአንድ ደሃ አገር የህልውና ጥያቄ ነው፡፡

{8} የህወሓት/ኢህአዴግ የሲቪልና ወታደራዊ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ሠራተኞች የጡረታ እድሜ 55 ዓመት እንዲሆን መወሰንና ለመጭው ትውልድ ለመተካትና የሥራ ዕድል መፍጠር አስፈላጊ፣ በሁሉም ፖለቲካ ጎራ የሚገኙ ፖለቲከኞችም ጡረታ ይውጡ፡፡ የወሬ ምርት በቃ!!!

{9} የህወሓት/ኢህአዴግ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተቆቆሙ የሚንስትሪዎች፣ ፅህፈት ቤቶች፣ ኤጀንሲዎች፣ ድግግሞሽ መንግሥታዊ መዋቅሮች ተጠንተው እንዲታጠፉ ማድረግና የመንግሥት መደበኛ ወጪ 82 ቢሊዮን ብር (ደሞዝ፣ አበል፣ ነዳጅ፣ ልዮ ልዮ ወጪዎች፣ ወዘተ) ቅነሳ ማድረግ፣ክልሎች ግብር የመሰብሰብ አቅማቸውን ማጠናከርና በሰበሰቡት ልክም ሠራተኛ መቅጠርና የፌዴራል መንግሥት የክልል ድጎማ ማቆም፣

{10} በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ሑለት ሦስት የመንግሥት ቦታ የወሰዱ የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት፣ የጦር መኮንኖች፣ ካድሬዎች ለመሬት ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ፡፡ ሜድሮክ አጥሮ የያዛቸው 11 ቦታዎች ካርታ ማምከን!!! በ‹‹ልማት ተነሺ›› በማለት የሚነሱ ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት ይቁም፡፡ በግፍ የተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው ካሳና ቤት እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡ በሙስና ሁለት ሦስት የኮንዶሚኒየም ቤቶች የተሰጣቸው ግለሰቦች እንዲመልሱና ተጀምሮ የነበረው የኮንዶሚኒየም ቆጠራ፣ የህዝብ ሃብት እንዲጠናከር ማድረግ፡፡ የቤቶችና ቁጠባ ባንክ (ሞርጌጅ ባንክ)ን ድጋሚ ማቆቆምና የኮንዶሚኒየም ግንባታዎች በሙሉ በባንኩ ሥር እንዲከወኑ ማድረግ፡፡

{11} ያለ ፕሬስ ነፃነት አንድ አገር አትሰለጥንም ሙሉ ፕሬስ ነጻነት ማወጅና የኢንተርኔት ስለላ ሥራ ማቆም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማንሳት!!! የተቀሩት የፖለቲካ እስረኞች መፍታት!!! የአጋዚ ጦር ገዳዬች ለፍርድ ማቅረብ!!! ሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሊ አረመኔ  አገዛዝ አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጆች ከቀያቸው ተፈናቀሉ፣ በግፍ ተገደሉ፣ ታሰሩ ፍትህ የለም የሚጮህ የሞቾች ድምፅ ይሰማል!!! ልጆቻቸው እንደ ፍየል የታረዱባቸው እናቶች ፍትህ ይሻሉ፣ የዘገየ ፍትህ አንሻም!!!  ፋሽስቱ አብዲ ኢሊ በቀብሪ ደሃር እስር ቤት በስቅላት ለሞተች 24 ዓመት ወጣት ታሲር ኦማር ፎድን ፍትህ ይሠጥ ዘንድ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአስቸኳይ ፍትህ እንጠይቃለን!!!  የአብዲ ኢሊ ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ! ለሶማሌ ህዝብ ፍትህ ይሠጥ፣የፍርድ ያለ!!! የህግ ያለ!!! የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

አያቶቻችን ለአባቶቻችን ነፃነት ነበር ያወረሱት፣ ታዲያ የዛሬ አባቶቻችን ለልጆቻቸው  እንዴት ዕዳ ያወርሳሉ!!!

