(ዘ-ሐበሻ) በአሜሪካ ሂውስተን ቴክሳስ ፖሊስ ተከታትዬ ደረስኩበት ባለው ጥፋት፣ ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት በመመልመልና በማሰማራት ሥራ ተጠርጥረው ከተያዙት 34 ሰዎች መካከል፣ በሚዙሩ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ፌሎውሺፕ ችርች ፓስተር የሆኑት አለማየሁ ደምሴ አንዱ ናቸው ብሏል።

ዜናውን በቪድዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

አድማስ ራድዮ የፖሊስን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ፓስተሩና ሌሎች 34 ተጠርጣሪዎች ወጣት ሴቶችን ለወሲብ ንግድ በማሰማራት ወንጀል ተከሰው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። አድማስ ሬዲዮ ስለ ፓስተሩ ለመጠየቅ የሚያሰተዳድሩት ቸርች ጋር በተደጋጋሚ ቢደውልም መልስ አላገኘም። ቤተክርስቲያኑ መልስ ካለው ግን በማንኛውም ሰዓት ለማቅረብ ዝግጁ ነን።

አድማስ ራድዮ “እንዲህ ዓይነት ጥፋትም የግለሰቡ የግል ባህርይ እንጂ የዕምነት ተቋሙ እንዳልሆነም እንረዳለን።” ሲል ግለሰቡ የተከሰሰበትን ግን ገና ጥፋተኛ ያልተባለበትን ድርጊት ሰዎች ከእምነት ተቋሙ ጋር እንዳያያይዙት ጥሪ አቅርቧል::