May 20, 2018
በመምህር ዮናታና ተስፋዬ የውይይት መነሻ ሃሳብ አቅራቢነት በሰማያዊ ፓርቲ ሰፊ ውይይት ተካሄደ ። ” ወቅታዊ የአገራችን ፓለቲካ ተስፋ እና ስጋቶች ” አስመልክቶ መምህር ዮናታና በሰጠው ገለፃ ፤ፖለቲካ ምንድነው? ከሚለው ጥያቄ በመነሳት ፣ በኢትዮጵያ ቀደምት ታሪካዊ ክስተት እና እሱን ተከትሎ የተፈጠረው ብሔራዊ አንድነት እና የዘውግ ፖለቲካ አራማጅነት ዋነኛ መንስኤዎችን በመዳሰስ ፣ አሁን ላይ የምንገኝበት የሃገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ ችግሮች እና መፍትሔዎች ላይ በማተኮር መምህር ዮናታን ባቀረበው ጽሁፍ ገለጻ ሰጥቷል ።
—
በተካሄደው ውይይት በዋነኝነት አሁን ላይ እየሆነ ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚፈጥረው ተስፋ እና ስጋት በዝርዝር በመለየት በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ መምህር ዮናታና ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን ፤ እንደ ስጋት በዋነኛነት ሰባት (7) መሰረታዊ ነገሮች በማስቀመጥ፣ ከእነኚህ ስጋቶች ለመላቀቅ የሚያስችል ቁልፍ የሆኑ ነገሮችን በአምስት (5) ክፍል በመከፋፈል ጥልቀት ያለው ማብራሪያ እና ውይይት ተካሄዷል ።
—
በውይይት ላይ ተሳታፊ የነበሩ ፤በቀረበው ገለጻ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እና አሰተያየት የሰጡ ሲሆን ፤ መምህር ዮናታን በገለፃቸው ወቅታዊ የአገራችን ፓለቲካ ተስፋ እና ስጋቶች ላይ መጨመር እና መቀንስ አለባቸው የሚሏቸውን ሃሳቦች አቅርቧል ። በተለይ እንደ ስጋት ከቀረቡት መካካል ” የህወሃት አልሸነፍ ባይነት እና የህወሃት’ዊያን የኢኮኖሚ የበላይነት “ሰፊ የመወያያ ነጥብ ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ “የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት እና ለውጡን ለማምጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ ” በቁጥር አንድ ተስፋ ሰጪነት በማስቀመጥ በይበልጥ እንዴት መጠናከር እንዳለበት ውይይት ተካሄዷል ።