 

 

 ‹‹ጊዬርጊስ ጊዩርጊስ!!!!….ትልቅ ትልቁን ገንድስ!!! የወያኔ ሙጋቤዎች ወደ ጡረታ!!! ››
‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ››

አቶ በረከት ስምኦን፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ አዲሱ ለገሠ

‹‹ጊዬርጊስ ጊዩርጊስ!!!!….ትልቅ ትልቁን ገንድስ!!! የወያኔ ሙጋቤዎች ወደ ጡረታ!!! ›› ‹‹ልጅ ከጦረው፣ ዓይን የጦረው!!!››

ዋናው ኦዲተር የፌዴራሉንና የሚኒስቴርና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ሂሳቦች በመቆጣጠር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመደበው ዓመታዊ በጀት፤ በበጀት ዓመቱ ለተሠራው ሥራዎች በሚገባ መዋሉን መርምሮ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡በብሄራዊ  ባንክ ውስጥ ከሚቀመጠው የማህበራዊ ዋስትና ተቆማት ገንዘብ ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የጡረተኛ ገንዘብ፣ ሁለተኛ የሃይማኖት ተቆማት ገንዘብ፣ ሦስተና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተቆማች ብዙ መቶ ቢሊዮን ብር ገንዘብ ባንክ ይቀመጣል፡፡ የጡረታ ሚኒስቴር ከመንግሥት ሰራተኖች በየወሩ  ከደሞዛቸው እየተቆረጠ ባንክ የሚቀመጥ የጡረታ ገንዘብ ሲሆን ባንኩ በበኩሉ ወርቅ ለጡረታ ሚኒስቴር መያዣነት እስከ ደርግ ዘመን ድረስ ያስቀምጥ ነበር፡፡ በኢህአዴግ ዘመን ጡረተኛው ባንክ ለሚያስቀምጠው ገንዘብ  የሚያስቀምጠው ወርቅ ማዕድን መያዣ የለም፡፡ ስለዚህ የመንግሥት ሠራተኛ ወደፊት በእድሜ ዘመኑ ላስቀመጠው የጡረታ ገንዘብ የማግኘት ዕድሉ የመነመነ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መንግሥት የጡረተኛውን ገንዘቡ እንደፈለገው ስለሚጠቀምበት ነው፡፡በኢህአዲግ ዘመን  የጡረታ ሚኒስቴር ሚኒስተር  ዳባ ዋቅጅራ ሲሆኑ፣ ለብዙ ዓመታት  የቦርድ አባሎች በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣  አዜብ መስፍን ሚሥጢር ቤት ሆነው የጡረታ ሚኒስትር ሚሥጥረኞች በመሆን የጡረተኛውን በብዙ ቢሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ለወያኔ መንግሥት በማበደር፣ ለተለያየ የፓርቲ ንግድ እንቅስቃሴ የጡረታ ተቀማጭ ገንዘብ ወጪ አድርገው እንዲመልሱ በመስጠት ህገውጥ ድርጊት በህዝብ ገንዘብ እንደሚፈጽሙ ውስጥ አዋቂዎች ገልጸዋል፡፡ ዋናው ኦዲተር የጡረታ ሚኒስቴርን ኦዲት ማድረጉን የሚገልጽ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡የመንግሥት ጡረተኞች በመላ ሃገሪቱ ከአንድ ሚሊዩን ሰዎች በላይ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ የመንግሥት ጡረተኞች በአዲስ አበባ ብቻ 160 ሽህ ሲሆኑ ዝቅተኛ 273 ብር ከፍተኛው 150 ሽህ ብር በወር የጡረታ ያገኛሉ፡፡ የህወሓት/ ኢህአዴግ የቶር አበጋዞች መንግሥት የጡረታ እድሜቸው አልፎል፣ ጡረታ ግን አይወጡም!!! ወያኔ ሹማምንት ከህግ በላይ ከሆኑ አመታት ተቆጥረዋል፡፡

