እንደ አዲስ በአማራ ላይ የተከፈተው የጥቃት ዘመቻና በወገናችን ላይ ያለኝ ሥጋት!

የበፊቱን ትተን ለመልካም አሥተዳደር መስፈን፣ ለአንድነት፣ ለዕኩልነት፣ ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለዲሞክራሲያዊ (ለመስፍነ ሕዝባዊ) ሥርዓት መጎልበት፣ ለኢትዮጵያዊ ማንነት መጉላት ባጠቃላይ ለለውጥ የቆረጥኩ ነኝ!” የሚለው በዐቢይ ይመራል የተባለው አሥተዳደር ሥራ ጀመረ!” ከተባለ ወዲህ እንኳ በአማራ ላይ የሚፈጸሙ አረመኔያዊ ግፎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በአዲስ ዘመቻ መፈጸም ተይዞ ከመተከል እስከ ናዝሬት፣ ከጅማ እስከ ምዕራብ ሸዋ፣ ከበሎ ደዴሳ እስከ ደቡብ አማራ እንደበግ እየታረደ፣ ዕድሜ ዘመኑን የደከመበትን ቤት ንብረቱን ተነጥቆ ተዘርፎ ባዶ እጁን ተፈናቅሎ እየተባረረ፣ ሕገመንግሥታቸው ማንኛውም ዜጋ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነጻ የመዘዋወር፣ ኑሮን የመመስረትና ንብረት የማፍራት ሙሉ መብት አለው!” የሚል ሆኖ እያለ እና ሕጋዊነቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ በእጁ እያለ ለዘመናት ከኖረበት ቀየ ሕገወጥ ነህ!” እየተባለ በዛሬ ዘመን ሰው ያለ ሀገሩ እንኳ በአውሮፓና አሜሪካ ተሰዶ ሰብአዊ መብቱ ተከብሮለት በነጻነት ሠርቶ ከዜጎቹ ጋር ዕኩል መኖር በሚችልበት በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ስንትና ስንት መራራ መሥዋዕትነት ከፍሎ በነጻነት ባቆያት በገዛ ሀገሩ የመኖር መብት ተነፍጎት በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ከቀበሌ አሥተዳደሮች የማስጠንቀቂያ ወረቀቶች እንዲደርሰው እየተደረገ ይገኛል ወዘተረፈ.

አብዛኛው ሰው እነኝህ በአማራ ላይ በተለያዩ ሥፍራዎች እንደአዲስ በዘመቻ እየተወሰዱ ያሉ አረመኔያዊ የግፍ እርምጃዎች ከከፍተኛው የአገዛዙ መዋቅር ዕውቅናና ትዕዛዝ ውጭ እየተደረገ ያለ ይመስለዋል፡፡ እውነታው ግን እንዲያ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ እየተደረገ ያለው ግፍ አሁን ባለው በነዐቢይ አሥተዳደር ዕውቅናና ትዕዛዝ እየተደረገ ያለና በተጠና ዓላማም ነው እየተፈጸመ ያለው፡፡

ዓላማውም በታወጀው ሐሰተኛ ለውጥ አማራ ነጻነትና መነቃቃት ተሰምቶት ቀና ቀና እንዳይልና እንዳይገዳደር፣ መብቱን እንዳይጠይቅና ብሶቱን እንዳይገልጽ አድርጎ አንገቱን እንደደፋ፣ እንደተሸማቀቀ፣ በሥጋት ተጠፍንጎ እንደተያዘ እንዲቆይ ለማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም አገዛዙ ፈጽሞ የአማራን ጥያቄዎች የመመለስና ችግሮቹን የመፍታት ፍላጎት የለውምና ነው፡፡ እናም አሁን በአማራ ላይ እንደ አዲስ በዘመቻ እየተደረገች ያለች እያንዳንዷ እርምጃ ሁሉ ሆን ተብሎ በተጠናና በታቀደ መልኩ ነው እየተፈጸመ ያለው የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም እዚህም እዚያም የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ያሉት፡፡

ለዚህም ነው ለውጥ በታወጀበት በዚህ ወቅት፣ በማንኛውም ባለሥልጣን ላይ ተጠያቂነት ይኖራል!” በተባለበት በዚህ ጊዜ እንደቀበሌ ያሉ የአገዛዙ የአሥተዳደር አካላት ሳይቀሩ ያለአንዳች መሳቀቅና የተጠያቂነት ፍርሐት ጥቃቱን እየፈጸሙና እያስፈጸሙ የሚገኙት፣ ማስጠንቀቂያውን በማኅተም እያተሙ እየሰጡ የሚገኙት፣ ጥቃቱን በፈጸሙ አካላት ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ ሲወሰድ የማይታየው፣ ግፉ የተፈጸመባቸው ተበዳዮቹ የብዙኃን መገናኛ ሽፋን ፈልገው በየብዙኃን መገናኛ መሥሪያቤቶች በቀረቡ ጊዜ ሽፋን ለመስጠት ያልተፈለገው፡፡