የእኛ ትውልድ ምስክርነታችን፤ በግ.ቀ.ኃ ዘመን የጡረታ መውጫ እድሜ 55 ዓመት ነበር፣ በወታደራዊ መንግሥት ዘመን 60 ዓመተ ሆነ፣ በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን 70 ዓመት ለማድረግ እየተዶለተ ነው፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ሹማምንትና ጀነራል መኮንኖች እድሜ በአብዛኛዎቹ ከ65 እስከ 75 ዓመትና በላይ ሲሆኑ መተካካት እያሉ በድዳቸው መግዛት ይሻሉ፡፡ በሃገሪቱ ህግ የጡረታ እድሜ መወሰኑ መጭው ትውልድን ለመተካት ሲሆን፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነውና የጡረታ እድሜው ሲደር መውጣት ግድ ይላል፡፡ ለወያኔ ህገአራዊት ግን አይሰራም፣ የወያኔ ያረጁ ጅቦች አውራው ስብሃት ነጋ 90 ዓመት አይጠቅማቸውም ይባላል፡፡ የጡረታ እድሜቸው ያለፈ ካድሬ ፖለቲከኞች ህግ አይገዛቸውም፡፡ ወያኔ የዮኒቨርሲቲ 40 መምህራኖችን ከሥራ በማባረር የእውቀትን  መጽሃፋችንን አስነጠቅን፡፡ የወያኔ ሹማምንትና ጀነራል መኮንኖች  በተገዛ ዲግሪ፣ ማስተርስና ፒኤች ዴ ተንበሽብሸው ሃገር በድዳቸው ይገዛሉ፡፡ እርጅናቸው እንዳይታወቅ ፀጉራቸውን ቀለም በመቀባት አላረጅም (የወያኔ ኪዊ ትውልድ) ፈጥረዋል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት  የወጣቱን 30 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች እንኮን የመሶቡን የእጄን ተውኩላችሁ!  ጥያቄን ህዝባዊ እንቢተኛነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን እየጣረ ይገኛል፡፡ በኦሮሚያ ክልል 10 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶች ይገኛሉ፣ በአማራ ክልል 8 ሚሊዩን፣ በደቡብ ክልል 5 ሚሊዮን፣ በሱማሌ ክልል 1.8 ሚሊዮን፣ በትግራይ ክልል 1.5 ሚሊዮን፣ በአዲስ አባባ 1.2 ሚሊዮን፣ አፋር 619 ሽህ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 338 ሽህ፣ ጋምቤላ 150 ሽህና፣ ሐረሪ 80 ሽህ ሥራ አጥ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ ከኢትዩጵያ ህዝብ 70 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው፡፡ የወጣቶችን ህይወት ለማስተካከል ዘላቂ የኢኮኖሚ መፍትሄ መሻት እንጅ ወጣቶችን በመግደልና በማሰር አይፈታም፡፡ ወያኔ ዳግም ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጅ ችግሩን አይፈታም፡፡ ወያኔ አዋጁን አንስቶ የክልል መንግሥታት ኃላፊነታቸውን በመወጣት፣ የወጣቶችን ችግር በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ ማድረግ ይገባል፡፡ ወጣቶችን ንብረት እንዳያጠፉና እንዳያወድሙ መምከር ያስፈልጋል፡፡ የወያኔ አጋዚ የሰው ህይወት እንዳይቀጥፍ ከክልሎች ወጥቶ ድንበር መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ የኦሮሚያ ቄሮ፣ የአማራ ፋኖ፣ የደቡበ አቦሸማኔ፣ የጉራጌ ዘማር፣ የሰሜን አናብስት ወጣቶች የወያኔን የጦር አበጋዞች መንግሥት ከክልላችን ውጣና ድንበር ጠብቅ  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሣ!!! ይላችኃል፡፡

አምራች ኃይል ያልሆኑ ተቆማቶች፤-

  • የህወኃት/ ኢህአዴግ የፖለቲከ ፓርቲ ድርጅቶች፣ ካድሬዎችና አባላቶች፣ በቁጥር 8 ሚሊዮን ሲሆኑ የሃገሪቱን ግማሽ 50 በመቶን ይቆጣጠራሉ፡፡ ለወያኔ ሹማምንቶች በቬርኔሮ ኮንስትራክሽን በብዙ ሚሊዩን ብር ወጪ የሚሰራ የቪላ ቤት፣ የመኪናዎችና፣ ልየ ልዩ ጥቅሞች በአስቸኮይ ይቁም!!! እድሜቸው ለጡረታ የደረሰ ባአፋታኝ ይወገዱ፣ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነውና!!!
  • የመከላከያ ሠራዊት፣ ጦር ሠራዊት፣ ፖሊስ፣ አየር ኃይል፣ ሚሊሽያ ወዘተ የህዝብ ደህንነት አባላት በቁጥር ከ 750 ሽህ እስከ 1 ሚሊዮን
  • የመንግሥት ሠራተኛ በፌዴራልና ክልሎች መንግሥታት እስከ አንድ ሚሊዩን ይቆጠራሉ፡፡
  • ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ከእጅ ወደ አፍ፣ አመቱን ሙሉ ፓርላማ ውስጥ እጅ ሲያወጡ ከርመው ክረምት ላይ የተሰቀለው   እጃቸው በወጌሻ ታሽቶ ይወርዳል፡፡ የእንጀራ ነገር!!!

የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች እድሜቸው ከ65 እሰከ 75 አመት ያለፋቸው፣ የጡረታ እድሜቸው ያለፈ የፖለቲካ ካሚሳሪያትና ካድሬዎች በጡረታ ይወገዱ፤ የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይስፈን!!! ለወጣቱ ትውልድ የሥራ እድል ይፍጠር፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት መደበኛ በጀት በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በ2007 እኢአ 45.05 ቢሊዩን ብር፣ በ2008ዓ/ም መደበኛው በጀት 50 ቢሊዩን ብር ከፍ ሲል በ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ በአንድ ግዜ የ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ጭማሪ ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ግብር እንደዳረገው የምጣኔ ሃብት ጠበብት ገልፀው ነበር፡፡ ጠቅላላ ዓመታዊ የፌዴራል መንግስት ባጀት 321.8 ቢሊዮን ብር 25.5 በመቶ ወይም የበጀቱን አንድ አራተኛ ሆኖል፡፡ የመገርመው የጡረታ እድሜቸው ያለፈ የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች በሃገሪቱ ህግ መሠረት ለምን ጡረታ እንደማይወጡ እንቆቅልሹ ያልተፈታ የሽፍታ አስተዳደር፣ አሊያም  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዳሉት የ‹ህገ-አራዊት›አስተዳደር ጡረታ የማይመለከታቸው  ሹማምንት ለፍርድ እንዲቀርቡ ወጣቱ ትውልድ ይጠይቃል፡፡

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መደበኛው ባጀት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ ያውለዋል፡፡ {1} (ለህወሃት) ሹማምንትና ካድሬዎች  ትግራይ ክልል፣{2} (ለኦሕዴድ)የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት  ሹማምንትና ካድሬዎች ለኦሮሚያ ክልል፣ {3} (ለብአዴን)ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  ሹማምንትና ካድሬዎች ለአማራ ክልል፣ {4} (ለደኢሕዴግ) የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር  ሹማምንትና ካድሬዎች ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ {5} (ለሶዴድ) ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት  ሹማምንትና ካድሬዎች ለሶማሌ ክልል፣ {6} (ለአዴድ) ሹማምንትና ካድሬዎች  የአፋር ክልል፣ {7} (ለቤህነን) ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ  ሹማምንትና ካድሬዎች  የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ {8} (ለጋሕነን) ጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ  ሹማምንትና ካድሬዎች ለጋምቤላ ክልል፣ {9} ለሃዴድ ለሃራሪ ክልል ሹማምንትና ካድሬዎች፣ ለሃረሪ ክልል፣ {10} ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሹማምንትና ካድሬዎች፣ {11} ለአዲስአበባ አስተዳደር ሹማምንትና ካድሬዎች የጡረታ እድሜቸው አልፎል፡፡

የህወሓትየጦር አበጋዞች መንግሥት የመከላከያ ሠራዊት፣ ጦር ሠራዊት፣ ፖሊስ፣ አየር ኃይል፣ ከ65 እሰከ 75 አመት ያለፋቸው፣ የጡረታ እድሜቸው እንዳለፈ የጡረታ ሚንስትርና ከመከላከያ ሠራዊት  ውስጥ አዋቂዎች ተረጋግጦል፡፡ በቅርቡ  ጀነራል መኮንኖች እንደተሸሙ ያስታውሱ፣ ወጣቱ ትውልድ ‹እንኮን የመሶቡን የእጄን ተውኩላችሁ!›  ድሮ ቀረ ይላችካል፡፡

High Ranking Military Officials፡ Principal Defense Departments

No Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 Armed Forces Chief-of-Staff General Smora Yenus Tigre
2 Armed Forces Head of Training Lt.General Tadesse Worde Tigre
3 Head of Logistics Lt.General Gezae Abera Tigre
4 Head of Intelligence Br. General Gebre Dela Tigre
5 Armed Forces Head of Campaign Major General Gebreegzher Tigre
6 Armed Forces Head of Engineering Lt.General Berhane Negash Tigre
7 Chief of the Air Force Chief of the Air Force Tigre