እኔ በወገን ላይ ያለኝ ሥጋት ይሄንን በየጊዜው በየቦታው እየተፈጸመ ያለውን ዘግናኝ የጥቃት ዜና ዘወትር እየሰማው ሲሔድ እንዳይላመደውና እንደቀላል ነገር ቆጥሮት ትኩረት እንዳይነፍገው ነው፡፡ ወገን ብየ ስል የአማራ ህልውና ጉዳይ ያንገበግበኛል፣ ይገደኛል ብሎ ለመፍትሔው ተነሥቻለሁ!” ያለውን ወገን ነው እንጅ ቀድሞውንም ቢሆን የዜጎች የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ያሳስበናል!” ብለው ሲያበቁ አማራ በአማራነቱ ሲጠቃና ግፍ ሲሠፈርበት ግን ምንም የማይመስላቸውንና የማይገዳቸውን፣ ጨርሶ ትኩረት ሊሰጡት የማይፈልጉትን ሐሰተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተብየዎችን፣ ሥልጣን ናፋቂ ፖለቲከኞችን (እምነተ አሥተዳደራውያንን) ፣ ከሃዲና አባይ የሃይማኖት አባት ተብየዎችን፣ ኢትዮጵያዊነትን በማጭበርበሪያነት የሚጠቀሙበትን ስሉጥ (አክቲቪስት) ነኝ ባዮችን፣ አድርባይ ጋዜጠኞችን፣ ተንታኝ ነኝ ተብየዎችን፣ የጥፋት ኃይሎችን (ወያኔ/ኢሕአዴግን፣ ኦነግን…) አልደግፍም ባይ አስመሳይ ዜጎችን አይደለም!!!

ከፍተኛ አደጋ ላይ ያለው የአማራ ህልውና ጉዳይ ያሳስበኛል፣ ያንገበግበኛል፣ ይገደኛል!” ብሎ ለመፍትሔው ተነሥቻለሁ!” ያለው ወገን ግን ይሄ ግፍ መፈጸሙ በተሰማ ቁጥር በማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛው ከመንጫጫት ባለፈ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ሊገታ የሚችል ምንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ ያለመሰልቸት ተግቶ እየተንቀሳቀሰ ባለመሆኑ እንቅስቃሴውን በማኅበራዊው የብዙኃን መገናኛ በመንጫጫት ገድቦ ይሄንንም የተለመደ ተግባር አድርጎት ከንፈር በመምጠጥ ብቻ እንዳይቀር ትልቅ ሥጋቴ ነው፡፡

መፍትሔው ቀድሞውንም ቢሆን በመጀመሪያው ጉባኤው ከክልላችን ውጭ ያለውን አምሐራ አልወክልም! ከክልላችን ውጭ ያለው አምሐራ የብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ነው፣ ነፍጠኛ ነው! መወገዝ መቀጣት አለበት!” ብሎ ውሳኔ በማሳለፍ ከጠላቶቻችን ጎን ለተሰለፈብን፣ የጠላቶቻችን መሣሪያ ሆኖ በለው ይሄንን ነፍጠኛ!” እያለ ሲፈጀንና ሲያስፈጀን ለነበረውና አሁንም በተለያየ መንገዶች እየፈጀንና እያስፈጀን ላለው፣ ከጅምሩ ፈጽሞ ላይሰማን በዚሁ በተናገረው መልክ ጆሮውን ለደፈነብን የአህያው ወያኔ የአህዮች ጥርቅም ብአዴን በመጮህና በማላዘን በከንቱ ጊዜን ማባከን አይደለም፡፡

ምን እናድርግ ታዲያ? ከተባለ በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን አረመኔያዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ግፍ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለያዩ መንገዶች ሳይሰለችና ተስፋ ሳይቆርጥ ከመክሰስ ከማሳወቅና ከመወትወት ጀምሮ አሁን ለጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች የማጥቃት እርምጃ መውሰድ ባንችልም ቢያንስ እንኳ ኅቡዕ አደረጃጀት ፈጥረን ሕጋዊ እራስን ከጥቃት የመከላከል መብታችንን በመጠቀም በወገናችን ላይ እርምጃ በሚወስዱ አካላት ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰድ ወደምንችልበት እንቅስቃሴ መግባት የግድ ይኖርብናል፡፡ በየቦታው ግፍ እየተፈጸመበት ያለውን ወገናችንን በኅቡዕ ካደራጀነው ይሄንን የመከላከል እርምጃ ለመውሰድና መሞቱ ካልቀረ ጠላቱን ይዞ ለመሞት ቁርጠኛና ዝግጁ ነው፡፡

ወገን ሆይ! መሞት ካለብንም ቢያንስ እንኳ ጠላታችንን ይዘን እንሙት እንጅ! ወደዚህ ቁርጠኛ እንቅስቃሴ ካልገባን በስተቀር 27 ዓመታት ሙሉ አድርገኸው አንዳችም ለውጥ ባላመጣው በአቤቱታና በለቅሶ ወያኔ ከበረሃ ይዞት የመጣውን ፀረ አማራ የጥፋት ዓላማንና ግብን ማስጣል እንችላለን ብለን ካሰብን ሲበዛ ቂሎች መሆናችንን ልነግርህ እወዳለሁ፡፡ እናም እባካቹህ እንንቃና እንመክት! ወደማጥቃት መሻገር የምንችልበትንም ሁኔታ ለመፍጠርም ሌት ተቀን እንትጋ!!! ወገን ሆይ ጨክን!!! ያለመጨከን ምንም መፍትሔ የለህምና ተው ተው መሸብህ ጨክን??? ወገን ሆይ! እባክህ እንዲህ በግልጽ አማራነት የመጠቂያ ምክንያት ሆኖ የትም በየቦታው እንደጦስ ዶሮ እየተቀነጠሱ የመጣል ደረጃ ላይ መድረስ በቅርብ ጊዜ ከምድረ ገጽ የመጥፋት ጉልህ ምልክት መሆኑን ተረዳና ከመጥፋትህ በፊት ህልውናህል ለመታደግ ፈጥነህ ተደራጅና ተነሥ!!!

ድል ለግፍ ተጋቹ አማራ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com