Heads of the Nation’s four Military Commands

No Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 Central Command General Abebaw Tadesse Agew
2 Northern Command Lt.General Saere Mekonene Tigre
3 South Eastern Command Lt.General Abraha Wolde Tigre
4 Western Command Br. General Seyoum Hagos Tigre

Army Divisional CommandersCentral Command

No Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 31st Army Division Colonel Tsegaye Marx Tigre
2 33rd Army Division Colonel Kidane Tigre
3 35th Army Division Colonel Misganaw Alemu Tigre
4 24th Army Division Colonel Work Aynu Tigre
5 22nd Army Division Colonel Dikul Tigre
6 8th Mechanized Division Colonel Jamal Mohammed Tigre
Northern CommandNo Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 14st Army Division Colonel Wodi Antiru Tigre
2 21st Army Division Colonel Gueshi Gebre Tigre
3 11th Army Division Colonel Workidu Tigre
4 25th Army Division Colonel Tesfay Sahiel Tigre
5 22nd Army Division Colonel Teklay Klashin Tigre
4th Mechanized Division Colonel Hinsaw Giorgis Tigre
South Eastern CommandNo Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 19st Army Division Colonel Wodi Guaae Tigre
2 44st Army Division Colonel Zewdu Tefera Tigre
3 13th Army Division Colonel Sherifo Tigre
4 12th Army Division Colonel Mulugeta Berhe Tigre
5 32nd Army Division Colonel Abraha Tselim Tigre
6 6th Mechanized Division Colonel G/Medhin Fekede Tigre
Western CommandNo Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 23rd Army Division Colonel Wolde Belalom Tigre
2 43rd Army Division Colonel Wodi Abate Tigre
3 26th Army Division Colonel Mebrahtu Tigre
4 7th Mechanized Division Colonel Gebre Mariam Tigre
Commanders in Different Defense Departments No Job Division Name & Rank Ethnic Group
1 Agazi Commando Division B.General Mohammed Esha Tigre
2 Addis Ababa & Surrounding Area Guard Colonel Zenebe Amare Tigre
3 Palace Guard Colonel Gerensay Tigre
4 Banking Guard Colonel Hawaz Woldu Tigre
5 Engineering College Colonel Halefom Eggigu Tigre
6 Military Health Science B.General Tesfay Gidey Tigre
7 Mulugeta Buli Technical College Colonel Meleya Amare Tigre
8 Resource Management College Colonel Letay Tigre
9 Siftana Command College B.General Moges Haile Tigre
10 Blaten Military Training Center Colonel Salih Berihu Tigre
11 Wourso Military Training Center Colonel Negash Heluf Tigre
12 Awash Arba Military Training Center Colonel Muze Tigre
13 Birr Valley Military Training Center Colonel Negassie Shikortet Tigre
14 Defense Administration Department B.General Mehari Zewde Tigre
15 Defense Aviation B.General Kinfe Dagnew Tigre
16 Defense Research and Study B.General Halefom Chento Tigre
17 Defense Justice Department Colonel Askale Tigre
18 Secretary of the Chief-of-Staff Colonel Tsehaye Manjus Tigre
19 Indoctrination Center B.General Akale Asaye Amhara
20 Communications Department Colonel Sebbhat Tigre
21 Foreign Relations Department Colonel Hassene Tigre
22 Special Forces Coordination Department B.General Fisseha Manjus Tigre
23 Operations Department Colonel Wodi Tewk Tigre
24 Planning, Readiness and Programming Department Colonel Teklay Ashebir Tigre
25 Defense Industries Coordination Department Colonel Wodi Negash Tigre
26 Defense Finance Department Colonel Zewdu Tigre
27 Defense Purchasing Department Colonel Gedey Tigre
28 Defense Budget Department Ato/Mr. Berhane Tigre

የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣በተጨማሪ አዲስ የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ ሚሊሽያ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ እስር ቤቶች መገንቢያ፣ አዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ለመገንባትና የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ/ም ባወጣው አዋጅ የተበጀተልን መደበኛ ወጪ ለሃገሪቱ ልማት ቢውል፣ ለረሃብተኛው ህዝብ እህል መግዣ ቢውል፣ ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ ወጣቶች የሥራ መስክ ፈጠራ ላይ ቢውል፣ ለህብረተሰቡ የውሃ፣ ጤና፣ ትምህርትና መብራት አገልግሎት ላይ ቢውል መልካም ነበር፡፡

ህወሃት በመላ ሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጂ፣በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማፈን ከ2008 እስከ 2009 ዓ/ም መጨረሻ፣ ኮማንድ ፖስቱ ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ የመኪና ነዳጅ፣ ለስራ ማስኪጃ፣ ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ፣ለመጎጎዣ፣ለአዲስ እስር ቤቶች መገንቢያና ለፖሊስ ጣቢያዎች መስሪያ ወዘተ የተለያዩ  ወጭዎች፣ በብዙ መቶ ቢሊዩን ብር የሚገመት ኪሣራ ተከናንቦል፡፡ ይህ ያገሪቱ አንጡራ ሃብት ለልማት ሥራ ውሎ ቢሆን፣በትንሹ ለተራቡ ወገኖቻችን በደረስልላቸው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ አዲሱን 2010 ዓ/ም አመታዊ በጀት መንፈቅ ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ብር በጀት ለወታደሩ ደሞዝ፣ለሥራ ማስኪጃ ወጪ ለማዋል ታቅዶል፡፡ የወያኔ መንግስት ወታደራዊ ወቺ በየግዜው በመጨመሩ የተነሳ ብዙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለካፒታል በጀት የተያዘ 115 ቢሊዩን ብርና፣ ለክልሎች 117 ቢሊዩን ብረና ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ  ሰባት ቢሊዩን ብር የተደለደለው በጀት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት ለወታደራዊ ወጪ መደልደሉን ታውቆል፡፡ የወያኔ መንግስት ቤሳቢስቲ ከካዝናው የለውም፡፡ በ2010 ዓ/ም  የተመደበው የፌዴራል መንግስት ባጀት የገቢ ምንጮች ከአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች፣ ከውጭ ብድርና እርዳታ የሚሞላ መሆኑ ተገልፆል፡፡ በአገሪቱ አምራቹ የሰው ሃይልና ግብር ከፋይ ዜጋዎች አምራች ባልሆኑ በሰው ተከሻ የሚኖሩ ጥገኛ የመንግስት ሹማምንት፣ካድሬዎች ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል ቀለብ ሲሰፍር ይኖራል፡፡ ከነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ‹መንግሥትና የህዝብ አስተዳደር› በሚል ርዕስ በ1916 እኢአ የታተመ መፅሃፋቸው ውስጥ የዛሬ ዘጠና አራት ዓመታት በፊት እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ብረት ሠሪውም ማረሻ አበጅቶ ጤፍ ይቀበላል፡፡ አራሹም ጤፍ ሰጥቶ የተሻለ ማረሻ ያገኛል፡፡በሌላም ነገር ሁሉ እንደዚሁ ነው፡፡ ዕውቀት ባለው ሕዝብ መካከል ግን በከንቱ የሚሰጥ ሰው የለም፡፡ በከንቱም የሚበላ ሰው የለም፡፡ የሁሉም  ትዳሩ ተለዋውጦ ነውና እንካ ሥራ አምጣ ሥራ ይባባላል፤ይህ ሳይሆን ቀርቶ በላተኛው ከሠራተኛው ሲበዛ በማናቸውም ቤት ሀብት ሊገባ አይችልም፡፡ ዕውቀትም ከሌለው ሕዝብ ውስጥ ከሠራተኛው በላተኛው፣ሹም ወታደር ነጋዴ እየሆነ ይበዛልና ባገሩ ሀብት ሊከማች አይችልም፡፡ የሥራው ፍሬ እንደ ገባ ወዲያው ያልቃል፡፡››

የሃይማኖት ተቆማቶች ቀሳውስት፣ ሼኮች፣ ፓስተሮች፣ ወዘተ በግምት አንድ ሚሊዮን ሲሆኑ የሃገሪቱን አንድ ሦስተኛ ኃብት ይቆጣጠራሉ፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምዕመናን በአመት አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ታገኛለች፣ ብዙ ፎቆች በከተማዋ ውስጥ ገንብታ በማከራየት ከፍተኛ ገንዘብ ታገኛለጭ፡፡ የቤተክህነት ቀሳውስትና ሠራተኞች ደሞዝ ከፍተኛ ነው፣ የጅ መንሻና በአንድ ዘር የሥልጣን ሹመት የታወሩና በሙስና የተዘፈቁ ካህናት በከተማው ውስጥ ቪላ ቤቶች ስርተው  ይኖራሉ፡፡ የኢትዮጵያን ህዝብ  እውነተኛ ባህልና መልካም ሥነ ምግባር፣ መልካም አስተዳደግና ግብረገብነት፣ ፈሪሃ እግዜአብሄርና የሞራል ዕሴቶች በማጎደል እውነተኛውን ትምህርት ያላስተማሩ የሃይማኖት አባቶችና ተቆማቶች ተልኮቸውን  ህገ እግዚሃብሄርን ማስተማር ባለማክበር ዋነኛ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ የሃይማኖት አባቶችና ተቆማቶች በፍቅረ ነዋይ ተለክፈው ዕምነትን በክህደት፣ እውነትን በሃሰት፣ ሃቅን በቅጥፈት፣ ተገዝግዞ እስኪበጠስ እያዩ እንዳላዮ፣ ስምተው እንዳልሰሙ፣ አስተውላው እንዳላስተዋሉ፣ አስመስለው በማደር፣ ፍቅርን ለጥላቻ፣ ቃልን ለንዋይ ሸጦት፡፡ የሃይማኖት ተቆማቶች ላለፉት ግማሽ ምዕተ ዓመት ሲሶ መንግሥት ሆነው የህዝብ መሬትና ሃብት፣ ተቀራምተው ሲያጥሩና ፎቅ ገንብተው ሲያከራዮ፣ ከምዕመናኑ የተሰበሰበ ሙዳየ ምጽዋት ወደ ግል ኪሳቸው ሲገለብጡ፣ ከምዕመናኑ የተበረከተ የስለት ንዋይ ለግል ጥቅም በማዋል ሃይማኖት ያረከሱ፣ ለግል ጥቅምና ክብር የተንበረከኩ፣ ሃሳዊ መሲህ  የሃይማኖት አባቶች የተፈበረኩባት ሃገር ሆናለች፡፡ የሃይማኖት አባቶችና ህዝቡን ቅዱስ መጸሃፍት ማስተማር፣ ወንጌልን መስበክ፣ የፈጣሪን ቃል፣ የታረዘን ማልበስ፣ የተጠማን ማጠጣት፣ የተራበን ማብላት ወዘተ የፈጣሪን ትዕዛዛት አውቆ ማሳወቅ ሲገባቸው እራሳቸው አረከሱት ከዛን ጊዜም ጀምሮ በሃገራችን ፍቅር በጥላቻ ተተካ፣ እኛ በእኔ ብቻ ተተካ፣ ቃለ እግዜብሄር በአፈ ካድሬ ታበሰ፡፡ የሃይማኖት ተቆማት የወደቁ ህፃናት ማሳደጊያ አላቆቆሙም፣ የወደቁ አረጋውያንን አልጦሩም፣ ለግላቸው ኃብትና ንብረት ሲያግበሰብሱ ይታያሉ፡፡ ምዕመናኑ ቅድስ መፍሃፋን ተነጠቀ፣ ዜጎች ብሄራዊ ፍቅራቸውን ተነጠቁ፣ ገበሬዎች መሬትና ምርታቸውን ተነጠቁ፣ የምሁራኖች ዕውቀትና ሥራ በካድሬ ፖለቲከኞች በወሬ ተተካ፣ በሃገሪቱ  መንግሥታዊ አስተዳደርና ቢሮክራሲ ውስጥ የትምህርትና ዕውቀት ሙያ በፖለቲካ  ፓርቲዎች ርዕዬትና ካድሬ ሠራተኞች ተተካ የሃገራችንና የህዝባችን ጥፋት መነሻና መድረሻ የተነጠቅነው የእውቀት መጽሃፋችንን ነው፡፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተነጠቀውን የእውነት፣ የፍቅርና የእውቀት መጽሃፋህን አስመልስ፡፡ ‹‹ሚዳቆ የማትዘለው፣ የቀንን ጎዶሎ!!!›› ነው፡፡ ለኢትዮጵያውያን ያችን የቀን ጎዶሎ ባለመዝለል ግማሽ ምዕተ ዓመት ተቆጠረ፣ እድሜ ባከነ፣ ድንቁርና ምርኩዛችን፣ ርሃብ ቀለባችን፣ ፍርሃት ጥላችን፣  ምቀኝነት  እትብታችን፣ ውሽት አንደበታችን፣ ማስመሰል መለያችን ሆኖ የሚያወራ እንጅ የሚፅፍ ታጣ፣ አንድ ሽህ አንድ ቃላት እንደአውቶማቲክ ጠመንጃ ጥይት የሚተፉ ሸምድደው የሚያነበንቡ ዳጋሚዎች አንድ ገፅ ያማይጽፉ ካድሬዎች እንደ አሸን ተፈለፈሉ እውቀት በድንቁርና ተጠመቀ፣ እንዲያ እንዲያ እያለ ትውልድ ቀጠለ፡፡  በዝሙት ሥራ የሚተዳደሩ ሴት እህቶቻችን በግምት  ከ250 ሽህ እስከ 350 ሽህ  ይሆናሉ፡፡ ብዙ ርሃብተኛ ወገኞች በሃገራችን ይኖራሉ፡፡ የሃይማኖት ተቆማቶች ይሄን የእህቶቻችንን ስቃይ እያዩ ይኖራሉ!!!  ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ሲገል ዝም ይላሉ!!! እስከመቼ ዝምታ፣ ህዝብ ተቃውሞ ካላሰማችሁ በሃይማኖት ተቆማቶች ላይ አድማ መጥራቱ አይቀሬ መሆኑን ተረዱ እንላለን፡፡ በቃ!!!

የዲጂታል ቴክኖሎጅ ዘመን ልበ ብርሃን ወጣቶች ተምረው ሥራ አጥ በሆኑባት ሃገር አረጋውያን ተጠዋሪዎች እድሜ ፈጅ ኪኒን እየዋጡ አንዴ ሚኒስቴር፣ አንዴ ዲፖሎማት፣ አንዴ ጀነራል መኮንን ይሆናሉ!!! ጸጉራቸውን ኪዊ ቀለም እየተቀቡ እነዚህ የጅንጀሮ ቆንጆዎች፣ ህግ አያውቁም፡፡

ጊዬርጊስ ጊዩርጊስ!!!!….ትልቅ ትልቁን ገንድስ

ሹገር ዳዲዎችና ማሚዎች፣ የፖለቲካ አድርባዬች፣ እንደ እስስት የሚቀያየሩ ሆድ አደሮች
ወዘተርፈ የኪዊ ዲፕሎማቶች

ሙስኛ ተዋናዬች!!! የመንግሥት ቤት ካርታ በስማቸው ያዞሩ ሹምምን ብዙ ናቸው ፍትህ በእናት ኢትዮጵያ!!!
የወያኔ አከርካሬ የሚመታው በህዝባዊ የኢኮኖሚ አድማ፣ ሱናሚ ማዕቀብ ነው!!! ያለመሠረታዊ ለውጥ ወያኔ እንደእባብ አፈር ልሶ ዳግም ይገዛናል!!! ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› እያሉ በድዳቸው ሊገዙን ነው የሚፈልጉት!!! ወያኔ ‹‹ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ›› ነው፡፡
ጀነራል ሳይሆኑ፣ ጀነራል አልናቸው!
ኮነሬል ሳይሆኑ፣ ኮነሬል አልናቸው!
ሚስቴን እቴ ብዬ ዳርኩላቸው!!!
‹‹ሞት ይቅር ይላሉ፣ ሞት ቢቀር አልወድም
ድንጋዩም አፈሩም፣ ከሰው ፊት አይከብድም!!!!››
ከባርነት ህይወት፣ ሞት ነፃነት ነው!!! ‹‹በትግል መሞት ህይወት፣ በአመጻ መሞት ህይወት ዳግም ትንሣኤ ልደት›› ብሎ ተሠውቶል አንድ ትውልድ!!! ሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋ ሆነን መኖር እስከመቼ ድረስ!!! ነፃነታችን እናስመልስ፣ ክብራችንን እናስመልስ! መሬታችንን እናስመልስ!!!
እድሜ ጠገብ የተቃዋሚ ፓርቲ ታጋዬችም ለወጣቱ ትውልድ በትረሥልጣኑን ለማስረከብ አርዓያ መሆን ይጠበቅባችኃል!!!የወያኔ መንግሥት ያረጁ ጅቦች ጡረታ ይዉጡ!!! የህግ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ይከበር!!! የወያኔ ሙጋቤዎች ወደ ጡረታ!!! ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሣ!!!

 

ጊዬርጊስ ጊዩርጊስ!!!!….ትልቅ ትልቁን ገንድስ!!!
ጂብሪል ጂብሪል!!!…. ሌባውን በመብረቅ ግደል!!!